ለአባይ ግድብ በግድ መዋጮ እንዲከፍሉ የተገደዱ ሰራተኞች በፍርድ ቤት ክስ ከፈቱ

ኢሳት ዜና :- በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ የግብርና ፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ቻላቸው ሞላ የግብርና ባለሙያ ሰራተኞችን ሳያነጋግሩና ፈቃዳቸውን ሳይጠይቁ፣ ከተወሰኑ ሀላፊዎች ጋር በመመካር የግብርና ባለሙያዎች በሙሉ ለአባይ ግድብ እንዲከፍሉ አድርገዋል። የግብርና ባለሙያዎች ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት መውሰዳቸው ታውቋል።