ቪኦኤ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ህዳር 13, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)
የብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ በተለያዩ መንገዶች ከሀገር የወጡ በርካታ ቅርሶችን እንዲመለሱ ለማድረግ ምሁራንና ባለሞያዎችን አወያየ።
ነፃነት ዘለቀ
ውድ አንባቢያን ዛሬ ትንሽ ለየት ባለ ሁኔታ የልብ የልባችንን ነው የምንጫወተው። መደባበቅ ብሎ ነገር አይኖርም። ለምኑ ብለን? ለየትኛው ጊዜስ ብለን እንወሻሽ? “በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ” – መተዛዘብን ለዛሬ እንርሳት።
ጓድ ካፍትሌ ከአርባምንጭ
የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የደርግ ሥርዓት መገርሰሱን በማስመልከት ያስተላለፉትን መልዕክት ሰምቼ ነበር። መልዕክቱ ባጭሩ እንዲህ የሚል ነበር። “የድህነት ዘበኛ የነበረው ሥርዓት ስለተወገደ ከዚህ በኋላ ጦርነታችሁ ከዘበኛው ጋር ሳይሆን ቀጥታ ከጠላቱ (ድህነት) ጋር ነው።” በእርግጥ ደርግ ሥልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ ”ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር!” እያለ ሕዝቡ በድህነት እንዲማቅቅ አድርጓል። ከዚህ የተነሳ የሥርዓቱ መውደቅ ብዙዎችን በደስታ አስፈንጥዟል።
ወለላዬ ከስዊድን
ቅዳሜ ጥቅምት 20 ቀን 2008 ዓ.ም. (ኦክቶበር 31 ቀን 2015 እ.ኤ.አ.) በስዊድን ዋና ከተማ በስቶክሆልም ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ መርጃ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተደረገ። በዝግጅቱ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ተገኝተዋል። በቦታው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት አቶ አበበ ቦጋለ የውጪ እንቢተኝነት ሊቀመንበር እና አቶ ቸኮል ጌታነህ የንቅናቄው ከፍተኛ አመራር ናቸው።
ኀዳር ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ረዳት አብራሪ የነበረውና በድርጅቱ ውስጥ ያለው ዘረኝነትና አድሎዋዊ አሰራር ስራዬን በነጻነት ለመስራት አላስቻለኝም በሚል ምክንያት ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየርመንገድ የሆነውን ከአዲስ አበባ ተነስቶ በካርቱም በኩል አቋርጦ ወደ ጣሊያን ይበር የነበረን ቦይንግ 767-300 አውሮፕላን በመጥለፍ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ካሰረፈ በሁዋላ ጉዳዩን ሲከታተለው የነበረው ፍርድ ቤት ክሱ …
በሀገራችን ያለው ድርቅ ክብደት ከ1977ጋር የሚመሳሰል እንደሆነ የመንግሰት ሹም ከሸገር ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ምልልስ አረጋግጠዋል፡፡ ልዩነቱ ግን አሁን መንግሰት ይህን ለመቋቋም የሚያስችል አቅም አለን የሚልው ጉዳይ ነው፡፡ ይህ አቅም ግን መሬት ላይ ወርዶ ስናየ ወኔ ብቻ ይመስላል፡፡ ከፕሮፓጋንዳ ያለፈ የፈረንጆቹን ደጅ እንዳይጠኑ የሚያደርጋቸው አይደለም፡፡ “ደርግ” በ1977 የነበረፈውን ድርቅ ለዓለም ይፋ አድርጎ የነበረ ሲሆን የዚያን ጊዜ […]
The post ፕሮፓጋንዳው ስብዓዊነት ይኑረው!!! ሰው እየሞተ ነው!! ቁጥሩን ቤቱ ይቁጠረው!!! ግርማ ሰይፉ appeared first on ሳተናው .
ጥቅምት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቅማንት ብሄረሰብ ጥያቄ ጋር በተያያዘ በአርሶ አደሩና በክልሉ ልዩ ሃይል መካከል ከማውራ 15 ኪሜ ርቃ በምትገኘዋ ሮቢት አካባቢ እንዲሁም በላይ አርማጭሆ ዋና ከተማ ትክል ድንጋይ ከፍተኛ ውጥረት ነግሶአል። እስከትናንት ድረስ በአርሰዶ አደሩና በልዩ ሃይል መካከል በተደረገ የተኩስ ለውጥጥ ከ100 በላይ የልዩ ሃይል አባላት ሲገደሉ፣ ከ36 ያላነሱ ንጹሃን …
ጥቅምት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ምስራቃዊ አካባቢዎች በዝናብ እጥረት ለረሃብ የተጋለጡ አርሶአደሮች በዚህ ችግር ላይ እያለን በአካባቢው አመራሮች ግብር እንድንከፍል በመገደዳችን ከፍተኛ ችግር ላይ ነን በማለት ተናገሩ፡፡ በድርቁ የተጎዱት አካባቢ የሚኖሩ የመንግስት ሠራተኞች በተለይ ለኢሳት ሲናገሩ ‹‹ የዝናቡ እጥረት እንዳለ ሆኖ መንግስት ለአርሶ አደሮች ግብአት አላቀረበም፡፡አርሶ አደሩ በዚህ ዓመት የሚቀምሰው …
ጥቅምት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን በጂንካ ከተማ አርኪሻ ቀበሌ ኬላ መንደር ነዋሪዎች ቤቶቻቸዉ በዶዘር እንዲፈርስ በመደረጉ ለጎዳና ተዳዳሪነት መዳረጋቸዉንና በእሪታና ለቅሶ መንገድ በመዝጋት ጥቅምት 25፣ 2008 ከሰዓት በኃላ በማሰማታቸዉ ልዩ ኃይልና ፖሊስ ለመበተን ሲሞክሩ ቦታ እየቀያየሩ ተቃውሞአቸውን እስከ ምሽት ሲያሰሙ ቆይተዋል። ጥቅምት 27ትም እንዲሁ ቤት ማፍረሱም ተቃዉሞዉም ቀጥሎ የዋለ …
ኀዳር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ ህዳር 2፣ 2008 ዓም ከጎንደር ወደ መተማ ሲጓዙ ከነበሩ ኦራል መኪኖች መካከል አንደኛው ግንድ መጣያ ቀበሌ ልዩ ስሙ ባለእግዚብሄር ቦታ ላይ ሲደርስ ባጋጠመው የቴክኒክ መበላሸት የተነሳ በመገልበጡ በሸራ ተሸፍነው ሲጓዝ ከነበሩት ወታደሮች መካካል 20 የሚሆኑት ወዲያውኑ ሲሞቱ፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ቆስለው ወደ ጎንደር ሆስታል …
ኀዳር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል ሰገን ዞን ኮንሶ ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች በዞን ደረጃ ራሳቸውን ለማስተዳደር እንዲፈቅድላቸው ጥያቄ በማቅረባቸው ብቻ የብሔረሰቡን አባላት ማሳደድ፣ ማሰር፣ መደብደብ ዘመቻው የቀጠለ ሲሆን፣በአካባቢው ያለው ውጥረት ተባብሷል፡፡ የደቡብ ክልል መንግስት የኮንሶን ጥያቄ በአግባቡ ከመመለስ ይልቅ ጥያቄውን በኃይል ወደማፈን በመሸጋገሩ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ ከጉዳዩ ጋር እጃቸው …

በየካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ በተለምዶ ወሰን ግሮሰሪ በመባል በሚታወቀው አካባቢ፣ የሚኖሩ ግለሰብን መኖሪያ ቤት በማሸጥና ገንዘባቸውንም ‹‹ፀሎት ይደረግበት›› በማለት አታለው ወስደዋል ተብለው ተጠርጥረው የታሰሩት [መምህር] ግርማ
ወንድሙ፣ ጥቅምት 30 ቀን 2008 ዓ.ም. በ50 ሺሕ ብር እንዲፈቱ የተፈቀደላቸው ቢሆንም፣ በተጠረጠሩበት ሌላ ወንጀል አልተፈቱም፡፡
ግለሰቡን በቁጥጥር ሥር አድርጐ በመመርመር ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መርማሪ ቡድን፣ ጥቅምት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት ባቀረበው የምርመራ ሥራው፣ ተጠርጣሪው ፈቃድ ማግኘት ከሚገባቸው ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን (ቤተ ክህነት) ፈቃድ ሳያገኙ፣ በሐሰተኛ ሰነድ (ፎርጅድ) ሲገለገሉ እንደነበር አስረድቷል፡፡
በመሆኑም ቀሪ ምርመራ እንደሚቀረው ገልጾ፣ ከጠየቀው 14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ሰባት ቀናትን ፈቅዶለታል፡፡ በመሆኑም [መምህር] ግርማ፣ ከቤት ሽያጭና ከሲም ካርድ ጋር በተያያዘ በቀረበባቸው ወንጀል በ50 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቢሰጥም፣ በሐሰተኛ ሰነድ የተጠየቀባቸው የሰባት ቀናት ጊዜ የሚያልቀው ኅዳር 2 ቀን 2008 ዓ.ም. በመሆኑ በማረፊያ ቤት ለመቆየት ተገደዋል፡፡
በዘንድሮው ድርቅ ምክንያት የደረሰው የምግብ እጥረት በምንም ዓይነት ከ1975ቱ ጋር የሚመሳሰል አይደለም ሲል ለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡
«በጀርመንየኢትዮጵያተማሪዎችናምሩቃንማሕበር» ከጥቂት ቀናት በፊት 6ኛውን ዓመታዊ ስብሰባ አካሂዷል።
ላለፈዉ ስድስት ወራት የህዳሴ ግድብ በመባል የሚታወቀዉ እንዲያጠኑ የፈረንሣዩ «ቢአርኤል» እና የኔዝርላንዱ «ዴልታሬስ» የአማካሪ ኩባኒያዎች መሃል የተፈጠረዉን ኣለመግባባት ካልተፈታ ከሌሎች አመራጮች ዳግም ጨረታ ማዉጣት እንደሚጠበቅባቸዉ በዉሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሙያ ለዶቼ ቬሌ ተናግሮዋል።
VOA ከምሽቱ አንድ ሰዓት የአማርኛ ዜና → listen
ኀዳር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከተማው ከሚገኙና በአብዛኛው የገዢው ፓርቲ ዋነኛ ደጋፊ ባለሃብቶች ተብለው ከሚታወቁት መካከል 14 ቱ በአራጣ ማበደር ወንጀል ተከሰው ከሶስት ቀናት በፊት ታስረዋል። ከተያዙት ባለሃብቶች መካከል አቶ ስማቸው፣ አቶ ዘገየ መላኩ፣ ዶ/ር በቀለ፣ ሞላ ጌታሁን፣ አውዱ፣ ኪዳኔ ካህሳይ፣ አበበ ደመቀ፣ አቶ እስራ፣ ፖለስ ጌታው አበሬ፣ እንዲሁም አቶ ካሳሁን …
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሐዋሳ ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት ሥራ አስኪያጅና የደንበኞች አገልግሎት መኮንን፣ በሥልጣን ያላግባብ የመገልገል የሙስና ወንጀል ክስ ጥቅምት 29 ቀን 2007 ዓ.ም. ተመሠረተባቸው፡፡
የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ክስ የመሠረተባቸው ሶስና ሀዲስ ገበየሁ (የደንበኞች አገልግሎት መኮንን)፣ አቶ ጌታቸው ዋቅሹም (የደንበኞች አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ በተጨማሪም በደቡብ ክልል መንግሥት ኦዲት ቢሮ የመዝገብ ቤት ሠራተኛ አቶ ፀጋዬ ግርማ ሲሆኑ፣ ክሱ የቀረበው ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ነው፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በጥቅም ተመሳጥረውና ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመገልገል፣ የባንኩ ባልደረባ የሆኑት ወ/ሮ አለፊያ ከድር ለቤት መግዢያ ባንኩ የፈቀደላቸውን 320,000 ብር ለግል ጥቅም ማዋላቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡
ተከሳሾቹ ባንኩ ለግለሰቧ የፈቀደውን ገንዘብ ቤቱን የሸጡላቸው ወ/ሮ ፅጌረዳ ሰይፉ አካውንት ማስገባት ሲገባቸው፣ በሁለተኛ ተከሳሽ ፀጋዬ ግርማ አካውንት ውስጥ በማስገባትና በተለያዩ ጊዜያት እያወጡ መጠቀማቸውም በክሱ ተገልጿል፡፡
የደንበኞች አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌታቸው ዋቅሹም፣ ገንዘቡ ለወ/ሮ ፅጌረዳ ሰይፉ ገቢ መደረጉን ሳያረጋግጡ በማፅደቃቸው፣ ከባድ ጉዳት በማድረስና ኃላፊነታቸውን ባለመወጣት ወንጀል ተከሰዋል፡፡ አቶ ጌታቸው የተጠረጠሩበት ወንጀል ዋስትና እንደማያስከለክል ተገልጾ፣ በ3,000 ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ በማዘዝ ለኅዳር 21 ቀን 2008 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ኀዳር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግንባሩ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ሲመክር አሉኝ የሚላቸውን ደጋፊዎች በሁለት እንደሚከፍላቸውና ሁለቱም ለግንባሩ በስልጣን ለመቆየት ቀዳሚ የስጋት ምንጭ ናቸው ሲል ፈርጇቸዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪዎች አቶ በረከት ስምኦን፣ የጠ/ሚኒስትሩ ሌላው አማካሪ አቶ አለበል ደሴ፣ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፣ የመረጃ መረብ ደህንነት የህዝብ አስተያየት ትንተና ክፍል ፣ የሁሉም የፖለቲካ ድርጅት …
ኀዳር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ የግብርና ፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ቻላቸው ሞላ የግብርና ባለሙያ ሰራተኞችን ሳያነጋግሩና ፈቃዳቸውን ሳይጠይቁ፣ ከተወሰኑ ሀላፊዎች ጋር በመመካር የግብርና ባለሙያዎች በሙሉ ለአባይ ግድብ እንዲከፍሉ አድርገዋል። የግብርና ባለሙያዎች ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት መውሰዳቸው ታውቋል።
ጆንሰን ማልዳን የታፈሰ አበበን ጉዳይ በቅርብ እየተከታተሉ ያሉ መርማሪ መኰንን ናቸው። “እኔ በአሁኑ ተጠርጣሪዎቹን እያፈላለግሁ ነው የምገኘው። ሌላ መረጃ የለኝም” ብለዋል።
ጥቅምት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል ሰገን ዞን የኮንሶ ወረዳ ሕዝብ በዞን ደረጃ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር መጠየቁን ተከትሎ የክልሉ መንግስት ልዩ ታጣቂ ኃይል ወደአካባቢው በማስገባት ነዋሪዎችን በማሰር፣ በመደብደብ እና በማስፈራራት ላይ ይገኛል። የዞኑ ባለስልጣናት ሕዝቡ ተሰብስቦ የዞን ይሰጠን ጥያቄ አላቀረብንም በማለት እንዲያወግዝ በማስጨነቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅትየመብት ጥያቄው አንቀሳቀሾች ናቸው የተባሉ …
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ
ጥቅምት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነገረ ኢትዮጵያ የዞኑን ሰብሳቢ ጠቅሶ እንደዘገበው በገላና ወረዳ የወረዳውን ሰብሳቢ አቶ በድሉ መንግስቱን ጨምሮ 10 የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ታስረዋል።ጥቅምት 24/2008 ዓ.ም የታሰሩት የድርጅቱ አባላት ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውንና በቤተሰብም አለመጎብኘታቸውን ዘግቧል። የወረዳው ሰብሳቢ አቶ በድሉ መንግስቱ ማስፈራሪያና ዛቻ እንደሚደርሳቸው ለፖሊስ ሲያመለክቱ ቢቆዩም ምንም ምላሽ ሳያገኙ ቀርተዋል።
ከምስራቅ አፍሪቃ ማህበረሰብ አባል አገራት አንዷ በሆነችው ቡሩንዲ መንግስት የጦር መሳሪያ አሰሳ እያካሄደ ነው። በአገሪቱ በተቃዋሚዎችና በፕሬዝዳንት ፒየር ንኩሩንዚዛ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ጅምላ ፍጅት እንዳያመራ አስግቷል።
« ሞት በኩላሊት ይብቃ» የተባለው የኩላሊት ህሙማን ማህበር ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ ባዘጋጀው የእግር ጉዞ ላይ የኩላሊት ህክምና የሚያስፈልገው ወጭ ከፍተኛ በመሆኑ መንግሥት የማከሚያ መሣሪዎች በነፃ እንዲገቡ እንዲፈቅድ ጥሪ አቅርቧል።
ከምሽቱ አንድ ሰዓት የአማርኛ ዜና → Listen
የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በዋና ሥራ አስኪያጅነት በመቀጠሉ “የምስጋና ሰርፕራይዝ” ነው ያልታቀደው ወጪ፣ የፓትርያኩን የመኖርያ ቤት ዕቃዎች ለመቀየር መዋሉ ተነግሯል ጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩን የማስተዳደር ሓላፊነት ያለው ጠቅላይ ጽ/ቤቱ አያውቀውም የሀ/ስብከቱ ሒሳብ፣ ያለተቆጣጣሪና ያለዕቅድ በየማነ ዓምባገነንነት እንዲባክን ተፈርዶበታል በወሬ እና በይስሙላ አካሔዶች የተሳሳተ ምስል እየፈጠረ ራሱን እንደ ለውጥ አራማጅ እና መሪ በመስበክ የሥልጣን ወራቱን እያራዘመ የሚገኘው የአዲስ …![]()
ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመንግስት ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጹት በቀድሞዋ ክብረመንግስት በአሁኑ አዶላ ወዮ ከተማ የሚገኘው ክብረመንግስት የኢትጵያ ንግድ ባንክ ካለፉት 9 ቀናት ጀምሮ ስራ በማቆሙ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ለመውሰድ ተችግረዋል። ቤተሰቦቻችን ለችግር ተዳርገዋል የሚሉት ሰራተኞች፣ አቤቱታ ቢያቀርቡም፣ የኔትወርክ ችግር ነው ጠብቁ ከመባል ውጭ መፍትሄ ሊያገኙ አልቻሉም። ፖሊሶችን ጨምሮ ሁሉም የመንግስት …
ሩስያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ግብፅ ውስጥ የሚገኙ 11,000 ሀገር ጎብኚ ዜጎቿን አስወጣች። ዛሬ እሁድም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ወደ ሀገሩ እንደሚመለስ የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አርካዲ ድዎርኮቪችን ዋቢ አድርጎ የሩሲያ ዓለም አቀፍ የዜና ኤጀንሲ (RIA) ዘግቧል።
በከፍተኛ ድርቅ ተመትተው ነዋሪዎቻቸው ክፉኛ ለጠኔ ተጋልጠው የሚልሱት የሚቀምሱት በማጣታቸው ከሞት አፋፍ ላይ ሆነው የሚገኙባቸው አምስቱ ቀበሌዎች ጨጨሆ፣ ፈንጠርያ፣ ቀንጠብጣ፣ አይጠላ እና እንድ ሌላ ለጊዜው ስሙን ያላወቅነው ቀበሌ ናቸው፡፡ በሰሜን ጎንደር የወገራ ወረዳዎቹን ሶሚያ፣ ጓሪ፣ ግጭሆ እና ቧግሽ የተባሉትን አራት ቀበሌዎች ጨምሮ እስካሁን ዘጠኝ ቀበሌዎች ክፉኛ በድርቅ ተመትተው ከ50ሺህ እስከ 60 ሺህ ህዝብ ተርቦ የስደትና […]![]()

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ቦርድ፣ የንግድ ምክር ቤቱን ዋና ጸሐፊ ከሥራ እንዲታገዱ ወሰነ፡፡
ዘጠኝ አባላት ያሉትና በአቶ ሰለሞን አፈወርቅ የሚመራው የንግድ ምክር ቤቱ ቦርድ፣ ዋና ጸሐፊው አቶ ጋሻው ደበበ ከኃላፊነታቸው እንዲታገዱ ውሳኔ ያሳለፈው ባለፈው ሐሙስ ጥቅምት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. እንደሆነ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ቦርዱ በዋና ጸሐፊው ላይ የዕገዳ ዕርምጃውን የወሰደበት ዋነኛ ምክንያት ግልጽ ባይሆንም፣ ከሥራ የታገዱ መሆናቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ በንግድ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት በኩል ተፈርሞ እንዲደርሳቸው ቦርዱ ከስምምነት ላይ መድረሱ ታውቋል፡፡
ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ወገኖች እንደተሰማው፣ በቦርዱና በዋና ጸሐፊው መካከል ከዚህም ቀደም በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ አለመግባባቶች ነበሩ፡፡ በዚህም ምክንያት እንዲህ ያለው ዕርምጃ ይጠበቅ ነበር ይላሉ ምንጮች፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞም ቦርዱ በንግድ ምክር ቤቱ ወቅታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ አሉ የሚባሉ ችግሮችን ሲያሰባስብ እንደነበር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በተለይ ንግድ ምክር ቤቱ በቅርቡ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔና ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ዕውቅና በሰጠበት ፕሮግራም ላይ ታየ የተባለው የፕሮግራም መፋለስና ጉድለት፣ የቦርድ አባላቱን አስቆጥቶ ነበር ተብሏል፡፡ በዚህ ምክንያትም አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር በማስታወስ፣ የዋና ጸሐፊው ከሥራ መታገድ አንደኛው ምክንያት ከዚህ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት የሚሰነዝሩ አሉ፡፡
የቦርዱ ዕገዳ ጊዜያዊ ይሁን ሙሉ በሙሉ ከሥራ ማሰናበትን የሚያጠቃልል መሆኑ ማረጋገጫ አልተገኘም፡፡ በሌላ በኩል ግን አቶ ጋሻው ከዚህ ውሳኔ በፊት መልቀቂያ ሳያስገቡ እንዳልቀሩ ይነገራል፡፡
ቦርዱ በአቶ ጋሻው ላይ እንዲወሰድ የወሰነው ዕርምጃ ንግድ ምክር ቤቱ በየዓመቱ በሚያካሂደውና ባለፈው ሐሙስ በይፋ በተከፈተው ‹‹የኢትዮጵያን ይግዙ›› ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት መክፈቻ ዕለት መሆኑ ደግሞ፣ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል፡፡
በዕለቱ አቶ ጋሻው የንግድ ትርዒቱን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ሲመሩ እንደነበር፣ የመክፈቻ ፕሮግራሙ ከተጠናቀቀ በኋላ ቦርዱ ተሰብስቦ ውሳኔውን ማሳለፉ የምንጮች መረጃ ያመለክታል፡፡
አቶ ጋሻው ንግድ ምክር ቤቱን ከስድስት ዓመታት በላይ በዋና ጸሐፊነት በመምራት፣ በንግድ ምክር ቤቱ ረዘም ላለ ጊዜ በያዙት ኃላፊነት የቆዩ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
በእሳቸው ዋና ጸሐፊነት ወቅት አራት ፕሬዚዳንቶች የተፈራረቁ መሆኑም፣ አቶ ጋሻው ከሌሎች ዋና ጸሐፊዎች በተለየ በቦታው የቆዩ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው ተብሏል፡፡
ወደ ንግድ ምክር ቤቱ ከመምጣታቸው ቀደም ብሎ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በንግድ ሚኒስቴር አገልግለዋል፡፡
በንግድ ምክር ቤቱ ቦርድ ዕገዳ የተደረገባቸውን አቶ ጋሻውንና የቦርድ ሰብሳቢውን አቶ ሰለሞን ሪፖርተር ለማነጋገር ጥረት ቢያደርግም፣ ሁለቱንም በአካልም ሆነ በስልክ ለማግኘት አልተቻለም፡፡
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና
ዶይቸ ቬለ የዓለም ዜና listen
“ክ/ከተማው ቦታው አይነካባችኹም ብሎ አዘናግቶናል፤ ለሌላ ዓላማ መዋሉ አሳዝኖናል” /ምእመናን/ “ለሌላ ዓላማ ሳይውል አጥቢያዎቹ በዕቅዳቸው እንዲያለሙት አመራር ይሰጥላቸው” /ቅ/ሲኖዶስ/ “ልማቱ በዓለ ጥምቀቱን ታሳቢ ያደረገ ነው፤ ቦታው በታቦት ማደርያነቱ ይቀጥላል” /ክ/ከተማው/ (አዲስ አድማስ፤ ናፍቆት ዮሴፍ፤ ቅዳሜ ጥቅምት ፳፯ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.) ላለፉት 52 ዓመታት በበዓለ ጥምቀት ማክበርያነት እና በታቦት ማደርያነት ሲያገለግል የነበረው የባሕረ ጥምቀት ቦታ ለሌላ …![]()

የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ችግራቸውን እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል
በእስር ላይ የሚገኘውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላለፉት 20 ቀናት መጠየቅና ማግኘት እንዳልቻሉ የጠቆሙት ቤተሰቦቹ፤ የጤንነቱ ጉዳይ እንዳሳሰባቸው በመግለፅ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ለችግራቸው እልባት እንዲሰጣቸው በደብዳቤ አመለከቱ፡፡
የጋዜጠኛው ቤተሰቦች በደብዳቤያቸው እንደገለፁት፤ ከጥቅምት 7 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ምክንያቱን ባላወቁት ሁኔታ ተመስገን በሚገኝበት ዝዋይ ማረሚያ ቤት ቤተሰብም ሆነ ወዳጅ ዘመድ እንዳይጠይቀው መከልከሉ መላው ቤተሰቡን ስጋት ላይ ጥሎታል፡፡
የጤናው ጉዳይ በእጅጉ ያሳስበናል ያሉት ቤተሰቦቹ፤ በተለይ ቀደም ብሎ የነበረበት ህመም ተባብሶ የግራ ጆሮው መስማት እስከመቸገር እንዳደረሰውና የወገብ ህመሙ እረፍት ነስቶ አላስተኛ እያለው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በተደጋጋሚ ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤት ቢመላለስም ተመስገንን ማግኘት እንዳልቻለ የሚናገረው የተመስገን ታናሽ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ፤ የማረሚያ ቤቱ ጥበቃዎች “ለምን መጠየቅ ተከለከልን?” ስንላቸው፤ “የበላይ ትዕዛዝ ነው” ይሉናል፤ ብሏል፡፡ በዚህም የተነሳ ተመስገንን ላለፉት 20 ቀናት እንዳላዩትና ቤተሰቡንም ለጭንቀት እንደዳረገ ይገልፃል፡፡
“የቤተሰባችን አባል በሆነው ተመስገን ላይ በተለየ ሁኔታ ተደጋጋሚ የህግ ጥሰት እየደረሰ ነው” ያሉት ቤተሰቦቹ፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከዚህ ቀደም እንዳደረገው ጣልቃ በመግባት ችግሩን እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል፡፡
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቀድሞ ይሠራበት በነበረው “ፍትህ” ጋዜጣ ላይ በወጡ ጽሑፎች ምክንያት፣ ተከሶ የ3 አመት እስራት ተፈርዶበት፣ ማረሚያ ቤት እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
ቴክኖ ሞባይል ላለፉት 3 ወራት አላመረተም
በሀገሪቱ በተከሰተው የውጭ ምንዛሪ እጥረት የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ምርት ማምረት እስከማቆም የደረሱ ሲሆን በአስመጪና ላኪነት የንግድ ስራ ላይ የተሠማሩ ነጋዴዎችም መቸገራቸውን ገልፀዋል፡፡
ከ900 በላይ ሠራተኞችን ይዞ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን በማምረት ሥራ ላይ የተሠማራው የቴክኖ ሞባይል አምራቹ ዊጉዩ ኩባንያ፤ በውጭ ምንዛሪ እጥረቱ የተነሳ ላለፉት 3 ወራት ምርት ማምረት ማቆሙን አስታውቋል፡፡
ኩባንያው የውጭ ምንዛሪ ከባንክ ቢጠይቅም “ትንሽ ጊዜ ታገሱ” የሚል መልስ እንደተሰጠው የቴክኖ የአስተዳደር ክፍል ሃላፊ አቶ ገነነ አዘነ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
ሃላፊው እንዳሉት፤ ኩባንያው ጠንካራ የገንዘብ አቅም ያለው በመሆኑ ለኪሣራ ባይዳረግም ስራ ባቆመባቸው ወራት በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አጥቷል፡፡
“ችግራችንን ለመንግስት አሳውቀናል፤ በቅርብ ጊዜ ችግሩ ይፈታል የሚል ተስፋ አለን” ብለዋል፤ ሃላፊው፡፡
ኩባንያው በቀን ከ10ሺህ በላይ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን አምርቶ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገራት ያቀርብ እንደነበርና በአሁን ሰአት በምንዛሪ እጥረቱ የተነሣ ሙሉ ለሙሉ ምርት ማቆሙን ጠቁመው፣ ያጋጠማቸው ችግር ጠንከር ያለ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በተመሳሳይ በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው በአስመጪነትና ላኪነት ስራ ላይ የተሠማሩ ነጋዴ በበኩላቸው፤ የዶላር እጥረቱ ከአንድ አመት በላይ እንደሆነው፤ ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጥረቱ እየተባባሰ እንደመጣና በንግድ ስራቸው ላይ ከፍተኛ ፈተና እንደጋረጠባቸው ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡
“ከ5ሺ ዶላር ጀምሮ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ለባንክ ፕሮፎርማ ካስገባን በኋላ እድል ከቀናን ከ3 እና 4 ወር በኋላ ነው የምናገኘው” የሚሉት ባለሃብቱ፤ በችግሩ የተነሳ ሠራተኛ በትነው ስራ ፈተው እስከመቀመጥ መድረሣቸውን ገልፀዋል፡፡
የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ስራ አስኪያጅ የሆኑ ግለሰብም ፋብሪካቸው በውጭ ምንዛሪ እጥረት የተነሳ ከውጭ ጥሬ እቃ ማስገባት መቸገሩን ጠቅሰው ባለፉት 4 ወራት ኢንዱስትሪያቸው ለከፍተኛ ኪሣራ እየተዳረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ “መንግስት በተደጋጋሚ ችግሩ በአጭር ጊዜ ይቀረፋል” የሚል ምላሽ ሲሰጠን ቆይቷል ያሉት ስራ አስኪያጁ፤ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን ችግሩ ይበልጥ እየተባባሰ መጥቷል ብለዋል፡፡
በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ችግሩ ካልተቃለለላቸው ሠራተኛ እስከመቀነስ የሚደርስ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ የጠቀሱት ስራ አስኪያጁ፤ በቅርብ የሚያውቋቸው ፋብሪካዎችም ተመሳሳይ እርምጃ መውሰዳቸውን እንደታዘቡ ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ በአስመጪነትና ላኪነት የንግድ ስራ ላይ የተሠማሩ ሌላው አስተያየት ሰጪ፤ የዶላር እጥረቱ ስራቸውን ሙሉ ለሙሉ እንዳስተጓጐለባቸው ጠቁመው፤ መንግስት በአጭር ጊዜ ውስጥ እልባት ካላበጀለት የስራ ዘርፋቸውን ለመቀየር እንደሚገደዱ ተናግረዋል፡፡
“የምንዛሬ ጥያቄ ስናቀርብ በአሁን ሰአት መንግስት ከውጭ ስንዴ እያስገባ ስለሆነ ትንሽ ታገሱ የሚል ቀጥተኛ ያልሆነ የቃል መልስ እየተሰጠን ነው ብለዋል – ባለሀብቶቹ፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሃጂ ኢብሣ ተጠይቀው ሲመልሱ፤ “ይሄ የኛም
ጥያቄ ነው ትክክለኛ ምላሽ የሚገኘው ከብሔራዊ ባንክ ነው” የሚል ምላሽ የሰጡን ሲሆን የብሔራዊ ባንክ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ መስፍን ደምሴ ጋር ደውለን መረጃ ለማግኘት ብንሞክርም በደብዳቤ መጠየቅ እንዳለብን ተገልፆልናል፡፡
–በዚህ ሳምንት በማዕከል የሚደረገው ለውጥ ይፋ ይሆናል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለክፍላተ ከተማና ለወረዳዎች 1,600 አመራሮችን ሾመ፡፡ ለተሿሚዎቹ ባለፈው ሳምንት ለሦስት ቀናት የቆየ የፖሊሲ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሙስናና በብልሹ አሠራር ገምግሞ ካሰናበታቸው አመራሮች በተጨማሪ፣ ከዲፕሎማ በታች የትምህርት ደረጃ ያላቸውን አመራሮች አንስቷል፡፡ በእነዚህ ተሿሚዎች ምትክ ለአሥሩ ክፍላተ ከተሞችና ለ116 ወረዳዎች የተሾሙት 1,600 አመራሮች ከመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ ያላቸው ናቸው ተብሏል፡፡
እነዚህ ተሿሚዎች አዳዲስና ከዚህ ቀደም በአስተዳደር መሥሪያ ቤቶች በተለያዩ ደረጃዎች ሲያገለግሉ የቆዩ ናቸው፡፡ ለእነዚህ ተሿሚዎች ባለፈው ሳምንት ከማክሰኞ ጥቅምት 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ቀናት የቆየ የፖሊሲ ማብራሪያ እንደተሰጣቸው ታውቋል፡፡
የፖሊስ ማብራሪያውን የሰጡት የአዲስ አበባ አቅም ግንባታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ይስሐቅ ግርማይና የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረ ፃድቃን ናቸው፡፡
በፖሊሲ ማብራሪያው እነዚህ ተሿሚዎች በከተማው መልካም አስተዳደር ማስፈን፣ የፀረ ሙስና ትግል በብቃት ማካሄድ እንዳለባቸውና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ተግባራዊ ለማድረግ ያቀደውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት መሥራት እንደሚኖርባቸው፣ በፖሊሲ ማብራሪያው ማሳሰቢያ እንደተሰጣቸው ከአቅም ግንባታ ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተለይ አቶ ይስሐቅ በሥልጠና ወቅት እንደተናገሩት፣ ከዲፕሎማ በታች የትምህርት ደረጃ ያላቸው ከኃላፊነት የተነሱ አመራሮች በቀጣይ ትምህርታቸውን የሚቀጥሉበት አሠራር ይፈጠራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የተነሱት የቀድሞ አመራሮች በጥቃቅንና በአነስተኛ ማኅበራት ተደራጅተው የተለያዩ ሥራዎችን እንዲያካሂዱ ይደረጋል ሲሉ አቶ ይስሐቅ በሥልጠናው ወቅት መግለጻቸው ታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በክፍላተ ከተሞችና በወረዳዎች ሲያካሂድ የቆየውን ሹም ሽር በማጠናቀቅ፣ ትኩረቱን በማዕከል ደረጃ በሚያካሂደው ለውጥ ላይ አድርጓል፡፡ በዚህ ሳምንት መጨረሻ በማዕከል ደረጃ የሚያካሂደውን የመዋቅርና የባለሥልጣናት ሹም ሽር ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ጥቅምት 20 ለ21 አጥቢያ 2008 ዓ.ም. የልጃቸውን ጓደኛ በሽጉጥ ተኩሰው በመግደል የተጠረጠሩ ሐኪም፣ ከነመሣሪያቸው በቁጥጥር ሥር ውለው እየተመረመሩ መሆኑ ታወቀ፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 13/14 ልዩ ሥፍራው ማጂክ ካርፔት በሚባለው ትምህር ቤት አካባቢ የተገደለው ወጣት ቴዎድሮስ ሲሳይ ይባላል፡፡
ቴዎድሮስ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን በዕለቱ የማንቸስተር ዩናይትድ ግጥሚያ ሲመለከቱ አምሽተው በዚያው ሲዝናኑ ያመሻሉ፡፡ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት አካባቢ ሟች ቴዎድሮስና ጓደኞቹ በግድያ ወደተጠረጠሩት ዶ/ር ተስፋዬ ያዕቆብ (በሰላም ከፍተኛ የጥርስ ክሊኒክ የጥርስ ሐኪም ናቸው ተብሏል) ቤት መሄዳቸውን ሪፖርተር ያነጋገራቸው የዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡
የተጠርጣሪው ልጅ መጠጥ ሲቀምስ የመጮህና የመበጥበጥ ባህሪ እንዳለበት የሚናገሩት የዓይን እማኞች፣ ጓደኞቹን ይዞ ቤቱ እንደደረሰ ባህሪው በመነሳቱ ሟችና ሌሎች ሁለት ጓደኞቹ ከግቢ ወጥተው በመሄድ ላይ እያሉ ተጠርጣሪው ሽጉጥ ይዘው መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ አንደኛው ወጣት ኳስ ሲያዩ ማምሸታቸውን በማስረዳት ላይ እያለ ተጠርጣሪው ወደ ሟች ተጠግተው በመተኮስ እንደገደሉት የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡
የሟች ጓደኞች ተጠርጣሪው ሐኪም ሆን ብለው እንደገደሉት የገለጹ ቢሆንም፣ ተጠርጣሪው ግን ባርቆባቸው እንደሆነ ለፍርድ ቤት ማስረዳታቸውን ሪፖርተር ከፖሊስ ያገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡
ተጠርጣሪውን ሐኪም በቁጥጥር ሥር አድርጎ በመመርመር ላይ የሚገኘው ፖሊስ፣ ፍርድ ቤት አቅርቦ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል፡፡ ሟች ቴዎድሮስ ሲሳይ በሳሪስ አቦዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ጥቅምት 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቀኑ ስምንት ሰዓት የቀብር ሥርዓቱ መፈጸሙም ታውቋል፡፡
በማላዊ ታስረው የነበሩት ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰውም እዚያው እስር ቤት እስከዛሬ ይገኛሉ። ከነዚህ ውስጥ ወደ 200 የሚሆኑ ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ፣ እስካሁን እስር ቤት ስለሚገኙት ፍልሰተኞች ጉዳይ የት ደርሷል?
ቀድሞው የኢትዮጲያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኣኤ ወይም ሰመጉን (HRCO) 139ኛው ልዩ መግለጫውን ይፋ አደረገ።
የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የመርካቶ ቁጥር ሁለት ቅርንጫፍ ከፍተኛ ኦዲተርና ሦስት ኦፊሰሮች ጉቦ በመቀበል ከባድ የሙስና ወንጀል ጥቅምት 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ተከሰሱ፡፡
ተከሳሾቹ የግል ተበዳይ አቶ ዮሐንስ ጥጋቡ የተባሉትን በጨርቃ ጨርቅ ንግድ የተሰማሩ ነጋዴ፣ ‹‹ግዢና ሽያጭ አልተጣጣመም፣ በቆጠራ የሚፈጠረውን ጉድለት ባላንስ እናደርግልዎታለን፤›› በማለት ሁለት ሚሊዮን ብር ጉቦ መጠየቃቸውን፣ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመሠረተው ክስ ያስረዳል፡፡
የጉቦ መቀበል ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሠራተኞች አቶ መሠረት ታደሰ የተባባሪዎች ምልመላና ሥልጠና ኦፊሰር፣ አቶ አበበ ደቦ ቡልቱሜ የኢንቬስትጌሺን ከፍተኛ ኦዲተር፣ አቶ አያና ጋሩማ የኢንተለጀንስ አሰባሰብ ጀማሪ ኦፊሰር፣ አቶ ሀብታሙ ታደሰ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምቦ ቅርንጫፍ ኦፊሰርና አቶ አብዲሳ ደቦ ቡልቱሜ የባንኩ የሰው ኃይል አስተዳዳር ባለሙያ ናቸው፡፡
ተከሳሾቹ ከላይ የተጠቀሰውን ሁለት ሚሊዮን ብር ጉቦ የጠየቋቸው አቶ ዮሐንስ ባለመስማማታቸው፣ አንደኛ ተከሳሽ አቶ መሠረት አደራዳሪ መስሎ ነጋዴውን በመቅረብ፣ ‹‹ኦዲተሮቹ ብዙ ገንዘብ መቀበል ስለለመዱ አንተ ሁለት መቶ ሺሕ ብር ብትሰጣቸው ምንም አይደለም፤›› ቢላቸውም ተበዳዩ አለመስማማታቸውን ክሱ ይጠቁማል፡፡
የነጋዴውን አለመስማማት የተረዱት ተከሳሾች ያላቸውን ዕቃ ብዛት በጽሑፍ እንዲያቀርቡ ጠይቀዋቸው እንደሰጧቸው የሚገልጸው የዓቃቤ ሕግ ክስ፣ በዝርዝር የሰጡት ዕቃ ጉድለት እንደሚያመጣና ጠቅላላ የዕቃውን ብዛት እንዳልሰጧቸው ሲገልጹላቸው፣ ተበዳዩም ካልተቆጠረ እንደማይታወቅ በመግለጽ እንደተከራከሯቸው ክሱ ያስረዳል፡፡
የግል ተበዳዩን በተለያየ መንገድ ስላስጨነቋቸው ግንቦት 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ለአንደኛ ተከሳሽ አራት መቶ ሺሕ ብር መስጠታቸውን፣ በድጋሚ በተለያዩ ቀናት በድምሩ ሁለት መቶ ሺሕ ብር መስጠታቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡ ተከሳሾቹ ሰነዱን ሲመረምሩ ተበዳዩ 12 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ከፍተኛ ዕዳ እንደሚመጣባቸው ማወቃቸውን በመንገር፣ ተበዳዩን በማስጨነቅ አራት መቶ ሺሕ ብር እንዲሰጧቸው ማድረጋቸውን፣ በአጠቃላይ በተለያዩ ቦታዎች በመቅጠር ተከሳሾች ከተበዳይ 1.2 ሚሊዮን ብር መቀበላቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡
አቶ መሠረት የተባለው ተከሳሽ ጉቦ በመቀበል ያገኘውን ገንዘብ ለመሰወርና ለመደበቅ፣ አምቦ ከተማ ለሚኖረውና ለአራተኛ ተከሳሽ ወንድሙ አቶ ሀብታሙ አምስት መቶ ሺሕ ብር መስጠቱ በክሱ ተጠቅሷል፡፡ አቶ ሀብታሙ የገንዘቡ አመጣጥ ሕገወጥ መሆኑን እያወቀ፣ አምቦ ከተማ ቀበሌ 02 ውስጥ ስፋቱ 200 ካሬ ሜትር ቦታ በ140 ሺሕ ብር በእናቱ ስም እንደገዛለት፣ 100 ሺሕ ብር ደግሞ ለሌላ ግለሰብ እንዲያስቀምጥለት መስጠቱን ክሱ ያብራራል፡፡ አቶ አበበ ደግሞ ለአቶ አብዲሳ 287,900 ብር ሲሰጠው ገንዘቡን መሬት ውስጥ መቅበሩን፣ አቶ አያና የተባለው ሦስተኛ ተከሳሽ ደግሞ በአምቦ ከተማ 400 ካሬ ሜትር መሬት በ80 ሺሕ ብር በመግዛት በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ ለማሰመሰል መሥራታቸውን ክሱ ያብራራል፡፡
በአጠቃላይ ተከሳሾቹ ፈጽመዋል በተባለው ጉቦ መቀበል ከባድ የሙስና ወንጀልና በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ የሙስና ወንጀል የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ መሥርቶባቸዋል፡፡
የኢትዮጵያው ጤፍ ወደ አሜሪካ ገበያዎች እየገባና ተወዳጅነትም እያገኘ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡
ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሳምንት መስተዳድሩ የባጃጅ አሽከርካሪዎችን በተመለከተ ያወጣውን ህግ የተቃወሙ አሽከርካሪዎች የ3 ቀናት የስራ ማቆም አድማ ካደረጉ በሁዋላ፣ የተወሰኑ አሽከርካሪዎች ተይዘው ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ለኢሳት ተናግረዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አሽከርከሪዎች እንደሚሉት ፣ ወደ እስር ቤት ከተወሰዱ በሁዋላ ጨማቸውን አውልቀው፣ እጆቻቸው በሲባጎ ገመድ ወደ ሁዋላ ታሰሮ የወስጥ እግራቸውን …
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)
የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳ ኢትዮጵያ ውስጥ በተካሄደው የ«ባላገሩ ምርጥ» የሙዚቃ ዉድድር በድምፅ አሸናፊ የሆነው ዳዊት ፅጌ ነው።