የኢትዮጵያ መንግሥትና የቢቢሲ ውዝግብ


በዘንድሮው ድርቅ ምክንያት የደረሰው የምግብ እጥረት በምንም ዓይነት ከ1975ቱ ጋር የሚመሳሰል አይደለም ሲል ለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡ ኤምባሲው ትናንት ባወጣው መግለጫው በተጨባጭ ያለው ሁኔታ ምዕራባዊያን የዜና አውታሮች እያወጡ ካሏቸው ዘገባዎች ጋር ተቃራኒ ነው ብሏል፡፡

ቢቢሲ በሚል የእንግሊዝኛ መጠሪያ ስሙ ምኅፃር የሚታወቀው የእንግሊዝ የዜና ማሠራጫ አውታር ሰሞኑን ባወጣው አንድ የቴሌቪዥን ሪፖርት ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም ወሎ – ቆቦ አካባቢ ዘንድሮ የደረሰ ድርቅ የከበደ ረሃብ ማስከተሉን ዘግቧል፡፡ ያዳምጡ → Listen