ገንዘቤ ዲባባ ቃሏን ጠበቀች (video)

በቤይጂንጉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ 1,500m ድል ተቀዳጅታ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ ለኢትዮጵያ አስገኘች። ገንዘቤ በዚህ ርቀት ሞናኮ ላይ በቅርቡ አዲስ የዓለም ክብረወሰን ማስመዝገቧ አይዘነጋም። የገንዘቤ እህት ጥሩነሽ ዲባባ ከሰባት ዓመታት በፊት እ አ አ በ 2008 ዓም እዚሁ ቤይጂንግ Bird’s Nest ወይም የወፍ ጎጆ ስታዲየም በኦሊምፒክስ በ 5 እና በ 10 ሺህ ሩጫ ውድድሮች በሁለቱም የወርቅ ሜዳልያ በማግኘት ታሪክ ሠርታለች። አሁንም ገንዘቤ እዚሁ ስታዲየም ውስጥ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ 1, 500 እና በ 5,000 ሜትር ሩጫ ውድድሮች በሁለቱም ወርቅ ለማግኘት ዓልማለች። የመጀመሪያውን ወርቅ ዛሬ ወስዳለች። ሁለተኛው የፊታችን ዕሁድ የሚታይ ይሆናል።