የህወሓት 12ኛ ጉባኤ መካሄድ ተከትሎ የሊቀ መንበርነት ስልጣን ሽኩቻ እየተካሄደበት ይገኛል። ኣብዛኛው የትግራይ የፌስቡክ ኣክትቪስቶች፣ ወጣቶችና ሙሁራን የህወሓት ኣባላት፣ ሌሎች ለውጥ ፈላጊ ኣክትቪስቶችና ሌሎች ፖለቲከኞች በጉጉት እየጠበቁት ይገኛሉ። የኣርከበ በድምፅ በጉባኤው መሳተፍ ለብዙዎች የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ወደ ኣሸናፊነት የተጠጋ ቢመስላቸውም ጉዳዩ ሌላ ነው። ኣርከበ ተመልሶ የማይወዳደር መሆኑ ስላረጋገጡ የትግራዩ ኣንጃም እንዲሳተፍ በኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ […]

በተጠረጠሩበት የሽብር ድርጊት ወንጀል ከአንድ ዓመት በላይ በእስር ከቆዩ በኋላ ነሐሴ 14 ቀን 2009 ዓ.ም. በነፃ የተሰናበቱት የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች፣ ዓቃቤ ሕግ ውሳኔውን በመቃወም ይግባኝ ስላለባቸው ሳይፈቱ ቀሩ፡፡

“በተጠረጠሩበት የሽብርተኝነት ወንጀል መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ ተሰናብተዋል” በማለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በነፃ አሰናብቷቸው የነበሩት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ አመራሮች አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና ለትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉዓላዊነት ፓርቲ አመራር አቶ አብርሃ ደስታና የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ እንዲሁም በእነሱ የክስ መዝገብ ተካተው የነበሩት አቶ አብርሃም ሰለሞን ነበሩ፡፡ በሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ያልተስማማው ዓቃቤ ሕግ፣ ያቀረባቸው የሰነድና የሰዎች ማስረጃዎች በአግባቡ እንዳልታዩለት በመግለጽ፣ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 188(5) መሠረት የይግባኝ አቤቱታውን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በማስገባቱ፣ በነፃ የተሰናበቱት አምስቱም ሰዎች እንዳይለቀቁ ዕግድ ተጥሏል፡፡

የሥር ፍርድ ቤት በተለይ አቶ ሀብታሙና አቶ አብርሃም ሰለሞን በዕለቱ (ነሐሴ 14 ቀን2007 ዓ.ም.) እንዲፈቱና አቶ አብርሃ፣ አቶ ዳንኤልና አቶ የሺዋስ ችሎት በመድፈር ወንጀል የተጣለባቸውን ቅጣት ሲጨርሱ እንዲለቀቁ የሰጠው ትዕዛዝ ታግዷል፡፡

በዕለቱ እንዲፈቱ ትዕዛዝ የተላለፈላቸው አቶ ሀብታሙና አቶ አብርሃም ቤተሰቦች፣ ነሐሴ 14 ቀን ከሰዓት በኋላና ነሐሴ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ሙሉ ቀን ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በመሄድ፣ የሚፈቱ ቤተሰቦቻቸውን በማጀብ ወደ ቤታቸው ይዘው ለመግባት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ሲጠብቁ ውለው፣ ምንም ዓይነት ምላሽ ሳያገኙ መመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡ ነሐሴ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ተመልሰው በመሄድ ሲጠይቋቸው እነ ሀብታሙም ምንም የሰሙትም ሆነ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ እንደነገሯቸው ገልጸዋል፡፡ ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ ጠይቆ “ይፈቱ” የሚለው ትዕዛዝ መታገዱን ያወቁት ነሐሴ 18 ቀን 2007 ዓ.ም. መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ፍርድ ቤት በአንድ መዝገብ ላይ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ እንደሰጠው ውሳኔ ስፋትና ጥበት፣ ውሳኔውን አስገልብጦ ለመውሰድ ፈጠነ ቢባል በአምስት ቀናት ውስጥ ሊደርስ እንደሚችል የገለጹት የሕግ ባለሙያዎች፣ የእነ ሀብታሙ አያሌው ውሳኔ 44 ገጽ ከመሆኑ አንፃር፣ አስገልብጦ ለመውሰድ ቢፈጥን ከአንድ ሳምንት በላይ ሊወስድ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን ዓቃቤ ሕግ በአንድ ቀን ልዩነት አስገልብጦና የይግባኝ አቤቱታ አዘጋጅቶ በማግሥቱ ውሳኔውን ማሳገዱ ያልተለመደ እንደሆነባቸው ገልጸዋል፡፡

ሌላው የሕግ ባለሙያዎቹ የገለጹት አንድ ተከሳሽ በነፃ ከተሰናበተ፣ ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ እንደሚፈልግ ስለገለጸ ብቻ ነፃ የተባለው ሰው በእስር እንዲቆይ የሚያደርግ የሕግ አግባብ በግልጽ እንዳልተቀመጠ ተናግረዋል፡፡ ይልቁንም በሥር ፍርድ ቤት ጥፋተኛ የሚባል ተከሳሽ ለበላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦ ጉዳይ እስከሚታይለት ድረስ፣ በእስር እንዳይቆይ ታግዶ እንዲቆይለት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር በ188(2) መሠረት መቆየት እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ ዓቃቤ ሕግ በበኩሉ ውሳኔ ያረፈበትን መዝገብ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 188(5) መሠረት ማሳገድ እንደሚችል ገልጿል፡፡ 

ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ ባለበት የእነ ሀብታሙ አያሌው መዝገብን መርምሮ “ያስቀርባል ወይም አያስቀርብም” ለማለት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለመስከረም 21 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል፡፡

 

ጀግኖቹ እነ ኣብራሃ ደስታ ዛሬ ጥዋት ሓሙስ 14 / 12 / 2007 ዓ/ም ከእስር በነፃ ተፈቱ። ከዓመት በፊት በሽብር ክስት ታስረው የነበሩት ጀግኖቹ የሰለማዊ ትግል ጀግኖች ከተከሰሱበት የፈጠራ ክስ ነፃ ተብለው ተፈትተዋል። ፩) ኣብራሃ ደስታ ከዓረና ፪) ሃብታሙ ኣያሌው ከኣንድነት ፫) የሺዋስ ኣሰፋ ከሰማያዊ ፬) ዳኑኤል ሺበሺ ከኣንድነት ከተከሰሱበት የሽብር ክስ በነፃ ተሰናበቱ። ለመላው ኢትዮዽያውያን […]

ነኅሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በታደለ ቱፋ የተጻፈውን የጋሞን ህዝብ ማንነት የሚያንቋሽሸውን መጽሃፍ ፣ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የሚመሩት የደቡብ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች የገንዘብ ደጋፍ በማድረግ አስጽፈውታል በሚል ምክንያት ፣ በአርባምንጭና በተለያዩ የጋሞ ወረዳዎች የተቃውሞ ሰለፎች መደረጋቸውን ተከትሎ፣ በከፍተኛ አመራሩ እና በታች አመራሩ መካከል ያለው አለመግባባት ይፋ ሆኗል። ለኢሳት የደረሰው …

ነኅሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያዋ የድንበር ከተማዋ መተማ አሁንም ኢትዮጵያዊያን መሰደዳቸውን አላቋረጡም ሲል ዘጋርዲያን ዘገብዋል። መንግስት ጥበቃውን አጠናክሮ በአካባቢው ብዙ ሰራዊት ቢያሰማራም በቀን ከ100 እስከ150 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞ ድንበር አቋርጠው ይሰደዳሉ። መተማ ከተማ ወደ መቶ ሽህ የሚገመት ነዋሪዎች ያላት ስትሆን የኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሌ ስደተኞች መተላለፊያ ናት።ከተማዋ መንግስት በወሰደው የጥበቃ ማጠናከር …

ነኅሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በሽብርተኝነት ወንጀል ከተጠረጠሩ በኋላ፤ በእነ ዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ፣ ከአንድ ዓመት በላይ ጉዳያቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ሲታይ ቆይቶ ባለፈው ሳምንት በነጻ እንዲሰናበቱ ከተፈረደላቸው አምስት ግለሰቦች መካከል 2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው እና 7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሠለሞን እስከአሁን ድረስ …

ነኅሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የመስተዳድሩም ምንጮች እንደገለጹት የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ በአማካሪዎቻቸው ብዛት ተጨናንቀዋል። አማካሪዎቹ ከተለያዩ አቅጣጫዎች እየተሹሙ የሚመጡ በመሆኑ፣ ከንቲባው ግራ ተጋብተዋል። አማካሪ የሚባሉት ሰዎች በጸሃፊያቸው በኩል አስፈቅደው ወደ እርሳቸው ቢሮ ከገቡ በሁዋላ ” እኔ እኮ የዚህ ዘርፍ አማካሪዎ ነኝ” ሲሉዋቸው፣ ከንቲባው በመደናገጥ ” ከስራ ብዛት …

ነኅሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቤጅንግ የዓለም ሻምፒዮና ትንሽዋ ልዕልት የ24 ዓመቷ ገንዘቤ ዲባባ ለኢትዮጵያ በ1,500 ሜትር የሩጫ ውድድር ርቀቱን 4:08.09 በሆነ ሰዓት በመግባት ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች። ባለፈው ወር ፈረንሳይ ሞናኮ ውስጥ በርቀቱ የዓለም ክብረወሰን ባለቤት የሆነችው ገንዘቤ ዲባባ ያስገኘችው ድል መላውን ኢትዮጵያዊ ያኮራ ውጤት ሲሆን ውድድሩን ገንዘቤ ዲባባ በመሪነት …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

በኦሮምያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረደ በተነሳዉ ግጭት 85 አባዎራዎች ማለትም 305 ሕዝብ በአጎራባች ደቡብ ክልል መፈናቀሉንና 124 ቤቶች መቃጠላቸዉን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮኃንስ ገ/ እግዚአብሄር የላከልን ዘገባ ያመለክታል።

በቤይጂንጉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና   በ 1,500m  ድል ተቀዳጅታ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ ለኢትዮጵያ አስገኘች።

ገንዘቤ በዚህ ርቀት ሞናኮ ላይ በቅርቡ አዲስ የዓለም ክብረወሰን ማስመዝገቧ አይዘነጋም።

የገንዘቤ እህት ጥሩነሽ ዲባባ ከሰባት ዓመታት በፊት እ አ አ በ 2008 ዓም እዚሁ ቤይጂንግ Bird’s Nest ወይም የወፍ ጎጆ ስታዲየም በኦሊምፒክስ በ 5 እና በ 10 ሺህ ሩጫ ውድድሮች በሁለቱም የወርቅ ሜዳልያ በማግኘት ታሪክ ሠርታለች።

አሁንም ገንዘቤ እዚሁ ስታዲየም ውስጥ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ 1, 500 እና በ 5,000 ሜትር ሩጫ ውድድሮች በሁለቱም ወርቅ ለማግኘት ዓልማለች።

የመጀመሪያውን ወርቅ ዛሬ ወስዳለች። ሁለተኛው የፊታችን ዕሁድ የሚታይ ይሆናል።

መልካም ዕድል እንመኛለን።

መከላከያ ሰራዊቱ ጥቃት ወይም ወረራ ለማድረግ ከፍተኛ ሰራዊት እያከማቸባቸዉ በሚገኙት በሰሜኑ አካባቢዎች አለመረጋጋት ነግሰዋል። በትናንትናዉ እለት አንድ ጓድ መሪ 9 የሰራዊት አባላትን ከመመሪያ ዉጭ ይዞ በመንቀሳቀሱ እርሱን ለመከተል ፍለጋ ላይ የነበረ አነስተኛ የጦር ክፍል የኤርትራን ቀጠና አልፎ በመሄዱ ተደምስሷል። ኤርትራም ያለው ሀይል በኢትዮጵያ በድንበር ላይ ተሰድሮ ዉጥረቱ እጅግ ተባብሶ መቀጠሉን ከስፍራዉ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። ድል […]

‹‹በአመራሩ መካከል ትርምስና ጥርጣሬ ተፈጥሯል›› ‹‹ሰማያዊና መድረክ ማሸነፍ ይችሉ ነበር›› አቶ ደሴ ዳልኬ በቅርቡ ታደለ ቱፋ የተባለ ግለሰብ በጋሞ ብሄር ላይ የጻፈውን መፅሃፍ አስመልክቶ በደኢህአዴን አመራሮች መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ በተደረገ ሚስጥራዊ ስብሰባ ላይ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደሴ ዳልኬ የደኢህዴን አመራር የህዝብ ቁጣ ላይ እሳት እየጨመረ ነው ሲሉ መግለፃቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ የደረሰው የድምፅ […]

ሰኔ 01 ቀን 2006 ዓ.ም በሽብርተኝነት ወንጀል ከተጠረጠሩ በኋላ፤ በእነዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ፣ ከአንድ ዓመት በላይ ጉዳያቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ሲታይ ቆይቶ ባለፈው ሳምንት ነሐሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም በነጻ እንዲሰናበቱ በችሎቱ ትዕዛዝ ከተሰጣቸው አምስት ግለሰቦች መካከል 2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው እና 7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሠለሞን እስከአሁን ድረስ ከቂሊንጦ እስር ቤት […]

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 19 2997) በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ተከስቶ ያለው ድርቅ የምግብ ፈላጊዎች ቁጥር እየጨመረ  እንዲሄድ ማድረጉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ተረጂዎች ቁጥር መጨመርን ተከትሎም የኢትዮጵያ መንግስት የተጨማሪ የ230 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ጥሪ ማቅረቡን ሮይተርስ ዘግቧል ። ለምግብ እጥረት አደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ ተብለው ከተገመቱ 14 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን መካከል 4.5 ሚሊዮን የሚሆኑት በተያዘው …

በኦጋዴን ነጻ አዉጭ በርበኞች ግንቦት 7 እና በጥምር ሐይሎች በሁለት አቅጣጫዎች ከፍተኛ ጦርነት ተቆስቁሶ ነገር ግን የመጨረሻ የማጥቃት እርምጃ ለመዉሰድ ታግደናል እየተደበደብን ነዉ፤፤ ይላል የወያኔ መንግስት የሰሜኑ እና የምስራቁ እዝ። ዛሬ ለሊት ከ23፡00 ሰአት ጀምሮ በሰሜን ጎንደር ልዩ ኮዱ 13.274645/ 37. 878478 በሰሜን ኦጋዴን ጋላዲ ጠረፍ አካባቢ ከባድ ዉጊያ ገጥሞናል በተለይ ሰራዊታችን በአየር ሐይሉ ላይ […]

ድርጅቱ በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ እንደገለጸው፣ ለረጅም ጊዜ በአመራርነት ቆይቶ ስልጣኑን በመተካካት ሂደት ባስረከበውና ቁልፍ ስልጣኑን በተረከበው መካካል የመግባባት ችግር መኖሩን ገልጿል። ነባሩ አመራር ሁሉንም ሃላፊነት አስረክቦ ድርጅቱን የመልቀቅና ራሱን ገለል አድርጎ ለመኖር ይፈልጋል ያለው ብአዴን፣ በዚህም ላይ ነባሩ አመራር በአዲሱ አመራር እንደማይረካና ተደጋጋሚ ቅሬታ እንደሚያቀርብም ገልጿል። ቁልፍ ስልጣን የተረከበው አዲሱ አመራርም የራሱን አቅም የማያውቅ፣ […]

በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ባለ ሃብቶች በትግራይ ክልል ኢንቨስት እንዲያደርጉ የተደረገላቸው ቅስቀሳ በክልሉ ውስጥ ያለው ስር የሰደደ ብልሹ የአስተዳደር ሁኔታመጀመሪያ ይስተካከል ማለታቸውን ተገለፀ። በምንጮቻችን መረጃ መሰረት- በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጅ ባለሃብቶች ያላቸውን ሃብት በትግራይ ክልል እንዲያሰማሩ ይርዳው በተባለ ከፍተኛ የህወሃት ካድሬ ነሓሴ 3/2007 ዓ/ም በተካሄደው ቅስቀሳ የተሞላበት ስብሰባ በብልሹ አሰራራችሁ የተጨማለቀውን አሰራራችሁ […]

በሶማሊያ ሀገር  እየተላኩና ህይወታቸው እያለፈ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ወታደሮች ከቀን ወደ ቀን ቁጥራቸው እየጨመረ እንደሆነ ከተለያዩ ያገራችን አካባቢዎች የደረሰን መረጃ አስታወቀ።በሶማሊያ ሃገር እየሞቱ ያሉትን የኢትዮጵያ ወታደሮች ቁጥራቸው ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የሟቾቹ ቤተሰብ በየግዜው በቴለፎን መርዶ እየደረሳቸው እንደሆነ የገለፀው መረጃው በተለይም የኦሮሚያ ክልል ህዝብ ለምንድነው ስልጣን ላይ ያለው ስርዓት የሞቱት ልጆቻችን የማይነግረን በመሰረቱ […]

ህወሀት ቴዲ አፍሮን ከልክ በላይ እየገፋው ነው:: ለቴዲ የህወሀት ኢትዮጵያ አላስቀምጥ ብላዋለች:: ምናልባትም ቴዲ ከሀገር ተሰደደ የሚል መራር ዜና ልንሰማ የምንችልበት ጊዜ እየቀረበ እንደሆነ ይሰማኛል:: በግሌ በተለይ ሰሞኑን የሚደርሱኝ መረጃዎች የህወሀትን የዕብሪት ለከት ማጣት የሚያሳዩ ቴዲንም ከሚወደው ህዝብና ከሚሳሳላት ሀገሩ እንዲለያይ የሚገፋፉ ናቸው:: ቴዲ መሰደድ እንደማይፈልግ የትኛውንም በደል ተቋቁሞ በሀገሩ መኖር ለምርጫም የማይቀርብ ጉዳይ እንደሆነ […]

የፌድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት ክስ ባልተነሳላቸው የዞን ዘጠኝ አምደኞች ጉዳይ ዛሬ ብይን ይሰጣል፤ ተብሎ ቢጠበቅም ለሌላ ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል። ተከሳሾች የተለያዩ አቤቱታዎችን ለችሎቱ አቅርበዋል።

በሌላ ዜና በዚሁ ችሎት ብይን ከእስር እንዲፈቱ ባለፈው ሳምንት ትዕዛዝ የተሰጠላቸው የቀድሞው የአንድነት የአመራር አባል አቶ ሃብታሙ አያሌው እና ሰባተኛው ተከሳሽ አቶ አብረሃም ሰለሞን እስከ ዛሬም ከእስር አልተፈቱም።

የፍርድ ቤቱ ብይን በአቃቤ ሕግ የይግባኝ አቤቱታ መታገዱ ነው፤ የተነገረው። በጉዳዩ ላይ የሕግ አስተያየት ባለ ሞያዎች ግን እግዱ የሕግ መሠረት የለውም ይላሉ።

ነሀሴ 14/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከተከሰሱበት የሽብርተኝነት ክስ ነጻ ናችሁ ያላቸው የፖለቲካ አመራሮች የሆኑት አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም በተመሳሳይ መዝገብ ተከሶ ነጻ የተባለው አብርሃም ሰለሞን ከእስር እንዳይለቀቁ ታግደዋል። አቃቤ ህግ ይግባኝ እንደጠየቀባቸው የታወቀ ቢሆንም እንደ ህግ ባለሙያዎች ግን የአቃቤ ህግ ይግባኝ ገና ተቀባይነት ባላገኘበት ሁኔታ ከእስር እንዳይለቀቁ እግድ […]

በኢትዮጵያ 4 ነብ 5 ሚሊዮን ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው መንግስትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አጋር የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። በተያዘው አመት 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ታስቦ የነበረ ቢሆንም፤ የተረጅዎች ከግምት ውጪ ላሻቀበው የተረጅዎች አሀዝ ብቻ 230 ሚሊዮን ዶላር ወይም ከ 4 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ […]

አማሳኝ ሓላፊዎች፤ በካህናት እና ሠራተኞች ስም የሚያቀርቡት አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ከብፁዕ ዋ/ሥራ አስኪያጁ ጀምሮ ብፁዓን አባቶች ለማስፈራራትና ለመደለል እየተሞከረ ነው “እጁ የተገኘበትን ኹሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ አሳልፋ ትሰጣለች፤ ይኼ የመጨረሻ አቋሜ ነው”                                    /ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ/  *       …

ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ እንደገለጸው፣ ለረጅም ጊዜ በአመራርነት ቆይቶ ስልጣኑን በመተካካት ሂደት ባስረከበውና ቁልፍ ስልጣኑን በተረከበው መካካል የመግባባት ችግር መኖሩን ገልጿል። ነባሩ አመራር ሁሉንም ሃላፊነት አስረክቦ ድርጅቱን የመልቀቅና ራሱን ገለል አድርጎ ለመኖር ይፈልጋል ያለው ብአዴን፣ በዚህም ላይ ነባሩ አመራር በአዲሱ አመራር እንደማይረካና ተደጋጋሚ ቅሬታ እንደሚያቀርብም …

ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ 4 ነብ 5 ሚሊዮን ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው መንግስትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አጋር የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። በተያዘው አመት 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ታስቦ የነበረ ቢሆንም፤ የተረጅዎች ከግምት ውጪ ላሻቀበው የተረጅዎች አሀዝ ብቻ 230 ሚሊዮን ዶላር …

ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተያዘው ክረምት በአብዛኛው ምስራቅና ሰሜን ምስራቅ የሃገሪቱ ክፍሎች የተከሰተውን የዝናብ እጥረት ተከትሎ የሰቆጣ ከተማና የአካባቢው ወንዞች በመድረቃቸው የውኃ እጥረቱ መከሰቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ነዋሪዎች ፣ በዝናቡ እጥረት የተነሳ የጉድጓድ ውሃ መጠን በማነሱ የሚጠጣ ውኃ እጥረት መከሰቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ “በከተማዋ በአጠቃላይ የውኃ ችግር ተከስቷል፡፡በከተማዋ የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ ልማት ጽህፈት …

ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አርሶአደሩ ፣ የመንግስት ሰራተኛውና ነጋዴው ለቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አካዳሚ ግንባታ በሚል በግዴታ ከ50 ብር ጀምሮ እንዲከፍል ቢደርግም፣ ምክንያቱ በውል ባልተገለጸ ሁኔታ ገንዘቡ ለኢህአዴግ አራት ድርጅቶች ማለትም ለህወሃት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴን ተከፋፍሏል። ሁሉም ድርጅቶች 80 ሚሊዮን 566 ሺ 221 ብር ደርሶአቸዋል። ገንዘቡን ለመንግስት ወይም ለከፈሉት ዜጎች …

ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ለሁለት ቀናት በመዲናዋ አዲስ አበባ ያደረገው ሰማያዊ ፓርቲ ኢ/ር ይልቃል ጌትነትን በድጋሜ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በድጋሜ ለቀጣዩ ሦስት ዓመታት ፓርቲውን እንዲመሩ የተመረጡ ሲሆን፣ አምስት የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን አባላትም በጉባኤው ተመርጠዋል፡፡ ጉባኤው የፓርቲውን የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትንም መርጧል፡፡ ኢ/ር …

ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አርበኞች ግንቦት ሰባት የጀመረውን የነፃነት ትግል በገንዘብ ለማጠናከር በላስቬጋስ ከተማ የተጠራው የሀገር አድን ጥሪ በከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎና በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን በእለቱ በተደረገው የገንዘብ ማሰባሰብ ከፍተኛ ገንዘብ መገኘቱን ለማወቅ ተችሏል፡ በዚህ ለሰማእታት በተደረገ የህሊና ጸሎት የተጀመረ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ አቶ ሙሉነህ እዩኤልና አቶ ጋሻው ገብሬ የንቅናቄው …

ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ሳዑዲ አረቢያ በሃኪም ቤት ዉስጥ ከሰመመን ሳይነቃ የተኛዉ ኢትዮጵያዊ እናት ለተፈጠረዉ የሕክምና ስህተት እንዲከፈላቸዉ የታዘዘዉን ካሳ እንደማይቀበሉ አስታወቁ። 2.4 ሚሊዮን ሪያል ወይም 13 ሚሊዮን በላይ ብር የካሳ ክፍያ የተወሰነላቸው እናት ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደውታል።

አይ ኤስ አይ ኤስ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ሰበብ የታሰሩት እነ ማቲያስ መኩሪያ ለነሃሴ 27/2007 ዓ.ም ተቀጠረባቸው፡፡ ፖሊስ በጊዜ ቀጠሮ ወቅት ‹‹የቪዲዮ ማስረጃም አለን›› በማለቱ ተከሳሾቹ ‹‹ቪዲዮው ይቅረብልን፡፡ የቪዲዮ ማስረጃው ለእኛም የመከላከያ ምስክርነት ይጠቅመናል›› ብለው ጠይቀው የነበር በመሆኑ፤ ፍርድ ቤቱ የቪዲዮ ማስረጃው መቅረብ እንዳለበትና እንደሌለበት ብይን ለመስጠት ለነሃሴ 5/2007 ዓ.ም […]

ሊባኖስ (ቤሩት) ከአንድ አመት በላይ ያለፕሬዘዳንት ኖራለች በዚህች ሀገር መንግስቱ እየተልፈሰፈሰ የሚገኝ ሲሆን የከተሞችን ቆሻሻ እንኳ በቅጡ መሰብሰብ አቅቶታል ነው የሚባለው ይህን ተከትሎ ከተሞቻችን በቁሻሻ ተወረሩ ያሉ ሊባኖሳዊያን ትናንትናና ሰሞኑን ከባድ አመጽ ማስነሳታቸው ነው የተነገረው አመጹ ዛሬ ጋብ ቢልም ከፖሊስም ሆነ ከተቃዋሚዎቹ ወገን የበርካታ ሰዎችን መቁሰልና መጎዳትን ማስከተሉ ነው የተነገረው እናንት ቁሻሾች በተባለው ሊባኖወሳውያኑ በዚህ […]

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ለመከላከል ወይም ሳይከላከሉ በነፃ ለመሰናበት ውሳኔ ዛሬ ለ35ተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት አራቱ በእስር የሚገኙት ጦማርያን በድጋሚ በተለዋጭ ቀጠሮ ተሸኝተዋል። በዛሬው ውሎ ችሎቱ ያልተሰየመ ሲሆን ተከሳሾች እና ጠበቆች በቢሮ ተጠርተው ዳኞች ተሟልተው ስላልተገኙ ችሎቱ ለመሰየም አለመቻሉን ዶክመንቶችን ማየትና ውሳኔውን ፅፎ ማጠናቀቅ አሁንም እንዳልቻሉ በመግለፅ ዳኛ ዘሪሁን ለጷግሜ 2 ተለዋጭ ቀጠሮ […]

በገዢው ስራዓት የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየተካሄደ ባለው ሰፊ የዓመቱ ግምገማ “የተቃዋሚዎች ሬድዮ መስማት” እንደዋነኛ መገምገሚያ ነጥብ ሆኖ መነሳቱን ተገለፀ።በምንጮቻችን መረጃ መሰረት- በሁሉም የስርዓቱ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየተካሄደ ያለውን መጠነ ሰፊ የዓመቱ ግምገማ ወታደሩ ያለማቋረጥ እየፈረሰ በመጥፋት ላይ ያለው የትጥቅ ትግል እያካሄዱ በሚገኙ ድርጅቶች የሚሰራጨውን ሬድዮ መስማት ዋናው ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ ስለሆነ ለምን ታዳምጣላችሁ፤ እነማን ናቸው የሚያዳምጡት መታወቅ አለባቸው በማለት እየተካሄደ ባለው ስብሰባ የሰራዊቱ አዛዦች ራሳቸው […]

‹‹መጠየቅ ካለብኝ በክልል እንጂ በፌዴራል አይደለም›› አቶ ወንድሙ ቢራቱ

ለመንግሥት መግባት የነበረበትን ተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች የመንግሥት የግብር ገቢዎች በማጭበርበር በግላቸውና በዘመዶቻቸው ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ በማካበት በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩት፣

የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ወንድሙ ቢራቱ ሰው በመግደል ወንጀል መጠርጠራቸው ለፍርድ ቤት ተገለጸ፡፡

ነሐሴ 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ውለው ነሐሴ 4 ቀን 2007 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው 11 ቀናት ለተጨማሪ ምርመራ ተሰጥቶባቸው የነበሩት አቶ ወንድሙ፣ በሰው መግደል ወንጀል የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኖች ያደረጉት የምርመራ መዝገብ ቀርቦ እየተጣራባቸው መሆኑ ተነግሯል፡፡ 

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ነሐሴ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት ተጠርጣሪውን አቅርቧቸዋል፡፡ ቀደም ብሎ በተፈቀደለት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ 13 ሚሊዮን ብር የተንቀሳቀሰበት ሰነድ ከባንክ ተፈልጐ መሰባሰቡን፣ በፌዴራልና በክልል ባሏቸው ቤቶች ብርበራ መካሄዱን፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የሲዲ መረጃ መሰብሰቡንና የሁለት ምስክሮችን ቃለ መቀበሉን መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ አስረድቶ፣ የሚቀረው ምርመራ እንዳለ በመግለጽ ተጨማሪ 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠይቋል፡፡

መርማሪ ቡድኑ ተጨማሪ ቀናት የጠየቀበትን ምክንያት ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው፣ ከአዲስ አበባና ከፌዴራል ፖሊስ የነፍስ ግድያ ወንጀል ምርመራ መዝገብ መጥቶለት፣ ምርመራው በደንብ መካሄዱን መገምገም ከፌዴራልና ከክልል የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ተጨማሪ የሰነድ ማስረጃዎች መሰብሰብ፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ የተለያዩ ሰነዶችን መሰብሰብ፣ ከኦሮሚያ ገቢዎች የኢንስፔክሽን ሪፖርት መሰብሰብና ሌሎች ተጠርጣሪዎችን መያዝ እንደሚቀረው አስረድቷል፡፡ 

በተጠርጣሪው ዘጠኝ ቤቶችና በአራት ከተሞች የተደረገውን የብርበራ መረጃ መተንተን፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሰባሰቡትን የመሬትና የቤት ባለቤትነት ሰነድና  ከተለያዩ ባንኮች ገንዘብ የተቀባበሉባቸውን ደረሰኞች ማስረጃ መሰብሰብ እንደሚቀረው፣ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት የተጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ቀን እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡

አቶ ወንድሙ በበኩላቸው ባቀረቡት ተቃውሞ፣ መርማሪው የፈለገውን ሰነድም ሆነ ሌላ ነገር ማግኘቱን ገልጸዋል፡፡ መርመሪዎች እሳቸውን ካሰሩ በኋላ መኖሪያ ቤታቸው በመሄድ የአምስት ዓመት ሕፃን ልጃቸው ላይ ሽጉጥ በመደቀን ያደረጉትን ማስፈራራት አምርረው ተቃውመዋል፡፡

ከታሰሩበት ዕለት ጀምሮ ማንም ቤተሰብ እንዳልጠየቃቸው፣ ምክንያቱ ደግሞ መርማሪዎቹ እንዳስፈራሯቸው መስማታቸውን ተናግረዋል፡፡ እሳቸው የክልል ተሿሚና የካቢኔ አባል መሆናቸውን በመግለጽ፣ መጠየቅ ካለባቸውም በክልል እንጂ በፌዴራል አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡ ኮሚሽኑ በመገናኛ ብዙኃን ስማቸውን እያጠፋ መሆኑን በመግለጽ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡

የኮሚሽኑ መርማሪ በበኩላቸው አቶ ወንድሙ ያቀረቡትን አቤቱታ የሰሙት በዕለቱ ለችሎቱ ሲያስረዱ መሆኑን ገልጸው፣ እሳቸው እንዳሉት ሆኖ ከተገኘ ኮሚሽኑ በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ ዕርምጃ እንደሚወስድ አሳውቀዋል፡፡ ሥልጣኑ የክልል ነው ስለመባሉ ግን፣ የግብር ጉዳይ የፌዴራሉ ጭምር መሆኑን በመጥቀስ አስረድተዋል፡፡ የቫትንና የጉምሩክ ቀረጥን በሚመለከት የማየት ሥልጣን የፌዴራል ፍርድ ቤቶች መሆኑንም አክለዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ አቶ ወንድሙ ያቀረቡትን አቤቱታ በሚመለከት በሰጠው ትዕዛዝ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው መከበር እንዳለበት አሳስቦ በቤተሰብ፣ በዘመዶቻቸው፣ በሃይማኖት አባትና በሕግ አማካሪያቸው የመጐብኘት መብት እንዳላቸው በመግለጽ ኮሚሽኑ ተግባራዊ እንዲያደርግ አዟል፡፡ 

በሕፃን ልጃቸው ላይ ተደረገ የተባለው እውነት ከሆነና ማስረጃ ከቀረበ ዕርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቆ፣ የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን በሕግና በአግባቡ መመርመር እንዳለበት፣ ከዚያ ውጪ የሆነ በግዳጅና በኃይል የሚገኝ መረጃን ውድቅ እንደሚያደርግ በማሳሰብ፣ መርማሪ ቡድኑ ለጠየቀው ተጨማሪ ምርመራ አሥር ቀናትን ፈቅዷል፡፡ 

 

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ከአክሰስ ቦርድ ሰብሳቢነታቸው ተነሱ

‹‹መንግሥት አክሲዮን ማኅበሩን ለማፍረስ በሚደረግ እንቅስቃሴ ላይ ጥብቅ ዕርምጃ ይወስዳል›› አቶ ኑረዲን መሐመድ፣ የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ

በድንገት ከአገር ወጥተው በተባበሩት ኤምሬት ዱባይ ከተማ ለሁለት ዓመታት ከቆዩ በኋላ ከመንግሥት ጋር ባደረጉት ድርድር ከለላ ተሰጥቷቸው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣

አገር ውስጥ ከተመለሱ በኋላ ቀድሞ ወደነበሩበት የአክሰስ ሪል ስቴት አክሲዮን ማኅበር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተሾሙ ቢሆንም፣ ‹‹ምንም ዓይነት ሥራ አልሠሩም›› ተብለው ከሰብሳቢነታቸው ተነሱ፡፡

የቦርድ አባላት ነሐሴ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ አቶ ኤርሚያስን ከቦርድ ሰብሳቢነታቸው ያነሷቸው፣ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ከተሾሙ ከመጋቢት 26 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በእሳቸው ሰብሳቢነት በርካታ ስብሰባዎችን ያደረጉ ቢሆንም፣ በሥነ ሥርዓት ጉዳዮችና አሉባልታ ወሬዎች ላይ ከመነታረክ ያለፈ ምንም ዓይነት ቁምነገር አለመሥራታቸውን የቦርዱ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባዔ ያስረዳል፡፡ አቶ ኤርሚያስ በሕግና በሥርዓት ሊሠሩ ባለመቻላቸው፣ ቦርዱ የኩባንያውን ችግር ለመፍታት በመንግሥት ለተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ በማሳወቁ ኮሚቴው መመርያ ሰጥቶ እንደነበርም በቃለ ጉባዔው ተገልጿል፡፡ ኮሚቴው በሰጠው መመርያ ቦርዱ ስለ አክሰስ ሪል ስቴት አካሄድ ፍኖተ ካርታ እንዲያቀርብ አዞ የነበረ ቢሆንም፣ ጥቃቅንና የትም የማያደርሱ ድርጅቱን ሥጋት ላይ የሚጥሉ ነገሮች ከመነሳታቸው ባለፈ ፋይዳ ያለው ነገር ሊሠሩ ባለመቻላቸው ከቦርድ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን የቦርዱ ቃለ ጉባዔ አስታውቋል፡፡ አክሰስ ሪል ስቴት በአቶ ኤርሚያስ ሲመራ ወደ ድርጅቱ ካዝና መግባት ያለባቸውን ተሰብሳቢ ሒሳቦች ከማንሳት ይልቅ ዕዳ መቀበልን እንዲያስቀድም መደረጉን ቦርዱ ገልጿል፡፡ ድርጅቱን ከውድቀት ሊያነሳ የሚችል ብዙ ተሰብሳቢ በሕጋዊ ሰነድ የተያዘ ገንዘብ ቢኖርም፣ በእሱ ጉዳይ ላይ ውይይት አለመደረጉንም ጠቁሟል፡ 

አቶ ኤርሚያስ ወደ አገር ቤት የተመለሱበት ዓላማ እንዲያሳካ በሚል ቦርዱ ብዙ ነገሮችን እያየ እንዳላየ ማለፉን ጠቁሞ፣ አሁን ግን ሥጋው መሬት ላይ እያለ የደረቀ ቋንጣ እያወረደ መሆኑን በመገንዘብ ዕርምጃውን ለመውሰድ መገደዱን ገልጿል፡፡ አቶ ኤርሚያስ ያለ ቦርዱ ተሳትፎ በራሳቸው ለተለያዩ ድርጅቶች ደብዳቤ መጻፋቸው፣ ቅጥር ማካሄዳቸውና ‹ፒንግል ሪል ስቴት› ከተባለ የቻይና ኩባንያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን ቦርዱ ጠቁሞ፣ ነገር ግን ኩባንያው በሕይወት ይኑር አይኑር የሚታወቅ ነገር እንደሌለ አስታውቋል፡፡ በአጠቃላይ አቶ ኤርሚያስ ከነሐሴ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ከቦርድ ሰብሳቢነታቸው ተነስተው ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት ወ/ሮ መብራት ወልደ ትንሳዔ በሰብሳቢነት እንዲመሩ በመስማማት መወሰኑን አስታውቋል፡፡ 

አቶ ኤርሚያስ መሥራችና የቦርድ ሊቀመንበር ከነበሩበት አክሰስ ሪል ስቴት፣ በአገር ውስጥና በተለያዩ አገሮች የሚኖሩ ከ2,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች የቤት ግዢ የፈጸሙ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ቤትም ሆነ ገንዘባቸውን አለማግኘታቸውን እየገለጹ ነው፡፡ አቶ ኤርሚያስ በድንገት ከአገር ሲወጡ ቤት ገዢዎቹ የተለያዩ ተቃውሞዎችን ሲያቀርቡ ከርመው፣ በመጨረሻ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ከአቶ ኤርሚያስ ጋር በመደራደር ለተለያዩ ግለሰቦች ቆርጠውት በነበረ ደረቅ ቼክ ምክንያት እንደማይታሰሩ ዋስትና ተሰጥቷቸው፣ በየካቲት ወር 2007 ዓ.ም. ወደ አገር ቤት ተመልሰዋል፡፡

አቶ ኤርሚያስ በወቅቱ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ከየካቲት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራ እንደሚጀምሩና ማንኛውም ቤት ገዢ የፈለገውን ማለትም ቤቱን ወይም ገንዘቡን ከነወለዱ እንደሚመልሱ ቃል መግባታቸው በወቅቱ ተዘግቧል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ቤት ገዢዎች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አቶ ኤርሚያስ እንኳን ገንዘብ ሊመልሱና ስለቤት ሊያናግሯቸው ቀርቶ በአካል አይተዋቸው እንደማያውቁ እየገለጹ ነው፡፡ መንግሥት የሰጣቸውን ተስፋም ማየት ባለመቻላቸው ተስፋ እየቆረጡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአጭር ጊዜ ተብሎ ላለፉት ስድስት ወራት ምንም ነገር አለማየታቸውን አስረድተዋል፡፡ 

የአቶ ኤርሚያስ ፍላጐት በተለያዩ መንገዶች ነገሮችን በማጓተት ድርጅቱ እንዲፈርስና ከተጠያቂነት ለመዳን ስለሆነ፣ ቃል የገባው መንግሥት በነገሩ ላይ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡ 

በቦርዱ ጽሕፈት ቤት ለሚሠሩ 13 ሠራተኞች የሰኔና የሐምሌ ወር ደመወዝ መክፈል ሳይቻል ቀርቶ ቴክኒክ ኮሚቴውና ከቤት ገዢዎች ለተለያዩ ወጪዎች ከሰበሰበው ገንዘብ አክሲዮን ማኅበሩ ተበድሮ መክፈሉን አስረድተዋል፡፡ ይኼ የሚያሳየው ድርጅቱ ችግር ውስጥ መሆኑን እንደሆነ አስረድተው መንግሥት አስቸኳይ ውሳኔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ 

የቴክኒክ ኮሚቴው ሰብሳቢ የንግድ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ኑረዲን መሐመድ ግን በቤት ገዢዎቹም ሆነ በቦርዱ ሐሳብ አይስማሙም፡፡ እሳቸው እንደሚሉት ሰው የፈለገውን ቢያወራ ኮሚቴው መሥራት የሚችለውን እየሠራ እንደሆነና በሥራውም ውጤታማ መሆኑን ነው፡፡ 

ከየአቅጣጫው እየጮሁ የሚገኙት ከቤት ገዢዎቹ አሥር በመቶ የማይሆኑትና አቶ ኤርሚያስ ሲነኩ የሚነኩ ሰዎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ አቶ ኤርሚያስ የሕግ ከለላ የተሰጣቸው ሥራዎች ተስተካክለው እንዲሄዱ እንጂ ከሕግ ተጠያቂነት ለማዳን አለመሆኑን የገለጹት አቶ ኑረዲን፣ በአቶ ኤርሚያስ በኩል ስላሉ ሰዎች መረጃ መጠየቅ ሲጀመር የእሳቱ ወላፈን የሚነካቸው ሰዎች ብዙ ነገር ለማድረግ እየጣሩና እየተወራጩ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ከአንድ ወይም ሁለት ሳምንት በኋላ በተለይ አምቼ አካባቢ ያለው ፕሮጀክት ይፋ እንደሚደረግና ሥራ እንደሚጀመር የጠቆሙት ሰብሳቢው ቦርዱ፣ የቦርዱ አባላትና አስፈጻሚው የየራሳቸው አጀንዳ ስላላቸው ምንም ነገር እንዳልተሠራ የሚያስወሩት ወሬ እንደሚቆም ተናግረዋል፡፡ ሁሉም የሚሮጠው የራሱን መብት ለማስከበር መሆኑን ጠቁመው መንግሥት ግን ተረጋግቶና ሁሉንም ነገር በአግባቡ በመሥራት እያንዳንዷን ነገር ማስተማሪያ ማድረግ እንደሚፈልግ ገልጸዋል፡፡ 

አክሲዮን ማኅበሩ ከፈረሰ ተጠያቂነት ስለማይኖር በንግድ ሚኒስቴር የአክሲዮን ማኅበራት ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት የመጀመሪያ የቤት ሥራው ጥንቃቄ አድርጐ ጅምሩን ዳር ማድረስ መሆኑንም አቶ ኑረዲን አስረድተዋል፡፡ አክሲዮን ማኅበሩን ለማፍረስ የሚደረግ እንቅስቃሴ ከታየ መንግሥት ጥብቅ ዕርምጃ እንደሚወስድም አስረድተዋል፡፡ የሆነ ያልሆነ መረጃ ወጥቶ ቤት ገዢውን ተስፋ የሚያስቆርጥ ወሬ እንደሚሰማ የገለጹት አቶ ኑረዲን፣ መንግሥት አቶ ኤርሚያስ ሳይኖሩ ኃላፊነት መውሰዱን ቤት ገዢው መዘንጋት እንደሌለበት አስታውሰዋል፡፡

አቶ ኤርሚያስ ወደ አገር ቤት እንዲመጡ የተደረገው ሥራ እንዲሠሩ፣ ሚስጥሮችን እንዲያወጡና ሦስተኛ ወገኖችን እንዲታገሉ መሆኑን የገለጹት አቶ ኑረዲን፣ ቦርዱ ራሱ ሾሞ ራሱ እንዳወረዳቸው መግለጹ አግባብ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሌላ መሾምም ሆነ መነሳት ካለባቸው በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽሕፈት ቤት የፀደቀ ሰነድ መኖር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ይኼ ባልሆነበት ሁኔታ ስለሚካሄደው ነገር የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ አሁን በቦርዱም ሆነ በጥቂት ቤት ገዢዎች እየተደረገ ያለው ነገር ሥራውን የሚያስትና የሚያደናቅፍ አለመሆኑን አቶ ኑረዲን ተናግረዋል፡፡     

ቦርዱ ባሳለፈው ውሳኔና ቤት ገዥዎች እያቀረቡት ስላለው ተቃውሞ ምላሽ እንዲሰጡ አቶ ኤርሚያስን ሪፖርተር ቢሮቸአው ድረስ በመሄድና በስልክ ጭምር ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡    

 

ከኤርሚያስ ለገሠ 1• ደስታ እና ሀዘን ሰሞኑን ፍቺ በፍቺ ሆነናል። የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ከፊል አካል ተፈታ። ደስ አለን። የተፈቱት ካልተፈቱት ያላቸው ልዩነት ለብዙዎች ግራ ቢያጋባም!…ዛሬ ደግሞ እነ ሀብታሙ አያሌው ተፈተዋል። ይህም በግለሰብ ደረጃ ደስ የሚል ዜና ነው። ቢያንስ በቅርብ የማውቀው ሀብታሙ (” ሀብትሽ!”) ክፋ ደጉን የማታውቀው ልጁ እጁ ላይ ስታንቀላፋ፣ ወደ አልጋዋ ወስዶ ሲያስተኛት፣ ከእንቅልፏ

The post የአዲሱ ህውሀት መንግስት መጥፎ አጋጣሚ!! – (ኤርሚያስ ለገሠ) appeared first on ሳተናው (Satenaw)-Latest Ethiopian News & Breaking News.

የደቡብ ሱዳን ጦርነት በእስከአሁን ሂደት ከ 10 ሺህ በላይ ዜጎችን ህይወት መቅጠፉና በመቶ ሺህዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ስደት መንስኤ መሆኑ አይዘነጋም ይሁን እንጂ ለሀገሪቱ ሰላም ያመጣል ተብሎ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት የቅርብ ጊዜው የአዲስ አበባ ድርድር ውጤቱ የተጠበቀውን ያክል መሆን ሳይችል ቀርቷል በሰላም ስምምነቱ ሰነድ ላይ ተቃዋሚው ሪክ ማቻር ፊርማቸውን ቢያኖሩም የሀገሪቱ መንግስት ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪር ግን […]

ዛሬ ለኢሳት የደረሰው ጥብቅ መረጃ 11ዓመታትን ወደ ኋላ በትዝታ ወሰደኝ:: ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዋናው ጸሀፊ ቢሮ አፈትልኮ የወጣው መረጃ እንደሚያጋልጠው ለሰላም አስከባሪ 11 ሺህ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሚከፈለው ደምወዝ ከ90 በመቶ በላይ የህወሀት ካዝና ውስጥ የሚገባ ነው:: በወር 13 ሚሊዮን ዶላር(500 ሚሊዮን ብር ገደማ) የወታደሩን ገንዘብ ህወሀቶች ይቀራመቱታል:: ይህን ጉዳይ የመንግስታቱ ድርጅት የሚያውቀው ይመስለኛል:: ለዚህም እኔ […]

የትግራይ ምእራባዊ ዞን አስተዳዳሪ የሆነው ፍስሃ በርሀ ከ44 ሚልዮን ብር በላይ ለግል ጥቅሙ በማዋሉ የተነሳ የዞኑ ነዋሪዎች ምሬታቸውን በማሰማት ላይ መሆናቸው ተገለፀ። ለደህሚት በደረሰው መረጃ መሰረት የምእራብ ትግራይ ዞን አስተዳዳሪ የሆነው ፍስሃ በርሀ ለሁመራ ከተማ መሰረተ ልማት ተብሎ በተለያየ መልኩ ከህዝብ የተዋጣው 44 ሚሊዮን ብር ስልጣኑን ተገን በማድረግ ለግል ጥቅሙ ማዋሉን ታውቆ እያለ እስከ አሁን […]

1• ደስታ እና ሀዘን ሰሞኑን ፍቺ በፍቺ ሆነናል። የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ከፊል አካል ተፈታ። ደስ አለን። የተፈቱት ካልተፈቱት ያላቸው ልዩነት ለብዙዎች ግራ ቢያጋባም!…ዛሬ ደግሞ እነ ሀብታሙ አያሌው ተፈተዋል። ይህም በግለሰብ ደረጃ ደስ የሚል ዜና ነው። ቢያንስ በቅርብ የማውቀው ሀብታሙ (” ሀብትሽ!”) ክፋ ደጉን የማታውቀው ልጁ እጁ ላይ ስታንቀላፋ፣ ወደ አልጋዋ ወስዶ ሲያስተኛት፣ ከእንቅልፏ ስትነቃ አቅፎ […]

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ይገኙ የነበሩትና በትላንትናው እለት ነሐሴ 15 ቀን 2007 ዓ.ም የልደታው ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በነጻ ያሰናበታቸው፤ የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ ህ/ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ ከእስር ሊለቀቁ እንዳልቻሉ ‹‹በበላይ ፍቃዱ›› ይመራ የነበረው አንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ገለፁ፡፡ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እንደገለፁት የአቶ ሀብታሙ […]

ነኅሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሁለት ወጣቶች ጫካ መግባታቸውን ተከትሎ ተጨማሪ አርሶአደሮች እየተያዙ ነው። እስካሁን ባለው መረጃ ከ380 በላይ ሰዎች ተይዘው ድብደባ እየተፈጸመባቸው ሲሆን፣ ከዚህ ቁጥር ውስጥ ገሚሶቹ ሴቶች ናቸው። አብዛኞቹ ሴቶቹ የተያዙት በርካታ አርሶአደሮች አፈሳውን ለማምለጥ ጫካ መግባታቸውን ተከትሎ በባሎቻቸው ቦታ ሲሆን፣ የተወሰኑት ደግሞ ለሽፍቶች ምግብና ውሃ አቀብላችሁዋል ተብለው ነው። …

ነኅሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፋር፣ በሶማሊና በሌሎች አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ አድማሱን በማስፋት ጎጃም ውስጥም ተከስትዋል።በድርቁ ጉዳት በርካታ እንሰሳት እየሞቱ መሆኑንና ሰውም ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። በተለይ ድርቁ በሶማ፣ አራራ፣ እነገ እና ሰንጠርጌ ቀበሌዎች ለበርካታ እንሰሳት ሞት ምክንያት ከመሆኑም ባሻገር ነዋሪዎችም ለከፍተኛ ችጋር ተጋልጠዋል፡፡ ድርቁ አስከፊ ደረጃ እንደደረሰ …