የገዥው የኢህአዴግ መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ህዝቦችን የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ የተቃዋሚ ድርጂቶች ዲሞክራሲያዊ ናቸው ብላችኋል በማለት ንፁሃን ዜጎችን እያሰረ መሆኑን ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን አስረድተዋል። በአዲስ አበባ ከተማ ጀሞ በተባለው አካባቢ ግንቦት 7 እና ሌሎችም የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ድርጂቶች ዲሞክራሲያዊ ናቸው የሚል በራሪ ወረቀት መበተኑን ተከትሎ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ የጀሞ አካባቢ ነዋሪ ግንቦት 22 ቀን […]

በጥያቄአቸው፣ በአስተዳደር ይኹን በልማት ሥራ ምንም ችግር የለም ብለዋል፤ በሌለ ልማት! ምእመናኑንም ‹‹ምንም ዓይነት ድርሻ የሌላቸውና ማንነታቸው የማይታወቅ›› ሲሉ ገልጸዋቸዋል የታሰሩት ምእመናን በፖሊስ ጣቢያ ‹‹ማዕተባችኹን በጥሱ መስቀላችኹን አውልቁ›› ተብለዋል የቀድሞው የደብሩ አለቃ ዘካርያስ ሓዲስና ኃይሌ ኣብርሃ ከውዝግቡ ለማትረፍ እያሰሉ ነው የቤተ ክርስቲያን ይዞታ ከቤተ ክርስቲያን አቋም ጋር በሚስማማ እና ሀብቷን በሚያስጠብቅ አኳኋን እንዲለማ በመጠየቅ በቅንጅት …

ኢሳት ዜና (ሰኔ 4 2007 ዓም) የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ማፈኑን ተከትሎ የተቃዋሚ ፓርቲዎች “ ቅድሚያ ለነጻነት ” ወደሚል ትግል ማዘንበላቸውን የእንግሊዝ ዘ-ጋርዲያን ጋዜጣ ሐሙስ ለንባብ ባበቃው እትሙ ዘገበ። ገዢው የኢሃዴግ መንግስት በቅርቡ በተካሄደው ብሄራዊ ምርጫ በብቸኝነት ለድል መብቃቱም በመንግስት ላይ ጥያቄ ያላቸው አካላት ሌሎች አማራጮችን እንዲመለከቱ ማስገደዱንም ጋዜጣው በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ …

ጃሚዮ በተባለ መንደር የሚኖሩ ነዋሪዎች በሁለቱ ሃይሎች መካከል ከፍተኛ ጦርነት መካሄዱንና ከባድ የጦር መሳሪያዎች ሲተኮሱ መስማታቸውን ተናግረዋል።አልሸባብ አገኘሁት ያለውን ድል በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተበባለ ነገር የለም። ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ሆርሲድ ሚዲያ እንደዘገበው ደግሞ የአልሸባብ ተዋጊዎች የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የጫኑ ወታደሮችን አድፍጠው በመጠበቅ ጥቃት ፈጽመዋል።ለ12 ሰአታት ያክል የቆየ በከባድ መሳሪያዎች የታጀበ ጦርነት መካሄዱን ነዋሪዎች ገልጸዋል። አልሸባብ […]

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ እንደዘገበው በማእከላዊ ሶማሊያ በተደረገው ጦርነት ታጣቂ ሃይሉ 30 የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉን አስታውቋል። ጃሚዮ በተባለ መንደር የሚኖሩ ነዋሪዎች በሁለቱ ሃይሎች መካከል ከፍተኛ ጦርነት መካሄዱንና ከባድ የጦር መሳሪያዎች ሲተኮሱ መስማታቸውን ተናግረዋል። አልሸባብ አገኘሁት ያለውን ድል በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተበባለ ነገር የለም። ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ሆርሲድ ሚዲያ እንደዘገበው …

በደቡብ አፍሪካ የሚደረገዉን የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ለመካፈል ወደዚያዉ ያመራዉ የወያነኔ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቴድሮስ አድሐኖም በጆሐንስበርግና በፕሪቶሪያ ዙሪያ እንዳይዘዋወሩ ጥብቅ መልእክት ከወያኔ መረጃ ቢሮ በፕሪቶሪያ ለሚገኘዉ የወያኔ ኢንባሲ መተላለፉን ከዉስጥ የወጣ መረጃ አመለከተ፤ ተላላኪዉ ቴድሮስ አድሐኖም በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ የወያኔ ደጋፊዎችን ሰብስቦ ሊያነጋግር በሞባይል ስልክ መልክት (text)እያደረገ ሳንድተን ሪክሬሽን ሴንተር ቀጠሮ እያስያዘ መሆኑን የደረሱበት በደቡብ […]

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን የመንግስት ተሿሚዎችን፣ ተመራጮችንና የመንግስት ሠራተኞች ሃብት የመመዝገብ ሥራዎችን ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እያከናወነ ቢሆንም ባሉበት ጫናዎች ምክንያት መረጃውን ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ አለመቻሉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ኮምሽኑ የባለስልጣናትን ሀብት እንዲመዘግብ ስልጣን ሲሰጠው በመንግስትና በሕዝብ መካከል መተማመን ይፈጥራል ተብሎ ነው፣ ይሁን እንጅ ኮምሽኑ …

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ለ3 ቀናት በደብረ ዘይት ከተማ በተካሄደው ግምገማ ባለስልጣኖቹ እርስ በርስ ሲወነጃጀሉ እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የመገምገሚያ ነጥቦቹ “አመራሮቹ በየምርጫ ምደባቸው የነበራቸው ውጤታማነትና ውስጣዊ ስኬት፤ በተቋማቸው የነበረው የኪራይ ሰብሳቢነት ትግልና የተመዘገበ ውጤት፣ እንዲሁም ግለሰባዊ ድክመታቸው ” የሚሉ ሲሆኑ፣ በግምገማውም ባለስልጣኖቹ ከኤ እስከ ዲ ያሉ ውጤቶችን …

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት15 ምርጫ ከመካሄዱ 2 ሳምንት በፊት መንግስት ዋና ዋና የሚባሉ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ እንዲቀንስ ቢያደርግም ፣ ከምርጫው በሁዋላ ተመልሶ መውጣቱን ዘጋቢያችን ገልጿል። ምስር በኪሎ ከ50 ብር በላይ፣ በርበሬ ከ120 ብር በመሸጥ ላይ መሆኑን የገለጸው ዘጋቢያችን፣ ዘይትና ስኳር ተመልሰው ከገበያ መጥፋታቸውን የስጋና የወተት ምርቶች እንዲሁም በሁሉም የእህል ዘሮች …

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ረቡዕ 200 ኢትዮጵያውያንን የጫኑ 2 ጀልባዎች ከ24 ሰአታት የባህር ላይ ጉዞ በሁዋላ ጅቡቲ በሰላም ደርሰዋል።ኢትዮጵያውያኑ የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ወደ አዲስ አበባ ይጓጓዛሉ። በየመን አሁንም በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ። በአገሮቱ ከሚኖሩት ከ80 ሺ በላይ ስደተኞች መካከል ወደ አገራቸው ለመመለስ ፍላጎት ያሳዩት ከ2 …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

አቶ አቻም ደምሴ በ2004 ዓ.ም ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ከ5400 አማራ ገበሬዎች ጋር ተፈናቅሎ ነበር፡፡ በጊዜው ሙሉ ንብረቱ ወድሞበታል፡፡ አሁን ከ3 ልጆቹ እና ባለቤቱ ጋር በባህር ዳር ከተማ አካባቢ ካለች መሸንቲ ከተማ በቀን ስራ ይተዳደር ነበር፡፡ የብዙ አማራ ገበሬዎች ፋይል በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየታየ ባለበት በአሁኑ ወቅት ለቅሶ ለመድረስ ቡለን ወረዳ […]

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከምርጫ ጋር በተየያዘ በርካታ ሰዎች እየታሰሩ እንደሚገኙ ከከተማዋ የሚገኙ ምንጮቻችን ገለፁ።በምንጮቻችን መረጃ መሰረት- በአዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 11 ለም ተብሎ በሚጠራው ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች በሃሰት እየተውነጀሉ በስርዓቱ ታጣቂዎች እየታሰሩ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው ከትምህርት ቤቱ ከታሰሩት ተማሪዎች ውስጥ ተማሪ ሲራክ ለማ የተባለ የ9ኛ ክፍል ተማሪ፤ ያሬድ ፋሲል እና አላምረው ይደግ የተባሉት […]

ናይጄሪያ ፕሬዘደንታዊ ምርጫ አድርጋለች. የቀድሞ ፕሬዘዳንት ጆናታን ተሸንፈው አዲስ ፕሬዘዳንት ተመርጠዋል. ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር ይሉታል ይሄ ነው. የናይጄሪያ ሕዝብ መብቱ ተከብሮ, የፈለገዉን እየሻረ, የፈለገዉን እየሾመ ትልቅ ደረጃ መድረሱን ለማየት ችለናል. ናይጄሪያ እንደ ኢትዮጵያ ብዙ ሕዝብ ያላት አገር ናት. እንደ ኢትዮጵያ የተለያዩ ብሄረሰቦች አሏት. እንደ ኢትዮጵይያ ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች በብዛት አሉባት. ወያኔዎች ሰዉን ሁሉ ሽብርተኛ እያሉ […]

ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን የቴፒ ወጣቶች ቡድን በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ የወሰደውን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ ሶስት ፖሊሶች ከተገደሉና በርካታ እስረኞች ካመለጡ በሁዋላ፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ታጣቂዎች መሽገውበታል ወዳለው አካባቢ በመሄድ ውጊያ የከፈቱ ሲሆን፣ ወጣት ታጣቂዎች አስቀድመው ዝግጅት አድርገው በመቆየታቸው በርካታ ወታደሮች መሞታቸውንና መቁሰላቸውን ምንጮች ገልጸዋል። የኢሳት ምንጮች እንደሚሉት በርካታ ወታደሮች …

ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማእከላዊ ስታትስቲክስ ጽ/ቤት በወጣው መረጃ በዚህ አመት የታየው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ7 በመቶ ጭማሪ ሲያሳያስ ፣ የምግብ ያዋጋ ግሽበት 6.9 በመቶ ምግብ ነክ ያልሆኑ ደግሞ 8 .2 በመቶ የዋጋ ጭማሪ አሳይተዋል። በዚህ አመት በግንቦት ወር የታየው የዋጋ ግሽበት አምና ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በ9.4 …

ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው አቶ ዳዊት አስራደ ሰኔ 3/2007 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ በ5 ሺ ብር ዋስ እንዲፈታ ዋስትና የተፈቀደለት ቢሆንም ገንዘቡን ካስያዘ በኋላ ዋስትናው እንደተነሳ ተነግሮት በእስር ላይ እንዲቆይ ተደርጓል። ፖሊስ አቶ ዳዊትና ሌሎች ተከሳሾች ምስክሮችን ያባብሉብኛል በሚል ለ14 ቀን ታስረው እንዲቆዩ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ጌታቸው ሺፈራው አሁን አሁንማ ዜና የሚሆን ነገር ጠፍቷል፡፡ መታሰር ተለምዷል፡፡ መደብደብ ተለምዷል፡፡ የሀሰት ምስክርነት ተለምዷል፡፡ ከአሁን ቀደም ‹‹ጉድ ነው!›› ያሰኙ የነበሩ ህገ-ወጥነቶች አሁን የቀን ተቀን ተግባር ሆነው ወደ ጎን እያየን እየተውናቸው ነው፡፡ በአጠቃለይ የስርዓት ነውር፣ ብልግና፣ ስርዓት አልበኝነትን ለዜናም የሚበቁ አልሆኑም፡፡ በአንድ ወቅት ‹‹እንትና ጠያቂ ተከለከለች፣ እንትና ምግብ እንዳይገባለት ተደረገ›› ተብሎ ዜና ይሰራ ነበር፡፡ እንደ […]

  የቁጥጥር እና የፋይናንስ ሓላፊዎች የትምህርት ዝግጅት እና ልምድ ዝቅተኛ ነው ከአጥቢያዎች የሚዘረፈው የሙዳይ ምጽዋት ገንዘብ ቢሯቸው ድረስ ይመጣላቸዋል የቤተሰብ ጉባኤ በሚመስለው የቁጥጥር ክፍሉ ስብሰባ የዘረፋ ስልቶች ይቀመራሉ ትኩረቱን ወደ ከፍተኛ ግዥዎችና ፕሮጀክቶች ለማዞር እስከ መምከር ተደርሷል እነኃይሌ ኣብርሃ እንዳሉት፣ ‹‹ንቡረ እድ ኤልያስን የተማመነ ምን ይኾናል!›› /ከሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች/ ‹‹ባለቤቷን የተማመነች በግ ላቷን ውጪ ታሳድራለች›› …

ማስታወሻ ፥ (የዚህን ጽሁፍ መሰረታዊ ይዘት በቅርቡ በተካሔደው ኢሳት ባዘጋጀው ጉባዔ ላይ አቅርቤው ነበር። የኢትዮጵያን ሁኔታዎች አዘውትሮ እንደሚከታተል ኢትዮጵያዊ በሀገራችን የሰፈነው ዘግናኝ ድህነት የፈጠረውን አሳዛኝና አዋራጅ ስደትና ወደፊትም መፍትሔ ካልተበጀ ሊፈጥር የሚችለውን ችግር ገምቼ የባሰ ድህነት ውስጥም ሳንዘፈቅ ችግሩን ምን ብናደርግ ነው መቋቋም የሚቻለው በሚለው ጥያቄ ላይ ሳሰላስል የመጣልኝ ሀሳብ ነው። የሰጠሁት የመፍትሄ ሃሳብ በጉባዔው […]

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከኢህአዴግ ጽ/ቤት ለመላ አገሪቱ በወረደ ጊዚያዊ አደረጃጃት፣ በመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች እንዲሁም በተለያዩ የግንባሩ ጽ/ቤቶች በተሰጠ መመሪያ መሰረት የተዋቀረው የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ ኮሚቴ የድጋፍ ሰልፍ የማድረግ እቅዱን ሰርዟል። ምርጫው ፍጹም ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መሆኑን ህዝቡ በድጋፍ እንዲመሰክር እና ሚዲያዎቹ በቀጥታ እንዲዘግቡት መመሪያ ከወረዳ በሁዋላ፣ የኢህአዴግ ምክር ቤት ተሰብስቦ ሰላማዊ …

ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ለ2008 ዓም ከመደበው በጀት ውስጥ መከላከያ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ ፍትህና ደህንነት ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቦላቸዋል። የፌዴራል መንግሥት የመደበኛ ወጪ ዝርዝር እንደሚሳየው የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር 9. 5 ቢሊየን ብር፣ የፌዴራል ፖሊስ 1. 6 ቢሊየን ብር፣ ፍትሕና ደህንነት 3. 5 ቢሊየን ብር ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸዋል፡፡ መከላከያ በ2007 ዓም ከተያዘለት …

ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በኤርትራ ይፈጸማሉ ያላቸውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ይፋ እንደሚያደርግ ካስታወቀ በሁዋላ፣ ኤርትራ መልስ ሰጥታለች። የድርጀቱ ሪፖርት በሃሰት የተሞላና ነው ያለው የኤርትራ መንግስት መግለጫ፣ ድርጅቱ ጥቃቱን የሰነዘረው በመንግስት ላይ ሳይሆን ለሰው ልጅ ክብርና ማንነት ከፍተኛ ከበሬታ በሚሰጠው ስልጡን በሆነው ማህበረሰብና ህዝብ ላይ ነው …

ከሁሉም በማስቀደም የከበረ ሰላምታዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ። በዋነኛነት ይህንን ደብዳቤ ልጽፍ ያነሳሳኝ ሰሞኑን በአንድ በጥላሁን ገሰሰ ስም የሚነግድ “መስፍን” በዙ የተባለ ተራና ስብእና የጎደለው አጭበርባሪ ግልሰብ ታማኝ በየነ ለምን ክብርና ሽልማት አገኘ በሚል በአደባባይ “ታማኝ በየነ ገዳይ እና ከፋፋይ” ነው ከማለት አልፎ ግለሰቡ በጥላሁን ገሰሰ ስም (Tilahun Gesesse TV / TGTV) በሚለቀው እውር ድንብሩ በወጣ ቪዲዮ […]

ለቀላል ባቡሩ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያሰራጩ ጣቢያዎች ሥራ ጀመሩ

ለአዲስ አበባ የቀላል ባቡር መስመር ከብሔራዊ ኃይል ማሰራጫ በመሳብ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያዳርሱ አራት ሰብስቴሽኖች ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ፡፡ በአያት አደባባይ አቅራቢያ ሲገነባ ቆይቶ የተጠናቀቀውን ኃይል

ማሰራጫ ሰብሰቴሽን፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስና ኢኪኖሚ ክላስተር አስተባባሪ፣ የመገናኛና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤልና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ  ግንቦት 30 ቀን 2007 ዓ.ም. ሥራ አስጀምረዋል፡፡ 

በስድስት ወራት ውስጥ ግንባታቸው ያለቀው አራት ሰብስቴሽኖች በጠቅላላው 160 ሜጋ ዋት ኃይል ለከተማው ባቡር የሚያቀርቡ ናቸው፡፡ ለባቡሩ መስመር ግንባታ ከተመደበው 470 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ በ85 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነቡት እነዚህ የኃይል ማሰራጫዎች በአያት፣ በምንሊክ አደባባይ፣ በጦር ኃይሎችና በቃሊቲ አካባቢ ተገንብተው ዝግጁ ሆነዋል፡፡ 

የሰብስቴሽኖቹን ግንባታ ያከናወነው የቻይናው ናሽናል ግሪድ ኩባንያ በእህት ኩባንያው ቻይና ኤሌክትሪካል ኤንድ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ በኩል አከናውኗል፡፡ ዶ/ር ደብረ ጽዮን ለጋዜጠኞች እንዳብራሩት፣ ለባቡሩ ኃይል የሚያቀርቡት ማከፋፈያዎች በቀጥታ ከዋናው ማሰራጫ እንዲቀበሉ በማድረግ ምንም ዓይነት የኃይል መቆራረጥ እንዳያጋጥማቸው የራሳቸው መስመር ተዘርግቶላቸዋል፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል ለባቡሩ የሚያቀርቡት ማከፋፈያዎች ሙሉ ለሙሉ ግንባታቸው ተጠናቆ ቢዘጋጁም፣ በቀጥታ ወደ ባቡሩ ለማድረስ የሚስችሉ ዝርጋታዎች በመካሄድ ላይ እንደሚገኙ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡ ኢንጂነር አዜብ በበኩላቸው ከማከፋፈያዎቹ ኃይል ተቀብለው ለባቡሩ የሚያደርሱ ኬብሎች ቀበራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ይፋ አድርገዋል፡፡ 

ምንም እንኳ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ በፍጥነት ግንባታቸው ተጠናቋል ቢባልም፣ የተወሰነ መዘግየት እንዳጋጠመና ይህም ከወሰን ማስከበር ጋር በተያያዘ መሆኑን ዶ/ር ደብረ ጽዮንና ኢንጂነር አዜብ ይፋ ተናግረዋል፡፡ የኃይል ማከፋፈያዎቹ ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ ደምሰው ዘለቀ በበኩላቸው፣ ለኃይል ማከፋፈያ ግንባታ ማካሄጃ የሚያስፈልጉትን ቦታዎች ማግኘት የተቻለው፣ በዚህ ዓመት ኅዳር ወር ውስጥ እንደነበርና ምንም እንከን ሳያጋጥም ሥራው ተጠናቆ ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የከተማው ቀላል ባቡር አገልግሎት ለመጀመር ፍተሻዎች እየተካሄዱ እንደሚገኙ የገለጹት ዶ/ር ደብረ ጽዮን፣ እየተካሄዱ የሚገኙት ሙከራዎችና ፍተሻዎች መጠናቀቅ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል፡፡ ባቡሩ በየትኛውም ጊዜ ሊጀምር ዝግጁ ቢሆንም፣ የሚካሄዱበት ሙከራዎች ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል ከአዲስ አበባ ጂቡቲ ለሚዘረጋው የባቡር መስመር በ100 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እየተገነባ ለሚገኘው መስመርም ስቴትግሪድ የተሰኘው የቻይና ኩባንያን ጨምሮ አራት ተቋራጮች ኮንትራቱን ወስደው እየገነቡት እንደሚገኝ የገለጹት ዶ/ር ደብረ ጽዮን፣ በመጪው ዓመት የአዲስ-ጂቡቲ መስመር ተጠናቆ እንደሚመረቅ ይፋ አድርገዋል፡፡ 

ኢንጂነር አዜብ በበኩላቸው፣ በመጪው ዓመት ጥር ወር ይጀመራል ተብሎ በሚጠበቀው የባቡር ኃይል ማሰራጫ ግንባታ የጂቡቲ መንግሥት የሚያካሂደውን ግንባታ እኩል መጀመርና ማጠናቀቅ እንደሚጠበቅበት ስምምነት መደረጉን አስታውሰዋል፡፡ 

በአዲስ አበባና በጂቡቲ መካከል የሚዘረጋው የባቡር መስመር በየቀኑ 1,500 የጭነት ተሽከርካሪዎች የሚያደርጉትን ምልልስ በመቀነስ፣ ሁለት ቀናት ይፈጅ የነበረውን ጉዞም ወደ አሥር ሰዓት ዝቅ በማድረግ፣ የገቢና የወጪ ንግዱን እንደሚያቀላጥፍ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ 752 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የአዲስ አበባ -ጂቡቲ መስመር ከቻይና መንግሥት በተገኘ ፋይናንስ በቻይና ኩባንያዎች በመገንባት ላይ ነው፡፡

 

 

 

ኢዴፓ ምርጫው ተዓማኒ አይደለም አለ

ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. የተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊና በኅብረተሰቡም ዘንድ ተዓማኒ አልነበረም በማለት፣ የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ተቃውሞውን አሰማ፡፡ በዚህ ምክንያትም የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበለው አስታውቋል፡፡ 

በተደጋጋሚ ሲያጋጥሙ የነበሩ እንቅፋቶችና ችግሮች በምርጫው ፍትሐዊነት፣ ዴሞክራሲያዊነትና ተዓማኒነት ላይ ችግር እየፈጠሩ መሆናቸውን በማሳሰብ በቅድመ ምርጫ ወቅት የገጠሙን ችግሮች መፍትሔ እንዲያገኙ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም፣ ችግሮቻቹ መፍትሔ እንዳላገኙ ኢዴፓ ጠቁሟል፡፡ ‹‹ችግሮቹ ከመፈታት ይልቅ ይበልጥ በመባባስና ታቅዶ የሚፈጸም በሚመስል ሁኔታ ጫናዎች የፓርቲያችንን እንቅስቃሴ በሚፈታተን ደረጃ ተጠናክረው ቀርበዋል፤ ያለው ፓርቲው፣ በቅድመና በድኅረ ምርጫ ገጠሙኝ በማለት የነቀሳቸውን 22 ተግዳሮቶች በባለ አራት ገጽ መግለጫው ውስጥ አካቷል፡፡ 

ፓርቲው ይህን ያስታወቀው ግንቦት 29 ቀን 2007 ዓ.ም. በግዮን ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ሲሆን፣ መግለጫውን የሰጡት ደግሞ የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጫኔ ከበደና ሌሎች የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ናቸው፡፡  

ፓርቲው በቅድመ ምርጫውና በምርጫው ዕለት አጋጠሙኝ ካላቸው ችግሮች መካከል የዕጩዎች መዋከብ፣ ከሥራ ገበታቸው መፈናቀል፣ ከዕጩነት ራሳቸውን እንዲያገሉ ማስፈራራት፣ በአካባቢያቸው የፀጥታ ችግሮች ቢፈጠሩ ተጠያቂ እንደሚሆኑ በመግለጽ ማሸማቀቅ፣ መደለያ መስጠት፣ ማሰር፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች በግልጽ የኢሕአዴግ የመወዳደርያ ምልክት ያለበትን ካኔቴራ ለብሰው ኢሕአዴግን ምረጡ በማለት በአደባባይ ሲቀሰቅሱ ምርጫ ቦርድ በዝምታ መመልከቱ፣ እንዲሁም ተቃዋሚዎች ፀረ ሰላምና የልማት ሒደታችንን ያደናቀፉ ኃይሎች ናቸው በማለት በአንድ ለአምስት አደረጃጀት በየመንደሩ የጥላቻ ሐሳቦችን በኅብረተሰቡ ውስጥ መበተን ተጠቃሾች ናቸው ሲል ኢዴፓ ገልጿል፡፡

በተጨማሪም ታዛቢዎችን በመደለል እንዳይታዘቡ ማድረግ፣ ማስፈራራትና ይህን ሁሉ ተቋቁመው ወደ ምርጫ ጣቢያ የሄዱትን ማባረርና ማሰር፣ በምርጫ ጣቢያ ውስጥ የታጠቁ የፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት አባላት በመገኘት መራጩን ሕዝብ በማሸማቀቅ ተፅዕኖ ውስጥ መክተት፣ እንዲሁም በቅሬታ አቀራረብ ደንብና አሠራር መሠረት ቅሬታዎችን ለመቀበል በየትኛውም ደረጃ ያሉ የምርጫ አስፈጻሚ አካላት ፈቃደኛ አለመሆናቸው በምርጫው ዕለት የገጠሙት ችግሮች እንደሆኑ ኢዴፓ አስታውቋል፡፡ 

‹‹በሒደቱም ሆነ በምርጫው ዕለት የተፈጸሙትን ድርጊቶች በነቂስ የመረመረው የኢዴፓ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣ ምርጫው በየትኛውም መመዘኛ ነፃ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ እንዳልነበር አረጋግጧል፤›› በማለት ሒደቱንና ውጤቱን ፓርቲው ተቃውሟል፡፡ 

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ከሌላው ዓለም በተለየና በላቀ ሁኔታ የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት ያለ ቢሆንም፣ የምርጫው ውጤት ግን ይህንን ፈጽሞ በማያሳይ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ በዓለማችን ዴሞክራሲያዊ ምርጫም ሆነ የይስሙላ ምርጫ በሚያካሂዱ አገሮች ላይ እንደዚህ ዓይነት ውጤት ተመዝግቦ አያውቅም፡፡ ውጤቱም ሆነ ሒደቱ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊና ነፃ አለመሆኑን ያረጋገጠ ነው፤›› በማለት አትቷል፡፡

ይህን መግለጫ ለመስጠት ለምን እንደዘገዩ ከሪፖርተር ጥያቄ የቀረበላቸው የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጫኔ ከበደ፣ ‹‹ፓርቲያችን ሕግ መከበር፣ በመርህ ላይ የተንተራሰ ሥራዎች መሠራት እንዳለባቸው ይገነዘባል፡፡ እንደ ሌሎች ፓርቲዎች ቀድመን መግለጫዎችን ያልሰጠንበት ምክንያት በጥናት ላይ መመሥረትና ምክንያታዊ መሆን ስላለብን፣ እንዲሁም ደግሞ ከሁሉም የአገሪቱ ክልሎች የሚደርሱን መረጃዎች እውነትና ተዓማኒ መሆናቸውን እስክናረጋግጥ ሒደቱ ጊዜ በመውሰዱ ነው፤›› በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ኢዴፓ ፓርቲው የጉዳዩ ባለቤት የሆነው ሕዝብ ‘እኔ ምን አገባኝ’ ከሚልና ከዳር ተመልካችነት ስሜት ራሱን በማራቅ፣ ለዚህች አገር ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ አስተዋጽኦ ይበልጥ እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርቧል፡፡  

 

 

የበጀት ጉድለቱ 27.6 ቢሊዮን ብር ይሆናል

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ የ2008 ዓ.ም. አጠቃላይ በጀትን ሰኔ 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ማክሰኞ ለሕዝብ ተወካዮች ሲያቀርቡ፣ ካቀረቡት 223.39 ቢሊዮን ብር ውስጥ መንገዶች፣ ትምህርትና ዕዳ ክፍያ ከአንድ እስከ ሦስት ያለውን ድርሻ ይዘዋል፡፡

ሚኒስትሩ አቶ ሱፊያን አህመድ ለ2008 ዓ.ም. ያቀረቡት አጠቃላይ በጀት ከዘንድሮው በ19.7 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ከጠቅላላው የወጪ በጀት ውስጥ 50.288 ቢሊዮን ብር ለመደበኛ ማለትም ለደመወዝ፣ ለአበልና ልዩ ልዩ ሥራ ማስኬጃ ክፍያዎች መመደቡን ገልጸዋል፡፡ ለካፒታል በጀት ደግሞ ብር 84.3 ቢሊዮን ብር መመደቡን፣ ለክልሎች ድጎማ ደግሞ 76.8 ቢሊዮን ብር መመደቡን አስረድተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እ.ኤ.አ. 2015 ማገባደጃ ላይ የሚጠናቀቁትን የምዕተ ዓመቱን የልማት ግቦች ለሚተካው ዘላቂ የልማት ግቦች ማስኬጃ 12 ቢሊዮን ብር መመደቡን አብራርተዋል፡፡

ሚኒስትሩ ካቀረቡት 223.39 ቢሊዮን ብር  ጠቅላላ በጀት ውስጥ የካፒታል በጀት 37.4 በመቶ በመያዝ ትልቁን ድርሻ አግኝቷል፡፡ ለክልል መንግሥታት የሚደረገው ድጎማ 34.7 በመቶ ሲሆን፣ ለመደበኛ ወጪዎችና ለዘላቂ ልማት ግቦች ማጠናከሪያ ወጪዎች በጀት ደግሞ በቅደም ተከተል 22.5 በመቶ እና 5.4 በመቶ ናቸው፡፡

ከአጠቃላይ የ2008 ዓ.ም. መደበኛና ካፒታል በጀት ውስጥ 66.6 በመቶ የሚሆነው የተመደበው ቅድሚያ ለተሰጣቸው የኢኮኖሚ ዘርፎች ቢሆንም፣ ከዚህ ቀደም በነበሩት ዓመታት ዝቅተኛ ትኩረት የነበረው የዕዳ ክፍያ በጀት በዚህ በጀት እጅግ ከፍተኛ ትኩረት ማግኘቱን ከበጀት ሰነዱ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ከመደበኛና ከካፒታል ወጪ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ካገኙት መካከል የኢትዮጵያ የመጀመርያው መንገዶች ባለሥልጣን ሲሆን፣ 33.386 ቢሊዮን ብር ተመድቦለታል፡፡ የትምህርት ዘርፍ 32.927 ቢሊዮን ብር በማግኘት በሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ በሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የዕዳ ክፍያ ወጪ 11.903 ቢሊዮን ብር ተመድቦለታል፡፡

መከላከያ ሚኒስቴር 9.5 ቢሊዮን ብር የተመደበለት ሲሆን፣ ግብርና ሚኒስቴር 9.125 ቢሊዮን ብር የተፈቀደ በጀት በማግኘት አራተኛና አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ትልቁን በጀት ማግኘት የቻለው የዋና መንገዶች ግንባታና አገናኝ መንገዶች ግንባታ ለማከናወን ነው፡፡ ነባሮቹን ለማሻሻልና ለማጠናከርም ከፍተኛ በጀት መያዙን ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡

የትምህርት ዘርፍ በሁለተኛ ደረጃ ትልቁን በጀት ማግኘት የቻለው ለአዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች ግንባታና ነባሮቹንም ዩኒቨርሲቲዎች ለማጠናከር መሆኑን የበጀት ሰነዱ ያስረዳል፡፡ ሚኒስትሩ አቶ ሱፊያን ያቀረቡትን የ2008 ዓ.ም. በጀት ለመሸፈን መንግሥት ያቀደው ከአገር ውስጥ ገቢ፣ ከውጭ ዕርዳታና ብድር ነው፡፡

በዚህም መሠረት 157.06 ቢሊዮን ብር ከአገር ውስጥ ገቢ ለመሰብሰብ፣ ከመሠረታዊ አገልግሎት ከለላ 6.67 ቢሊዮን ብር፣ ከፕሮጀክት ዕርዳታ 13.06 ቢሊዮን ብር፣ ከፕሮጀክት ብድር 18.95 ቢሊዮን ብር እንደሚገኝ ታስቧል፡፡ ይህም ማለት ከአጠቃላይ በጀት ውስጥ 195.7 ቢሊዮን ብር ገቢን እንደሚይዝ የሚኒስትሩ አቶ ሱፊያን የበጀት ሰነድ ይገልጻል፡፡

በ223.397 ቢሊዮን ብር የታቀደ በጀትና ታሳቢ በተደረገው 195.754 ቢሊዮን ብር ገቢ መካከል የ27.643 ቢሊዮን ብር ጉድለት ይታያል፡፡ 

መንግሥት የበጀት ጉድለቱን ለመሸፈን ያቀደው ከአገር ውስጥ ምንጮች መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ የበጀት ጉድለቱ ከአጠቃላይ የአገሪቱ ምርት ያለው ድርሻ 1.8 በመቶ ብቻ በመሆኑ በማክሮ ኢኮኖሚው ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

ምክር ቤቱ የሚኒስትሩን የበጀት መግለጫ ካዳመጠ በኋላ የመጀመርያ ዙር ጠቅለል ያለ ውይይት አካሂዷል፡፡ በዚህም መሠረት በቀረበው በጀት ላይ የሚታየው የበጀት ጉድለት የሚሸፈነው ከአገር ውስጥ በመሆኑ የዋጋ ግሽበት አያስከትልም ወይ? የአገሪቱ የወጪ ንግድ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት ያሳየውን ዝቅተኛ አፈጻጸም ለማስተካከል በዚህ በጀት ዓመት ምን ታቅዷል? መንግሥት ዓለም አቀፍ ቦንድ በመሸጥ ያገኘው አንድ ቢሊዮን ዶላር የት ደረሰ? የሚሉ ዋና ዋና ጥያቄዎች ቀርበውላቸዋል፡፡

አቶ ሱፊያን የቀረበው በጀትና የበጀት አሸፋፈን የዋጋ ግሽበት እንደማያስከትል፣ በአጠቃላይ የ2008 ዓ.ም. የዋጋ ግሽበት በአማካይ ስምንት በመቶ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

መንግሥት የበጀት ጉድለቱን የሚሞላው ከአገር ውስጥ ቢሆንም በቀጥታ ከብሔራዊ ባንክ በመበደር አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡ ከመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ የበጀት ጉድለቱን ለመሙላት እንደሚቻልና ይህ መንገድ ደግሞ የዋጋ ንረት እንደማያስከትል ገልጸዋል፡፡

የአገሪቱ የኤክስፖርት ዘርፍ በጣም ደካማ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ ይህ ዘርፍ በጣት በሚቆጠሩ የምርት ዓይነቶች ላይ መንጠልጠሉን ካላቆመ ወዳቂ ነው ብለዋል፡፡

ትልቁ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማነቆ በኤክስፖርት (ወጪ ንግድ) ያለው ችግር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በሌሎች ዘርፎች ያሉ ችግሮች፣ በዋና ኦዲተር የሚጋለጡ ችግሮችና የመሳሰሉ የፕሮጀክት ዝግጅት ችግሮች በስኬት ውስጥ ተሁኖ የሚታዩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

‹‹በኤክስፖርት ዘርፍ ያሉ ችግሮችን ካልቀረፍን ግን ኢኮኖሚው መቀጠል የሚችል አይመስለኝም፤›› ብለዋል፡፡ በዚህ ችግር ላይ መንግሥት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየተወያየ ይገኛል ያሉት ሚኒስትሩ፣ በተለይ ለውጭ ገበያ በሚቀርቡ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ውጤቶች ላይ ማተኮር እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

በኤክስፖርት ዘርፍ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የኢንዱስትሪ ዞኖችን መንግሥት በራሱ ወጪ በመገንባት የውጭ ባለሀብቶች በፍጥነት ገብተው እንዲያመርቱ መታቀዱን ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ አዋጭ መሆናቸው በተለያዩ ጥናቶች የተረጋገጡ የጨርቃ ጨርቅና የቆዳ ዘርፎች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ 

ከዓለም አቀፍ የቦንድ ሽያጭ የተገኘው አንድ ቢሊዮን ዶላርም የሚውለው ለዚሁ ልማት መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ብሔራዊ ባንክ ይህንን ገንዘብ ለኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን በማበደር ጥቅም ላይ ያውለዋል ብለዋል፡፡

 

 

 

 

ከ3.5 ሚሊዮን ብር በላይ ያላግባብ ክፍያ እንዲፈጸም ማድረጋቸው ተጠቅሷል

የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ዘካርያስ አሰፋና የኢንስቲትዩቱ የፋሲሊቲና ሰርቪስ አስተዳደር ኃላፊና የጨረታ ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ጉይቴ ወልደ ማርያም፣ ሳሊም መሐመድ ባሙኒፍ

ከሚባል አጠቃላይ አስመጪ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ጋር በመመሳጠር ሙስና ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ 

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ዘካርያስ ሥልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም፣ ለኢንስቲትዩቱ አገልግሎት የሚውሉ የአዳራሽ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ ፑልፒት/አንትሮንስና መድረክ ከእነአክሰሰሪዎቹ ግዢ ሲፈጸም፣ የፌዴራል የግዥ አፈጻጸም መመርያን በመተላለፍ 3,590,179 ብር ክፍያ አላግባብ እንዲፈጸም ማድረጋቸውን፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት የመሠረተው ክስ ያስረዳል፡፡ ግዢው የተፈጸመው ከ1998 ዓ.ም. እስከ 2002 ዓ.ም. ድረስ ባሉት የተለያዩ ጊዜያት መሆኑንም ክሱ ይጠቁማል፡፡ 

ለኢንስቲትዩቱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ለመግዛት በተለያዩ ጊዜያት የወጡትን ጨረታዎች ማሸነፉ የተጠቆመው ሳሊም መሐመድ ባሙኒፍ አጠቃላይ አስመጪ ቢሆንም፣ ሐምሌ 1 ቀን 1997 ዓ.ም. የወጣውን የፌዴራል መንግሥት የግዥ አፈጻጸም መመርያ ቁጥር 28ን የጣሰ መሆኑን ክሱ ይገልጻል፡፡ መመርያው እንደሚያብራራው በማንኛውም ሁኔታ ጨረታውን ላሸነፈ ድርጅት ከጠቅላላ ዋጋው 30 በመቶ በላይ ቅድሚያ ክፍያ አይፈጸምም፡፡ ነገር ግን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ለአሸናፊው ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ከጠቅላላ ዋጋው 60 በመቶ የሚሆነውን ገንዘብ በቅድመ ክፍያ እንዲሰጥ መፍቀዳቸውን ክሱ ያብራራል፡፡ 

የግዥ መመርያ ቁጥር 28 አንቀጽ 2 እንደሚያስረዳው፣ ቅድመ ክፍያ የሚፈጸመው አሸናፊው ድርጅት በቅድሚያ ክፍያ ከሚወስደው ገንዘብ መጠን ጋር እኩል የሆነ ዋስትና ሲያቀርብ ብቻ መሆኑን ቢደነግግም፣ ዋና ዳይሬክተሩ ግን ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመጠቀም ያለምንም ዋስትናና ከመመርያ ውጪ 60 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ ያለዋስትና እንዲከፈል መፍቀዳቸውን፣ የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ 

በሌላ በኩል የመንግሥት የግዥ ሥርዓትን ለመወሰንና ተቆጣጣሪ ኤጀንሲውን ለማቋቋም የወጣው አዋጅ ቁጥር 430/1997 አንቀጽ 43 እና የግዥ መመርያ ቁጥር 28 አንቀጽ 11.14 ላይ የተደነገገውን፣ ተከሳሾቹ መተላለፋቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡ ድንጋጌዎቹ እንደሚያስረዱት፣ የጨረታው አሸናፊ ቢያንስ የውሉን ዋጋ አሥር በመቶ ለውል ማስከበሪያነት ለመንግሥት መሥሪያ ቤቱ ማስያዝ እንዳለበት ቢገልጽም፣ ድንጋጌውን በመተው ግዴታዎቹ በውሉ እንዳይካተቱ ማድረጋቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡ አሸናፊው ድርጅትም በድንጋጌው መሠረት ገቢ ማድረግ ያለበትን ገንዘብ እንዳላስያዘ ክሱ አክሏል፡፡ 

የጨረታው አሸናፊ ዕቃዎቹን በውሉ መሠረት ገቢ ማድረግ ሲገባው ሳያደርግ ቢቀር፣ በግዥ መመርያው መሠረት ዕቃውን ካላቀረበበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ዜሮ ነጥብ አንድ በመቶ በጠቅላላ ሒሳቡ (በተከፈለው መጠን) ተባዝቶ ቅጣት እንደሚከፍል መደንገጉን ክሱ ያስረዳል፡፡ ተከሳሾቹ ይህንን ባለመፈጸማቸው መንግሥት 1,058,953.4 ብር በድምሩ ማጣቱን ጠቁሟል፡፡ 

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘካርያስና አቶ ተስፋዬ በዋና ወንጀል አድራጊነት፣ ጠቅላላ አስመጪው አቶ ሳሊም መሐመድ (በሌሉበት) በልዩ ወንጀል ተካፋይነት የሙስና ወንጀል መከሰሳቸውን የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ 

አቶ ሳሊም በሌሉበት የተከሰሱ ሲሆን፣ አቶ ዘካርያስ የተጠቀሰባቸው የሕግ አንቀጽ ዋስትና እንደሚከለክል ተነግሯቸው ክሳቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ታዟል፡፡ አቶ ተስፋዬ የተከሰሱበት የወንጀል ሕግ ዋስትና እንደማይከለክል ተገልጾ በ7000 ብር ዋስትና ውጭ ሆነው እንዲከራከሩ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ የአቶ ሳሊምን መቅረብ ለመጠባበቅ ለሰኔ 11 ቀን 2007 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ 

 

ውኃ እስኪሞላ የሚጠበቀው ግልገል ጊቤ ሦስት በአምስት ተርባይኖች ሊጀምር ነው

የግልገል ጊቤ ሦስት ኤሌክትሪክ ኃይል ማሰራጫ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት ግንባታው ከ92 ከመቶ በላይ ተጠናቆ ግድቡ ውኃ ማጠራቀም እንደጀመረ ተገልጾ፣ በክረምቱ ወራት ጥሩ ዝናብ ማግኘት ከቻለ በአምስት ተርባይኖች ኃይል ለማሰራጨት ዝግጁ መሆኑ ተነገረ፡፡ 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ እንዳስታወቁት፣ የፕሮጀክቱ ግንባታ በአብዛኛው ተጠናቋል፡፡ ከ1,870 ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎ የሚጠበቀው ጊቤ ሦስት፣ በአሁኑ ወቅት ከጠቅላላው የማመንጨት አቅሙ ግማሽ ያህሉን ለማሰራጨት ዝግጁ መሆኑም ተገልጿል፡፡ 

በጠቅላላው አሥር ተርባይኖች ያሉትና በአንዱ ብቻ 187 ሜዋ ጋት ኃይል የሚያመነጨው ጊቤ ሦስት፣ ቁመቱ 276 ሜትር የሚረዝም ግድብ አለው፡፡ ምንም እንኳ የዚህ ግድብ ቁመት ሙሉ ለሙሉ ተገንብቶ ባይጠናቀቅም፣ ውኃ የመያዝ አቅም ላይ በመድረሱ ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ ግድቡ ውኃ እንዲያጠራቅም መዘጋቱን ኢንጂነር አዜብ አስታውቀዋል፡፡ 

ግልገል ጊቤ ሦስት ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ በመንግሥት ከተገነቡ አራት ትልልቅ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች በርዝማኔው ከአፍሪካ ትልቁ ሲሆን፣ 11.8 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ የመያዝ አቅም አለው፡፡ ከቻይና መንግሥት ከተገኘ 470 ሚሊዮን ዶላር ብድር ጨምሮ በጠቅላላ ወጪው 1.47 ቢሊዮን ዶላር እንደወጣበት የሚነገርለት ጊቤ ሦስት፣ አካባቢያዊ ተፅዕኖው ሰፊ ነው ተብሎ በርካታ ተቃውሞዎች ሲነሱበት መቆየቱ አይዘነጋም፡፡  

 

 

 

የምስክሮች ቃል እንዳይዘገብ ፍርድ ቤት ከለከለ

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው የቀድሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ (አንድነት)፣ የአረናና ሰማያዊ ፓርቲዎች አመራሮች ላይ፣ ዓቃቤ ሕግ ምስክሮቹን ከሰኔ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ማሰማት ጀመረ፡፡

ክሱን የመሠረተው የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ምስክሮቹን አቅርቦ ከማሰማቱ በፊት፣ በፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ አንቀጽ 32 መሠረት ምስክርነቱ በዝግ እንዲታይ ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ‹‹በምስክሮቼ ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ ደርሶባቸዋል›› የሚል ነበር፡፡ 

ተከሳሾቹ ግን የተጠቀሰባቸው ሕግ እስከ ሞት ድረስ ሊያስቀጣ የሚችል መሆኑን በመጠቆምና ምስክርነቱን ሕዝብ መስማት እንዳለበት በመግለጽ፣ ምስክርነቱ በግልጽ ችሎት እንዲታይ ፍርድ ቤቱን በመጠየቅ የዓቃቤ ሕግን ማመልከቻ ተቃውመዋል፡፡ 

ሁሉንም እስረኞች በመወከል ለፍርድ ቤቱ ያመለከቱት የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራር አቶ ሀብታሙ አያሌው ሲሆኑ፣ ያሉት ማረሚያ ቤት ውስጥ መሆኑንና የምስክሮቹ ዝርዝር ሊደርሳቸው የሚገባ ቢሆንም መከልከላቸውን አስረድተዋል፡፡ 

በመሆኑም በምስክሮቹ ላይ ማንም ዛቻና ማስፈራሪያ ሊያደርስ የሚችልበት መንገድ እንደሌለ ጠቁመው፣ የዓቃቤ ሕግ ጥያቄ ውድቅ እንዲደረግላቸው አመልክተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ምስክርነቱን በዝግ ችሎት የሚያየው ከሆነ፣ ሁሉም ተከሳሾች የግፍ ፍርደኛ ሆነው ወደ እስር ቤት እንደሚመለሱና በቀጣይም ምንም ዓይነት ክርክር እንደማያደርጉ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡ 

ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገኖች ክርክር በማዳመጥ ውይይት ካደረገ በኋላ፣ የዓቃቤ ሕግን ማመልከቻ ውድቅ በማድረግ፣ ምስክርነቱ በግልጽ ችሎት እንዲታይ ብይን ሰጥቷል፡፡ ነገር ግን የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች የሚናገሩትንም ሆነ ስማቸውን ጠቅሰው የኅትመትም ሆነ የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙኃን መዘገብ እንደማይችሉ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ 

በዕለቱ በአሥረኛ ተከሳሽ አቶ ተስፋዬ ተፈሪ ላይ አንድ የዓቃቤ ሕግ ምስክር ተሰምተዋል፡፡ 

ተከሳሾቹ አቶ ዘለዓለም ወርቅአገኘሁ ጋሻው፣ የአንድነት አመራር የነበሩት አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ የአረና ፓርቲ አመራር አቶ አብርሃ ደስታ፣ እንዲሁም አቶ ዮናታን ወልዴ፣ አቶ አብርሃም ሰለሞን፣ አቶ ሰለሞን ግርማ፣ አቶ ባህሩ ደጉና አቶ ተስፋዬ ተፈሪ መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሪል ስቴትና ለባለ አምስት ኮከብ ሆቴሎች ግንባታ የሚውሉ ቦታዎችን ለአልሚዎች ለማስተላለፍ ልዩ ጨረታ አወጣ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ባንክና ማስተላለፍ ኤጀንሲ ለሁለተኛ ጊዜ ያወጣው ይህ ልዩ ጨረታ፣ ስምንት ቦታዎችን ብቻ የያዘ ቢሆንም ቦታዎቹ ሰፋፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡ 

ስድስቱ ቦታዎች ለሪል ስቴት ልማት፣ ሁለቱ ቦታዎች ደግሞ ለባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ግንባታ የሚውሉ ናቸው፡፡ ቦታዎቹ በአራት ክፍላተ ከተሞች የሚገኙ ሲሆን፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አራት ቦታዎች ለሪል ስቴት ልማት ቀርበዋል፡፡ ዝቅተኛው የቦታ ስፋት 14,089 ካሬ ሜትር ሲሆን፣ ከፍተኛው ደግሞ 55,386 ካሬ ሜትር ነው፡፡ የቦታዎቹ መነሻ ዋጋ በካሬ ሜትር 191 ብር ሆኖ 60 ዓመት የሊዝ ዘመን ተሰጥቷቸዋል፡፡ 

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ሁለት ቦታዎች ለጨረታ የቀረቡ ሲሆን፣ 23,913 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው አንድ የሪል ስቴት ቦታና 8,998 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው አንድ ቦታ ለባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ግንባታ ቀርቧል፡፡ የእነዚህ ቦታዎች የመነሻ ዋጋም በካሬ ሜትር 191 ብር ነው፡፡ 

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማም አንድ ቦታ ለሪል ስቴት ልማት ቀርቧል፡፡ የቦታው ስፋት 57,752 ካሬ ሜትር መነሻ ዋጋው በካሬ ሜትር 299 ብር ነው፡፡ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ውስጥ አንድ ቦታ ለባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ግንባታ የሚውል 6,014 ካሬ ሜትር ቦታ ለጨረታ ቀርቧል፡፡ 

ጨረታው እስከ ሐምሌ 23 ቀን ድረስ ይፋ ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ በዚያው ዕለት ከሰዓት በኋላ ይከፈታል ተብሏል፡፡ 

የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ፣ መሬት በዋነኛነት ለአልሚዎች የሚቀርበው በጨረታ እንደሆነ ይደነግጋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቀላል ፕሮጀክቶች 14 ጊዜ ጨረታ አውጥቷል፡፡ ለሆቴል፣ ለሪል ስቴት፣ ለትምህርትና ለጤና ተቋማት ግንባታ የሚውሉ ቦታዎችን ለአልሚዎች ያቀረበው በሁለት ጨረታዎች ብቻ ነው፡፡ 

የመጀመርያው ጨረታ ግንቦት 2 ቀን 2006 ዓ.ም. ወጥቶ ሰኔ 3 ቀን 2006 ዓ.ም. መከፈቱ ይታወሳል፡፡ በዚህ ጨረታም የወጡት ቦታዎች ሰፋፊ ቢሆኑም ቁጥራቸው አሥር ብቻ ነበር፡፡ 

ባለሙያዎች አስተዳደሩ የመሬት ዋጋ ንረትን ለማርገብ በርካታ ቦታዎችን ለጨረታ ማቅረብ እንዳለበት ያሳስባሉ፡፡ 

 

የቻይና ሪል ስቴት ኩባንያ በአራት ቢሊዮን ብር ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር ሊገነባ ነው

ከፀሐይ ሪል ስቴት ቀጥሎ ሁለተኛው የቻይና ኩባንያ በአራት ቢሊዮን ብር በአዲስ አበባ ከተማ የሪል ስቴት ፕሮጀክት ግንቦት 30 ቀን 2007 ዓ.ም. የመሠረት ድንጋይ አኖረ፡፡

ሲኖ ማርክ የተባለው ይህ የቻይና ኩባንያ አገር በቀል ኩባንያ ከሆነው ሳባ ኢንጂነሪንግ ጋር ግንባታ ለማካሄድ ስምምነት የፈጸመው፣ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር ለመገንባት ነው፡፡ 

ግንባታው የሚካሄደው ሳባ ኢንጂነሪንግ ከፕራይቬታይዜሽንና ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በገዛው አዲስ ብሎክ ሼር ኩባንያ ይዞታ በሆነው፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጎተራ አካባቢ በሚገኝ 60 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ነው፡፡ 

የሳባ ኢንጂነሪንግ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ሳምሶን በኩረ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በዚህ ሥፍራ ላይ ከፍታቸው 20 ፎቅ የሆኑ 21 ሕንፃዎች ይገነባሉ፡፡ ለዚህ ፕሮጀክት ግንባታ አራት ቢሊዮን ብር በጀት የተያዘ ሲሆን፣ በኢንቨስትመንቱ ላይ ሁለቱም ኩባንያዎች እኩል ድርሻ እንደሚኖራቸው ኢንጂነር ሳምሶን ተናግረዋል፡፡ 

ሕንፃዎቹ በ30 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፉ ሲሆን፣ በተቀረው ቦታ ላይ የተለያዩ የስፖርት ማዕከላት፣ የገበያ ማዕከላት፣ የሕፃናት መጫወቻዎችና አረንጓዴ ሥፍራዎች ይካተታሉ፡፡

ይህ ግንባታ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የሚጠናቀቅ መሆኑን፣ ሽያጩም ግንባታው ከተጠናቀቀ በኋላ እንደሚካሄድ ኢንጂነር ሳምሶን ተናግረዋል፡፡ 

የሕንፃዎቹን ግንባታ ለማስጀመር ባለፈው እሑድ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የመሠረት ድንጋይ አኑረዋል፡፡ የመሠረት ድንጋይ በተቀመጠበት ወቅት የሲኖ ማርክ ኩባንያ ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ያን ሲን ሊ እንደተናገሩት፣ የሕንፃዎቹ ግንባታ በፈረንሳይ የሕንፃ አሠራር ዘይቤ ይከናወናል፡፡ 

የቻይና ኩባንያዎችን ጨምሮ የህንድ፣ የቱርክና የአውሮፓ ኩባንያዎች በአዲስ አበባ ከተማ በሪል ስቴት ልማት ለመሳተፍ ፍላጎት ከማሳየት አልፈው ፕሮፖዛል በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ 

ነገር ግን መንግሥት የውጭ ኩባንያዎች በራሳቸው መንገድ፣ በሪል ስቴት ልማት እንዲሳተፉ ለማድረግ የጀመረውን የፖሊሲ ጥናት ማጠናቀቅ ባለመቻሉ ጉዳዩ በእንጥልጥል ላይ ይገኛል፡፡ 

የቻይናው ግዙፍ ኩባንያ ሲጂሲ ኦቨርሲስ መንግሥት ለውጭ ኩባንያዎች መሬት ስለመስጠትም ሆነ ስለመከልከል አቅጣጫ ከመያዙ በፊት፣ በየካ ክፍለ ከተማ ሲኤምሲ አካባቢ ባገኘው መሬት የሪል ስቴት ልማት በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ 

ሲጂሲ ኦቨርሲስ ከሌላ የቻይና ኩባንያ ጋር በመሆን ያቋቋመው ፀሐይ ሪል ስቴት በ30 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ በ2.5 ቢሊዮን ብር በጀት፣ ከፍታቸው 12 ፎቅ የሆኑ የመኖሪያ ሕንፃዎችን እየነባ ይገኛል፡፡ 

አዲሱ የቻይና ኩባንያ ሲኖ ማርክ ከሳባ ኢንጂነሪንግ ጋር ግንባታ የሚያካሂድበት መሬት ባለቤት አዲስ ብሎክ ሼር ኩባንያ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ዕቃዎችን የሚያመርት ሲሆን፣ ሳባ ኢንጂነሪንግ ከፕራይቬታይዜሽንና ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ገዝቶታል፡፡ 

ሳባ ኢንጂነሪንግ ከኢትዮጵያ ባሻገር በሩዋንዳ፣ በኡጋንዳ፣ በታንዛኒያ ቅርንጫፍ ቢሮዎች በመክፈት በውኃ ሥራዎችና በተለያዩ የግንባታና የማማከር ሥራዎች የተሰማራ አገር በቀል ኩባንያ ነው፡፡ ሲኖ ማርክ ደግሞ ከአሥር ዓመታት በላይ በሪል ስቴት ልማት ውስጥ እንደቆየ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ 

 

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ከዘጠኝ ዓመት በኋላ በድጋሚ በተደረገበት ኦዲት ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡንና የደኅንነት ደረጃውን አስጠብቆ መቀጠሉን አስታወቀ፡፡

ኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ጠንካራ ከሚባሉት አምስቱ አንዱ ተቋም መሆኑም ተገልጿል፡፡ 

አምስት አባላት ያሉት የዓለም የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ኦዲተሮች ለአሥር ቀናት ባካሄዱት የኦዲት ምርመራ፣ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣንና የሚቆጣጠራቸውን ኢትዮጵያ የአየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ የበረራ ደኅንነትን ለማስጠበቅ የተሠሩትን ሥራዎችና የተወሰዱ ቁጥጥሮችን በመመርመር ኦዲት አካሂደዋል፡፡

 በዚህም መሠረት ባለሥልጣኑ በአጠቃላይ ውጤት 68.68 በመቶ በማግኘቱ ከዓለም አማካይ ውጤት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን፣ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው አስታውቀዋል፡፡ በዓለም የአቪዬሽን ድርጅት የዓለም አማካይ ውጤት ተብሎ የተቀመጠው 60 በመቶ ነው፡፡ 

ሲቪል ኢቪዬሽን ባለሥልጣን ከተፈተሸባቸው ስምንት ዋና ዋና የኦዲት ይዘቶች ውስጥ በተለይ በአምስቱና ባለሥልጣኑ በራሱ በሚተገብራቸው መስኮች 78 በመቶ በማምጣት ትልቅ ውጤት ማስዝገቡን አስታውቀው፣ ባለሥልጣኑ በሚቆጣጠራቸው ሦስቱ ተቋማት የተገኘው ውጤት 51 በመቶ በመሆኑ በአንፃራዊነት ዝቅተኛ ሊባል እንደሚችል ይፋ አድርገዋል፡፡ ምንም እንኳ በአጠቃላይ ውጤቱ በዓለም ከተቀመጠው አማካይ ውጤት ከፍ ያለ ቢሆንም፣ በሦስቱ ተቋማት የተመዘገበውን ዝቅተኛ አንፃራዊ ውጤት ለማሻሻል ሥራዎች እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡ 

ከዘጠኝ ዓመት በፊት ኦዲት ተደርጎ ያስዘመገበው ውጤት 66 በመቶ ነበር ያሉት ኮሎኔል ወሰንየለህ፣ በአሁኑ መጠነ ሰፊና አጠቃላይ ኦዲት ተፈትሾ ያስመዘገው ውጤት፣ ሲቪል አቪዬሽን የመቆጣጠር ብቃቱና ጥንካሬው የታየበት ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየትኛውም መዳረሻ የመብረርና የተጓዦችን ደኅንነት የማስጠበቅ ብቃት እንዳለው የተረጋገጠበት ውጤት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በኦዲት ሪፖርቱ መሠረት ምንም ዓይነት መሠረታዊ የደኅንነት ክፍተቶች አለመኖራቸውንም አስታውቀዋል፡፡ 

ከዚህ ባሻገር የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን በአሜሪካው የአቪዬሽን አስተዳደር ኦዲት ተደርጎ በዘርፉ ደረጃ አንድ የተባለውን ደኅንነት ደረጃ በማስጠበቅ፣ በአሜሪካም ሆነ በሌሎች አገሮች ያለምንም የደኅንነት ክፍተቶች በረራዎችን ማካሄድ እንደሚችል አረጋግጦ እንደነበር አይዘነጋም፡፡  

 

 

 

ሰኔ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ከአምስት አመት በፊት አውጥቶት በነበረው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ከወጪ ንግድ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚሰበስብ ገልጾ ነበር፣ ይሁን የገንዘብ ሚኒስትሩ ዛሬ ይፋ እንዳደረጉት የታቀደው እቅድ አለመሳካት ብቻ ሳይሆን የውጭ ንግዱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ መሄዱን ገልጸዋል። አቶ ሱፊያን አህመድ የ2008 በጀት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በፓርላማ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በውጭ …

ሰኔ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ሚያዚያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም አረመኔው የአይ ኤስ አይ ኤስ ቡድን በዜጎቻችን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ላይ በራሱ በመንግስት ላይ ተቃውሞ ያሰሙ ዜጎችን በእለቱ በአሰቃቂ ሁኔታ በኃይል ከመደብደብና ከማዋከቡም በተጨማሪ አልፎ ተቃውሞ አነሳስተውብኛል ብሎ ያሰባቸውን በቦታው ያልተገኙ …

ሰኔ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሁለት አመት ሊሞላው ጥቂት ወራት የቀሩት የደቡብ ሱዳን ግጭት ከዛሬ ነገ መፍትሄ ይፈለግለታል ቢባልም እስካሁን ጦርነቱን የሚያስቆም መፍትሄ ሊገኝ አልቻለም። በቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም መስፍን ዋና መሪነት ሲካሄድ የነበረው ድርድር ለወራት ከተቋረጠ በሁዋላ እንደገና ለማስጀመር የሁለቱም ተፋላሚ ሃይሎች ተወካዮች አዲስ አበባ ገብተዋል። ቀድም ብሎ በተቀመጠው …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

የታሸገው የሰሚት መድኃኔዓለም ሰንበት ት/ቤት ሳያውል ሳያድር መከፈት፤ የታሰሩት አባላት እና ምእመናን መፈታት በተሰላፊዎቹ ሰንበት ት/ቤቶች እና በዋና ሥራ አስኪያጁ መካከል ወሳኝ ልዩነት የፈጠረ ጉዳይ ኾኗል፤ ‹‹በአንድ ደብዳቤ እንዳዘጋኸው በአንድ ደብዳቤ ዛሬውኑ አስከፍት!›› የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ውስጥ ለውስጥ በቤተ ክርስቲያን እና በአገልግሎቷ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ እንዳለ በማመን በትጋት እና በጽናት እንዲሠራበት በአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ …

(ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ) – ገዥው ፓርቲ የ2007 ዓ.ም አጠቃላይ ምርጫን የመንግስትን መዋቅርና ኃብት ያለገደብ በመጠቀም የዜጎችን በነፃነት የመምረጥ መብት በመዋቅር በማፈን አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት እጅግ በርካታ ህገ ወጥ ተግባራት ሲፈፅም ቆይቷል፡፡ በዚህ ዓይነቱ የለየለት የውንብድና ስራ ተቃውሞ ያላቸው ዜጎች በመንግስት ላይ ያላቸውን ቅሬታ የሚያባብስ ሊቢያ ውስጥ በስደት ላይ በሚገኙ በኢትዮጵያውያን ላይ […]

በክንውን ላይ፤ ከረፋዱ 4፡50፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት

ኢሳት ዜና ) ባለፈዉ ሃሙስ ሌሊት፥ አርብ ንጋት ላይ የቴፒ ወህኒ ቤትን ሰብረው ፖሊሶችን ገድለው እስረኛ ያስለቀቁት ታጣቂዎች የፍትህና የነጻነት ጥያቄ አንግበው መነሳታቸውን የእንቅስቃሴው መሪ ካለበት ለኢሳት በሰጠዉ ቃለምልልስ ገልጸ። ጥቃቱት ተከትሎ በእነሱ ወገን ሁለት ሰዎች መገደላቸዉን ያመነ ሲሆን፥ አንደኛው የንቅናቄው መስራች፥ ሌላኛዉ ሟች ቡድኑን በቅርቡ የተቀላቀለ መሆኑን አመልክቷል። ስሙ እንዲገለጽ ያልፈለገው የእንቅስቃሴው መሪ፥ ከዚህ […]

የሺዋስ አሰፋ ከተቀመጠበት አልነሳም አለ ‹‹ምስክሬ ላይ ዛቻ እና ድብደባ ስለተፈጸመ ምስክርነቱ በዝግ ችሎት ይሁን›› አቃቤ ሕግ ‹‹በማስረጃ ባልተረጋገጠ አቤቱታ ችሎት በዝግ ሊታይ አይገባም›› የተከሳሽ ጠበቆች ‹‹ሞት የሚያስቀጣ ክስ ቀርቦብን ጉዳያችን በአደባባይ መታየት አለበት፤ እናንተ ብቻ አይደላችሁም ፈራጆች…›› ዳንኤል ሺበሺ ‹‹ምስክርነቱ በዝግ ችሎት የሚታይ ከሆነ ዛሬውኑ የምትፈርዱብንን ተቀብለን ለመመለስ ዝግጁ ነን›› ሀብታሙ አያሌው ‹‹የአቃቤ ህግን […]