አቡጊዳ – አመራር አባልና የቀድሞ ዋና ጸሃፊ አቶ አስራት ጣሤ ታሰሩ

የአንድነት ፓርቲ ለበርካታ አመታት በዋና ጸሃፊነት ያገለገሉት አቶ አስራት ጣሴ መታሰራቸዉን የአንድነት ፓርቲ ሚሊየም ድምጽ፡ለነጻነት ፌስቡ ገጽ ዘገበ።

«የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ፣ በክስ ሂደት ላይ የነበረው የአኬልዳማ ዶክመንተሪ በድጋሚ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መታየቱን ተከትሎ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ከፃፉት አስተያየት ጋር በተያያዘ “ዘለፋ አዘል ጽሑፍ” ጽፈዋል በሚል ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲያስረዱ ትዕዛዝ በተላለፈባቸው መሰረት በዛሬው እለት በፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት የተገኙ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ለ7 ቀን ታስረው በቀጣዩ ሳምንት እንዲቀርቡ በማለት የእስር ትዕዛዝ ወስኖባቸዋል » በሚል ነበር ዘገባው የቀረበዉ።

በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶ ነጻነት እንደሌላዉ የሚታእቅ ሲሆን፣ በአቶ አሥራት ጣሴ ላይም ሆነ በሌሎች የተቃዋሚ አመራር አባላት ላይ እየታዩ ያሉ ጥቃቶች፣ፍርድ ቤት ወለድ ሳይሆኑ፣ ሆን ተብሎ አንድነትን ለማዳከም ከኢሕአዴግ ጽ/ቤት በመጣ መመሪያ መሰረት መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ።