Tag: Ethiopians
በአማሳኞች በደል እና በፍትሕ ዕጦት የተመረሩ ምእመናን ርምጃ መውሰድ ጀመሩ፤ በቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ሓላፊዎችን በማስወጣት እና መኪኖቻቸውን በማገት ጽ/ቤቱን ተቆጣጠሩ
አስተዳደሩ፣ በሕገ ወጥ ኪራይ የደብሩን ጥቅም ለሦስተኛ ወገን አሳልፎ በመስጠት ይታወቃል ጽ/ቤቱን አስበይደው በማሸግ የተቆጣጠሩት ምእመናኑ የተመሩት በሰንበት ት/ቤቱ አባላት ነው * * * በመ/ፓ ቅ/ቅ ማርያም፣ የሒሳብ ፈራሚነቱን ለቄሰ ገበዙ ለማሳለፍ የተደረገው ጥረት ከሽፏል ሒሳብ ሹሙ ‹‹ጉረሮዬን ዘግተኽ አትኖርም›› እያለ በምእመኑ ተወካይ ላይ ሲዝት ሰንብቷል * * * በደ/ሲና እግዚአብሔር አብ ያለደንቡ የታሰበው የሰ/ት/ቤት …![]()
በቡሌ ሆራ የኒቨርስቲ ተቃውሞ አስነስታችሁዋል የተባሉ ተማሪዎች ታገዱ
ሰኔ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ በዩኒቨርስቲው ውስጥ ግጭት ከተፈጠረ በሁዋላ የዩኒቨርስቲው አስተዳደር ለግጭቱ መነሳት መንስኤ ሆነዋል፣ ጥቃትም ፈጽመዋል ያላቸውን ሁለት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው አግዷል። ተማሪዎቹ ከዛሬ ጀምሮ ዩኒቨርስቲውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል። አንደኛው ተማሪ የዩኒቨርስቲውን ፕሬዚዳንት መኪና በድንጋይ ወረውሮ ሰብሯል የሚል ክስ ሲቀርብበት ሌላው ተማሪ ደግሞ ጩቤ ይዞ ተገኝቷል የሚል …
አቃቢ ህግ በእስር ላይ በሚገኙ ታዋቂ ፖለቲከኞች ላይ ምስክሮችን ማሰማት ጀመረ
ሰኔ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ በተከሰሱት በአብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሽና ሌሎች ስድስት ተከሳሾች ላይ አቃቤ ህግ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አቅርቦ ማሰማት ጀምሯል። አቃቢ ህግ “ምስክሮቼ ዛቻና ማስፈራሪያ ደርሶባቸዋል” በሚል ችሎቱ ምስክሮችን በዝግ እንዲያሰማ እንዲፈቅድለት ጠይቋል። ተከሳሾች በበኩላቸው የአቃቢ ህጉን መከራከሪያ አጥብቀው መቃወማቸውን …
ርዕሳነ መምህራን መብታችን አልተከበረልንም አሉ
ሰኔ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ርዕሳነ መምህራን በልዩ ልዩ ምክንያት ከቦታቸው ሲነሱ በአስተማሪነት የሚያገለግሉ ቢሆንም በዲግሪ ሲከፈላቸው የነበረው ደመዎዝ ተቀንሶ በዲፕሎማ ፣በሁለተኛ ዲግሪ የተመርቁ ደግሞ በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሰሩ በመደረጋቸው እንዲሁም በራሳቸው ጥረትና ገንዘብ ዲግሪያቸውን የያዙ መምህራን በተመረቁበት የትምህር ዓይነት ማስተማር ባለመቻላቸው መምህራኑ ዲግሪያቸውን እንደተቀሙ እንደሚቆጥሩት ተናግረዋል፡፡ ቅሬታ አቅራቢ ርዕሳነ መምህራኑና መምህራኑ …
የኢህአዴግ ካድሬዎች ግብዣ ላይ እርስ በእርሳቸው ተደባደቡ
ሰኔ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየካ ክፍለ ከተማ የግንቦት 16/2007 ዓ.ም የምርጫ ውጤት እንዲሁም የግንቦት 20 በዓልን ለማክበር ግንቦት 292007 ዓ.ም ባዘጋጀው ግብዣ ላይ የኢህአዴግ ካድሬዎች እርስ እርሳቸው መደባደባቸውን ምንጮች ገለጸዋል፡፡ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 መሰብሰቢያ አዳራሽ በተደረገው ግብዣ ብዙ ወጭ የፈሰሰበትና በርካታ የኢህአዴግ ካድሬዎች የተገኙበት እንደነበር የገለፁት ምንጮቹ፣ ስጋና ሌሎች ለግብዣው …
የሰኔ 1 ሰማዓታት ተዘከሩ
ሰኔ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የ1997 ዓም ምርጫ ተከትሎ በአጋዚ ወታደሮችና በፌደራል ፖሊስ አባላት የተገደሉ ኢትዮጵያውያን እየተዘከሩ ነው። በአቶ ማሙሸት አማረ የሚመራው መኢአድ ለሰማአታቱ 10 ሻማዎችን በማብራት ዕለቱን አስቦ የዋለ ሲሆን፣ በእስር ላይ የሚገኙ መሪዎችና አባላቱ እንዲፈቱ ከመጠየቅ በተጨማሪ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። ኢትዮጵያውያን የሰማዓታቱን ፎቶ ግራፎች በፌስቡክና በማህበራዊ ድረገጾች በመለጠፍ እየዘከሩዋቸው ነው። …
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኤርትራ በሰው ልጅ ላይ የሚፈጸም ወንጀል ሳትፈጽም እንደማትቀር ገለጸ
ሰኔ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጀቱ ለአንድ አመት ሲያካሂድ የነበረውን ጥናት በሚቀጥሉት 2 ሳምንታት ውስጥ ይፋ የሚያደርግ ሲሆን፣ በሪፖርቱ የኤርትራ መንግስትን ይወቀሳል። የኤርትራ ህዝብ ከህግ ይልቅ በፍርሃት ነው የሚገዛው የሚለው ድርጅቱ፣ ከፍርድ ቤቶች እውቅና ውጭ ሰዎች በዘፈቀደ ይገደላሉ ብሎአል። ወጣቶች አገራቸውን ጥለው እንደሚሰደዱና ገደብ ለሌለው ብሄራዊ ውትድርና አግልግሎት እንደሚሰጡ ሪፖርቱን ዋቢ በማድረግ የተለያዩ …
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ሰኔ 08, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና
በዝግ ችሎት ምስክሮችን የምትሰሙ ከሆነ ዛሬውኑ የግፍ ፍርደኞች ሆነን ወደ እስር ቤት ለመመለስ ዝግጁዎች ነን፤ ከዚህ በኋላም አንዳችንም ክርክር አናደርግም፡፡››አቶ ሀብታሙ አያሌው
በሽብርተኝነት ተከሰው ጉዳያቸው እየታየ የሚገኙት የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች ላይ የአቃቤ ህግ ምስክሮች መሰማት ተጀመረ፡፡ በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተካተቱት አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሽና ሌሎች ስድስት ተከሳሾች ላይ አቃቤ ህግ አሉኝ ያላቸውን የሰው ማስረጃዎች ምስክርነት ዛሬ ሰኔ 01/07 ዓ.ም በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ማሰማት ጀምሯል፡፡ ምስክሮች መሰማት ከመጀመራቸው […]![]()
‹ከ500 በላይ ሰራተኞች ከወርልድ ቪዥን ሊለቁ ይችላሉ ተባለ
‹‹ከ500 በላይ ሰራተኞች ከወርልድ ቪዥን ሊለቁ ይችላሉ፡፡እስካሁን 170ሰራተኞች መልቀቂያ አስገብተዋል፡፡››ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ሰራተኛ። መንግስት ባወጣው አስገዳጅ ህግ ምክንያት ከ500በላይ ሰራተኞቹን ሊያጣ መሆኑንና በአሁኑ ወቅት 170ሰራተኞች መልቀቂያ ማስገባታቸው እየተነገረ ነው፡፡በ2012(2004) ዓም በወጣው የማሃበራዊ ዋስትና አዋጅ መሰረት የጡረታ ፈንድ ተቋቁሞ ሁሉም ሰራተኛ ማሃበራዊ ዋስትና እንዲኖረው ሲደረግ የዕርዳታ ድርጅቶች ደግሞ ከፕሮቪደንት ፈንድ እና ከጡረታ እንዲመርጡ መደረጉ ይታወሳል፡፡በዚህም መሰረታ […]![]()
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ሰኔ 07, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡
ሰበር ዜና – በሰሚት መድኃኔዓለም የሰንበት ት/ቤት አባላት እስር ወደ ምእመናን ተሸጋገረ፤ በአንድ ሳምንት ለሦስተኛ ጊዜ የተፈጸመ ነው
‹‹ጉዳዩን በፌስቡክ እያጋጋላችኹ ነው›› የተባሉ 16 የሰንበት ት/ቤት አባላትና ምእመናን ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል በሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መመሪያ፣ ያለው ፈርሶ በአዲስ ምዝገባ በሚቋቋመው ሰንበት ት/ቤት ዕድሜአቸው ከ30 በላይ የኾኑ ይባረራሉ ‹‹አዲስ ሰንበት ት/ቤት እንዲቋቋም ያዘዝኹት እኔ ነኝ፤ ዑራኤል ጸሐፊ ኾኜ 700 ሰንበት ተማሪ በትጥቅ ድጋፍ አስበትኛለኹ››/ሥ/አስኪ. ሊ/ማእ. የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ/ በአዲስ አበባ […]![]()
ሳምንታዊ ዜናዎችናን ከDCESON ሬዲዮ ይከታተሉ
የጎንደር ህዝብ ድምፃችን ተሰርቃል በሚል ተቃውሞ ሰልፍ ማድረጉ ተነገረ የአየር ንብረት ለውጥ አፍሪካን እየጠቀመ ነው የሚል አንድ አወዛጋቢ የጥናት ውጤት ይፋ ሆነ የወያኔ መከላከያ ሠራዊት እየፈረሰ የትጥቅ ትግሉን በመቀላቀል ላይ ነው፡፡ የተዳከመውን የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ለማጠናከር ሲባል የተባረሩት አመራሮች እንዲመለሱ መስማማታቸውን ተገለፀ፣ POSTED BY ASEGED TAMENEFiled under: NEWS Tagged: Addis Ababa, Addis Ababa University, Africa, […]![]()
ኢህአዴግ ካባረራቸው አባላቱ ጋር ለእርቅ እየተነጋገረ ነው

Ethiopia Zare (እሁድ ግንቦት 29 ቀን 2007 ዓ.ም. June 7, 2015)፡- የትግል ታሪኩ ጥንካሬ በገዛ አባላቱ ተጋኖ የሚነገርለት ኢህአዴግ ሥልጣን ይዞ በቆየበት 24 ዓመታት ለህልውናው አስጊ የሆኑ ፈታኝ ጊዚያቶች በተደጋጋሚ አሳልፏል። ከእነዚህ ውስጥ በ1993 ዓ.ም. አመራሩ ለሁለት ተሰንጥቆ በነበረበት ጊዜ የደረሰው ውጣውረድ፣ በቀድሞው ጠ/ሚንስትር ሞት የደረሰው ክፍተት እንዲሁም የ1997ቱ ምርጫ ባስከተለው ህዝባዊ ዓመጽ መሬት ነክቶ የመመለሱ አደጋ የሚጠቀሱ ናቸው።
በሁለት የዓባይ ተፋሰስ ገባር ወንዞች ላይ 2026 ሜጋ ዋት የኃይል ማመንጫ ሊገነባ ነው

መንግሥት ለዓባይ ተፋሰስ ገባር በሆኑ ሁለት ወንዞች ላይ በድምሩ 2,026 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኑ ታወቀ፡፡
የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ ዓለማየሁ ተገኑ ግንቦት 18 ቀን 2007 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት የበጀት ዓመቱ የአሥር ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ በሚቀጥለው ዓመት ሊተገበሩ የታቀዱትን የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ይፋ አድርገዋል፡፡
የሚኒስትሩ ሪፖርት እንደሚያስረዳው፣ ቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተጠኑ ካሉ ፕሮጀክቶች መካከል በታምስ ወንዝ ላይ በጋምቤላ ክልል ውስጥ የሚገነባው 1,700 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ታምስ ኃይድሮ ፓወር ፕሮጀክት አንዱ ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ በዳቡስ ወንዝ ላይ የሚገነባውና 326 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የዳቡስ አንድ ኃይድሮ ፓወር ፕሮጀክት መሆኑን በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡ የሁለቱም የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ዝርዝር ጥናት በመካሄድ ላይ መሆኑንና የታምስ ኃይድሮ ፓወር ፕሮጀክት ዝርዝር ጥናት 81 በመቶ መከናወኑን፣ የዳቡስ አንድ ኃይድሮ ፓወር ፕሮጀክት ደግሞ 71 በመቶ መከናወኑን ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡
በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጡ ሪፖርተር ጥያቄ ያቀረበላቸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የፕላንና ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ መኩሪያ ለማ፣ የታምስ ኃይድሮ ፓወር ፕሮጀክት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሸካ ተራራ አናት የሚመነጨውና በጋምቤላ አድርጐ የባሮ ወንዝን፣ በመቀጠልም ከነጭ ዓባይ ተፋሰስ ጋር የሚቀላቀለው የታምስ ወንዝ ላይ የሚገነባው ነው፡፡ የታምስ ወንዝ ባሮ ወንዝን ከመቀላቀሉ በፊት በጋምቤላ ክልል ኃይል አመንጭቶ እንዲያልፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡
ይህንንም እውን ለማድረግ በኢትዮጵያ ውኃ ሥራዎች ዲዛይን ድርጅትና በአንድ የጣሊያን ኩባንያ ዝርዝር ጥናቱ በመከናወን ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የዚህ ፕሮጀክት አጠቃላይ ወጪ ምን ያህል ይሆናል የሚለው ዝርዝር ጥናቱ ሲጠናቀቅ እንደሚታወቅ አስረድተዋል፡፡ ከታምስ ኃይድሮ ፓወር ፕሮጀክት የማመንጨት አቅም በመጠኑ ብልጫ ያለውና በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክት ግንባታው ከ90 በመቶ በላይ የተጠናቀቀው 1,870 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሲጀመር፣ የተያዘለት በጀት 1.8 ቢሊዮን ዶላር እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይህ ፕሮጀክት ከተጀመረ አምስት ዓመታትን ያሳለፈ ቢሆንም፣ የታምስ ኃይድሮ ፓወር ፕሮጀክት አጠቃላይ ወጪ ማነፃፀሪያ ተደርጎ ይገመታል፡፡
የዳቡስ ኃይድሮ ፓወር ማመንጫ ፕሮጀክት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልን በወለጋ በኩል ከኦሮሚያ በሚያዋስን አካባቢ በሚፈሰው የዳቡስ ወንዝ ላይ የሚገነባ ነው፡፡ ይህ ወንዝ የጥቁር ዓባይ ገባር ሲሆን፣ ዓባይን ከመቀላቀሉ በፊት ቤንሻንጉልን ከወለጋ በሚያዋስነው አካባቢ 326 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያመነጭ ታቅዶ፣ የፕሮጀክቱ ጥናት በመካሄድ ላይ መሆኑን አቶ መኩሪያ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ይህ ፕሮጀክት በመንግሥት ቅድሚያ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን፣ በመጀመሪያ ጥናቱ 628 ሚሊዮን ዶላር በጀት ያስፈልገዋል ተብሎ እንደተገመተ፣ ነገር ግን ትክክለኛ ወጪው የተጀመረው ዝርዝር ጥናት ሲጠናቀቅ የሚታወቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
መንግሥት ዘንድሮ በሚጠናቀቀው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ከአምስት ዓመት በፊት በአገሪቱ የነበረውን አጠቃላይ 2,000 ሜጋ ዋት የኃይል አቅርቦት ወደ 10,000 ሜጋ ዋት ለማሳደግ አቅዶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የዕቅድ ዘመኑ ሊጠናቀቅ የአንድ ወር ዕድሜ እየቀረው በተግባር ማቅረብ የቻለው ተጨማሪ ኃይል 310 ሜጋ ዋት መሆኑን፣ ሚኒስትሩ አቶ ዓለማየሁ ለፓርላማ ያቀረቡት ሪፖርት ያስረዳል፡፡
ይሁን እንጂ በዕቅድ ዘመኑ ይጠናቀቃሉ ተብለው የተገመቱት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች አማካይ አፈጻጸማቸው ከ60 በመቶ በላይ በመሆኑ፣ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ የኃይል አቅርቦት ወደ አገሪቱ የኃይል ማስተላለፊያ ቋት ይገባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተለይ 1,870 ሜጋ ዋት የሚያመነጨው ጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትና 254 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ገናሌ ሦስት ፕሮጀክት በግንቦት ወር ውስጥ የነበራቸው አጠቃላይ የፕሮጀክት አፈጻጸም 90.27 በመቶ እና 73.82 በመቶ በመሆኑ፣ በ2008 ዓ.ም. 2,521 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ወደ ሥርጭት ሥርዓት ውስጥ እንደሚገባ ይገመታል፡፡
ከቀሪዎቹ መካከል የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 6,000 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም፣ ከቆሻሻና ከጂኦ ተርማል ኃይል ለማመንጨት ከተጀመሩት ፕሮጀክቶች የአፈጻጸም ደረጃ በመነሳት፣ እስከ ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ማገባደጃና እስከ 2009 ዓ.ም. እንደ ቅደም ተከተላቸው እንደሚጠናቀቁ ይጠበቃል፡፡
ከእነ አቶ መላኩ ፈንታ የሙስና ክስ ጋር ግንኙነት እንደነበራቸው በተጠረጠሩ አምስት ድርጅቶች ላይ ምርመራ እየተካሄደ ነው
–ከጁባ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ 20 ሚሊዮን ብር የመዘበሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ
በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ከሁለት ዓመት በላይ ካስቆጠሩት፣ የቀድሞው የገቢዎችና ጉምሩክ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ጋር የተያያዙ ሌሎች አምስት የንግድ ተቋማት ላይ ክስ ለመመሥረት በምርመራ ላይ መሆኑን፣ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የቀድሞ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር በነበሩት አቶ መላኩ ፈንታና በምክትላቸው አቶ ገብረዋህድ ገብረጊዮርጊስ እንዲሁም በሌሎች የባለሥልጣኑ ሠራተኞችና በንግድ ሥራ በተሰማሩ የግል ተቋማት ባለሀብቶች ከግብርና ከታክስ ጋር በተገናኘ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ በግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. እንደነበር ይታወሳል፡፡ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ረጅም የምርመራ ጊዜ ቢወስድም ክስ ከተመሠረተባቸውና ክርክር ከተጀመረ ከዓመት በላይ አስቆጥሯል፡፡ በአሁኑ ወቅት ጉዳዩን በማየት ላይ የሚገኘው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዓቃቤ ሕግ ምስክርን በመስማት ላይ ይገኛል፡፡
የእነ አቶ መላኩ ፈንታና ሌሎች የባለሥልጣኑ ሠራተኞችና ባለሀብቶች የክስ ሒደት ከላይ በተገለጸው ደረጃ ላይ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት፣ የ11 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበው የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ ከእነ አቶ መላኩ ፈንታ የወንጀል ምርመራ ጋር የተያያዙ ናቸው ያላቸው አምስት ድርጅቶች በመንግሥት ላይ የ361.6 ሚሊዮን ብር ጉዳት እንዳደረሱ በማረጋገጥ፣ በተጨማሪ ምርመራ ላይ እንደሚገኝ ለምክር ቤቱ አሳውቋል፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌማን ባለፈው ሐሙስ ለፓርላማው ባቀረቡት ሪፖርት፣ ‹‹በቀድሞ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣናት፣ አንዳንድ የባለሥልጣኑ ሠራተኞችና ከፍተኛ ነጋዴዎች ላይ ተጀምሮ ከነበረው ምርመራ ጋር በተያያዘ የአገር ውስጥ ግብርና የጉምሩክ ቀረጥ ባለመክፈል በተጠረጠሩ አምስት የግል ኩባንያዎች ላይ የኢንስፔክሽን ኦዲት በማስደረግ በተገኘው ማጣራት፣ 361.6 ሚሊዮን ብር የመንግሥት ታክስ አለመከፈሉ በመረጋገጡ ምርመራው እየተከናወነ ይገኛል፤›› ብለዋል፡፡
ኮሚሽነሩ ባቀረቡት ሪፖርት የተጠረጠሩትን ድርጅቶች ማንነት አልገለጹም፡፡ የድርጅቶቹን ማንነት ለማጣራት ሪፖርተር ያደረገው ሙከራም አልተሳካም፡፡ ይሁን እንጂ የፀረ ሙስና ኮሚሽን በእነ አቶ መላኩ ፈንታና በሌሎች ባለሀብቶች ላይ ክስ በመሠረተበት ወቅት፣ ምርመራ የተደረገባቸውና ክስ ያልተመሠረተባቸው 15 የግል ኩባንያዎች መኖራቸው ይታወቃል፡፡
እነዚህም ኒያላ ሞተርስ፣ ፔትራም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ ሞኤንኮ፣ ጌትአስ ትሬዲንግ፣ አልሳም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ ሜቴክ፣ አይካ አዲስ ትሬዲንግ፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ፣ ሆላንድ ካርስ፣ ቶታል ኢትዮጵያ፣ ሚድሮክ፣ ሳሊኒ ኮንስትራክሽን፣ ድሬ ኢንዱስትሪያል ትሬዲንግ፣ ኢትዮ ሌዘር፣ ኢትዮ ቆዳ ፋብሪካ አክሲዮን ማኅበር ናቸው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኮሚሽኑ በሌሎች በጠረጠራቸው የሙስና ወንጀሎች ላይም ምርመራ እያደረገ መሆኑን ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡
ቦሌ ክፍለ ከተማ በሐሰተኛ ማስረጃ መሬት እንዲያገኙ ተደርጓል በሚል በቀረበ ጥቆማ፣ 89 የመሬት ጉዳዮች ላይ ምርመራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት በተለያዩ የግንባታ ሳይቶች ለሚከናወኑ ግንባታዎች የሚውሉ ጠጠር፣ ፕሪካስትና ብሎኬት ግዥ ጋር በተያያዘ አምስት ሚሊዮን ብር ጉዳት በማድረስ በተጠረጠሩ ሠራተኞችና አቅራቢዎች ላይ ምርመራ እየተከናወነ መሆኑን የኮሚሽኑ ሪፖርት ያስረዳል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በደቡብ ሱዳን (ጁባ) ቅርንጫፍ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በመመሳጠር ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ በመውሰድ ለግል ጥቅም በማዋላቸው፣ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ሆነው ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡
የግል ድርጅቶች የጡረታ አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ ተቃውሞ አስነሳ
በፕሮቪደንት ፈንድ የታቀፉ የግል ድርጅት ሠራተኞችን በመንግሥት በሚተዳደረው የግል ድርጅቶች ጡረታ እንዲዘዋወሩ የሚያስገድድ ማሻሻያ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡ፣ በግል ድርጅቶች ሠራተኞች ዘንድ ተቃውሞ ቀሰቀሰ፡፡
የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ 7/5/2003 በሐምሌ ወር 2003 ዓ.ም. ተግባራዊ መሆን ከመጀመሩ በፊት፣ የፕሮቪደንት ፈንድ ሽፋን ያላቸው የግል ድርጅት ሠራተኞች በነበራቸው የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚነት ለመቀጠል እንዲወስኑ፣ ወይም በግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ስለሚሸፈኑበት ሁኔታ ሊስማሙ እንደሚችሉ ይደነግጋል፡፡
በዚህ የተነሳም በአገሪቱ የሚገኙ በርካታ የግል ድርጅቶች ሠራተኞች በተሰጣቸው አማራጭ ላይ ውይይት በማድረግ በፕሮቪደንት ፈንድ መታቀፍን መምረጣቸው ይታወሳል፡፡ ነገር ግን ከአራት ዓመት በኋላ ባለፈው ሐሙስ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ማሻሻያ አዋጅ የቀድሞውን አማራጭ በማስቀረት፣ ሁሉም የግል ድርጅቶች ሠራተኞች በጡረታ ዕቅድ እንዲሸፈኑ ማሻሻያ አቅርቧል፡፡
ማሻሻያው በዚህ ላይ ብቻ ሳይሆን የግል ኩባንያ ባለቤቶች በግል ድርጅቶች ሠራተኞች የጡረታ ዐቅድ ሥር እንዲታቀፉ፣ እንዲሁም ከአሥር ዓመት በታች ያገለገሉ የግል ድርጅት ሠራተኞች በሚለቁበት ወቅት ቀደም ሲል ይፈቀድ የነበረውን ክፍያ ያስቀራል፡፡
በጉዳዩ ላይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንድ የግል ባንክ ኃላፊ፣ አሁን በሥራ ላይ በሚገኘው የግል ድርጅቶች ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ በሚፈቅደው መሠረት፣ በሁሉም ቅርንጫፎች የሚገኙ ሠራተኞች በፕሮቪደንት ፈንድ እንዲታቀፉ በፍላጎታቸው መምረጣቸውን ገልጸዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ለፓርላማ በመቅረቡ ግን ከሠራተኞች ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት እያደረጉ መሆኑንና ውሳኔ ለመወሰን መቸገራቸውን አስረድተዋል፡፡
ለዚህ የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ በፕሮቪደንት ፈንድ ወይም ቀድሞ በነበራቸው ጡረታ ለመቀጠል ተስማምተው ሲቆጥቡ የነበሩ ሠራተኞች፣ የፕሮቪደንት ፈንድ ወደ ግል ድርጅቶች ሠራተኞች ጡረታ ፈንድ እንደሚዘዋወር በረቂቅ አዋጁ የተካተተ በመሆኑ ቢፀድቅ የሕግ ተጠያቂነትን ያስከትል እንደሆነ ከሕግ ባለሙያዎች ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
አንድ ስማቸውንም ሆነ የሚሠሩበትን መሥሪያ ቤት መጥቀስ ያልፈለጉ ሥራ አስኪያጅ ‹‹እንዴት በሕግ የተሰጠን መብት ተጠቅመው ፕሮቪደንት ፈንድን የመረጡ ሠራተኞችን ገንዘብ ለመውሰድ መንግሥት ሕግ ያወጣል?›› ሲሉ ድርጊቱን ተችተውታል፡፡
በማከልም ጉዳዩ የሠራተኞችን መብት መደፍጠጥ እንደሆነና መንግሥት ማድረግ የነበረበት ለፕሮቪደንት ፈንድ የማኅበራዊ ዋስትና የሕግ ከለላ በመስጠት፣ በቀጣሪዎች እንዳይመዘበር መቆጣጠር ነበረበት በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የግልግልና ዳኝነት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተርና የሕግ ባለሙያው አቶ ዮሐንስ ወልደ ገብርኤል፣ በረቂቅ አዋጁ ላይ የግል አስተያየታቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ አቶ ዮሐንስ አስተያየታቸውን መስጠት የጀመሩት፣ የግል ጡረታ ቦርድ ውስጥ የግል ባለሀብቶች እንዲወከሉ በሕጉ የተቀመጠ መሆኑን አስታውሰው፣ በዚህ ቦርድ ውስጥ የግሉ ዘርፍን በመወከል የተቀመጠ ሰው በዚህ ረቂቅ ማሻሻያ ላይ በስምምነት ፈርሞ ከሆነ፣ የግሉን ዘርፍ የሚወክል ግለሰብ ነው ብለው እንደማያምኑ በመግለጽ ነው፡፡ ‹‹እነዚህ ተወካዮች የግሉን ዘርፍ የሚወክሉ ናቸው ብዬ አላምንም፡፡ ምክንያቱም የግሉ ዘርፍ የመንግሥት ተጧሪ የመሆን ፍላጐት አለው ብዬ አላምንም፤›› ብለዋል፡፡
በ2003 ዓ.ም. ፀድቆ ወደ ሥራ የገባው የግል ድርጅቶች ጡረታ አዋጅ ቀደም ሲል በፕሮቪደንት ፈንድ ወይም በጡረታ ዐቅድ ተሸፍነው የነበሩ ሠራተኞች፣ ከፕሮቪደንት ፈንድና ከጡረታ ዐቅድ እንዲመርጡ በተሰጣቸው ዕድል ነፃ ውይይት አድርገው ፕሮቪደንት ፈንድን ይጠቅመናል ብለው መወሰናቸውን አቶ ዮሐንስ ይገልጻሉ፡፡ ‹‹የግሉ ዘርፍ ሠራተኞች ውሳኔ እንዳልወሰኑ አድርጐ በመውሰድ እንደገና ወደኋላ ሄዶ ሠራተኛው የወሰነውን ውሳኔ መሻር የሕግ መርሆዎችን የሚጥስ ነው፤›› ብለዋል፡፡
‹‹በንጉሡ ጊዜ ፀረ አብዮት ወንጀል ፈጽመሃል፤›› ተብለው በደርግ ጊዜ ሰዎች እንደሚከሰሱ ገልጸው፣ ይህንንም ረቂቅ አዋጅ ከዚህ ሥርዓት ጋር አነፃፅረውታል፡፡ ሌላው አቶ ዮሐንስ ያነሱት በዚህ ረቂቅ አዋጅ ላይ የግል ኩባንያ ባለሀብቶች በጡረታ ዐቅድ እንዲታቀፉ ማሻሻያ ማቅረቡ ትክክለኛነት ላይ ነው፡፡
የኩባንያ ባለቤቶች ወይም ባለሀብቶች በርካታ የማኅበራዊ ዋስትና አማራጮች እንዳሏቸው፣ ከእነዚህም መካከል የጡረታ ኢንሹራንስ ሊገዙ እንደሚችሉና ሌሎች የመሳሰሉትን ማድረግ እንደሚችሉ እየታወቀ፣ መንግሥት የራሱ ተጧሪ ሊያደርጋቸው መፈለጉ አስገራሚ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ የግል ድርጅት ማለት በኢትዮጵያውያን ብቻ የተያዘ አለመሆኑንና ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ዜጎች ያቋቋማቸው ኩባንያዎችም እንዳሉ የሚገልጹት የሕግ ባለሙያው፣ እነዚህ የውጭ ዜጎች በአገራችው የተሻለ የማኅበራዊ ዋስትና ሽፋን የሚያገኙ ሆነው ሳለ መንግሥት እነዚህንም ተጧሪ ለማድረግ ማሰቡ አስደናቂ ነው ብለዋል፡፡
መንግሥት ይህንን ማሻሻያ እያደረገ የሚገኘው ካለው ከፍተኛ የገንዘብ ፍላጎት አንፃር እንደሆነ እንደሚገምቱ የሚገልጹት ባለሙያው፣ ‹‹መንግሥት ያልተረዳው ከመንግሥት የተሻለ አገር የሚያለማው የግል ባለሀብቱ መሆኑን ነው፤›› ሲሉ ተከራክረዋል፡፡
ይህ ረቂቅ ማሻሻያ ሙሉ አይደለም ብለው የሚከራከሩበት ሌላው ነጥብ የጡረታ ሽፋን ያላቸው የቤተሰብ መሪዎች፣ ‹‹የተሽከርካሪ አደጋ ሊሆን ይችላል ወይም በፍትሕ እጦት በሚደርስ የሕግ ተጠያቂነት ለእስር በሚዳረጉበት ወቅት፣ የእሱን ወይም የእሷን እጅ ጠበቀው የሚኖሩ ቤተሰቦቹን የማይሸፍን ጎደሎ ነው፤›› ብለውታል፡፡
እንደ ደቡብ አፍሪካ፣ ግብፅና ሞሪታንያ የመሳሰሉ አገሮች በተገለጸው ዓይነት ችግር ለሚፈጠር የቤተሰብ ቀውስ ‹‹የቤተሰብ አበል›› የሚል ዋስትና እንዳላቸው፣ ይህ ማሻሻያ የሚፀድቅ ከሆነ ይህንን ነጥብ ሕግ አውጪው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡
ፓርላማው ባለፈው ሐሙስ በአዋጁ ላይ አጭር ውይይት ካደረገ በኋላ ጉዳዩን ለሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዋናነትና፣ በተደራቢነት ደግሞ ለሕግ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ መርቶታል፡፡
የሸራተን አዲስ ዋና ሥራ አስኪያጅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ሸራተን አዲስን ከ16 ዓመታት በላይ በዋና ሥራ አስኪያጅነት ሲመሩ የቆዩት፣ የዴንማርክና የፈረንሣይ ጥምር ዜግነት እንዳላቸው የሚነገረው ሚስተር ዢያን ቪ. ማኒጐፍ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡
ከሸራተን አዲስ ማኔጅመንት የወጣው መረጃ እንደሚያስረዳው፣ ሚስተር ማኒጐፍ ላለፉት ወራት በከባድ ሕመም ሲሰቃዩ ከርመው በቅርቡ በሕክምና እየተረዱ ባሉበት አሜሪካ ሕይወታቸው አልፏል፡፡
ከ20 ዓመታት በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደኖሩና ላለፉት 16 ዓመታት ሸራተን አዲስን ሲመሩ የነበሩት ሚስተር ማኒጐፍ፣ የአርመን ዝርያ እንዳላቸውም ተጠቁሟል፡፡
ዋና ሥራ አስኪያጁ ሆቴሉን እየመሩ በቆዩባቸው ጊዜያት፣ በተለይ ከሆቴሉ ሠራተኞች ጋር ባለመስማማታቸውና ከሠራተኞቹ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲደርስባቸው መቆየቱም ይታወሳል፡፡ አንድ የውጭ ዜጋ በአገሪቱ ዜጐች ላይ በደል መፈጸም እንደሌለበትና ካለመኖሪያ ፈቃድ ለረጅም ጊዜ መኖር እንደሌለበት በመጠቆም፣ ሠራተኞቹ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተቃውሞ ደብዳቤ ማቅረባቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡ በርካቶችም ከሥራ መሰናበታቸው አይዘነጋም፡፡
ስለሚስተር ማኒጐፍ ሕልፈት የሸራተን አዲስ ማኔጅመንት ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጠው ሪፖርተር ጥረት ቢያደርግም፣ ‹‹ፋክስ እናደርግላችኋለን›› ከማለት ባለፈ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡
ሚስተር ማኒጐፍ ልጅም ሆነ ትዳር እንደሌላቸው በቅርብ የሚያውቋቸው የሪፖርተር ምንጮች ተናግረዋል፡፡
መርካቶ ሸራ ተራ በደረሰ እሳት ቃጠሎ ንብረት ወደመ

–ሰባት ሰዎች በጭስ ታፍነው ጉዳት ደርሶባቸዋል
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሸራ ተራ ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ፣ ግንቦት 28 ቀን 2007 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ግምቱ ያልታወቀ ንብረት ወደመ፡፡
አደጋውን ለመቆጣጠር በአካባቢው ያለው የፕላስቲክ ጫማ፣ ዘይት፣ ሳሙና፣ ብርድ ልብስና ለመቀጣጠል አደገኛ የሆኑ ዕቃዎች ክምችት አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ አካባቢው በጭስ በመታፈኑ እሳት አደጋ ተቆጣጣሪዎች ወደ ውስጥ ደፍረው ለመግባት እንዳዳገታቸውና ለረዥም ሰዓታት እሳቱን መቆጣጠር ሳይቻል መቆየቱንም አክለዋል፡፡
የእሳት ቃጠሎው ከቀኑ 8፡00 ሰዓት አካባቢ መጀመሩን በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ የአካባቢው ነጋዴዎች በመተባበር ከየጊቢው ውኃ በመቀባበልና በየጣራው ላይ ወጥተው ውኃ በመርጨት የተቻላቸውን ካደረጉ በኋላ፣ የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች እንደደረሱላቸውም ተናግረዋል፡፡
የእሳቱ መነሻ በውል ባይታወቅም ከመሀል አካባቢ እንደተነሳና ቤቶቹም እርስ በርስ የተያያዙ በመሆናቸው፣ ለመኪና መግቢያ አስቸጋሪ እንደነበር የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ባለሥልጣን ሠራተኞች ገልጸዋል፡፡ እሳቱ እየጨመረ በመሄዱ ከሰባቱም ክፍለ ከተማ የእሳት መከላከያ ማሽነሪዎች ቢመጡም፣ እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት አለመጥፋቱም ታውቋል፡፡ አራት የውኃ ቦቴዎች ውኃ በማቅረብ ሲተባበሩ እንደነበር፣ አንድ የኤርፖርቶች የእሳት ማጥፊያ ተሽከርካሪ ተጨምሮ በቁጥጥር ሥር ለማዋል እንደተቻለም ገልጸዋል፡፡ የተዳፈነ እሳት፣ የፕላስቲክ ዕቃዎችና ጨርቃ ጨርቆች ለማጥፋት ሲያስቸግሩ ተስተውሏል፡፡ ሠራተኞቹ እሳቱን እያጠፉ ባለበት ጊዜ ከሥር ከሥር የሱቆቹ ባለቤቶችም ከተቃጠለው ዕቃ ክምር የተለያዩ ዕቃዎችን ለማውጣት ሲረባረቡ ታይተዋል፡፡
አብዛኞቹ በአካባቢው ያሉ ነጋዴዎች ዕቃቸውን በማውጣትና እሳቱ ያልደረሰበት ቦታ በመከመር የማዳን ሥራ ሲሠሩ ተስተውለዋል፡፡ ነጋዴዎቹ አይሱዙ በመከራየት ዕቃቸውን በመጫን ወደተለያዩ ቦታዎች ሲወስዱና ቤታቸውም የተቃጠለባቸው ነዋሪዎች እያለቀሱ በከፍተኛ ሐዘን ሲዋከቡ ታይተዋል፡፡ ንብረታቸውንም አድነው በየቦታው የከመሩት ነጋዴዎች ሲመሽባቸው በላስቲክ እየሸፈኑ ወደ ቤታቸው ለመሄድ ተገደዋል፡፡
በወቅቱ ከአሥር በላይ የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎች በማሰማራት ከ150,000 ሊትር በላይ ውኃ፣ 300 ሊትር ፎም እንደተጠቀሙ የገለጹት አቶ ሰለሞን መኰንን፣ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከልና መቆጣጠሪያ ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነት ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ናቸው፡፡ እንደሳቸው ገለጻ፣ የእሳት አደጋው ተነስቷል ተብሎ የተደወለው ከቀኑ 8፡57 ሰዓት ላይ ነው፡፡ ከተደወለላቸው በኋላ ግን፣ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀድሞ በመድረስ ዕርዳታ እንደጀመረ፣ ሌሎቹም ስድስቱ ክፍላተ ከተሞች በየተራ መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡ እሳቱ አስቸጋሪ ቢሆንም ከአራት ሰዓት በኋላ ለመቆጣጠር መቻሉን አስረድተዋል፡፡ እስከ ዓርብ ግንቦት 28 ቀን 2007 ዓ.ም. ምሽት ድረስ ስለደረሰው ጉዳት መጠን ማወቅ አልተቻለም ነበር፡፡
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱት የቤቶች ልማት ምክትል ሥራ አስኪያጅ በነፃ ተሰናበቱ
–አብረዋቸው የተከሰሱ የድርጅት ባለቤት በዋስ ተለቀቁ
በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የግብዓት አቅርቦትና አስተዳደር መምርያ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ በፈቃዱ አሰፋ፣ ተጠርጥረው ከተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ግንቦት 27 ቀን 2007 ዓ.ም. በነፃ ተሰናበቱ፡፡
አብረዋቸው ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው የኤቢ ፕላስት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ አብርሃም ጌታቸው በየነ፣ የተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ወደ ማታለል ወንጀል ተቀይሮ የ200 ሺሕ ብር ዋስ አስይዘው እንዲፈቱ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
ሁለቱም ተጠርጣሪዎች ተመሳጥረው በሕገወጥ መንገድ የ3,211,411 ብር የግዥ ውል እንዲፈረም በማድረግ በመንግሥትና በሕዝብ ጥቅም ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን በመጥቀስ፣ የሙስና ወንጀል ክስ መስከረም 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 18ኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ነው፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በሐምሌ ወር 2006 ዓ.ም. ነው፡፡
አስተዳደሩ ለሚያስገነባቸው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግብዓት የሚሆን የሳኒተሪ ዕቃ እንዲገዛ የወጣውን የጨረታ የግዥ አፈጻጸም መመርያን ባልተከተለ መንገድ፣ ከደረጃ በታች የሆነ የሳኒተሪ ዕቃ እንዲገዛ መደረጉን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ ሁለተኛ ተከሳሽ ጨረታውን አሸንፈው ያቀረቡት ምርት ደግሞ ዩፒቪሲ መሆኑ ሲገባው ዩፒቪሲ የሚል ማኅተም የተለጠፈበት የፒፒሲ ምርት መሆኑን ክሱ ያስረዳል፡፡ ይኼም የሆነው ምክትል ሥራ አስኪያጁና ነጋዴው ተመሳጥረው መሆኑን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሶ፣ በመንግሥትና በሕዝብ ላይ የ3.2 ሚሊዮን ብር ጉዳት እንደደረሰም አስረድቷል፡፡ ሁለተኛው ተከሳሽም በተደጋጋሚ በጨረታ እንዲሳተፉና አሸናፊ እንዲሆኑ አቶ በፍቃዱ እንደረዷቸው ክሱ ይገልጻል፡፡
አቶ አብርሃም ጌታቸው የተባሉት የፒቪሲ ፕላስት ድርጅት ባለቤት የሌሎችን ሰዎች አለማወቅ ተጠቅመው በፒፒሲ ምርት ላይ ዩፒቪሲ የሚል ማኅተም በማስቀመጥና በማታለል፣ በመንግሥት ላይ የ78,147,296 ብር ጉዳት ማድረሳቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡
አቶ በፈቃዱ ሌላው የተከሰሱበት ወንጀል በጽሕፈት ቤቱ የግብዓት አቅርቦትና አስተዳደር መምሪያ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሲሠሩ ተገቢ ምክንያት ሳይኖራቸው፣ የ8551 ብር ባለ24 ካራት ስምንት ግራም ብራስሌት ወርቅ ቶፕና ሰላም ኮንስትራክሽን ከተባሉ ተቋራጮች መቀበላቸውን የሚገልጽ ነው፡፡
የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቦ አሰምቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ያቀረባቸው የሰዎች ምስክሮች፣ የሰነድ ማስረጃዎችና የኤግዚቢት ማስረጃዎች በተጠርጣሪዎቹ ላይ የቀረቡት ክሶች ስለመፈጸማቸው አስረድተዋል? ወይስ አላስረዱም? የሚለውን ጭብጥ ይዞ መመርመሩን በውሳኔው ገልጿል፡፡
አቶ በፍቃዱ ሁለተኛው ተከሳሽ ጨረታ እያሸነፉ የሚያቀርቧቸው የሳኒተሪ ምሮቶች ከስፔስፊኬሸን በታች ስለመሆናቸው ጥቆማ ሲደርሳቸው፣ ሁለተኛው ተከሳሽ (ኤቢ ፕላስት) እንዳይሳተፍ የማድረግና ጨረታውንም የመሰረዝ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል? የሚለውን ከፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ የአደረጃጀትና የሥራ መዘርዝር መመርያ ላይ መመልከቱን እንዲሁም ከሁለተኛ ተከሳሽ ጋር መመሳጠራቸው በዓቃቤ ሕግ ማስረጃዎች መረጋገጥ አለመረጋገጡንም ጭብጥ ይዞ መመርመሩን ዘርዝሯል፡፡
አቶ በፈቃዱ ኤቢ ፕላስት የተባለው ድርጅት የሚያቀርበው የሳኒተሪ ዕቃ ከጥራት በታች መሆኑ ጥቆማ ሲደርሳቸው፣ ወደሚመለከተው የሥራ ክፍል መምራታቸውንና በኢትዮጵያ ምዘናና ተስማሚነት ተቋም ተልኮ እንዲመረመር መደረጉን ፍርድ ቤቱ በተጨማሪ አስረጂነት የጠራቸው የጽሕፈት ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መመስከራቸውን ገልጿል፡፡ ከጥራት በታች መቅረቡ ተረጋግጦ ጨረታው መሰረዙን ማስረዳታቸውንም አክሏል፡፡ ቅሬታ ቀርቧል ተብሎ ሳይጣራ ጨረታ መሰረዝ እንደማይችልና ወደሚመለከተው ክፍል ተልኮ ማጣራት መደረጉን፣ ከምስክሩ መረዳት መቻሉን ፍርድ ቤቱ በስፋት ተንትኗል፡፡ አቶ በፍቃዱ ለሚመለከተው ክፍል መርተውና ለዋና ሥራ አስኪያጁ የክፍሉን ውሳኔ አቅርበው ጨረታውን ያሰረዙ በመሆኑ፣ በቀረበው ክስ የአቶ በፈቃዱ ኃላፊነት ነው ተብሎ በማስረጃነት የቀረበው እሳቸውን የማይመለከትና እሳቸውም ቢሆኑ ኃላፊነታቸውን የተወጡ መሆኑን ከማስረዳት ባለፈ፣ የሚያስጠይቃቸው ሆኖ አለመገኘቱን በውሳኔው ጠቅሷል፡፡
ጥራትን የመቆጣጠር ሥልጣን በጽሕፈት ቤቱ አደረጃጀት መሠረት የአቶ በፍቃዱ ሳይሆን የሌላ ኃላፊ መሆኑን፣ የተለያዩ ጽሕፈት ቤቱ ያወጣቸው መመርያዎች እንደሚያረጋግጡ ፍርድ ቤቱ በዝርዝር ገልጿል፡፡ ቀርበው በመሰከሩት ሰዎችም ሆነ የሰነድ ማስረጃዎች በአቶ በፈቃዱ ላይ ስላላስረዱባቸው በወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ/141 መሠረት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ፍርድ ቤቱ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
አቶ አብርሃም ጌታቸው የኤቢ ፕላስት ድርጅት ባለቤትም የተጠረጠሩበት ወንጀል ሙስና ሳይሆን ወደ ማታለል ወንጀል ተቀይሮላቸው በ200 ሺሕ ብር ዋስ ሆነው እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል፡፡ አቶ በፍቃዱ ላይ የቀረበው ስምንት ግራም ብራስሌት ወርቅን በሚመለከት ምስክሮች ካለመሰማታቸውም በተጨማሪ፣ ወርቁ የተገዛው በስማቸውና በአግባቡ መሆኑን ጠቅሶ በእሱም በነፃ እንዲሰናበቱ ብይን ሰጥቷል፡፡ አቶ በፍቃዱ ከእስር እንዲፈቱና ብራስሌት ወርቃቸው ከኮሚሽኑ ኤግዚቢት ክፍል እንዲመለስላቸው አዟል፡፡ በሁለተኛ ተከሳሽ ላይ የመከላከያ ምስክር ለመስማት ለሐምሌ 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
የአገሪቱ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ከአቅም በታች እያመረቱ ነው

–ዳንጎቴ የገነባውን ግዙፍ ሲሚንቶ ፋብሪካ በእጥፍ እንደሚያሳድግ አስታወቀ
በአገሪቱ ሲሚንቶ በማምረት የተሰማሩ 17 ፋብሪካዎች በኤሌክትሪክ ኃይል እጦት ሳቢያ፣ ከአቅማቸው ከግማሽ በታች እያመረቱ ነው፡፡ ሰሞኑን ኢንዱስትሪውን የተቀላቀለው ዳንጎቴን ጨምሮ ዋና ዋና የአገሪቱ ፋብሪካዎች በአሁኑ ወቅት ማምረት የቻሉት በዓመት 5.4 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ብቻ ነው፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ አብተው እንዳስታወቁት፣ በአገሪቱ ይመረታል ተብሎ የታቀደው የሲሚንቶ መጠን ከ17 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ነበር፡፡ ሆኖም በአሁኑ ወቅት ፋብሪካዎቹ ያመርታሉ የተባለው መጠን 11.2 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ሲሆን፣ ፋብሪካዎቹ ማምረት የቻሉት ግን 5.47 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ብቻ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ሲሚንቶ ወደ ሶማሊያ፣ ጂቡቲና ደቡብ ሱዳን እየተላከ እንደሆነ አቶ አህመድ አስረድተዋል፡፡
እነዚህን ፋብሪካዎች ይቀላቀላል ተብሎ የሚጠበቀው ዳንጎቴ፣ በዓመት 2.5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ሲሚንቶ የሚያመርተውን ፋብሪካ ሥራ ያስጀመረው ግንቦት 26 ቀን 2007 ዓ.ም ነው፡፡ በማግሥቱም የናይጄሪና የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት ፋብሪካውን አስመርቋል፡፡ ከአዲስ አበባ 85 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ሙገር ከተማ አዳዓ በርጋ ወረዳ ውስጥ በ134 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈው ግዙፍ ፋብሪካ 600 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገበት መሆኑን ናይጄሪያዊው ቢሊየነር የዳንጎቴ ግሩፕ ሊቀመንበርና መሥራች አሊኮ ዳንጎቴ አስታውቀዋል፡፡
አሊኮ ዳንጎቴ አዲሱ ፋብሪካ ገና ሥራ ከመጀመሩ የእሱን ተመሳሳይ ፋብሪካ በተመሳሳይ ወጪ ለመገንባት መነሳታቸውንና የፋብሪካው ግንባታም በዚህ ዓመት ውስጥ እንደሚጀመር፣ ፋብሪካውን ለመመረቅ ለተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ለሌሎች ባለሥልጣናት ይፋ አድርገዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም በበኩላቸው፣ አሊኮ ዳንጎቴ ተጨማሪ ማስፋፊያ ለማካሄድ መወሰናቸው እንዳስደሰታቸውና በግላቸውም የማስፋፊያ ፕሮጀክቱን ክትትል እንደሚያደርጉለት ለዳንጎቴ ቃል ገብተውላቸዋል፡፡
መቶ በመቶ ከራሳቸውና ከአገራቸው በተገኘ ገንዘብ ፋይናንስ ተደርጓል የተባለለት የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርት መጀመር፣ በአገሪቱ በወቅቱ የተከሰተውን የሲሚንቶ እጥረትና የዋጋ ንረት ያረግባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከ400 ብር በላይ በኩንታል እየተሸጠ የሚገኘው ሲሚንቶ ከጥቂት ወራት በፊት በ230 ብር በችርቻሮ ገበያው ውስጥ ሲሸጥ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ዳንጎቴ ሲሚንቶ አንዱን ኩንታል በፋብሪካ ዋጋ በ207 ብር እንደሚያቀርብ ይፋ አድርጓል፡፡ በአገሪቱ ካሉት 17 ፋብሪካዎች በተጨማሪ 18ኛው ሆኖ የተመዘገበው ዳንጎቴ፣ 40 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት የሚያስችለው መሠረተ ልማት ተዘርግቶለታል፡፡
በአንፃሩ ሌሎች ትልልቅ ፋብሪካዎች በኃይል አቅርቦት እጦት ሳቢያ ከአቅማቸው በታች ለማምረት መገደዳቸው ይታወቃል፡፡ በሰኔ ወር በከፊል ማምረት የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚያመነጭ የሚጠበቀው የግልገል ጊቤ ሦስት ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት፣ የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን ችግር እንደሚያቃልል ተስፋ ተደርጓል፡፡
ዳንጎቴ ግሩፕ ምንም እንኳ በኢትዮጵያ ዕውን ያደረገው ፋብሪካ በምሥራቅ አፍሪካ ግዙፉ እንደሆነ ቢነገርለትም፣ በናይጄሪያ ያሉት ሦስት ፋሪካዎች በዓመት ከ20 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ሲሚንቶ ያመርታሉ፡፡
በሌላ በኩል በናይጄሪያው ባለሀብት አሊኮ ዳንጎቴ የሚመራው ዳንጎቴ ግሩፕ፣ በኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ የፖታሽ ማዕድን ምርት ላይ ለመሠማራት ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ መስጠቱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ዳንጎቴ ሲሚንቶ በምሥራቅ አፍሪካ ግዙፍ የተባለውን ፋብሪካ ሥራ ኢትዮጵያ ውስጥ አስጀምሯል፡፡
የማዕድን ሚኒስትሩ አቶ ቶሎሳ ሻጊ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ ኩባንያው ፈቃድ እንዲሰጠው በደብዳቤ ጠይቆ ነበር፡፡ ሚኒስቴሩ ኩባንያው ያቀረበውን የፖታሽ ማዕድን የማምረት ፈቃድ ሲያጠና ቆይቶ እምነት የሚጣልበት ሆኖ በማግኘቱ፣ ያቀረበውን የፈቃድ ጥያቄ መቀበሉን አቶ ቶሎሳ ተናግረዋል፡፡ እስካሁን ሦስት የውጭ ኩባንያዎች በፖታሽን ማዕድን ምርት ላይ በማሰማራት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ የማዕድን ሚኒስቴር ለመሥራት ቆርጠው የመጡ መሆናቸው እስካልተረጋገጠ ድረስ ፈቃድ መስጠት አቋርጦ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ ዳንጎቴ ፈቃድ መስጠት ከቆመ በኋላ ፈቃድ የተሰጠው ኩባንያ ሆኗል፡፡
‹‹ደብዳቤ አስገብተው ነበር፡፡ የዳንጎቴ ኩባንያ ባለቤት አገራችንን አምኗል፡፡ ይህን ሁሉ ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት ሲያደርግ የሚሠራ ሰው መሆኑን አረጋግጠናል፡፡ ስለዚህም ፈቃድ ልንሰጠው ወስነናል፡፡ ቦታውን ለይቶ እንዲያቀርብ እየጠበቅነው ነው፡፡ ልክ እንደ ሲሚንቶው በፖታሽም እንደሚሠራ ይጠበቃል፤›› በማለት አቶ ቶሎሳ ለዳንጎቴ ፈቃድ እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል፡፡ በፖታሽ ማዕድን ላይ ለመሰማራት እየተንቀሳቀሱ ካሉት ሦስት የውጭ ኩባንያዎች በተጨማሪ ዳንጎቴ አራተኛው እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
ዳንጎቴ ግሩፕ በኢትዮጵያ አፋር ክልል በዳሎል አካባቢ በከፍተኛ ደረጃ ክምችት እንዳለው የሚታወቀውን የፖታሽ ማዕድን፣ በናይጄሪያ ለሚገነባው የማዳበሪያ ፋብሪካ ግብዓት ሊያውለው ይፈልጋል፡፡ ከዳንጎቴ በተጨማሪ የካናዳው አላና ፖታሽ የምርት ፈቃድ ማግኘቱን አቶ ቶሎሳ አስታውሰዋል፡፡ ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት የምርት ፈቃድ ያገኘው አላና ፖታሽ፣ የመሠረተ ልማትና የማምረቻ ፋብሪካ የመትከል ሥራ ማከናወን እንደሚጠቅበት፣ ሚኒስቴሩም ኩባንያው ይህንን ሥራ በወቅቱ ያከናውናል ብሎ እንደሚጠብቅ ገልጸዋል፡፡
የኖርዌይ ያራ ኢንተርናሽናል እህት ኩባንያው በሆነው ያራ ዳሎል ቢቪ አማካይነት ባቀረበው ጥናት መሠረት የምርት ፈቃድ ሊሰጠው መሆኑን፣ የፋይናንስ ችግር ስለሌለበትም በፍጥነት ማምረት ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥም የመሠረተ ልማት ሥራዎችን አጠናቆ ወደ ምርት እንደሚገባ ይታሰባል፡፡ ሦስተኛው የእንግሊዝ ኩባንያ የሆነው ሰርከም ሚነራልስ የሚባለው ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የአዋጭነት ጥናቱን በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተነግሮለታል፡፡ በስምንት ወራት ጊዜ ውስጥ የምርት ፈቃድ ለማግኘት ወደ ሚኒስቴሩ እንደሚመጣ አቶ ቶሎሳ ገልጸዋል፡፡
በአፍሪካ ቁንጮ ከበርቴ የሆኑት አሊኮ ዳንጎቴ በአንዳንዶች ዘንድ ‹‹ከብክለትና ከብድር የፀዳ›› እየተባለ ከተነገረለት የሲሚንቶ ፋብሪካቸው በተጨማሪ፣ በጥጥና በሸንኮራ አገዳ ልማት ላይ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ ሆኖም የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ዳንጎቴ ጥናት ላይ በመሆኑ ያቀረበው የፈቃድ ጥያቄ የለም፡፡
ቢሊየነሩ አሊኮ ዳንጎቴ ከዓለም ሀብታሞች ተርታ ያሰለፋቸው የ20 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ የግል ሀብት ያላቸው ባለፀጋ ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ. እስከ 2018 ባለው ጊዜ ውስጥም 16 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት በማድረግ በ16 አፍሪካ አገሮች ውስጥ ያንሰራፏቸውን የንግድና የኢንቨስትመንት መስኮች እንደሚያስፋፉ፣ አዳዲሶችንም እንደሚገነቡ ይፋ አድርገዋል፡፡ በቀን 650 ሺሕ በርሜል ነዳጅ የማጣራት አቅም ያለውን ማጣሪያ ጨምሮ፣ ሦስት ሚሊዮን ቶን ዩሪያና አሞኒያ የሚያመርቱ ፋብሪካዎችን በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ ዕውን ለማድረግ እየሠሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
እ.ኤ.አ. በ1996 ወደ አምራች ኢንዱስትሪዎች ፊታቸውን በማዞር በአፍሪካ ግዙፍ ግዛት የፈጠሩት አሊኮ ዳንጎቴ፣ በ20 ዓመታቸው ከአያታቸው በተበደሩት 500 ሺሕ ኒያራ (የናይጄሪያ መገበያያ ገንዘብ) በሲሚንቶ ንግድ ሥራ እጃቸውን አፍታትዋል፡፡ በሁለት ዓመት የሚከፍሉትን ገንዘብ በሦስት ወራት ውስጥ ለአያታቸው በመመለስ ስኬታማ የንግድ ጉዞ የጀመሩት ዳንጎቴ፣ ፎርብስ መጽሔት በሚያወጣው የሀብታሞች ዝርዝር ውስጥ ከአፍሪካ አንደኛው በመሆን እየመሩ ይገኛሉ፡፡
ለሚቀጥለው ዓመት ከ223.3 ቢሊዮን ብር በላይ ረቂቅ በጀት ቀረበ
የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ አቶ ሱፊያን አህመድ የቀጣዩን ዓመት 223.4 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ካቀረቡ በኋላ፣ ምክር ቤቱ አፅድቆ ለፓርላማ ላከው፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ በ2008 ዓ.ም. የኢትዮጵያ መንግሥት በጀት 223 ቢሊዮን 397 ሚሊዮን 819 ሺሕ 216 ብር እንዲሆን ወስኗል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይህንን ከፍተኛ በጀት ተቀብሎ ካፀደቀ፣ ከሐምሌ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል፡፡
ይህ በጀት በ2007 ዓ.ም. ከተያዘው 178.6 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር በ44.8 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው፡፡ ነገር ግን ለደመወዝ ጭማሪ በዓመቱ መጀመሪያ በተያዘው በጀት ላይ ስምንት ቢሊዮን ብር ተጨማሪ የበጀት ሥሌት ቀርቦ በመፅደቁ፣ የ2007 ዓ.ም. በጀት በአጠቃላይ 186.6 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡
ለ2008 ዓ.ም. ከተያዘው በጀት ትልቁ ለፕሮጀክቶች የተመደበው ነው፡፡ ከአጠቃላይ በጀቱ 37.4 በመቶ ለካፒታል ፕሮጀክቶች፣ 34.7 በመቶ የሚሆነው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባቀረበው ቀመር ላይ ተመሥርቶ ለክልሎች የሚከፋፈል ነው፡፡ የበጀቱ 22.6 በመቶ ለመደበኛ ወጪዎች ይውላል፡፡ 5.4 በመቶ ደግሞ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ይውላል ተብሏል፡፡
ለክልሎች ከሚከፋፈለው በጀት የአዲስ አበባ አስተዳደር በቀጥታ ተቋዳሽ ባይሆንም፣ በተለይ ለግዙፍ ፕሮጀክቶች በፌዴራል መንግሥት አማካይነት ያገኛል ተብሏል፡፡
በተለይ በመጠጥ ውኃ፣ በቀላል ባቡር ትራንስፖርትና በተወሰነ ደረጃ ለቤቶች ልማት በጀት እንደሚመደብለት ታውቋል፡፡
ይህ በጀት ይሸፈናል ተብሎ የሚጠበቀው በተለይ ከአገር ውስጥ የገቢ ምንጮች፣ ከዕርዳታና ከብድር ነው፡፡
የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በየዓመቱ የሚያቀርበው በጀት እየጨመረ የመጣ ሲሆን፣ የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በሚጀመርበት 2008 ዓ.ም. የቀረበውም በጀት በአገሪቱ ታሪክ ትልቁ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ይህንን በጀት በማስፈጸም በኩል ዘንድሮ በተካሄደው ምርጫ መንግሥት መመሥረቱን ያረጋገጠው ኢሕአዴግ የሚያዋቅረው አዲስ ካቢኔ ኃላፊነት ይሆናል ተብሏል፡፡
የቀድሞ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚዳንት ቅጣት ተቀንሶላቸው ከእስር ተፈቱ

–ጥፋተኛ የተባሉበት የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ፀንቷል
ሥልጣንን ያላግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል ተከሰው ሰባት ዓመታት ጽኑ እስራትና 20 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት የተጣለባቸው የቀድሞው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ያረጋል አይሸሹም፣ ከሦስት ዓመታት የእስር ቆይታ በኋላ ቅጣቱ ተቀንሶላቸው ግንቦት 18 ቀን 2007 ዓ.ም. ከእስር ተለቀቁ፡፡
አቶ ያረጋል በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በነበሩበት ወቅት ከፌዴራል መንግሥት በተሰጠ የበጀት ድጎማ ከክልሉ በጀት የግልገል በለስ መምህራን ኮሌጅ፣ የጣና በለስ የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤትና የአሶሳ የቴክኒክና የሙያ ማሠልጠኛ ተቋማትን ለማስገንባት በክልሉ የወጣውን የግዥ መመርያ ቁጥር 1/1992 አንቀጽ 9.1 እና 2 ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ ግዥ እንዲፈጸም፣ የሦስቱ ፕሮጀክቶች ጨረታ ያላግባብ እንዲሰጥ አድርገዋል በሚል ግብረ አበሮቻቸው ከተባሉ ጋር መከሰሳቸው ይታወሳል፡፡
የሥር ፍርድ ቤት የቀረቡለትን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች መርምሮ እንዲከላከሉ ካደረገ በኋላ፣ የዓቃቤ ሕግን ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻላቸው ጥፋተኛ በማለት ቅጣቱን ወስኖባቸው ነበር፡፡
አቶ ያረጋል በሕዝብና በመንግሥት ጥቅም ላይ ጉዳት በማድረሳቸው የሰባት ዓመታት ጽኑ እስራትና የ20 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት ሲጣልባቸው፣ የሥር ፍርድ ቤት ፍርድን በመቃወም ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብለው ነበር፡፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበለትን አቤቱታ ተመልክቶ፣ ‹‹የሥር ፍርድ ቤት የቅጣት ውሳኔ የሚነቀፍ ሆኖ እንዳላገኘው ጠቁሞ ‹‹አያስቀርብም›› ብሎ መዝገቡን ዘግቶት ነበር፡፡ የሥር ፍርድ ቤቶች የሕግ ጥሰት ፈጽመዋል በማለት ለሰበር ሰሚ ችሎት የመጨረሻ አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡
ለሰበር ችሎቱ ባቀረቡት አቤቱታ እንዳስረዱት በወንጀል ድርጊት እንዲጠየቁ የተደረገው ተገቢ ማስረጃ በዓቃቤ ሕግ በኩል ስላልቀረበ ነው፡፡ ከወንጀል ተጠያቂነት መርህ መንፈስና ይዘት ውጪ ነው ብለዋል፡፡ የመከላከያ ማስረጃቸው ይዘት ውድቅ የተደረገውም ያላግባብ እንደሆነ፣ የእስራት ቅጣቱም በወቅቱ ያለውን የቅጣት መመርያ መሠረት ያላደረገ መሆኑን፣ እሳቸው ያቀረቧቸው የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች የታለፉት ያላግባብ መሆኑን ዘርዝረው የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲሻርላቸው ወይም እንዲስተካከልላቸው ጠይቀው ነበር፡፡
አቶ ያረጋል የተከሰሱት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1) (ሀ) (ለ) በዋና ወንጀል አድራጊነት በአንቀጽ 33 በወንጀል ድርጊቱ በዋናነት በመሳተፍና በአንቀጽ 407 (1) (ሀ) (ለ)፣ (2) እና (3) ሥልጣንን አለግባብ መጠቀም ወንጀሎች ነበር፡፡ ወንጀሉን ክደው በመከራከራቸው ከሳሽ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ምስክሮቹንና የሰነድ ማስረጃዎቹን አቅርቦ ወንጀሉን መፈጸማቸውን ማረጋገጡን የሥር ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ተረጋግጧል፡፡ ሰበር ሰሚ ችሎቱም የክርክር ሒደቱንና ውሳኔውን አልተቃወመውም፡፡ የመመርመርም ሥልጣን እንደሌለውም አስታውቋል፡፡ ነገር ግን ፍርድ ቤት የወንጀል ቅጣቶችን የሚወስነው የወንጀል አድራጊውን የሕይወት ታሪክ፣ ወንጀል ለመፈጸም ያነሳሱትን ምክንያቶችንና የሐሳቡን ዓላማ፣ የግል ኑሮውን ሁኔታ፣ የትምህርት ደረጃውን፣ የወንጀሉን ከባድነትና የአፈጻጸሙን ሁኔታዎች በማመዛዘን መሆኑን ጠቁሟል፡፡
የወንጀል ሕጉንና የቅጣት መመርያውን ያገናዘበ መሆኑን የሥር ፍርድ ቤት ከሰጠው ውሳኔ መገንዘቡን የገለጸው ሰበር ችሎቱ፣ መነሻ ቅጣቱ ከተወሰነ በኋላ መጠኑ መሰላት ያለበት ሕጉ ስለቅጣት አወሳሰን የተመለከቱትን ድንጋጌዎች፣ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወጣው የቅጣት አወሳሰን መመርያም እንደሚያሳይ ጠቁሟል፡፡
ዓቃቤ ሕግ በአቶ ያረጋል ላይ የቅጣት ማክበጃ አለማቅረቡን የሥር ፍርድ ቤት ማረገገጡን ሰበር ችሎቱ ገልጾ፣ ቅጣቱን በተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመርያ ማስላቱ ግን የሕግ ስህተት መሆኑን አስረድቷል፡፡ የሥር ፍርድ ቤት ቅጣቱን ሲወስን የቅጣት ውሳኔ የሚመጣው የጥፋተኝነት ውሳኔ ሲሰጥ መሆኑንና የጥፋተኝነት ውሳኔ ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች ቆይቶ ሊወሰን የሚችል በመሆኑ፣ የጥፋተኝነት ውሳኔ በተሰጠበት ጊዜ በሥራ ላይ ያለው የቅጣት አወሳሰን መመርያ ተፈጻሚነት ሊኖረው ይገባል የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱ አግባብ አለመሆኑን ሰበር ችሎቱ በፍርዱ ተችቷል፡፡
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 20 (1) እና ኢትዮጵያ ተቀብላ ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ስምምነት አንቀጽ 14 (2) (ሐ)፣ በአፍሪካ የሰዎችና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር አንቀጽ 7 (1) (መ) መሠረት አንድ ተከሳሽ የተፋጠነ ውሳኔ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ የተደነገጉትን ድንጋጌዎች፣ የሥር ፍርድ ቤት በውሳኔው አለማገናዘቡን በመጥቀስ ሰበር ችሎቱ ተችቷል፡፡
አቶ ያረጋል ክስ የተመሠረተባቸው ጥቅምት 20 ቀን 2004 ዓ.ም. መሆኑን የጠቆመው ሰበር ችሎቱ፣ ክሱ በቀረበበት ወቅት የነበረው የቅጣት አወሳሰን መመርያ ቁጥር 1/2002 መሆኑን ገልጿል፡፡ ይኼ መመርያ በቁጥር 2/2006 መሻሻሉንም እክሏል፡፡ መመርያው ቁጥር 1/2002 የቅጣት ማቅለያ በሚያስቀንሰው እርከን ላይ የእርከን ቅጣት መጠኑን መሠረት አድርጎ ቅጣትን የሚቀንስ ሲሆን፣ የተሻሻለው መመርያ ቁጥር 2/2006 ግን የማቅለያ ምክንያቶች በሚያስቀንሱት የእርከን መጠን ላይ ያደረገው ልዩነት አለመኖሩን ሰበር ችሎቱ በፍርዱ አስቀምጧል፡፡ በቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ምላሽ የእርከን አቀናነስ ላይ መመርያ ቁጥር 1/2002 ከመመርያ ቁጥር 2/2006 የተሻሻለና አቶ ያረጋልን የሚጠቅም መሆኑንም ሰበር ችሎቱ አስረድቷል፡፡ ከወንጀል ሕግ አንቀጽ ስድስትና ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 22 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ አንፃር የተሻለው መመርያ ተፈፃሚነት አንዲኖረው እንደሚገባ በሰበር ችሎቱ የተለያዩ መዝገቦች የሕግ ትርጉም እንደተሰጠበት አስታውሶ፣ ለአቶ ያረጋል አይሸሹም የቅጣት አወሳሰን መመርያ 1/2002 የተሻለ ሆኖ በማግኘቱ የሥር ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የሕግ ስህተት ፈጽሞ እንዳገኘው አስታውቋል፡፡
ሌላው የፍርድ ቤት ለአቶ ያረጋል ከያዘላቸው ሦስት የቅጣት ማቅለያዎች በተጨማሪ፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነው በሚሠሩበት ወቅት ለረዥም ጊዜ ሕዝብንና መንግሥትን ማገልገላቸው የራሱ የሆነ ዋጋ ያለው አገልግሎት እንጂ በደፈናው ‹‹የኃላፊነት ግዴታ ነው›› ተብሎ በሥር ፍርድ ቤት የሚታለፍ አለመሆኑን ሰበር ችሎቱ ገልጿል፡፡ አቶ ያረጋል በአካባቢ ጥበቃና በአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ የመሪነት የሚናቸውን የተወጡ በመሆናቸው በወቅቱ ከአገሪቱ ፕሬዚዳንትና ከአረንጓዴ ልማት ፕሮግራም የበላይ ጠባቂ ሽልማት የተቀበሉና ሌሎች ልማቶችን በአመርቂ ሁኔታ የፈጸሙ መሆናቸው፣ እንደ አንድ የቅጣት ማቅለያ ሊያዝላቸው እንደሚገባ ሰበር ችሎቱ ገልጿል፡፡ በድምሩ አራት የቅጣት ማቅለያ ሲያዝላቸው በመመርያ ቁጥር 1/2002 አንቀጽ 16(17) ድንጋጌ መሠት እያንዳንዱ የቅጣት ማቅለያ ሦስት እርከን የሚያስቀንስላቸው በመሆኑ፣ አቶ ያረጋል በ12 የቅጣት ማቅለያ የሥር ፍርድ ቤት ለቅጣት ከያዘው እርከን 27 ወደ እርከን 15 ወርዶ ቅጣቱ የሦስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲሆን ፍርድ ሰጥቷል፡፡ የገንዘብ መቀመጫውን እንደማይነካም አክሏል፡፡ የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔዎች መሻራቸውንም አስታውቋል፡፡
በ120 ሚሊዮን ብር የተገነባው ቆርኪ ፋብሪካ ሥራ ጀመረ
በ120 ሚሊዮን ብር ወጪ በለቡ ኢንዱስትሪ መንደር ውስጥ የተገነባው የግል የቆርኪ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታው ተጠናቆ ማምረት መጀመሩ ተገለጸ፡፡
ጵንኤል ኢንዱስትሪ በተባለ ኩባንያ የተገነባው ፋብሪካ፣ አሁን ባለው የማምረት አቅም አንድ ቢሊዮን ቆርኪዎችን በዓመት እንደሚያመርት፣ በቅርቡ የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም አቅሙ 1.8 ቢሊዮን እንደሚደርስ ታውቋል፡፡
የኩባንያው ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሪት ብርቱካን በቀለ፣ ፋብሪካውን ገንብቶ ለመጨረስ ሁለት ዓመት እንደወሰደና 40 በመቶ የሚሆነው የግንባታ ወጪ ከኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ በተገኘ ብድር መሸፈኑን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የለቡ ኢንዱስትሪ መንደር ውስጥ ፋብሪካው 2,000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ መገንባቱን ዋና ሥራ አስኪያጇ አስረድተዋል፡፡ ፋብሪካው ዓለም አቀፍ ጥራቱን እንዲያሟላ ተደርጎ የተገነባ መሆኑንና የእጅ ንክኪ ሳይኖረው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ቆርኪዎችን እንደሚያመርትም ወ/ሪት ብርቱካን አስታውቀዋል፡፡
ፋብሪካው ምንም ዓይነት ብክነት እንዳይኖረው ተደርጎ መገንባቱን፣ በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ የምርት ሥራ እንዳይስተጓጎል የራሱ ጄኔሬተር ተተክሎለታል ብለዋል፡፡
ፋብሪካው በዋናነት ለአገር ውስጥ የቢራ፣ የለስላሳና የኮስሞቲክስ ውጤቶችን ለሚያመርቱ ፋብሪካዎች ምርቱን እንደሚያቀርብ፣ ከአጠቃላይ ምርቱ 40 በመቶ የሚሆነውን ወደ ጂቡቲና ፑንትላንድ የመላክ ዕቅድ እንዳላቸው ወ/ሪት ብርቱካን ገልጸዋል፡፡
ፋብሪካው ለ63 ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ መሆኑን፣ በቅርቡም መጠነ ሰፊ የማስፋፋት ሥራ እንደሚኖረውም ተገልጿል፡፡ ጵንኤል ኢንዱስትሪ በ2006 ዓ.ም. በ120,000 ብር የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡ በአገሪቱ ሥራ ፈጣሪ ከሆኑ ሴቶች አንዷ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ወ/ሪት ብርቱካን፣ አልሙኒየምን ከመሳሰሉ ምርቶች የሚሠሩ የሕንፃ በርና መስኮቶች፣ መሰል ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ቆይተዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ አምስት የቆርኪ ፋብሪካዎች ሲኖሩ፣ አጠቃላይ የማምረት አቅማቸው የምርቱን ፍላጎት ባለሟሟላቱ ዋና ዋና የመጠጥ አምራቾች ከውጭ አገር በብዛት ቆርኪ ለማስገባት መገደዳቸው ይነገራል፡፡
“የድረሱልኝ ጥሪ” ያሰሙት የስልጤ ዞን ቂልጦ ቅድስት ማርያም ምእመናን “ሃይማኖታዊ ግጭት ለማስነሣት ተንቀሳቅሳችኋል” ተብለው ፍርድ ቤት ቀረቡ
፳፩ የምርመራ ቀናት የጠየቀባቸው የወረዳው ፖሊስ የ፲ ቀን ጊዜ ተፈቅዶለታል በድረሱልኝ ጥሪው÷ ከሥራቸው የታገዱ፣ ከደረጃ ዝቅ የተደረጉ እና የታሰሩ አሉ የሀ/ስብከቱ ሓላፊዎችና ምእመናኑ ከወረዳው አስተዳደር ጋር እየተነጋገሩበት ነው በተቃጠለው የቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የተሠራው መቃኞ ሰኔ ፳፩ ይመረቃል (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ 15 ቁጥር 803፤ ቅዳሜ ግንቦት 29 ቀን 2007 ዓ.ም.) በደቡብ ክልል የስልጤ ዞን ምሥራቅ አዘርነት …![]()
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ሰኔ 06, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና
86 ኤርትራውያን በISIS መታገታቸው ተነገረ
86 ኤርትራውያን ስደተኞች በአይሲስ ታጣቂዎች ተጠልፈው ከትሪፖሊ ውጭ መወሰዳቸው ተሰማ። እስካሁን ግን አይሲስ ሀላፊነት መውሰዱን አልገለፀም። አንድ በእንጊሊዝ የሚታተም ጋዜጣ እንደጠቀሰው በምህራብ ሊቢያ ነው 86 ኤርትራውያን በISIS የተጠለፉት Militants from Islamic State of Iraq and the Levant (Isil) are believed to have kidnapped 86 Eritrean refugees from a smugglers’ caravan in westernLibya. The militants struck […]![]()
ከቀድሞ የእሥራኤል ፓርላማ አባል ሺሞን ሰሎሞን ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ – ሰኔ 06, 2015
Interview with Shimon Solomon, Former Israeli Knesset Member, 06-05-15
ከሙስሊም ኮሚቴ በአቶ ዓሊ መኪ ላይ ተፈረደ – ሰኔ 06, 2015
Ethiopia, sentence on Ali Meki Bedru of Ethiopia’s Muslim Committee – 06-05-15
ሌላ የትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ሠልፍ በቴል አቪቭ – ሰኔ 06, 2015
Ethiopian Jews protest in Tel Aviv for second time – 06-05-15
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ሰኔ 05, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)
በቴፒ አቅራቢያ ከፍተኛ ውጊያ ተካሄደ- ታጣቂዎች ፖሊስ ጣቢያ ሰብረው በመግባት ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል
ግንቦት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋምቤላና ደቡብ ክልል አዋሳኝ ከተማ በሆነቸው ቴፔ ትናንት ሌሊት 11 ሰአት ላይ ለተሻለ ፍትህና ነጻናት እንታገላለን የሚሉ ታጣቂዎች በአንድ የፖሊስ ጣቢያ ላይ በወሰዱት እርምጃ 3 የሌሊት ተረኛ ፖሊሶች ሲገደሉ በርካታ እስረኞችንም አስፈትተዋል። ቁጥራቸው ከ100 እስከ 150 የሚሆኑ በቴፒና አካባቢው የሚታየውን ዘረኝነትና የአስተዳደር በደል እንዋጋለን በማለት ራሳቸውን …
የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ክስ ተመሰረተባቸው
ግንቦት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ያለፉትን 9 ወራት በእስር ሲማቅቁ የቆዩት የሰማያዊ፣ የቀድሞው አንድነትና የመኢኢድ ፓርቲዎች የአመራር አባላት ላይ ክስ መመስረቱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። በአንደኛ ተከሳሽ ጌታቸው መኮንን መዝገብ 16 ሰዎች በሽብር ወንጀል መከሰሳቸውን ጋዜጣው ዘግቧል። ተከሳሾቹ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን ፣ በላይነህ ሲሳይ፣ አለባቸው ማሞ፣ አወቀ ሞኝሆዴ፣ ዘሪሁን በሬ፣ ወርቅየ …
በመርካቶ የደረሰው ቃጠሎ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ
ግንቦት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እኩለቀን ላይ ሸራ ተራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የተነሳው ቃጠሎ በርካታ የንግድ ቤቶችን አውድሟል። የእሳት ማጥፋያ መኪኖች እሳቱን ለመቆጣጠር ጥረት ቢያደርጉም፣ ይህን ዘገባ እስካጠናከርንበት በኢትዮጵያ ከቀኑ 11 ሰአት ድረስ እሳቱ በቁጥጥር ስር አልዋለም። ዘጋቢያችን እንደገለጸው በቃጠሎው ከፍተኛ ንበረት ሳይወድም አልቀረም። የእሳቱ መንስኤ በውል አለመታወቁንም ገልጿል።
ውዝግብን ያስተናገደው የዛሬው የጦማሪያኑ እና የጋዜጠኞቹ የፍርድ ቤት ዝርዝር ዘገባ (ኤልያስ ገብሩ)
በትናንቱ የቪኦኤ ዘገባ ላይ አቃቤ ሕግ ቅሬታ አቀረበ ጦማሪ አቤል ዋበላ ችሎት በመድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ተባለ ‹‹ሥነ-ሥርዓት ያዝ!›› ዳኞች ‹‹እናንተ ራሳችሁ ሥነ-ሥርዓት ያዙ! ይህ ችሎት ነው፡፡ ግልጽ ነው›› አቤል ዋበላ ‹‹ውሳኔው ለሁሉም ከሆነ፣ ለአቃቤ ህጉም ሆነ ለአለቃው ጠ/ሚኒስቴርም መሆን አለበት፡፡›› ‹‹ጓደኛዬ (አቤል) የሚቀጣ ከሆነ ውሳኔው እኔም ላይ ይታዘዝ›› ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ትናንት ምሽት ከ3፡00 ሰዓት […]![]()
የፌዴራል ዋና ኦዲተር የፋይናንስ ሕጋዊነትን ያልተከተሉ ቢሊዮን ብሮች መኖራቸውን ይፋ አደረገ
የተሟላ ማስረጃ ሳይኖር በወጪ የተመዘገበ 368 ያልተወራረደ ሒሳብ መገኘቱን፣ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ውዝፍ ገቢ መኖሩንና ሌሎችንም ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ ዱቢሶ ለምክር ቤቱ አሳውቀዋል፡፡ ዋና ኦዲተር በ2006 ዓ.ም. የፌዴራል መንግሥት በጀት ተጠቃሚ የሆኑ 135 መሥሪያ ቤቶችን ኦዲት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሠረት የፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲትን ያልተከተሉ 78 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሕጉ መሠረት ያላወራረዱት ሁለት […]![]()
“ከአገር የሚሰደዱት ገጠሬ ወጣቶች ናቸው”ዲና ሙፍቲ
አሸባሪነት በኢትዮጵያ ሊስፋፋ ያልቻለው ሕዝቡ በሙሉ ሰላይ በመሆኑን ዲና ሙፍቲ አስታወቁ፡፡ ከአገር ተሰድደው የሚውጡት አብዛኛዎቹ ገጠሬ ወጣቶች እንደሆኑና ሟቹ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ህዳሴ አባት በጣም እንደሚናፍቋቸው ተናገሩ፡፡ ቀድሞ በቃል አቀባይነት ሲሰሩ የነበሩት በአሁኑ ወቅት ደግሞ በኬኒያ ተወካይ የሆኑት አቶ ዲና ሙፍቲ ስታንዳርድ ዲጂታል ከተባለ የኬኒያ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ለቀረቡላቸው በርካታ ጥያቄዎች ድርጅታቸውን በመወከል […]![]()
ፓትርያርኩ: የረዳት ሊቀ ጳጳሱን የባንክ ሒሳብ የማንቀሳቀስ ሓላፊነት ያለቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ ቀየሩ፤ ‹‹ተጠያቂነት እና መንፈሳዊ መከባበር የሌለበት የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኹኔታ አፋጣኝ መፍትሔ የሚያሻው ነው›› /ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ/
አስተዳደሩን፣ የገንዘብ እና ንብረት እንቅስቃሴውን የመቆጣጠር ሕጋዊ ሓላፊነታቸው ተገድቧል በዕቅድ ባልተያዙ ከፍተኛ ግዥዎች እና የወጪ ሰበቦች ምዝበራ ሊፈጸም እንደሚችል ተጠቁሟል በቅ/ሲኖዶስ የተመደቡትን ረዳት ያጣው ሀ/ስብከቱ ከ50 ሚልዮን በላይ ተቀማጩ ለአደጋ ተጋልጧል * * * የሠራተኞች ደመወዝ እና አይቀሬ የኾኑትን ዕለታዊ የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች እንዳይወጡ ፈቃደኛ ያልኾንኩበት እና ሥራዎች እንዲጓተቱ ያደረግኹበት ወቅት እስከ ዛሬ ድረስ የለም፡፡ …![]()
የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሪፖርት – 2007 ዓ.ም – ሰኔ 05, 2015
Report by Ethiopian Ethics and Anti-Corruption Commission, 06-04-15
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ስለፊፋ ፕሬዚዳንት – ሰኔ 05, 2015
Juneidi Basha, President of Football Federation of Ethiopia about the crisis inside FIFA, 06-04-15
በኢትዮጵያ ሶማሊያ ድንበር በተነሳው ግጭት የመከላከያ ሰራዊት አባላት የገደሉዋቸው ሰዎች ቁጥር ጨምሯል
ግንቦት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምንጮች እንደገለጹት የሶማሊ ክልል ልዩ ሚሊሺያ አባላትና የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በወሰዱት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አልቀዋል። ሂራን በተባለው አካባቢ ለቀናት በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት መንስኤ በውል አልታወቀም። ዛሬ በማህበራዊ ድረገጾች የተላለፈው አስደንጋጭ ቪዲዮ በርካታ የሞቱ ሲቪሎችንና የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ያሳያል። ቪዲዮውን የለቀቀው የአልጃሲራ …
በኢትዮጵያ ባለፉት 5 ዓመታት ብቻ ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ወደ ውጭ ተሻግሯል
ግንቦት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ ባወጣው ልዩ ዘገባ በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2008 እስከ 2012 ባለው ጊዜ ውስጥ ከኢትዮጵያ በተለያዩ ህገወጥ መንገዶች ከ70 በሊዮን ብር ወይም ከ3 ቢሊዮን 550 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ወደ ውጭ ወጥቷል። በ5 ዓመታት ውስጥ ተሰርቆ የወጣው ገንዘብ ወደ አገሪቱ ከገባው የውጭ የቀጥታ ኢንቨስትመንት መጠን ጋር …
የዶላር እጥረቱ ተባብሶ ቀጥሎአል
ግንቦት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የሚታየው ከፍተኛ የዶላር እጥረት መባባሱን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።በአስመጭና ላኪነት ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ስራቸውን መስራት እንዳልቻሉ አቤቱታ በማቅርብ ላይ ናቸው። በርካታ ፋብሪካዎችም በዶላር እጥረት የተነሳ የመለዋወጫ እቃዎችን ማስገባት አለመቻላቸውን እየገለጹ ነው። መንግስት የዶላር ችግር እንደሌለ በተደጋጋሚ ቢናገርም፣ በመሬት ላይ ያለው እውነታ ከዚህ እንደሚለይ ነጋዴዎች ይገልጻሉ። …
በጀርመን የኢትዮጵያ ኢምባሲ የተዘመረው መዝሙር ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጠረ
ግንቦት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው የግንቦት20 በአልን ለማክበር ጀርመን በርሊን ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባዘጋጀው ዝግጅት ላይ ያልተጠበቀ ክስተት መታየቱን ምንጮች ገልጸዋል። በዝግጀቱ ላይ የኢትዮጵያና የጀርመን ከፍተኛ ባለስልጣናት በእንግድነት ተገኝተዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ መዝሙር ያለምንም ችግር የተፈጸመ ቢሆንም፣ የጀርመን ብሄራዊ መዝሙር በሚዘመርበት ጊዜ ግን የጀርመንን ባለስልጣናት ያስደነገጠ መዝሙር ቀርቧል። የኢትዮጵያ ኢምባሲ …
በአቶ አሊ መኪ ላይ የ 15 አመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት
ግንቦት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አሊ በኡስታዝ አቡበክር አህመድ መዝገብ ተከሶ የሚገኝ ሲሆን፣ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ፣ በሌሉበት የ15 አመት ጽኑ እስራት ፈርዶባቸዋል። ታህሳስ 23/2005 የዋለው ችሎት አቶ አሊን በነጻ ቢያሰናብታቸውም፣ አቃቢ ህግ ይግባኝ ብሎባቸው ክሱ እንደገና እንዲታይ ተደርጓል። በአቶ አሊ ላይ የተሰጠው ውሳኔ በሌሎች የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ …
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ሰኔ 04, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት