ህወሀት ቴዲ አፍሮን ከልክ በላይ እየገፋው ነው:
ህወሀት ቴዲ አፍሮን ከልክ በላይ እየገፋው ነው:: ለቴዲ የህወሀት ኢትዮጵያ አላስቀምጥ ብላዋለች:: ምናልባትም ቴዲ ከሀገር ተሰደደ የሚል መራር ዜና ልንሰማ የምንችልበት ጊዜ እየቀረበ እንደሆነ ይሰማኛል:: በግሌ በተለይ ሰሞኑን የሚደርሱኝ መረጃዎች የህወሀትን የዕብሪት ለከት ማጣት የሚያሳዩ ቴዲንም ከሚወደው ህዝብና ከሚሳሳላት ሀገሩ እንዲለያይ የሚገፋፉ ናቸው:: ቴዲ መሰደድ እንደማይፈልግ የትኛውንም በደል ተቋቁሞ በሀገሩ መኖር ለምርጫም የማይቀርብ ጉዳይ እንደሆነ […]
ተኮረኮምን
ፍትህ አጣን
ነፃነትን ተገፈፍን
ተሠደድን
የወያኔን ዘረኛ ሥርአት ያመጣው መዘዝ ነው!!
አሜሪካ ሁነህ የወረወርከው ሿፊ ድንጋይ ኢትዮጵያ አይደርስም:ድንጋይ መሆን ከግሪክ ብድር የበለጠ ትልቅ እዳ ነው!ቴዲ አፍሮ ግን አዋቂና በሳል ድምጣዊ ነው!
በኩርኩም እንጂ በብእር የማያምነው ወያኔ ምን ይሻለዋል? ይህ የሚያሣየው ጥበብ ምን አይነት ረቂቅ መሆኗን ነው ወያኔ ተፈጥሮን በቁጥጥሬ ሥር ካልሆነች የሚል የህገ አራዊትን ሥርአት ይከተላል ለዚህም ነው በፍትህ በኢኮኖሚው በፖለቲካ የሠብአዊ መብት ረገጣ እያካሄደ ሁለተኛዋ ጎንታናሞ የሚል ሥም ያሠጠን።