አቡጊዳ – ኢሳትና ኢቲቪ አብረው ይሰሩ ይሆን ሲል ጃዋር ሞሃመድ ጠየቀ
«ኢትዮጵያዉያን ከኦሮሚያ ይዉጡ» የሚል መፈክር በማሰማቱ የሚታወቀውና በቅርቡ የተቋቋመው፣ የኦሮሞ ሜዲያ ግሩፕ ቴሌቭዥኝ ጀርባ ዋናው ሰው ተብሎ የሚገመተው፣ ጃዋር ሞሃመድ፣ ኢሳትን ከኢቲቪ ጋር የሚሰሩ ሲል ክስ አቀረበ።
በጊምቢ የሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያን ላይ ጥቃት ጥቃት እየተደረሰ እንደሆነ ኢሳት ሜያ 12 ቀን የዘገበዉን የተቃወመው ጃዋር፣ የኢሳትን ዘገባ የተጋነነ ብሎታል።
ኢሳት የጊምቢ ነዋሪዎችን ሁሉ ሳይቀር በማነጋገር፣ አክራሪዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ሁሉ ሳይቀር ጥቃት እያደረሱ እንደሆነ በስፋት መዘገቡ ይታወቃል።
ኢሳት አገዛዙ በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የወሰደውን አሰቃቂ እርምጃ በስፋት የዘገበ ሲሆን፣ በጉዳዩ ላይ ከበርካታ ጉዳዩን በቅርበት ከሚከታተሉ ባለሞያዎች ጋር ቃለ ምልልስ በስፋት ማድረጉ ይታወቃል።
በኦሮሚያ ለተፈጠረው የዘር ግጭት፣ ከኦህደድ በተጨማሪ ብዙዎች ጃዋር ሞሃመድ እና በዉጭ አገር ያሉ አክራሪ ኦሮሞዎችን ተጠያቂ ያደርጋሉ። «እንደ ኦዴፍ ፣ ኦፌኮ የመሳሰሉ ድርጅቶች በኦሮሞዉና እና በተቀረው ኢትዮጵያዊ ዘንድ መቀራረብ እንዲኖር እየሰሩ ባለበት ወቅት፣ በአንድ በኩል የአኖሌ የጥላቻ ሃዉልትን ያቁመው የነ ሙክታር ከድሩ ኦሕዴድ፣ በሌላ በኩል የኦሮሚያ ፈርስት በሚል ዘረኛ አጀንዳ ጸረ-ኢትዮጵያ እንቅሳሴ በማድረግ በኢንተርኔት ጥላቻን የሚረጩ በዉጭ የሚገኙ የኦሮሞ ዘረኛ አክራሪዎች ናቸው፣ እየታየ ያለው የዘር እልቂት እንዲፋፋም ያደረጉት» ያሉት በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ ጉዳዩን እጅግ በጣም አሳሳቢ እንደሆነ ያናገራሉ።