‹‹ ስሜ አቤል ዋበላ ነው፡፡ አዲሱ አመት ሲጠባ በአዲስ መንፈስ አዲስ ህልም ለአገሬ ማለም የነበረኝንም ማጠናከር እፈልጋለሁ፡፡ ኢትዮጵያችን የብሄር፣ የሃይማኖት፣ የሀብት፣ የትምህርት፣ የፖለቲካ አመለካከት እና ሌሎችም ልዩነቶች አብሮነታችንን የማያደናቅፉባት ከነልዩነታችን በጋራ ለታላቅነት የምንጠቀምባት ለሁላችንም ዕኩል ዕድል እና ተጠቃሚነት የሚቀርብባት ሁላችንም እንደየ ችሎታችን ለጋራ ደህንነታችን ነፃነታችን እና ብልፅግናችን የምንሰራባት ብቻ ሳይሆን በጋራ ስኬታማ የምንሆንባት እንዲሁም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዕኩል የሚያፈቅራት ኢትዮጵያ እንድትሆን እመኛለው፡፡ ይህ የእኔ ኢትዮጵያዊ ሕልም ነው፡፡››
ከላይ የሰፈረው ጽሁፍ ዞን ዘጠኝ ባዘጋጀው አራተኛው የበይነ መረብ ዘመቻ(Online Campaign) ላይ የተጠቀምንበት ነበር፡፡ የዘመቻው ርዕስ ‹ኑ አብረን ኢትዮጲያዊ ህልም እናልም › ሲሆን የተካሄደውም በ2005ዓ.ም መገባደጃ ወር ጰግሜ ላይ ነው፡፡ በአጋጣሚ ዘመቻው መንግስት የማናውቀውን ‹ወንጀል› እየፈለገብን እንደሆነ ከሁነኛ ምንጮች ከተረዳንበት ወቅት ጋር ገጥሟል፡፡ ለነገሩ ጠቅላይ ሚንስትሩ በቀደም ፓርላማ ቀርበው ‹‹ኢህአዴግ ሀሳብ የሚፈራ ድርጅት አይደለም››ሊሉ እንደፎከሩት ሳይሆን የሃሳብ ልዩነት እንደሚያስበረግገው ስለምናውቅ መስጋታችን አልቀረም፡፡ ከሌሎች ምንጮችም እርግጠኛ ያልሆኑመረጃዎች ደርሰውን ነበር፡፡ ይሄኛው ግን እርግጥ የሆነ ጅቡ ከበራፍ ላይ እንደቆመ የሚያበስር ነው፡፡
እንደ ሌሎች ዘመቻዎች ሕገ መንግስታዊነት፣ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ….. የመሳሰሉ ለሃገራችን “ቅንጦት” የሚመስሉ ርዕሶችን ማንሳት አልፈለግንም፡፡ አሁን የድራማው ዘመን ተቀይሮ እውናዊ  ሆኗል፡፡ ይህም የኔ የምንለው ትውልድ ምን አይነት ውስብስብ ችግር ውስጥ እንደተዘፈቀ በብርቱ እንድናስብ አደረገን፡፡ ለዚህም ነበር ሁሉን የሚያሳትፍ የትውልድ አቻዎቻችንን የሚጠራ ሰፊ ርዕስ የመረጥነው፡፡ ሁላችንም እንደምናስታውሰው ውጤቱ አርኪ ነበር፡፡
ስርዓቱ ግን ስለሃገራችን ያገባናልማለታችንን የትውልድ አቻዎቻችንን መፈለጋችንን አልወደደውም፡፡ የዘውጉን እውናዊነት ለማጠናከር ትምህርት ሊሰጠን ወደደ፡፡ መምህራን፣የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ቤተ ሙከራ ተዘጋጀ፡፡ አንደ አጋጣሚ ብቻ ሆኖ ከዞን ዘጠኝ ኢ-መደበኛ የጦማሪያን ቡድን ስድስታችን እና ሌሎች ሶስት ጋዜጠኞች (ኤዶም ካሳዬ፣ ተስፋለም ወልደየስ እና አስማማው ኃ/ጊዎርጊስ) ለተማሪነት ተመረጥን፡፡ ትምህርቱም ሚያዚያ17/2006 ዓ.ም በፌደራል ፖሊስ ውንጀል ምርመራ ዘርፍ (በተለምዶ ማዕከላዊ) ተጀመረ፡፡
ትምህርት አንድ
የመጀመሪያው ትምህርት የሀገራችን ኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ መረዳት ነበር፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የፖለቲካ ትንታኔ የሚሰጥ ወዳጃችን በዞን ዘጠኝ የሚደረጉ ሙከራዎችን አድንቆ ተጨማሪ መስራት ያለብንን ስራዎች ሊጠቁመን ‹‹ እናንተ ብዙ ጊዜ የምታተኩሩት የከተማ ፖለቲካ ላይ ነው፡፡ እስኪ ወደገጠር ጫንጮ እንኳን ሂዱ ከገበሬው ጋር ጠጅ እየጠጣችሁ ብሶቱን አድምጡና ጻፉ፡፡›› እንዳለን አስታውሳለሁ፡፡
እኛም ይህን ትችት ሙሉ ለሙሉ ተቀብለን በተግባር ባናደርገውም ከከተማ ወጣ ብሎ ለመመለስ ዕቅድ ይዘን ነበር፡፡ ማእከላዊ ግን ይህን ድካማችንን አቅልልሎ ሁሉንም አይነትኢትዮጵያዊ መልኮችን ከየአቅጣጫው አመጣልን፡፡ እነ ኡባንግን ከጋምቤላ፣ እነዚያድን ከደጋሃቡር፣ እነ አብድልከሪምን አቤኒሻንጉል፣እነ አያያዎን ከጎንደር፣እነ ቄስ ብርሃኔ ከአክሱም፣ እነ ሼህ መሀመድን ከጅማ አሰባሰበልን፡፡ የእስር ቤቱን ጨለማ ቀን እና ጨለማ ሌሊቶች ከልብ በሆኑ ወሬዎች አደመቅናቸው፡፡ ፖለቲካዊ ብልጣብልጥነት ያልነካካው ከጭቆናው የመጀመሪያ ረድፍ ገፈት ቀማሾች የሚቀዳ እውነትን አደመጥን፡፡በሰውነት ከመከበር አንስቶ እስከ የምድሪቱን ፍሬ በዕኩልነት መጠቀም ጥሮ ግሮ ኑሮን ለማሸነፍ የሚያስችሉ ዕድሎች ፍትሕአዊነት፣ ሳይፈሩና ሳያፍሩ ሀሳብን መግለጽ በወረዳና ቀበሌ ደረጃ የሚያስከፍለው ዋጋ፣ ከስር ባሉ የቢሮክራሲው አካላት የሚፈፀም ተቋማዊ ግፍ በአጠቃላይ አድርባይነትና አስመሳይነት በመላው ሀገሪቱ እንዴት እንደሰፈነና ብዙሃኑም ኑሮውን በቀቢጸ ተስፋ እንደሚገፋ ተረዳን፡፡ ሁሉም የጎላው ምስል ግን ዛሬም ፌደራሊዝሙ መሰረታዊ የሆኑትን የስልጣንና የሀብት (Power and Resource)ጥያቄዎች እንዳልመለሰ በጉልህ ይናገራል፡፡
ከመታሰሬ በፊት በነበረኝ ግምት በርካታ የኦሮሞዎ ተወላጆችን በማረሚያ ቤት እንደማገኝ ጠብቄ ነበር የመጀመሪያው ሰሞን  ከዚህ የተለየ ነበር፡፡ በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ከታሰሩ አንዳንድ ሙስሊም ኦሮሞዎችበስተቀር ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች አልነበሩም፡፡ ይሄ ግን ብዙ አልቆየም፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ የኦሮሚያ ልዩ ዞንን በሚነካው አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ ማስተር ፕላን የተነሳ በተፈጠረው ግርግር በርካታ ኦሮሞ ተማሪዎች ከየዩንቨርስቲው ተለቅመው መጡ፡፡ ያን የስቃይ ቤት በሳቅ ጨዋታቸው አደመቁት፡፡ ውይይታችንም ብዙ ርዕሰ ጉዳዮችን ዳሰስን፡፡ እኛም ብዙ ተማርን፡፡ በእነርሱ መሪነት በህብረት የምናዜማቸው የኦሮሚኛ ዘፈኖች የነበርንበትን አስቸጋሪ ሁኔታ አስረሱን፡፡
ከሁሉም ከሁሉም biyya Toodhuufen silaala yaa Biyaa Dubro maagala (የጠይም ቆንጆዎች መፍለቂያ ሀገሬ መጥቼ አይሻለሁ) የሚለውን እንጃ የኔን ቀልብ የሳበ ዜማው አንጀቴን ሰርስሮ የገባ ነበር፡፡ አገሬ ጠያይም ቆንጆ ልጆችሽ በነፃነትና በእኩልነት እንዲኖሩብሽ አልማለሁ፡፡ይህ የኔ ኢትዮጵያዊ ሕልም ነው፡፡   
ትምህርት ሁለት
ሁለተኛው ትምህርት በተግባር የተደገፈነው፡፡ በተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት የተሰሩ የሰብዐዊ መብት አያያዝ ሪፖርቶችን ማንበብ ከጀመርኩኝ ጥቂት አመታት አልፈዋል፡፡ሁሌም እንደተለመደው ኢትዮጵያ የዜጎቻቸውን ሰብዐዊ መብት ከሚጥሱ እና የማሰቃየት ተግባር የሚፈፅሙ በተለይም በተለምዶ ማዕከላዊ ተብሎ የሚጠራው የመንግስት ተቋም በዋነኝነትእንደሚጠቀስ ብዙዎቹ ሪፖርቶች ያስረዳሉ፡፡ ከዚህ በመነሳት እስካሁን ድረስ የማሰቃየት ተግባርን (Torture) እኔም ሆነ ጓደኞቼ የምንረዳው እንደማንኛውም የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲሁ ነበር፡፡በተለይ እኔ በበኩሌ የተለየ ትኩረት እንደማልሰጠው አልሸሽግም፡፡
አሁን እነዚያ የአለማወቅ ወራት አልፈዋል፡፡ በታሪክ መጽሃፍት ላይ በዘመነ ደርግ እንደሚፈጸሙ ያነበብናቸው አስከፊ ተግባራት አሁንም በሃገራችን እንደሚፈፀሙ ህያው ምስክሮች ሆነናል፡፡ ከስነ ልቦናዊ የማሰቃየት ተግባር አንስቶ የተለያዩ የማሰቃያ ቁሳቁስ በመጠቀም እስከሚፈፀሙ ዘግናኝ ተግባሮች በእኛና በሌሎች ላይ ሲፈፀም ተመልክተናል፡፡በከፍተኛ ድብደባ እግሮቹ የሚወላከፉ፣ መራመድ አቅቶት በሸክም ወደ ማረፊያ ቤት የሚመለስ፣ በግርፋት ብዛት ጀርባው ብዙ ሰንበርየተጋደመበት፣ ብልቱ ላይ ሁለት ሌትር ውሃ በመንጠልጠሉ ምክንያት ሽንቱን መሽናት የተቸገረ፣ ጆሮው በጥፊ ደንቁሮና አፍንጫው የሚደማሰው መመልከት የየዕለት ተግባራችን ሆነ፡፡ በኤሌክትሪክ ሾክ የተደረጉና ‹ወፌ ላላ› ተገልብጠው እንደተገረፉ የሚናገሩ ተጠርጣሪዎችም አጋጥመውኛል፡፡ ስድብ፣ ዛቻውና የማዋረዱ ተግባር አእምሮ ሊቆጣጠረው የሚችል አይደለም፡፡ የቀረውን የማሰቃየት ተግባር ሲፈፀም ያዩና በራሳቸው ላይ የተፈፃመባቸው ይናገሩት፡፡   
ይህ ተቋም ባለበት ከተማ ምንም ነገር እንዳልተፈጠሩ ቆጥሬ ስራዬን እየሰራሁ እየበላሁ እና እየጠጣሁ በቆየሁባቸው ዓመታት አፈርኩኝ፡፡ በአገሬ ኢ-ዲሞክራሲያዊነት እንዲታለፍ ዲሞክራሲያዊነት እንዲጀመር ከዜሮ ትንሽ ከፍ የሚል መፍጨርጨር በማድረጌ ግን ተፅናናሁኝ፡፡ የማሰቃየት ተግባርን በንድፈ ሀሳብ ደረጃ መረዳትና  መረጃዎችን በልብ ማኖር አንድ ነገር ነው፡፡ ዘግናኝ የማሰቃየት ተግባር የተፈፀመበት ተጠቂ ማግኘትና ማናገር ሌላ አንድ ነገር ነው፡፡ የማሰቃየት ተግባርን በራስ ሰውነት ማስተናገድ ግን ከሁሉም ይለያል፡፡ ባለቅኔው ሰው የሚማረው አንድም በሳር ‘ሀ’ ብሎ አንድም በአሳር ‘ ብሎ እንዳለ ከዚህ በላይ ትምህርት ከወዴት ይገኛል!?
የፌደራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ትልቅ ተቋም ነው፡፡ ምርመራ ደግሞ ሳይንስ፡፡ ሀገራችን የምር በሽብርና የሌሎች ወንጀሎች ስጋት ቢኖርባት ተጠርጣሪዎችን መርምሮ ለፍርድ የማቅረብ ዋና ሀላፊነት ያለበትይህ የፍትህ አካል ነው፡፡ በአግባቡ ከተከናወነ ሕጋዊነትን ባህል የሚያደርግ ነገር ግን ተጠርጣሪዎች ላይ የማሰቃየት ተግባር የሚፈፀምበት ከሆነ ደግሞ ሙሉ የፍትህ ስርዓቱን አቀጭጮ የሚያስቀር ነው፡፡ ይህንን የሰው ልጅ ማሰቃያ ስፍራ ለቀን ወደ ማረሚያ ቤት ስንወሰድ አበራ ጀምበሬ Agony in the grand palace ላይ ያሰፈረውን
Commit to the paper the suffering in that dark chamber
Announce to the world all the unbearable torture
የሚለውን ግጥም እያሰብኩኝ አንድ ተጨማሪ ህልም አለምኩኝ፡፡ ይህን ፖለቲካዊ የሀሳብ ልዩነትን መዳመጫና የህሊና እስረኞችን ደም ማፍሰሻ የሆነ ተቋም ወደ ሙዚየም ተቀይሮ ማየት ነው፡፡ ይህ የኔ ኢትየጵያዊ ህልም ነው፡፡
ትምህርት ሶሰት -የትውልድ እዳ
ሶስተኛው ትምህርት የሚገኘው መንግስት ወደ ጦማርያን እጁን እንዲሰድ ያደረገውን ተግባርና እስሩን ተከትሎ የታየውን ምላሽ በመገምገም ነው፡፡ ከዚያ በፊት ግን ቮልቴር  If you wish to converse with me define your terms እንዳለው ከዚህ በኋላ ‹‹ትውልድ›› ወይም ‹‹የትውልድ ልሂቃን›› ስንል ምን ማለታችን እንደሆነ ብያኔ ሰጥቼ እቀጥለላሁ፡፡ የነገሩን ውል ለመጨበጥ ትንሽ ወደኋላ መንደርደር አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡ ትውልድ ስንል ተቀራራቢ የእድሜ ክልል ውስጥየሚገኝ መሰረታዊ ለውጥ በሌለውና አንድ ሊባል በሚችል ስርዓተ ትምህርት ያለፈ የአንድ ስርዓት(Regime) ውጤት የሆነ እና የዘመኑን መንፈስ የተሸከመ ማለታችን ነው፡፡ የትውልድ ልሂቃን ስንል ደግሞ ሰፊውን የልህቅነት ትርጓሜ ሊገኝ ከሚችለው ነገር አብላጫውን ያገኙ(those who get the most of what there is to get)የሚለውን እንወስዳለን፡፡ ይህንን ብይን መሰረት በማድረግ አንድ ሰው ያገኘውን የትምህርትና የስራ እድል የገቢ መጠንና በማህበረሰቡ ያለውን ቦታ ከጠቅላላው የሀገሪቱ ዜጋ ጋር በማወዳደር የእርሱ ስፍራ የቱጋ እንደሆነ ይረዳል፡፡
አንድ ትውልድ ዘመኑ የሚጠይቀውን ኃላፊነት በአግባቡ ካልተወጣ በዚያች ሀገር ያሉ ችግሮችን ለማስተካከል ያለው እድል እየጠበበ ይመጣል፡፡ ሳንካ መፍትሄ ሳያገኝ በዘገየ መጠን የበለጠ እየከበደ እና እየተወሳሰበ ስለሚሄድ መፍትሔ ለመስጠት አዳጋችና ብዙ ዋጋ የሚያስከፍል ይሆናል፡፡ 
የሀገራችንን የቅርብ ጊዜ ታሪክ በዚህ አውድ ስናጤን ከጣሊያን ወረራ በኋላ ሀገሪቱን የተረከበው ልሂቅ የፊውዳል ስርዓቱ ዘመኑን እንደማይመጥን እና የሕዝቡን ችግር የመፍታት አላማ እንደሌለው ተገንዝቦ ለመሰረታዊ ለውጥና ማሻሻል ከመስራት ይልቅ ስርዓቱ የፈጠረለትንና የፈቀደለትን የትምህርትና የስራ እድል በመጠቀም ስርዓቱን ማገልገል ምርጫው አድርጓል፡፡ የነዚህ አዳዲስ ምሁራን ዘመኑን ያልዋጀ ጥረት የተመለከተው ማኅበረሰብም ‹‹ከእጅ አይሻል ዶማ›› ብሎ ይጠራቸው ነበር፡፡ በዘመኑ ከነበሩት ስመጥር ቴክኖክራቶች አንዱ የሆኑት የቀድሞውብሔራዊ ባንክ ገዢ  ተፈራ ደግፌ “Minutes of an Ethiopian Century” በተሰኘው መጽሐፋቸው ይህንን እውነታ በሀዘኔታ ያስታውሱታል፡፡
‹‹The tragedy of our Post-war generationof Ethiopian elite was that we adapted an attitude of public silence and private passivity on this professional level walking away from society instead of confronting its problems››
ልሂቁ ከ1953ቱ መፈንቅለ መንግሥት በቀር ምንም ሊጠቀስ የሚችል እንቅስቃሴ ሳያደርግ ዝምታን መምረጡ ለሚቀጥለው ትውልድ ግዙፍ ያልተሰሩ የቤት ሥራዎችን እንዳስረከበው መረዳት አያዳግትም፡፡ በክፍሉ ታደሰ ስሌት መሰረት 1930ዎቹ፣ በ1940ዎቹ እና በ1950ዎቹ የመጀመሪያ አጋማሽ የተወለዱና በ1960ዎቹ እና በ1970ዎቹ ንቁ የፖለቲካ ተሳትፎ የነበረውን ልሂቅ ያቀፈው ‹‹ያ ትውልድ›› ከወታደራዊው መንግሥትና እርስ በእርሱ ብዙ ዋጋ ያስከፈለ ትግል አድርጓል፡፡እንደመሬት ላራሹ ያሉ ውጤቶች ቢገኙበትም ሕጋዊነትን ዲሞክራሲያዊነት እንዲጀመር መሰረት ባለመጣሉ በኋላ ለመጡት ሁለት አምባ ገነንሥርዓቶች መነሳት መንስዔ ሆኗል፡፡ 
ወታደራዊ መንግሥት ወድቆ የሽግግር መንግስት የተቋቋመ ሰሞን ስመ ጥሩ ኢኮኖሚስት እሸቱ ጮሌ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሐዊ ማኅበረሰብ እንዲመሰረት የ1966ቱን አብዮት ለመራው ትውልድ የሰጠው እድል በወታደራዊው ኃይል መጨናገፉን በመጥቀስ ‹‹ታሪክ ሀገራችንን የምንታደግበት እና ከገባችበት አዘቅት ውስጥ ጎትተን የምናወጣበት ተጨማሪ እድል ሰጥቶናል፡፡ ለአንድ ትውልድ የሚሰጥ ሁለት እድል እንዲሁ በዋዛ የሚገኝ አይደለም፡፡ ሁለቱንም በግዴለሽነትና በሞኝነት ማባከን በቀጣዩ ትውልድ ይቅር የማይባል ወንጀል ነው፡፡››ብለው ቢመክሩም ያ ትውልድ ከራሱ ታሪክ ሳይማር ቀርቶ ዳግም አገሪቱን ወደኋላ የሚጎትት ስህተት ሰርቷል፡፡ 
በስርዓቱ አምባገነንነት የተነሳ በአገሪቱ ፖለቲካዊ ጉዳዮች በንቃትመሳተፍ የነበረበት አዲስ ትውልድ (በ1980ዎቹ እና በ1990ዎቹ) ምንም ሊጠቀስ የሚችል ነገር ሳይሰራ አልፏል፡፡ ስደተኛው ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ ከምርጫ 97 ጋር ከተያያዙ እንቅስቃሴዎች በስተቀር ጉልህ ድርሻ ያልነበረውን ይህንን ትውልድ ‹‹የጠፋ ወይም የባከነ›› ብሎ ጠርቶታል፡፡ ምርጫ 97ትም በቅንጅትም ሆነ በሕወሀት ኢኅአዴግ በኩል የመሪነት ሚና የተጫወቱት የያ ትውልድ አባላት በመሆናቸው ለትውልዱ ሙሉ እውቅና ለመስጠት ይከብዳል፡፡
ከዚህ ተስፋ ሰጭ ሙከራ በኋላ ስርዓቱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የግል ሚዲያውንና ሲቪል ማኅበረሰቡን አዳዲስ አፋኝ አዋጆች በማውጣት ፣ በማሰር እና በሌሎች እኩይ ተግባራት ማዳከሙ ሁላችንም የምናስታውሰው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ በዚህ አካባቢ ነው ዞን ዘጠኝ ኢ-መደበኛ የጦማርያን ቡድን  መንቀሳቀስ የጀመረው፡፡ የመጀመሪያዋ ጦማር ‹‹የሚያገባው ትውልድ ፍለጋ›› በሚል ርዕስ የወጣች ሲሆን ይህም ዞኑ ከዚያ በኋላ ያደረጋቸውን እንቅስቃሴዎች በሙሉ የቃኘ ነበር፡፡ በአጠቃላይ ከየትኛውም ብሔር ፣ ሃይማኖትና ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ያልወጣና አማራጭ ትርክት በማቅረብ ትውልዱ በሀገሪቱ ጉዳዮች ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ማነቃቃትን አላማው ያደረገ ነበር፡፡ አቅማችን በፈቀደ መጠን ከአለፉት ትውልዶች በተለይም ከያ ትውልድ ለመማር ሞክረናል፡፡ የሀገሪቱ ችግሮች ውስብስብ መሆናቸውን በመረዳት የትውልድ አቻዎቻችንን እኛም የምንማርበት መድረክ እንዲሆን ምኞታችን ነበር፡፡ ዝምታው ተሰብሮ በኃላፊነት ውይይት እንዲጀመር ተነሳሽነቱን ወሰድን፡፡ 
የውይይቱ መንፈስም ከጽንፈኝነት የፀዳ የሀሳብ ልዩነትን የሚያከብር እና ለአካዳሚያዊ ሀሳቦች ልዕልና የሚሰጥ ለማድረግም ሞክረናል፡፡( ህገ መንግስቱ ይከበር ሰንል የወያኔን ህገ መንግስት እውቅና ሰጡ ብለው ያጣጣሉን ድምጾች ቀላል አልነበሩም) ሀገራችን ያላት ደካማ የውይይት ባህልና ሥርዓቱ በየጊዜው የሚፈጥሯቸው ወደር የለሽ ብሶቶች ዋነኛ ተግዳሮቶች ነበሩ፡፡ እኛም የዚህ ማኅበረሰብ ባህልና ታሪክ ውጤቶች በመሆናችን መፈተናችን አልቀረም ፡፡ ነገር ግን ለጫና አልባው ውይይት (endless conversation) በተለይ እርስ በርሳችን በነበረን መስተጋብር ታማኞች ነበርን፡፡
ብዙዎች እንደቂልነት ሊወስዱት ቢችሉም የውይይቱ መድረክ አፍቃሪ ኢኅአዴግ የሆኑ ሰዎችና ራሱን ስርዓቱን የሚጨምርና የማያበሳጭ እንዲሆን በተቻለን መጠን ጥንቃቄ እናደርግ ነበር፡፡ ይህንን ጥረታችንን ብዙ ሰዎች  ትንሽ ሙከራችንን በለጋስነት እንዲወስዱት አደረጋቸው፡፡ ይህ ለጋስነት በሀገር ውስጥ እና በባህር ማዶ የሚገኙ የምናከብራቸው ሰዎችንና ተቋማትን ይጨምራል፡፡ እንደጠበቅነውም ብዙ ያልሆኑ ነገር ግን በቂ ሊባሉ የሚችሉ የትውልድ አቻ ወዳጆችን አፈራልን፡፡ ዞኑም የዘጠኝ ሰዎች ብቻ መሆኑ አከተመ፡፡ ‹‹ይህንን ብታስተካክሉት›› ‹‹ይህቺን ደግሞ እንዲህ ብታደርጓት›› እያሉ ድካማችንን እና ስንፍናችንን ማየት የማይፈልጉ ብዙ ሆኑ፡፡ 
በዚህ ሂደት እኛም ብዙ ተማርን፡፡ የተወሰኑ ኢ-መደበኛ የቡድኑ አባላትም የሕይወት ውሳኔዎችን በመወሰን ስራዎችን በመተው አራማጅነትን እና ጦማሪነት ጋር የተያያዙ ሙያዎች ውስጥ ገቡ፡፡ በፊት የምናከናውናቸውን ትንንሸ ስራዎች መስራት ለእኛ የማያረካ አክባሪዎቻችንንም መናቅ ሆኖ ተሰማን፡፡ ለበለጠ ስራ እራስን ወደ ማዘጋጀት ያሉብንን የአቅምና የቁርጠኝነት ችግሮች ለመፍታት ረዘም ያሉ እቅዶችን ያዝን፡፡ 
እኛ እንዲህ እና እንዲያ እያልን እናስባለን፡፡ መንግስት ደግሞ ስልካችንን ጠልፎ ከዋልንበት እየዋለ በብዙ ጆሮዎችና አይኖች እየሰለለን ወንጀል ሳይሆን ሰበብ ፈልጎ ሊያስረን አድፍጧል፡፡ በመጀመሪያ ‹‹ለራሳችን ትክክል ያልሆነ ትልቅ ግምት ስለሰጠን ነው እንጂ መንግሥት እኛን ምን ሰራችሁ? ምንአጠፋችሁ ብሎ ያስረናል?›› ብለን አጣጣልነው፡፡ የመታሰራችን ምልክቶች ሲገዝፉ ደግሞ ከብዙ ማሰላሰሎችእና ክርክሮች በኋላ እስከአሁን ያደረግነው ‹‹ወንጀል››  ከሆነ ካቴናው በእጃችን እንዲገባ ፈቅደን ጡመራውን እንደምንቀጥል በይፋ አውጀን ተመለስን፡፡ 
ጤናማ ሕዝባዊ ተዋስኦ (Public Discourse) እንዲዳብርና ኃላፊነትየሚሰማው ትውልድ እንዲፈጠር መድከም በእኛ የተጀመረ አይደለም፡፡ ብዙዎች በእስር፣ በግዞት (በስደት) እና በሞት ዋጋ የከፈሉበትነው፡፡ የኛን ትውልድ መንፈስ ለማረቅ ያደረጉት እያንዳንዱ ነገር በህሊናችን የገነነና በታሪክ ተመዝግቦ የሚቀመጥ ነው፡፡ ማንም ሊቀይረው በማይችለው የተፈጥሮ ኡደት እኛም ባለተራ ሆነናል፡፡ አገር አገር የምንለው በግልብ ብሔረተኝነትና በአጉል አርበኝነት መንፈስ በመነሳት አይደለም፡፡ የሀገር አመሰራረት ንድፈ ሀሳብና የአለማችን ጂኦ-ፖለቲካዊ እውነታ በመገንዘብ ነው እንጂ፡፡ ሀገራችን ከታሪኳ፣ከራሷና ከአሁኗ ጋር እንድንታረቅ ዋና ፍላጎታችን ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሚሆነው የመናገር ነፃነት ሳይገደብ ሁሉም የሀገሪቱ ጉዳዮች የሰለጠነ ጫና አልባ ውይይት ሲደረግባቸው እንደሆነ እናምናለን፡፡
ከትውልድ ጥቂቶችን በማሰር፣ ከሀገር እንዲወጡ በማስገድዶ በማሰደድ እና በመግደል የትውልድ ጥያቄን መቀልበስ ይቻላል ብሎ የሚያስብ ቢኖር እንዳይስት ይጠንቀቅ፡፡ የ1953ቱን መፈንቅለ መንግሥት  መክሸፍን ተመልክቶ ንጉሱ የመፈንቅለ መንግሥቱን ጠንሳሾች በማሰርና በአደባባይ በመስቀል የትውልዱን የለውጥ ጥያቄ ያዳፈኑ መስሏቸው መሰረታዊ ማሻሻል ማድረጉን እንዳይዘነጉ ከመከሩ ሰዎች ውስጥ አንዱ ደራሲ ዶክተር ሀዲስ አለማየሁ ናቸው፡፡ በዚህ ታሪካዊ ምክራቸውን ንጉሱ ከቁብ ባይቆጥሩትም‹‹ለማናቸውም ነገር መነሻ የሆነው ሥሩ እንደተደበቀ ተቀምጦ ከላይ እንደሚታየው ቅርንጫፉን ብቻ ቢጨፈጭፉትና ለጊዜውእንኳ የጠፋ ቢመስል የተመቸ ጊዜ ሲያገኝ የተደበቀው ስር ዳብሮ ተስፋፍቶ ለመጥፋትም እንደሚያስቸግር ሆኖ ይነሳል›› ብለው ተንብየው ነበር፡፡ የዚህ ዘመንም ነገር ጥቂት እድሜ የሰጠው ሰው ሲፈፀም የሚያየው ነው፡፡ 
እስር ሲታሰብ ብዙ ስጋቶች ወደ አዕምሮ ይመጣሉ፡፡ ከሁሉም የሚከብደው ግን ቤተሰብን ማንገላታትና በማረሚያ ቤት ተረስቶ መቅረት ነው፡፡ ቀበቶዬን አስረክቤ ወደማረሚያ ቤት ስወሰድ ይህንን እያወጣሁኝ እያወረድኩኝ ነበር፡፡ ያለፉት ሰባት ወራት የእስር ቆይታዬን ግን በመጠኑም ቢሆን መሳሳቴን ነግሮኛል፡፡ ማዕከላዊ ጨለማ ቤት በነበርኩኝ ጊዜ ጠያቂ ሰው ማግኘት የሚፈቀደው በሳምንት አንድ ቀን ለቤተሰብ አባላት ብቻ ነበር፡፡( እሱም ከሁለት ሳምንት “ምርመራ” በኋላ ከቤተሰብ ውጭ ጠያቂ ሲመጣ እኛን ማግኘት ስለማይፈቀድ የጠያቂው ስም በቁራጭ ወረቀት ላይ ተፅፎ ይመጣ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ለእኔ ብዙ ትርጉም ነበራቸው፡፡ በእስር ቤት አለመረሳቴን እና ስለእኔ እስር የሚጨነቁ ወዳጆች እንዳሉኝ እዚያ ጨለማ ቤት ያለሁት ለግልጉዳዬ ሳይሆን ማኅበረሰባዊ ጉዳይ(public cause) ይዤ መሆኑ እያስታወሰ መንፈሴ ሳይሰበር ያኖረኝ ነበር፡፡ ፍርድ ቤት ስንቀርብ ከሩቅ የማያቸው ብዙ ፊቶች መንፈስን የሚያረጋጉና የሚያጽናኑ ናቸው፡፡ በሀገር ውስጥ እና በባህር ማዶ ያሉ የቅርብ ጓደኞቻችን በአካልነው እንጂ በመንፈስ ከእኛ ጋር አልታሰሩም ማለት ይከብዳል፡፡ ከከንፈር መጠጣ በዘለለ  እስሩ እንዳይከብደን እና በሕግ ፊት (ይፈተን ዘንድ ነው እንጂ የፍትሕ ስርዓቱ ብቻውን ተነጥሎ ጤናማ እንደማይሆን ለቀባሪው ማርዳት ነው) ንጽህናችንን ለማረጋገጥ የሚያስፈልገውን ከማድረግ አልቦዘኑም፡፡ 
ማንዴላ አንድ ሰው ወህኒ እስኪወርድ

Image
የተለያዩ መፈክሮችን የያዙ ፊኛዎች ወደ ተውለብለበዋል :: ፊኛዎቹ የተለያዩ መፈክሮች የተጻፈባቸው ሲሆን ከነዚህም መካከል : – ትግሉ ይቀጥላል ፍትህ ነጥፏል ፤ሂጃብ መለያችን፤ኒቃብ ውበታችን ፤ትግላችን ቀጥሏል
ፍትህን ማዘግየት ፍትህን መንፈግ ነው ፤ትግላችን እንደቀጠለ ነው ::

ፍትህ ፍትህ ፍትህ ;We Need Justice ፤Hijab Is Beauty ፤ justice Is Denied የሚሉት መፈክሮች ይገኙበታል፡፡ በርካታ ፊኛዎች የተውለበለቡና ወደ ሰማይ የተለቀቁ ሲሆን ተቃውሞው በከፍተኛ ድምቀት ተከናውኗል፡፡ መንግስት በሴኩላሪዝም ሽፋን እየፈጸመ ያለውን የሂጃብ ገፈፋ የሚያወግዝ ሲሆን በተጨማሪም በህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ እጸፈጸመ ያለውን የፍትህ መዛባት ፤ በማረሚያ ቤቱ የሚፈጸሙ ግፎችን ለማውገዝ ነው፡፡ መንግስት ሙሉ በሙሉ ተቋሞውን በሃይል አስቁሚያለሁ ሲል የነበረ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙ ግን ድንገተኛ ተቃውሞ በማድረግ አስገራሚ ተቃውሞውን ገልጽዋል፡፡

Please wait, video is loading…

የባህዳር ነዋሪ በነቂስ በመውጣት በክልሉ ም/ቤት ፊት ለፊትና በአዲሱ ም/ቤት(ቀበሌ 10) መስቀል አደባባይ የቤተክርስያን የታቦት ማደሪያ ፣ ንብረትነቱም የቤተ-ክርስቲያን ነው ልትነጠቅ ወይም መንግስት እንደሚለው ለባለሀብት ሊሰጥ አይገባም በማለት ቁጣቸውን በማሰማት ላይ ናቸው፡፡ የባጃጅ ሾፌሮችም በየቦታው ትላክስና ጩኸት እያሰሙ ነው፡፡ የመስቀል አደባባይን መፍረስ በመቃወም በባህርዳር ከተማ የነበረው ሰልፍ ጥያቄውን አሰምቷል:: ሆኖም በአሁኑ ሰዓት በባህርዳር ከተማ በሕዝበ […]

ቁም ነገር መፅሔት ቁጥር 193 ታህሣስ 2007

ለሶደሬ

ሰሞኑን አዲስ ስያሜ ይዘህ የወደፊት መለያዮን/ፈረንጆች ሎጎ ይሉታል/ ስሩልኝ፤ የጣቢዬንም መርህ /ሞቶ/ ሰይሙልኝ ብለህ ያስነገርከውን ማስታወቂያ ተመልክተናል፡፡ እርግጥ ነው ገና ስያሜህን ቀይረህ በኢቲቪ መስኮት ብቅ ባልክበት ሰሞን አንድ ጦማር በዚሁ ገፅ ላይ መፃፋችንን…

ምርጫ በአንባገነን መንግስት ውስጥ? ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ስርአት መገለጫ የሚሆነው ነጻ፣ ፍትሃዊና ተወዳዳሪ (free, fair and contested) ባህሪያትን የተላበሰ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ በኢ-ዴሞክራሲዊ መንግስት ውስጥ የሚደረጉ ምርጫዎች በምንም መመዘኛ የዴሞክራሲ ስርዓት መገለጫዎች አይሆኑም፡፡ በሀገራችን በአጼው፣ በደርግ እና በኢህአዴግ ዘመነ-መንግስታት ተደርገው የነበሩ ምርጫዎች የአጼውን፣ የደርጉንና የኢህአዴግን የአገዛዝ ስርዓቶች የስልጣን ዘመን ለማራዛም የተደረጉ (“mechanism of regime maintenance”) ምርጫዎች […]

ቁም ነገር መፅሔት ቁጥር 193 ታህሣስ 2007
ለሶደሬ

ስለ ሜሮን ጌትነት ግጥምና ውዝግቡ
መቼም ሰሞኑን በማህበራዊ ድረ ገፆች ላይ ህዝቡ እየተቀባበለው ያለውን ‹አትሂድ› የሚለውን የሜሮን ጌትነት ግጥም አልሰማሁም አትለኝም? ወር በገባ በመጀመሪያው ረቡዕ በራስ ሆቴል በሚቀርበው የግጥም ምሽት ላይ ያቀረበችው ግጥም የመንግስት ደጋፊና ተቃዋሚዎችን የጦፈ ውዝግብ…

Minilik Salsawi – ባሳለፍነው የትግል አመታት ውስጥ የተቃዋሚዎች እርስ በ እርስ መፈራረጅ መወነጃጀል መናናቅ ለስልጣን ጥመኝነት መሮጥ እንዲሁም ለስም እና ለዝና መትጋት ያለመደማመጥ እና ያለመከባበር ፖለቲካ ተቀራርቦ ያለመነጋገር እና ያለመመካከር ፖለቲካ ሃገራኢ ሆደሰፊነት እና መቻቻልን ያላዘለ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተረፈው ነገር ቢኖር ከጭቆን ወደ ጭቆና ማቅ ውስጥ ከመዘፈቅ ውጪ ምንም የናፈቀውን የነጻነት አየር እንዲተነፍስ አላደረግነውም። የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተመቻቸ የሃሳብ መግባባት ተቻችሉ እና ተግባብቶ የትግል ስትራቴጂን ግብ ለማድረስ ለአንድ ወጥ ህዝባዊ እና ሃገራዊ አጀንዳ ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል።

ወያኔ የተቃዋሚዎችን እና የለውጥ ሃይሎችን እርስ በእርስ መፈነካከት በማየት አርጩሜውን ተስፋ በሚጣልባቸው ግለሰቦች እና ፓርቲዎች ላይ እያወናጨፈ ባለበት እንዲሁም የውስጥ አሰራራቸውን በመሰለል በትግሉ ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲኮላሽ በመስራት የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመጠቀም እርስ በርስ እንዲፋጁ እና ተቃዋሚዎች እንዲከስሙ ጥንካሪያቸውን እንዳያገኙ ሲሰራ ይህንን እንዴት አድርገን በማሻሻል የወያኔን ሴራ ማክሸፍ አለብን የሚል አመኔታ የሚያስገኝ ሕዝባዊ ስራዎችን በመስራት ጥንካሬን ማግነት እንዲሁም ሕዝባዊ ድጋፎችን ማግኘት ግድ የሚልበት ጊዜ ላይ መሆናቸውን ተቃዋሚዎች ሊያውቁት ይገባል::ተቃዋሚዎች ካለፈው ድክመቶቻችን ተምረን ከዘለፋ እና ከስድብ እንዲሁም ከመፈራረጅ የሴራ ፖለቲካ በመውጣት ጥንካሬዎቻችንን የምናሳይበት ለውጥ የምናመጣበት አመት እንዲሆን በጋራ ጠንክረን መስራት አለብን።አንድነት ሃይል ነው የሚለው ብሂል ለሃገራዊ አጀንዳ መተግበር ትልቅ አስታውጾ አለው::ከኛ በላይ ላሳር ከኛ በላይ አዋቂ የለም የሚል አመለካከት ይዞ ከመክነፍ የህዝብን ጥያቄ መሰረት አድርጎ ተቀራርቦ በመነጋገር እና በመወያየት ሃገራጂ ማኒፌስቶ በማምጣት የጋራ ሃገራዊ አጀንዳ በመቅረጽ ለለውጥ መትጋት ግዴታ ነው::

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል። ይህ ሳይታለም የተፈታ እና የሁሉም የነጻነት ፈላጊ ሃይሎች ጥያቄ ነው። በሃገር ውስጥ ያሉትን ፓርቲዎች መዋቅሮቻቸውን በማጠናከር የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመቅረፍ እንዲጠነክሩ የማድረግ ግዴታ ከለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ይጠበቃል። መመካከር መተራረም ግድ ይላል። በውጪው አለም የሚገኙ የነጻነት እና የለውጥ ሃይሎች እንዲጠናከሩ እና ከጥልፍልፎሽ ፖለቲካ ወተው ጠንካራ ሃይል እንዲሆኑ የዲያስፖራው ሃይል ከበፊቱ በበለጠ መልኩ ሊሰራ ግድ ይለዋል። የወያኔ የጎን ውጋት እና የራስ ምታት የሆነው ዲያስፖራው የጀመረውን የትግል ስልት እና ትጋት በማስፋት ሚዲያዎችን በማጠናከር እና የነጻ አውጪ ፓርቲዎችን በመርዳት በማግባባት ጠንካራ ሰንሰለት ከሃገር ቤት ጋር በመፍጠር ሕዝብን ከጨቋኞች ነጻ ማውጣት አለበት።ዲያስፖራው በየቀኑ ወያኔ የሚፈጥረውን ተራ የቤት ስራ እና የማደናገሪያ ማዘናጊያ አሉባልታ ፊት ሳይሰጠው በለውጡ ጉዳይ ላይ በማተኮር በሃገር ቤት ያለው ሃይል እንዲስማማ የፖለቲካ ጡዘቶች ክፍተት እንዳይኖር ተቀራርቦ እንዲሰራ ትልቁን ሚና መጫወት አለበት::

የሚዲያ ተቋማት እና የድህረገጽ ውጤቶች ሕዝብን በማስተማር ሕዝብን መብቱን እና ነጻነቱን አውቆ ለሌላው እንዲያስተምር በማድረግ ረገድ አስፈላጊውን ወቅታዊ መረጃ እና መነሳሳትን በማስረጽ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል። ያለፉ እና የከሰሙ ወሬዎችን እና አሉባልታዎችን ከመርጨት የወያኔ የፈጠራ አደናባሪ እና አዘናጊ አጀንዳዎችን እኝኝ በማለት ከማውራት ብሄር ተኮር ክፋፋይ ሃሳቦችን ከማርከፍከፍ አዛኝ መሳይ መርዝ ሃሳቦችን ከመናገር ተቆጥበን ሕዝቡን ስለመብቱ እና ነጻነቱን በማስተማር ረገድ መትጋት ከተያዘ ለውጥ የማይመጣበት ምንም ምክንያት የለም። ትችትን እና ሂስን ላለመዋጥ እውነትን ላለመቀበል የሚደረጉ ሩጫዎች ታጥቦ ጭቃ እንጂ የትም እንደማያደርሱ እንዲሁም ፓርቲዎችን እና ሰዎችን መፈረጅ እና መወንጀል ሃሳቦችን ማጣጣል ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ካለፈው ተምረናል ። ያሳልፍነው የትግል ሂደት ከጭብጨባ እና ስብሰባ ያለፈ ፋይዳ እንዳሌለው ተገንዝበን የወሬ እና ሆይሆይ ትግል ስለማያዋጣ ጥንካሬን እና ለውጥን የምናመጣበትን የትግል ስልት በመመካከር እና በመወያየት ሃሳብን በማቻቻል መረጃ በመለዋወጥ ሃገራዊ የጋራ አጀንዳ ሊኖረን ይገባል እላለሁ።



ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
—–
በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ለአፍሪቃ አህጉር የመጀመሪያ የሆነውን መስጊድ ነው፡፡ ይህ መስጊድ የተሰራው በ641 ሲሆን የሚገኘውም በግብፅ መዲና ካይሮ ውስጥ ነው፡፡ መስጊዱ የሚጠራው በመስራቹ በ“አምር ኢብን ኣስ” ስም ነው፡፡ ይሁንና አምር እና ጓዶቹ መስጊዱን የሰሩት በአል-ፉስጣጥ እንጂ በካይሮ አልነበረም፡፡ ታዲያ መስጊዱን ወደ ካይሮ ማን ነው ያስገባው?… እስቲ የዛሬ ወጋችንን በአምር ታሪክ እንጀምርና ስለፉስጣጥም ትንሽ እናውራ፡፡
       *****
አምር ኢብን ኣስ የዐረቢያ ምድር ካበቀለቻቸው ታላላቅ ፖለቲከኞችና የጦር መሪዎች አንዱ ነው፡፡ የተወለደው በመካ ከተማ ሲሆን ነቢዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ያፈራው የቁረይሽ ጎሳ አባል ነው፡፡ አምር የጉርስምና ዘመኑን እንደ ሌሎቹ የዐረቢያ ወጣቶች በግመል ግልቢያና በፈረስ ጉግስ አላሳለፈም፡፡ የርሱ ቀልብ ወደ ንግዱ ነበር ያተኮረችው፡፡ በመሆኑም  በዘመኑ በገበያ ውስጥ ተፈላጊ የሆኑ ሸቀጦችን ለማምጣት ወደ የመንና ሻም (ሶሪያ) በብዛት ይመላለስ ነበር፡፡ ሀብቱ እየተስፋፋ ሲሄድ ደግሞ እስከ ፋርስ (ፐርሺያ)፣ መስር (ግብፅ)፣ አቢሲኒያ (ሐበሻ/ኢትዮጵያ) እና ኦማን ድረስ እየሄደ ሸቀጦችን ያመጣ ጀመር፡፡ በነዚህ ሀገራትም በርካታ የንግድ ሸሪኮችን ለመፍጠር ቻለ፡፡ በሸሪኮቹ በኩልም ከየሀገራቱ ገዥዎች ጋር በመተዋወቅ ልዩ ልዩ ገጸ-በረከቶችን ይወስድላቸው ነበር፡፡
Mosque of Amr in Old Cairo in 19th Century
ይህ በእንዲህ እንዳለ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በ610 ገደማ እስልምናን ማስተማር ጀመሩ፡፡ የዐረብ ጎሳዎች የድንቁርና ህይወታቸውን ትተው እንደ ጥንቱ ቅድመ-አያቶቻቸው እንደ ነቢዩ ኢብራሂምና እንደ ዒስማዒል ፈጣሪን ብቻ እንዲገዙ ሰበኩ፡፡ ጥቂት ሰዎች እምነቱን ተቀበሉ፡፡ አብዛኞቹ ግን “የአባቶቻችንን መንገድ ልታስተወን ነው እንዴ…?” በማለት በነቢዩ ላይ በጠላትነት ተነሱባቸው፡፡ በነቢዩ ያመኑትንም ያሰቃዩ ጀመር፡፡ ነቢዩ በተከታዮቻቸው ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ሊከላከሉላቸው አልቻሉም፡፡ ስለዚህ ከተከታዮቻቸው መካከል የተወሰኑትን በሚስጢር ጠርተው ወደ ሐበሻ (ኢትዮጵያ) እንዲሰደዱ አዘዟቸው፡፡ በዚሁ መሰረት አንድ መቶ የሚሆኑ ሰዎች ወደ ሐበሻ ተሰደዱ፡፡
የቁረይሽ ባላባቶች የነብዩ ተከታዮች ወደ ሐበሻ መሰደዳቸውን ሲሰሙ “እዚያ ሄደው ሳይደራጁ በቶሎ ልናስመልሳቸው ይገባል” በማለት አንድ የልዑካን ቡድን ወደ አክሱም ሰደዱ፡፡ ቡድኑ ሁለት አባላት የነበሩት ሲሆን እነርሱም አምር ቢን ኣስ እና አብዱላህ ቢን ረቢዓ ናቸው፡፡ ያ ቡድን በሚችለው መንገድ ሁሉ ተደራድሮ የሐበሻውን ንጉሥ አርማህን (አስሓማ) በማሳመን የነቢዩን ተከታዮች ወደ መካ እንዲያስመልስ ታዟል፡፡ ነገር ግን ወደ ሐበሻው ንጉሥ ቀርቦ ድርድሩን እንዲፈጽም ስልጣን የተሰጠው ለአምር ቢን ኣስ ነው (አብዱላህ ቢን ረቢዓ “አምር” መልዕክቱን በትክክል ማድረሱን እንዲታዘብ ብቻ የተላከ ነው የሚመስለው)፡፡

አምር በንግድ ሰበብ ወደ ኢትዮጵያ በተመላለሰባቸው ዓመታት ከሐበሻው ንጉሥ ጋር ለመተዋወቅ ችሏል፡፡ ሆኖም አምር ለድርድሩ የተመረጠው በዚህ ብቻ ሳይሆን በዘመኑ ከነበሩት የመካ መኳንንት መካከል ተናግሮ በማሳመን ብቃቱ የተዋጣለት ሆኖ በመገኘቱም ጭምር ነው፡፡
       *****
አምር ከንጉሡ ዘንድ ቀርቦ ባደረገው ድርድር ያሰበው አልተሳካለትም፡፡ ንጉሡ ስደተኞቹን ለማንም አሳልፎ እንደማይሰጥ እቅጩን ነግሮታል፡፡ ይሁንና አምር በዚህ ተበሳጭቶ ወደ አክሱም መምጣቱን አላቆመም፡፡ ከድርድሩ በኋላም ቢሆን ለሁለት ጊዜያት ወደ ሐበሻ መጥቷል፡፡ ታዲያ ለመጨረሻ ጊዜ ከንጉሡ ጋር በተገናኘበት ጊዜ ንጉሡ እንዲህ ሲል መከረው፡፡
  “አምር ሆይ! አንተን የመሰለ ሰው የነቢዩ ሙሐመድን ትምህርት አልቀበልም ሲል ይገርመኛል፡፡ እናንተ ዐረቦች ከማንኛውም ህዝብ ወደ ኋላ ቀርታችኋል፤ ሙሐመድ ያመጣው ዐረቢያን ከጭለማ የሚያወጣውን አዲስ ብስራት ነው፡፡ በእርሱ ያመነ ሰው በፈጣሪ ዘንድ ከሚያገኘው ምንዳ በተጨማሪ ይህችን ዓለም ይገዛል፡፡”
ንጉሥ አርማህ አምርን እንዲህ ብሎ በሚመክርበት ጊዜ ለራሱም የነቢዩን እምነት ተቀብሏል፡፡ ይሁንና መላው የሐበሻ ህዝብ አዲሱን እምነት እንዲቀበል አዋጅ አልነገረም (አንዳንድ ጸሐፊያን “ንጉሥ አርማህ በነቢዩ ማመኑን በሚስጢር ይዞት ነበር” ይላሉ)፡፡
       *****
አምር ከሐበሻው ንጉሥ ከተለየ በኋላ በቀጥታ ወደ መካ ነው ያመራው፡፡ እዚያም ታዋቂው ጀግና ኻሊድ ቢን ወሊድ (ረ.ዐ) ወደ መዲና ለመሰደድ ሲዘጋጅ አገኘውና ከርሱ ጋር መሄድ እንደሚፈልግ ነገረው፡፡ ኻሊድም ሀሳቡን በደስታ ተቀበለው፡፡ ሁለቱ ሰዎች መዲና በደረሱ ጊዜ ነብዩ ሁለቱንም ሸሃዳ አስያዟቸው፡፡ ይሁንና ነቢዩ እነዚህን የዐረቢያ ጎምቱዎች አላሳረፏቸውም፡፡ ኻሊድን በሰሜን በኩል በነቢዩ መንግሥት ላይ አደጋ የጋረጡትን ሮማዊያንን ለመዋጋት በሚዘምተው የዘይድ ቢን ሓሪሳ ቡድን ውስጥ ቀላቀሉት፡፡ አምር ቢን ኣስ ደግሞ ወደ ኡማንና ባህሬን ሄዶ የዲፕሎማሲ ስራ እንዲሰራ አደረጉት፡፡ አምር ወደ ኡማን (ኦማን) የተጓዘው እነ አቡበከር፣ ዑመር እና አቡ ኡበይዳን (ረ.ዐ) የመሳሰሉ ታላላቅ ሰዎች የተካተቱበትን ቡድን በመምራት ነው፡፡ ነቢዩ አምር የቡድኑ መሪ እንዲሆን ያደረጉት የዲፕሎማሲ ችሎታውን በሚገባ ያውቁት ስለነበረ ነው፡፡ አምርም የዲፕሎማሲ ስራውን በደንብ ከመፈጸሙም በላይ የኦማን ሰዎች ወደ እስልምና እንዲገቡ ለማድረግ ችሏል፡፡
       *****
አምር ከነቢዩ ህልፈት በኋላም በአቡበከርና በዑመር ኺላፋዊ መንግሥት ውስጥም አገልግሏል፡፡ በጦር ግንባርም ሆነ በዲፕሎማሲ ስራ አንቱታን ያጎናጸፉትን ተግባራት ፈጽሟል፡፡ ከአምር ጋር የሁልጊዜ ተጠቃሽ ሆኖ የዘለቀው ግን ሮማዊያንን ከግብጽ በማባረር ወደ ኸሊፋዎቹ ግዛት የቀላቀለበት ዘመቻው ነው፡፡
አምር የግብጽን ዘመቻ (the conquest of Egypt) ያመነጨው በራሱ ነው ይባላል፡፡ በመሆኑም ኸሊፋ ዑመር ቢን ኸጣብ ሐሳቡን ተቃውመውት ነበር፡፡ የዑመር ተቃውሞ ዘመቻውን በመጥላት ሳይሆን “በተለያዩ ግንባሮች የተበተኑትን ወታደሮቻችንን በቶሎ አሰባስበን በዘመቻው እንዲሳተፉ ለማድረግ አንችልም” ከሚል የመነጨ ነው፡፡ ይሁንና አምር በወቅቱ በነበሩት ወታደሮች ብቻ ዘመቻውን በመጀመር ተጨማሪ ጦርን መጠባበቁን ነው የመረጠው፡፡
 
  አምር በ639 ዓ.ል በአራት ሺህ ወታደሮች የሲናይ በረሃን አቋረጠ፡፡ ሮማዊያንን በድንገተኛ ጥቃት በማራወጥ “ቢልቢስ” እና “ባቢሎን” በሚባሉት ስፍራዎች አሸነፋቸው (ይህቺ የግብጿ “ባቢሎን” የኢራቋ “ባቢሎን” አምሳያ እንድትሆን በሮማዊያን የተፈጠረች ናት)፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ ደግሞ በጥንቷ የኦኑ ከተማ (በፈረንጆች አጠራር Heliopolis) አጠገብ አሸነፋቸው፡፡ ከአንድ አመት በኋላ 12,000 ወታደሮች ከሶሪያ ሲመጡለትም አምር የዘመኑ የአፍሪቃ ታላቅ ከተማ የነበረችውን እስክንድርያን (አሌክሳንደሪያ) ለመያዝ ዘመተ፡፡ ሮማዊያን በከተማዋ ከሰማኒያ ሺህ የሚበልጥ ጦር የነበራቸው ቢሆንም ከነርሱ በአምስት እጥፍ በሚያንሰው የአምር ቢን ኣስ ጦር ድል ተመቱ፡፡ ግብጽም ሙሉ በሙሉ የሙስሊሞቹ ኺላፋ አካል ሆነች፡፡
ታዲያ አምር ግብፅን በአንድ ዓመት ውስጥ ለመያዝ የበቃው በጦር ሃይሉ ጥንካሬ ብቻ አልነበረም፡፡ በወቅቱ የግብጽ ክርስቲያኖች ከፍተኛ እርዳታ ስላደረጉለት ጭምር ነው ታላቁን ድል ለማጣጣም የበቃው፡፡ ክርስትያኖቹ አምርን የደገፉበት ምክንያት አለ፡፡
  ግብጻዊያን ክርስቲያኖች የሚያምኑበት የ“ተዋሕዶ” እምነት “ክርስቶስ የሁለት ባህሪ ባለቤት ነው” ከሚለው የሮማዊያን ክርስትና ይለያል፡፡ በዚህም ምክንያት ሮማዊያኑ የግብጽ ክርስቲያኖችን እንደ “መናፍቃን” ያዩዋቸው ነበር፡፡ ከቁስጥንጥንያ (የአሁኗ ኢስታንቡል) ተሹመው ግብጽን የሚገዙት እንደራሴዎችም የግብጽ ክርስትያኖች እምነታቸውን እንዲለውጡ ለማድረግ በልዩ ልዩ መንገዶች ይጨቁኗቸው ነበር፡፡ አንዳንዴም ፓትሪያኮቻቸውን እያሰሩ “እምነትህን ተው” እስከማለት ይደርሳሉ፡፡ አምር ቢን ኣስ ግብጽን ለመያዝ በሚዘምትበት ዘመን እንኳ የግብጽ ፓትሪያርክ የነበሩት “አቡነ ብንያም” (ቤንጃሚን) ከሀገር ተባረው ነበር፡፡ በመሆኑም ግብጻዊያኑ ከጭቆናው ለመገላገል ሲሉ አምር ቢን ኣስን በዘመቻው በእጅጉ ረድተዋል፡፡ (በነገራችን ላይ ከ5ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ ግብጽን ይገዟት የነበሩት ሮማዊያን መቀመጫውን በሮም ከተማ ያደረገው የታላቁ ኢምፓየር አካል አልነበሩም፡፡ የሮም ኢምፓየር በ395 “ምስራቅ” እና “ምዕራብ” ተብሎ ለሁለት ተከፍሏል፡፡ የሮማ ከተማ በ476 በጀርመን ጎሳዎች ስትወረር የምዕራቡ ኢምፓየር ህልውና አክትሟል፡፡ የምስራቁ ኢምፓየር ግን እስከ 1431 ድረስ ቆይቷል፡፡ ብዙዎች የምስራቁን ኢምፓየር የሚጠሩት “ቤዛንታይን” በሚል ስም ነው፡፡ ሆኖም ዐረቦችም ሆኑ የኢምፓየሩ ነዋሪዎች ግዛቱን “ሮም” እያሉ ስለሚጠሩት እኔም ይህንን ልማድ ተከትያለሁ)፡፡  

  አምር ግብጽን በሚያስተዳድርበት ጊዜ በክርስትያኖቹ ላይ ይደርስ የነበረውን ጭቆና ሙሉ በሙሉ አስወግዷል፡፡ በህዝቡ ላይ በየምክንያቱ ይጣሉ የነበሩትን ልዩ ልዩ የታክስ ዓይነቶች በማስቀረት ሁሉም ዜጎች ዓመታዊውን “ዑሽር” (አስራት) እና “ዘካት” ብቻ እንዲከፍሉ አድርጓል፡፡ በመንግሥቱ ቢሮክራሲ ውስጥም ክርስትያኖቹን አሳትፏል፡፡ የቤተ-ክርስቲያኖች ይዞታ የሆኑ መሬቶችና ንብረቶች እንዲከበሩም አድርጓል፡፡
       *****
 አምር ቢን ኣስ ግብጽን ማስተዳደር በጀመረ በዓመቱ ነው “አል-ፉስጣጥ” የተባለችውን ከተማ የቆረቆረው፡፡ ስለ“አል-ፉስጣጥ” ምስረታና ስለሌሎች ጉዳዮች በሚቀጥለው ክፍል እናወጋለን፡፡
አፈንዲ ሙተቂ
ህዳር 3/2007
ገለምሶ-ሀረርጌ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ፣ ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ በስንት ውጣ ውረድ ያገኙትን ሥልጣን ጥርሳቸውን ነክሰው ከያዙ ሁለት ዓመት ከሁለት ወርና 26 ቀን አስቆጥረዋል። በእነዚህ ወራት ውስጥም፡ ኃይለማርያም ሥልጣን የረገጡ ቀን ስለራሳቸው ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሰጡት ምስክርነትና ግምት ከዛሬው ኃይለማርያም በአያሌው የተለያዩ ናቸው። ገና መጀመሪያ ላይ ከመለስ ጀርባ ከጦር አዝማችነታቸው ወጥተው (በካድሬነታቸው) በሙቱ ማግሥት የሥልጣንን በር ሲይንኳኩ፣ […]

ከ250 አመታት በፊት ፣ 13 ኮሎኒዎች፣ ተብለው የሚታወቁት የአሜሪካ ግዛቶች በእንግሊዝ ሥር ነበሩ። አሜሪካኖቹ የግብር ጫና ስለበዛባቸው ለነጻነት መታገል ጀመሩ። በአሜሪካኖች እና በእንግሊዞች መካከል ጦርነት ተጀመረ። የአሜሪካኖች መሪ ጀነራል ጆርጅ ዋሺንግተን ነበሩ። እንግሊዞች ብዙ ጦር አሰልፈው ያመጹ አሜሪካዉያንን ለማስገበር ተንቀሳቀሱ። በኑዮርክ አሜሪካኖች ትልቅ ሽንፈት ደረሰባቸው። የእንግሊዝን ጦር መቋቋም አልቻሉም። ጆርጅ ዋሽንግተን፣ በሌሊትና በጉም ወደ 9 […]



አፈንዲ ሙተቂ
      —–
      የህንድ ፊልም ማየት የጀመርኩት በ1978 ይመስለኛል፡፡ በዘመኑ ቶማስ የሚባል የህንድ ክልስ ነበር፡፡ ይህ ሰው ፊልሞቹን ከድሬ ዳዋ ያስመጣና በሌሎች የሀረርጌ ከተሞች እያዞረ በፕሮጀክተር ያሳያል፡፡ በዘመኑ “የአሜሪካ ፊልም ውሸት ነው፤ የህንድ ፊልም እውነት ነው” የሚል አስተሳሰብ ስለነበረ የሰዎች ምርጫ በአብዛኛው የህንድ ፊልም ነበር፡፡ በመሆኑም ቶማስ ከሚያሳያቸው ፈልሞች መካከል ከመቶ ዘጠና የሚሆኑት የህንድ ፊልሞች ነበሩ፡፡ 
   በዚህም መሰረት ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት የህንድ ፊልም “T.D” የሚል ርዕስ የነበረው ሲሆን አክተሩም “ጄተንድራ” ነው (በኋላ ላይ እንደተረዳሁት ያ ፊልም First Blood  ከሚባለው የራምቦ ፊልም የተቀዳ ነው)፡፡ ቶማስ ፊልሙን የሚያሳየው በሁለት ብርና በሶስት ብር ነው፡፡ በቶማስ ሲኒማ ስር ካየኋቸው ሌሎች የህንድ ፊልሞች መካከል Disco Dancer, Jimmy and His Elephant, Mard የተሰኙት ይታወሱኛል፡፡  
        በ1981 የአውራጃችን አኢወማ ቪዲዮ ሲያስመጣ ግን የቶማስ ሲኒማ “በጣም ውድ ነው” በሚል ተረሳ፡፡ ቶማስም ወደኛ መምጣቱን ተወ፡፡ በዚህም መሰረት Mister India, Ashanti, Kassam Paeda, Love Story, የመሳሰሉ ፊልሞችን በአኢወማ አየን፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ “ፎቶ ማወርዲ” የሚባለው ፎቶ ቤት ሌላ ቪዲዮ ማሳያ ከፈተና ከአኢወማ ጋር ፉክክር ውስጥ ገቡ፡፡ ሁለቱም በርካታ ፊልሞችን አስኮመኮሙን፡፡ በፎቶ ማወርዲ ካየኋቸው ፊልሞች መካከል “Ter Kassam”, “Maa Kassam”, “Numberi Admi”, “Khoj”, “Marry Kassam”, “My Name is Lakan”, “Tarzan”, “Coolie”, የሚባሉትን ከነ ስሞቻቸው አስታውሳቸዋለሁ፡፡ የብዙዎቹን ስም ግን አላስታውስም፡፡
*****  *****  *****
        በህንድ ፊልሞች የምናውቃቸው አክተሮች በከተማችን በትክክለኛ ስማቸው አልነበረም የሚጠሩት፡፡ አንዳንዶቹ እኛ ባወጣንላቸው ስሞች ነው ይበልጥ የሚታወቁት፡፡ ለምሳሌ “ሚቱን ቻካርቦርቲ” የሚባለው አክተር “ጂሚ” በሚለው ስም ነው የሚታወቀው፡፡ “ዳርሜንድራም” በኛ አጠራር “ሻንካር” ነው የሚባለው፡፡ “ሪሽ ካፑር” ደግሞ “ኮጅ” እየተባለ ነው የሚጠራው፡፡ እውነተኛ ስሙ “ሰኒ” የሆነው አክተር ደግሞ በኛ አጠራር “ገባር” ነው የሚባለው፡፡ “አጄይ ኩማር”ም “ላቭ ስቶሪ” ተብሎ ነበር የሚጠራው፡፡ ከነዚህ ስሞች መካከል አንዳንዶቹ (እንደ “ጂሚ” እና “ሻንካር” ያሉት) አክተሩ ታዋቂ በሆነበት ፊልም ውስጥ ከሚጠራበት ስም ነው የተወሰዱት፡፡ እንደ “ኮጅ” እና “ላቭ ስቶሪ” የመሳሰሉት ደግሞ አክተሮቹ የተወኑባቸው ፊልሞች አርዕስት ናቸው፡፡    
        ከዚህ ሌላ አክተሩ በፊልሙ ውስጥ ሲያንጸባርቀው የነበረውን ድርጊት በመመልከት የተሰጡ ስሞችም አሉ፡፡ ለምሳሌ “አኒል ካፑር” የሚባለው አክተር በአንድ ፊልም ውስጥ ያለ ማቋረጥ “ማስቲካ” ያኝክ ስለነበረ “ማስቲካ” ተብሎ ተሰይሟል፡፡ “ቆሮንዴ” ደግሞ “Sholay” በተሰኘው የአሚታብ ባችቻን ፊልም ውስጥ በአፍ የሚታኘክ ትምባሆ ስለሚጠቀም ነው እንዲህ ተብሎ የተጠራው (“ቆሮንዴ” በአፍ የሚታኘክ የትምባሆ ዐይነት ነው)፡፡ እንደ ከማል ሐሰን፣ ነስሩዲን፣ አሚታብ ባችቻን፣ ሻሽ ካፑር፣ ጄክ ሸሪፍ፣ ጎቪንዳ፣ ሳንጃይ የመሳሰሉትን ግን በትክክለኛ ስማቸው ነው የምንጠራቸው፡፡
     ታዲያ በጣም ያስገረመኝ ይህ በኛ ከተማ የምንጠቀምበት የስም አጠራር ዘይቤ ድሬ ዳዋና ሀረርን ጨምሮ በሌሎች ከተሞችም በስፋት የሚታወቅ መሆኑ ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ ያደረግኩት ጥናት እንደሚያመለክተው ከስሞቹ መካከል አንዳንዶቹን እኛ መፍጠራችን ትክክል ቢሆንም ሌሎቹ ስሞች ከድሬ ዳዋ ልጆች የተኮረጁ ናቸው፡፡
      በድሮው ዘመን “አክተር” የምንለው በፊልሙ ውስጥ መልካም ስብዕና የሚያሳየውን ብቻ ነው፡፡ እኩይ ባህሪ ተላብሶ የሚተውነው በኛ ቋንቋ “ሙጅሪም” ነው የሚባለው፡፡ በአንደኛ ደረጃ ከሚነሱ ሙጅሪሞች መካከል “አሻንቲ”፣ “ሻክቲ”፣ “ጃሉ”፣ “ሼራ”፣ “ቆሮንዴ”፣ “ፋሩቅ” የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ (ፋሩቅ Disco Dancer በተሰኘው ዝነኛ የጂሚ ፊልም ውስጥ የተወነው ወፍራም ሙጅሪም ነው፤ አስታወሳችሁት አይደል?)፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ከሚመደቡ ሙጅሪሞች መካከል ደግሞ “ሳምሶን መላጣ” እና “መለኪያ” የተባሉት ይጠቀሳሉ:: እነዚህኛዎቹ ሙጅሪሞች በአብዛኛው በታላላቆቹ ሙጅሪሞች እየታዘዙ ጥፋት የሚፈጽሙ ናቸው፡፡ ከማል ሐሰንም ሲያሻው ከነዚህ ጋር ይደመርና ሙጅሪም ይሆናል፡፡
      በህንድ ፊልም ውስጥ ዘወትር የሚታይ ሶስተኛ አክተር አለ፡፡ ይህ ሰው በፊልሙ ውስጥ የሚሰጠው ሚና እንደ ቤተሰብ አጫዋች ሆኖ ሰዎችን ማሳቅ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አስቂኝ ገጸ-ባህሪ በያኔው አጠራር “ማህሙዴ” ይባላል፡፡ እጅግ ዝነኛ ከሆኑ ማህሙዴዎች መካከል “ሻክቲ” ተጠቃሽ ነው (“ሻክቲ” ሲፈልግ “ሙጅሪም”፤ ሲያሻው ደግሞ ማሕሙዴ ይሆናል)፡፡
*****  *****  *****
        የህንድ ፊልም ልዩ ገጽታው በርካታ ዘውጎችን አንድ ላይ የሚደበላልቅ መሆኑ ነው፡፡ የአክሽን ፊልም ውስጥ ኮሜዲ አለ፣ አስማት አለ፣ ሮማንስ አለ፤ ዳንስ አለ፤ በአንዱ ፊልም ውስጥ ሁሉም ነገር ይገኛል፡፡ ደግሞም አክተሮቹ ሲደንሱ ድምጻቸው አንድ ዓይነት መሆኑ በጣም ያደናግራል፡፡ የሴትም ሆነ የወንድ ድምጽ ለመለየት ያስቸግራል፡፡
      ከዚህ በተጨማሪ የህንድ ፊልም ውስጥ የሚታየው ግነት ከፍተኛ ነው፡፡ ለምሳሌ Mard በተሰኘው ፊልም ውስጥ አሚታብ ለመብረር የሚያኮበኩበውን ሂሊኮፕተር በገመድ ጠልፎ እንዳይበር ያደረገበት ትዕይንት ዘወትር አይረሳኝም፡፡ በልጅነታችን ያንን ትዕይንት እንደ ጉድ ነበር ያጨበጨብንለት፤ አሁን ቢሆን ግን “አንተ ውሸታም! ሞኝህን ፈልግ ” ብዬ ቪዲዮውን የምዘጋው ይመስለኛል፡፡
      የህንድ ፊልም ሲነሳ ዘወትር የሚታወሱኝ ሁለት ልጆች አሉ፡፡ አንደኛው ታገል ዲሪብሳ ይባላል፡፡ ሌላኛውን ልጅ ግን ስላላስፈቀድኩት ስሙን አልነግራችሁም፡፡ ታገል ምን አደረገ መሰላችሁ?.
     የጄተንድራን ፊልም እያየን ነበር፡፡ በፊልሙ መሀል ላይ ሻክቲ የተባለው ሙጅሪም የጄተንድራን እህት በመኪና ካሯሯጣት በኋላ ይገድላታል፡፡ ትዕይንቱ በጣም ያሳዝናል፡፡ በተለይ ልጅቷ በደም አበላ ተነክራ ላያት ሰው ልብ ትሰብራለች፡፡ ይሁን እንጂ ብዙዎቻችን ፊልም መሆኑን አልሳትንም፡፡ ታገል ግን ከመመሰጡ ብዛት የእውነት ትዕይንት መሰለው፡፡ እናም ጮክ ብሎ “ህግ የለም እንዴ?” አለ፡፡ በቪዲዮ ቤቱ የነበረው ሰው ሁሉ በሳቅ ፍርስ አለ፡፡
      የሁለተኛው ሰው ማስታወሻዬ ግን ከዚህ ይብሳል፡፡ በጊዜው ከነበሩት የሀብታም ልጆች ነን ባዮች መካከል አንዳንዶቹ የለየላቸው ጅላጅሎች ነበሩ፡፡ አሪፍ መኪና ሲያዩ “የዘመዳችን ናት” ማለት ይቀናቸዋል፡፡ “ነዋይ ደበበ ቤታችን ሊመጣ ነው” የሚሉም ነበሩ፡፡ እኛም ለነዚህ ጅሎች ነገር እያሟሟቅን ብራቸውን እናጫርሳቸው ነበር፡፡ ከነዚያ ልጆች አንዱ “አሚታብ ዘመዳችን ነው” እያለ ያወራልን ነበር፡፡ እኛም እያወቅን እንሞኝለታን:: አብዛኛውን ጊዜ የፊልም መግቢያ ዋጋውን የሚከፍልልን እርሱ ስለሆነ ለርሱ መሞኘታችን የግድ ነበር፡፡
      ታዲያ በብዙ ፊልሞች ውስጥ ሲሞት የማይታየው “ጀግናው” አሚታብ ባችቻን ሲያቀብጠው Sholay በተሰኘው ፊልም መጨረሻ ላይ ሞተ፡፡ ነገሩ በጭራሽ ያልተገመተ በመሆኑ ብዙዎች ተገረሙ፡፡ “ጉድ ነው! አሚታብም ይሞታል እንዴ?”… ተባባልን፡፡ እኛ እንዲህ ያልነው “አሚታብ ወክሎት የሚጫወተው ገጸ-ባህሪ ዘወትር አይሞትም” ከሚል መነሻ ነበር፡፡ ያ የኛ ስፖንሰር የሆነው ልጅ ግን እየየውን አቀለጠው፡፡ “ዘመዴ ሞቶ የት አባቴ ነው የምገባው?” እያለ አነባ፡፡ ፊልም ለመመልከት የሄደው ሰው ግራ ተጋባ፡፡ ለምን እንደሚያለቅስ ብንነግራቸው ሁላችንንም እንደ ጅል ይቆጥሩናል ብለን ፈራን፡፡ ስለዚህ ቶሎ ብለን ልጁን ደጋግፈን ወደ ውጪ ካወጣነው በኋላ እያባበልነው ከቤታቸው ወሰድነው፡፡
   ይህ ትዕይንት በአሁኑ ዘመን ይከሰታል ተብሎ የማይታሰብ ነው መቼስ! ከዛሬ ሀያ አመት በፊት ግን ተመሳሳይ ድርጊቶችን ማየት የተለመደ ነው፡፡
—–
      የህንድ ፊልም ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት በ1995 ይመስለኛል፡፡ በወቅቱ ያየሁት Kabi Ghushi Kabi Gham የሚል የሻህሩኽ ኻን እና አሚታብ ፊልምን ነው፡፡ ያየሁበት ስፍራ አዲስ አበባ በመሆኑ ግን እኛ ስናደርግ እንደነበረው “ማህሙዴ፣ ሙጅሪም፣ ወዘተ…” እያለ ስለ ፊልሙ የሚተርክ ሰው አላጋጠመኝም፡፡ ከዚያ ወዲህ እኔና የህንድ ፊልም አንተዋወቅም፡፡ ለመሆኑ አሁን ምን ደረጃ ላይ ደርሷል?… እስቲ ስለ ህንድ ፊልም ያላችሁን ትዝታችሁ አካፍሉን፡፡
ሰላም!
የካቲት 17/2006
ሸገር

IOM በሚል አህጽሮት የሚታወቀው አለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት በያዝነው ወር የሚያበቃው 2014 አም ግጭትን፣ የፖለቶካ ወከባንና የኢኮኖሚ ችግርን በመሸሽ ለሚሰደዱት ሰዎች አደገኛ አመት ሆኖ እንደቆየ አስታውቋል።

ታኀሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውሃ፣ የመስኖና የኢነርጂ ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ ህዳር 26 ቀን 2007፣ በቁጥር ውመአሚ 1/01/67 በጻፉት ደብዳቤ ” በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች በከፍተኛ ወጪ ተገንብተው ለበርካታ ኢንተርፕራይዞች የመስሪያና መሸጫ አገልግሎት የሚውሉ ህንጻዎችና ሼዶች በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ችግር ምክንያት ለታለመላቸው አላማ ለማዋል ” አልተቻለም ብለዋል። “በእነዚህ ማእከላት ውስጥም በከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ የገቡና …

ታኀሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው  የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ 10ሩም ተከሳሾች የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት  ቤት ቢቀርቡም ሌላ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ …

ታኀሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባንኩ እንደሚለው በርካታ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባቸው አገሮች ቅርንጫፎችን በመክፈት በአመት እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነውን፣ ከባንክ ውጭ የሚደረገውን ገንዘብ የማስተላለፍ ዘዴ ለመቆጣጠር አስቧል። አሜሪካ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስና ሳውድ አረቢያ በመጀመሪያው ዙር የንግድ ባንኮች ቅርንጫፎች ከሚከፈትባቸው አገራት ተርታ ተመድበዋል። ባንኮቹ መከፈታቸው ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው የሚልኩትን ገንዘብ ለመጨመር እንደሚረዳም …

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

የፖለቲካ እንቅስቃሴ፣ ሰላማዊም የትጥቅም፣ በባህሪው ትብብርን ይጠይቃል። ሕብረተሰብ በማሳትፍ የሚደረግ የትብብር ሥራ ነውና። የኢትዮጵያ ገዥ ጥምር ድርጅት አንድ አካል የኾነው ህወሓት የፈር ቀዳጅነት ሚናውን ወስዶ የዛሬ አርባ ዓመት በትግራይ በረኻዎች የትጥቅ ትግል ጀምሮ በሚያካሂድበት ጊዜ፣ “ተወዲቡ ብጽንዓት ዝተቓለሰ ይዕወት” (ሲተረጎም፣ ተደራጅቶ በጽናት የታገለ ለድል ይበቃል) የሚል መፎክር ከአነገባቸው መፎክሮች አንዱ ነበር። በነገራችን ላይ የህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥም ኢህአዴግ እንደ መንግስት ሀገር ሲመራ የተከተለው ህዝብን አደራጅቶ እና አስትፎ የመስራት ባህልም ከዚኽ መፎክር የተወረሰ ሳይኾን አይቀርም። ለዚህም ነው ኢህአዴግ ነጥሮ በመውጣት በትጥቅ ትግሉም ሀገር በመምራቱም ወቅት ውጤታማ ሊኾን የበቃው። አሁን በፖለቲካው ተደራጅተው ሳይደራጁም እየተንቀሳቀሱ ያሉ የተቃውሞ፣ ሕጋዊ የኾኑትም ያልኾኑትም በዋናነት የዚኽ የተባብሮ መስራት ድክመት ስላለባቸው ነው ለውጤት ያልበቁት። ሲጣመሩ፣ ሲቀናጁም ኾነ ሲያብሩ፣ የአብሮ መስራት ምክንያታቸው የመላው ህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ በፖሊሲ፣ ስትራቴጂ እና ፖለቲካዊ ፕሮግራም ነጥሮ የወጣ ፖለቲካዊ አቋም ይዘው መስዋእት ለመክፈል ተዘጋጅተው ሳይኾን በጥላቻ እና የስልጣን ጥም ብቻ መሰረት አድርገው ነው ወደ አንድ የሚሰባሰቡት። በዚኽ አካሔድ ደግሞ ጠብ የሚለ ውጤት አላገኙም። በተለይ ለመስዋዕትነቱ የሚመርጡት ሌላ አካል እንዲኾንላቸው ይፈልጋሉ። እነሱ በአቋራጭ ስልጣን ላይ ለመፈናጠጥ እንዲያስችላቸው። ከዚኽ አንጻር የሀገራችን ተቃዋሚዎች ትጥቅ ትግል አውጀው በሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩት እና በስመ አክቲቪዝም የሚከትሏቸው (ሁለቱንም መንገድ የሚያጣቅሱ ቡድኖች) እንዲኹም በሰላማዊ ሕጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱት በተደጋጋሚ የመተባበር እና ለህዝብ መስዋዕት የመኾን መሰረታዊ ባህሪ ስለሚጎድላቸው እና የስልጣን […]

ኢትዮጵያ ውስጥ የታሰሩ ጋዜጠኞች እና የአምደ መረብ ጸሓፍት ቁጥር ከአምናው በእጥፍ ማደጉን CPJ በሚል ምኅፃረ-ቃል የሚጠራዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ገለጠ። የCPJ የምሥራቅ አፍሪቃ ተወካይ ቶም ሮድስ ኢትዮጵያ ውስጥ ገዢው ፓርቲ ምርጫው ከመድረሱ አስቀድሞ ተቺዎች ድምፃቸው እንዳይሰማ እያፈናቸው መሆኑን ተናግረዋል።

«አርሶ አደሩ እያጉረመረመ ሲለዉ ከረመ፤ አርሶ በሌዉ መጣ ጠላ ሊጠጣ፤ አርሶ በሌዉ ካለ ምን ችግር አለ፤ አርሶ በሌዉ ጎፈር ማረስ መቆፈር፤ ላለዉ መንገዱን አለስልሶ ከርሞ ይመጣል ያልሞተ ሰዉ፤ እመቤቴ ያደረችበቱ እጣን ይሸታል መሬቱ» እያለ ሆ ይላል ያዜማል ፤ የኢትዮጵያ ገበሬ የዘራዉን ሰብል በታህሳስ ሲሰበስብ።

የሩስያ ማዕከላይ ባንክ የሀገሩ ገንዘብ «ሩብል» ዋጋ እያሽቆለቆለ የተገኘበትን ሁኔታ ለማከላከል በአሁኑ ጊዜ የሚቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ይገኛል፣ ይሁንና፣ የእስካሁኑ ጥረቱ አንድም የረባ ውጤት አላስገኘለትም። የሩብል መውደቅ ሩስያን ወደ ከፋው የኤኮኖሚ ቀውስ ወስጥ ይጥላት ይሆን?

የኤቦላ ተኀዋሲ በምዕራብ አፍሪቃ ፣ በተለይ በሶስቱ በበሽታው በጣም በተጠቁት ሀገራት፣ ላይቤርያ፣ ጊኒ እና ሲየራ ልዮን ላይ እያደረሰ ስላለው ማህበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ተፅዕኖ የተመድ በአፍሪቃ አዳራሽ ባካሄደው ጉባዔ ላይ ዝርዝር መግለጫ ሰጠ።

ኢትዮጵያ ውስጥ የታሰሩ ጋዜጠኞች እና የአምደ መረብ ጸሓፍት ቁጥር ከአምናው በእጥፍ ማደጉን CPJ በሚል ምኅፃረ-ቃል የሚጠራዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ገለጠ። የCPJ የምሥራቅ አፍሪቃ ተወካይ ቶም ሮድስ ኢትዮጵያ ውስጥ ገዢው ፓርቲ ምርጫው ከመድረሱ አስቀድሞ ተቺዎች ድምፃቸው እንዳይሰማ እያፈናቸው መሆኑን ተናግረዋል።

Image

በአዳር ሰልፍ ወቅት ተይዘው ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መአሕድ) ምክትል ፀኃፊ መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ ራሳቸውን ስተው ሆስፒታል እንደገቡና ሕይወታቸው አደጋ ውስጥ እንደሆነ የፓርቲው ፕሬዝደንት አቶ ሽዋንግዛው ገ/ስላሴ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ በአዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት ተይዘው ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው ሲሆን ለአምስት ቀናት ቀዝቃዛና ጨለማ ቤት ውስጥ ታስረው ቆይተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ የስኳር በሽታ መድሃኒታቸውን በመቀማታቸውና ህክምናም ባለማግኘታቸው ታመው እንደነበር ለማወቅ መገለጹ ይታወሳል፡፡

መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ በድብደባውና በስኳር በሽታ ምክንያት በአሁኑ ወቅት ዘውዲቱ ሆስፒታል የሚገኙ ሲሆን ሆስፒታል ከገቡበት ቅዳሜ ታህሳስ 4/2007 ዓ.ም ጀምሮ ሰው ማናገር አለመቻላቸውን የፓርቲው ፕሬዝዳንት አክለው ገልጸዋል፡፡

Image
የሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ አቶ እያስፔድ ተስፋዬ ከሚሰራበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአዳር ሰላማዊ ሰልፉን ተከትሎ በደረሰበት እስር ምክንያት ከስራው ታገደ፡፡ እያስፔድ ተስፋዬ በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ጨለማና ቀዝቃዛ ክፍል ታስረው ከነበሩት አመራሮች መካከል አንዱ ሲሆን ከእስር ከተፈታ በኋላ ታስሮ ስለመቆየቱ ማስረጃ ቢወስድም ለ15 ቀን ከስራ ታግዶ እንዲቆይ ተደርጓል፡፡

‹‹ታስሬ መቆየቴን የሚያሳይ ማስረጃ ወደምሰራበት ቅርንጫፍ ስወስድ ከእኛ አቅም በላይ ስለሆነ ወደ ዲስትሪክት ውሰድ ተባልኩ፡፡ ዲስትሪክት ስወስድ የንግድ ባንክ ዳይሬክተር የሰው ኃይል አስተዳደር ማመልከቻና ታስረህ የቆየህበትን ማስረጃ አስገባና እነሱ ወደ ስራ ገበታህ ተመለስ ካሉህ ነው የምትመለስ፤ እነሱ ተመለስ እስኪሉህ ድረስ ግን ወደ ስራ ገበታ መመለስ አትችልም አሉኝ፡፡ ባሉኝ መሰረትም ለሰው ኃይል አስተዳደር ደብዳቤና ከፖሊስ ጣቢያ የተሰጠህን ማስረጃ ወሰድኩ፡፡ እሱ እስኪያየው ድረስ ተብሎ አንድ ቀን ቀጠሮ ተሰጠኝ›› የሚለው እያስፔድ በቀጠሮው መሰረት ሲሄድ ጉዳዩ ለቅሬታ ሰሚ ኮሜቴ እንደተላከ፣ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባሎች ስልጣና ላይ በመሆናቸው ለ15 ቀን ስራ መግባት እንደማይችልና ለታገደበት ቀናትም ደመወዝም እንደማይከፈል እንደተገለጸለት ለነገረ ኢትዮጵያ አስረድቷል፡፡

ቀደም ሲል የሰላማዊ ሰልፉን ተከትሎ አቶ ወሮታው ዋሴ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተባረሩ መሆናቸው ይታወሳል፡፡

Image

በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮችን ጨምሮ 10ሩም ተከሳሾች ለታህሳስ 15 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ተከሳሾቹ የክስ መቃወሚያ አቅርበዋል

ዛሬ ታህሳስ 9 ቀን 2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት የቀረቡት የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም አንደኛ ተከሳሽን ጨምሮ ስድስት ተከሳሾች በጠበቆቻቸው አማካኝነት የክስ መቃወሚያቸውን ይዘው ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

ሆኖም ግን 7ተኛ ተከሳሽ አቶ አብርሃም ሰለሞን የሰጠው የተከሳሽነት ቃል ከክሱ ጋር ተያይዞ ለጠበቃው አለመቅረቡን ተከትሎ ጠበቃው የክስ መቃወሚያ ለማዘጋጀት ባለመቻላቸው የተከሳሽ ቃልን የያዘውን ዶክሜንት ከጽ/ቤት ወስደው መቃወሚያቸውን እንዲያስገቡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን የክስ መቃወሚያ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለታህሳስ 15 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ተከሳሾች በእስር ላይ ባሉበት ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሊጎበኟቸው የሚሄዱ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው ወደ እስር ቤቱ ሲገቡ በተለየ መዝገብ እንዲመዘገቡ እየተደረጉ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡ ተከሳሾች ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዱት ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው በተለየ መዝገብ በመመዝገባቸው ከሌላው በተለየ ማሸማቀቅ እየተፈጸመባቸው ነው፡፡

ይህን በተመለከተ ለማረሚያ ቤቱ አቤት ቢሉም ሊሻሻል አለመቻሉን ተከሳሾቹ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ለማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም አቤቱታቸውን ተቀብሎ በቀጣይ ቀጠሮ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ስለጉዳዩ ቀርቦ እንዲያስረዳ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ሃገሪቱን የሚያሰጋት የሃይማኖት አክራሪነት/አሸባሪነት ሳይሆን የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አሸባሪነት ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ነው:: ጥላችሁን እንዳታምኑ እየተባለ ሃይማኖት መንግሥታዊ ቅርጽ ይዞ እንዲወጣ ለማድረግ መሞከር አክራሪነት ነው፡፡

«መጾም፣ መጸለይ፣ ሥርዓተ-አምልኮን መፈጸም ሃይማኖታዊ አልባሳትን መልበስ ለሃይማኖቱ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንጂ አክራሪነት ሊባል አይችልም፤»…የአክራሪ ክርስትና ወይንም እስልምና ቡድን መኖር የክርስትና እና እስልምና ተከታዮችን በሙሉ «አክራሪ» አስብሎ ሊያስፈርጃቸው አይችልም::አክራሪ ተብሎ የሚፈረጀው የሚራመዱ የፖለቲካ ጡዘቶች በሰዎች ላይ ሌላ እምነትን በመጫን በግዳጅ እና በሃይል ሊያስገድዱ ሲሞክሩ ይህ ማለት አህበሽን እና ተሃድሶን በጥንታውያኑ እስልምና እና ተዋህዶ ላይ በኢትዮጵያ እንደተሞከረው ማለት ነው::

አክራሪነት አሉታዊ ትርጉም ሲኖረው የራስን እምነትና አመለካከት በሌሎች ላይለመጫን መሞከር ነው፡፡ ሃይማኖት መንግሥታዊ ቅርጽ ይዞ እንዲወጣ ለማድረግ መሞከር ራሱ አክራሪነት ነው፡፡ አክራሪነት የፖሊቲካ ገጽታ ያለው ነው፡፡ ኾኖም ግን ሃይማኖትን ማጥበቅ አክራሪነት አይደለም፡፡ሃይማኖት ፍጹም እውነታን በፍጹም እምነት ስለሚቀበል ከሌሎች ግላዊ አስተሳሰቦች የተለየ ነው፡፡ የሃይማኖት መገለጫዎችን መጠቀም የዚያን ሃይማኖት ጥልቀት የሚያሳይ እንጂ እንደ ችግርም የሚወሰድ ወይም አክራሪነት ሊኾን አይችልም፡፡ «መጾም፣ መጸለይ፣ ሥርዓተአምልኮን መፈጸም ሃይማኖታዊ አልባሳትን መልበስ ለሃይማኖቱ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንጂ አክራሪነት ሊባልአይችልም፤» ይላሉ የዘርፉ ምሁራን፡፡

የአክራሪነትና የአጥባቂነት ፅንሰ ሐሶቦች በጥሩ ኹኔታ ተለይተው ተገልጸዋል፡፡ አንዳንድ ሰነዶች ወያኔም ለይስሙላ የገለበጣቸው ሰነዶቹ አክራሪነትንና አጥባቂነትን በአግባቡ ለይተውና ተንትነው ያስቀምጣሉ፡፡ በዚሁ መሠረት አጥባቂነትን፣ ‹‹የግል ሃይማኖትን ሃይማኖቱ በሚያዘው መሠረት ሳይንጠባጠብ ሁሉንም ትእዛዛት መፈጸም ነው፤» በማለት ሲፈታው አክራሪነትን ደግሞ፣ «ከራስ እምነት ወጥቶ ሌላውን መተንኮስና የሌሎችን ሃይማኖት መኖር አለማመንና አለመፍቀድወይም ሌሎቹን አስገድዶ የራስ እምነት ተከታዮች ለማድረግ መጣር ነው፤» ይላል፡፡ በተግባር ላይ አለመዋሉ እና በጣልቃ ገብነት መተርጎሙ ጉዳት አመጣ እንጂ::

ከዚህ ብያኔ ስንነሣ ክርስቲያንም ሆነ ሙስሊም ከርሱ ውጭ የኾኑትን የሌሎቹን መኖር የማይቀበልና ከግለሰቦቹ ፈቃድ ውጭ አስገዳጅ እስከኾነ ድረስ እርሱን አክራሪ ማለት ይቻላል፡፡መብትን መጠየቅ ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት መሸሽ አክራሪነት አይደለም:: በዚህ መልኩ አክራሪው ይህንኑ ድርጊት ሊፈጽም የተነሣውን ቡድን ብቻ እንጂ «አክራሪው ቡድን» የወጣበትን/የተገኘበትን ቤተ እምነት ሊወክል አይችልም፡፡ ስለዚህ በአለማቀፍ ደረጃ የአክራሪ ክርስትና እና እስልምና ቡድን መኖር የክርስትና እና እስልምና ተከታዮችን በሙሉ «አክራሪ» አስብሎ ሊያስፈርጃቸው አይችልም፤ ለሌላው ቤተ እምነትም እንዲሁ፡፡ ሃገሪቱን የሚያሰጋት የሃይማኖት አክራሪነት ሳይሆን የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አሸባሪነት ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ነው:: #ምንሊክሳልሳዊ

(ይህ የግሌ አስተያየት ነው!)

ምርጫ ካልተገባ ሌላኛው አማራጭ ትጥቅ ትግል ብቻ ነው ያለው ማነው? ሲጀመርስ ምርጫ የዲሞክራሲ መገለጫ ነው እንጂ ከመቼ ወዲህ ነው የሰላማዊ ትግል አካል ሊሆን የሚችለው፡፡ ሰላማዊ ትግል ዲሞክራሲ በሌለበት የሚደረግ ትግል ከሆነ ዘንዳ የዴሞክራሲ መገለጫ የሆነው ምርጫ ሰላማዊ ትግል ነው ማለትስ ምን ማለት ነው?

ሰላማዊ ትግል እኮ ሰላማዊ ትግል ያስባለው መሳሪያ የሚያስነሳ ጭቆና መኖሩ ነው፡፡
ግልፅ በሆነ መንገድ ለማስቀመጥ
በምርጫ የሚደረግ ትግል ህዝቡ የስልጣኑ ባለቤት በሆነበት ሀገር እንጂ ሁሉም ነገር በአገዛዙ መዳፍ ስር በሆነበት ሁናቴ አይደለም፡፡

ሰላማዊ ትግል ዲሞክራሲ ጨርሶውኑ በሌለበትና እየሞቱ ማሸነፍ ግድ የሆነበት የትግል አካሄድ ነው፡፡
የትጥቅ ትግልም ዲሞክራሲ ፈፅሞ በሌለበት ሀገር ውስጥ እየገደሉም እየሞቱም ለማሸነፍ የሚደረግ ትግል ነው፡፡

ከዚህ በመነሳት
1- አሁን ባለንበት ሁናቴ ምርጫ ማካሄድ የዴሞክራሲ ሂደት ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ማለት ሲሆን
2- ኢህአዲግን በፈቃዳችን እንደ መንግሰት እውቅና መስጠት ነው

ስለዚህ፡- ትግሉ ሰለማዊ ትግል ነው የምንለው ምርጫ ማድረግ የሚቻልበትን ምህዳር መፍጠር፤ ህዝቡን የስልጣኑ ባለቤት ማድረግ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ በመሁኑ ነው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ማቸውንም የፖለቲካ ስራ በነፃነት መስራት በማይቻልበት ሁናቴ ነፃነት እንዲኖር መታገል ከሁሉ በፊት መሆን ያለበት ትግል ነው፡፡ ይህ ትግል በባህሪይው እልህ አስጨራሽ፣ ተስፋ አስቆራጭ፣ ብዙ ዋጋ የሚያስከፍል … ፍሬው ግን ዘላቂና እጅግ አስደሳች ነው፡፡ ለዛ ነው ደጋግመን ህይወታችንንም ቢሆን እስከመስጠት ድረስ ፍፁም ሰላማዊ ሆነን እንታገላለን የምንለው፡፡

ሰለማዊ ትግል ከነፍጥ ትግል የሚለየውም በዚሁ ባህሪይው ነው፡፡ በመውደቅ በመነሳት ውስጥ ማሸነፍ፤ ሳይገድሉ በመሞት ማሸነፍ፡፡ ይህ መንገድ በምርጫ ከሚደረግ የስልጣን ትግልም ሆነ መሳሪያ አንስተው በሀይል ስልጣን ለመያዝ ከሚደረግ ትግል ፍፁም የተለየ ነው፡፡ ነፃነት ትግል ይፈልጋል፡፡ ፍፁም ሰላማዊ ሆነን እናሸንፋለን!
Image

ሃገሪቱን የሚያሰጋት የሃይማኖት አክራሪነት/አሸባሪነት ሳይሆን የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አሸባሪነት ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ነው:: ጥላችሁን እንዳታምኑ እየተባለ ሃይማኖት መንግሥታዊ ቅርጽ ይዞ እንዲወጣ ለማድረግ መሞከር አክራሪነት ነው፡፡ «መጾም፣ መጸለይ፣ ሥርዓተ-አምልኮን መፈጸም ሃይማኖታዊ አልባሳትን መልበስ ለሃይማኖቱ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንጂ አክራሪነት ሊባል አይችልም፤»…የአክራሪ ክርስትና ወይንም እስልምና ቡድን መኖር የክርስትና እና እስልምና ተከታዮችን በሙሉ «አክራሪ» አስብሎ ሊያስፈርጃቸው አይችልም::አክራሪ ተብሎ […]


ጸሓፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
  ዛሬ በወግ ሽርሽር ብዙ ሀገር አቋርጠን “ፋርስ” ገብተናል፡፡ የዑመር ኻያም ሀገር! የፊርደውሲ ሀገር! የኒዛሚ ሀገር! የጃሚ ሀገር! የሓፊዝ ሀገር! በሩባኢያትና በገዛላት ዓለምን እያስፈነደቁ ለብዙ ክፍለ ዘመናት የዘለቁ የቅኔ ጠቢባን የተገኙባት ምድር!
  
   ዛሬ ፐርሺያ ነን! ዛሬ ኢራን ነን፡፡ ዛሬ ቴህራን ነን፡፡ ዛሬ ኒሻፑር ነን፡፡ ዛሬ ጠብሪዝ ነን፡፡ ዛሬ ሂልማንድ ነን፡፡ ዛሬ ኢስፋሓን ነን፡፡ ዛሬ ሺራዝ ነን! እዚያ ትልቅ የጥበብ ድግስ ተደግሶ ይጠብቀናል፡፡ እዚያ ከመድረሳችን በፊት ግን ለውዲቷ ኢራን ይህንን “ሩበእ” ብንቀኝላትስ?!  
አንቺ ሀገረ-ፋርስ የሀገር ጥበበኛ
ሁሉንም ያበቀልሽ አድርገሽ መልከኛ
የቅኔሽ መዓዛ ጠርቶኝ መጥቻለሁ
እጅሽን ዘርግተሸ መርሓባ በይኛ!
ሞክሬዋለሁ አይደል?. አዎን! “ሩበእ” (ሩባኢያት) ማለት እንዲህ ነው፡፡ ባለ አራት መስመር ቅኔ ሆኖ ሶስተኛው ስንኝ ከሌሎቹ አፈንግጦ ሲጻፍ በፋርሲ ቋንቋ “ሩበእ” ይባላል (ከዐረብኛው “ራቢዕ” የተገኘ ቃል ነው)፡፡ አንደኛ፣ ሁለተኛ እና አራተኛ መስመሮች በተመሳሳይ ፊደል ነው የሚያበቁት፡፡ ሶስተኛው ስንኝ ግን ከነርሱ ጋር አይገጣጠምም፡፡ “ሩበእ” ነጠላ ስም ነው፡፡ ለብዙ ቁጥር “ሩባኢያት” ይሆናል፡፡ አንዳንዶች የግጥሙ ዘውግ ከዐረቢያ ነው የተወረሰው ቢሉም “ሩባኢያት” ኦሪጂናሌ የኢራን የግጥም ዘይቤ መሆኑ በምሁራን ተረጋግጧል፡፡
ኢራናዊያን በሩባኢያት በጣም ይኮሩበታል፡፡ እንደ ብሄራዊ ቅርሳቸው ያዩታል፡፡ በተለይ The Zenith of Persian Literature በሚባለው ዘመን (ከ950 እስከ 1400 ድረስ) የተጻፉ ሩባኢያቶችን ከልብ ያፈቅሩአቸዋል፡፡ እኛም እንደ ዕድል ሆኖ በተስፋዬ ገሠሠ በኩል የዑመር ኻያም ሩባኢያትን በአማርኛ ለማንበብ በቅተናል፡፡ ዳሩ ግን እኛ ካጣጣምናቸው ሩባኢያት በላይ በኢራናዊያን የሚወደዱት የነ ሩሚ፣ ሳዲ፣ ጃሚ እና ሓፊዝ “ሩባኢያ”ት ናቸው፡፡ (ኢራናዊያን ከዑመር ኻያም በጣም የሚያደንቁለት የሒሳብ ሊቅነቱን ነው እንጂ ገጣሚነቱን አይደለም)፡፡
*****
ኢራን ነፍስ የሆነች ሀገር ናት! በጣም ውብ ባህልና የዳበረ ቋንቋ አላት፡፡ ታሪኳም ከቅድመ ክርስቶስ በፊት ከነበረው ዘመን ጀምሮ ነው የሚሰላው፡፡ በዚህ ረገድ ከመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት በእድሜ እርሷን የሚቀድሙት የርሷ ጎረቤት ሀገራት የሆኑት ሜሶጶጣሚያ (ኢራቅ) እና ሶሪያ ብቻ ናቸው፡፡ ዓለምን ያስደመሙ ታላላቅ ባለቅኔዎችን በማብቀል ግን ኢራን ከሁሉም ሀገራት ትበልጣለች፡፡
ኢራን ከጥንትም ጀምሮ ትክክለኛ ስሟ “ኢራን” ነው፡፡ የርሷ ተወላጆች ሀገራቸውን በዚሁ ስም ነው የሚጠሯት፡፡ ነገር ግን አብዛኛው የዓለም ህዝብ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ “ፋርስ” ወይንም “ፐርሺያ” ይላት ነበር፡፡ ኢራናዊያኑ “ይህ ስም አንዱን ክፍለ ሀገር እንጂ ሀገሪቱን በሙሉ ስለማይወክል ሀገራችንን ፐርሺያ እንዳትሏት” የሚል ዘመቻ ከፍተው ተሳክቶላቸዋል፡፡ ዛሬ ይኸው ኢራን ትባላለች፡፡ ይሁንና ቋንቋው “ፋርሲ” ነው የሚባለው፡፡ በዚህ ላይ ኢራዊያኑ ተቃውሞ የላቸውም፡፡ እንግዲህ በዚህ የፋርሲ ቋንቋ ነበር እነዚያ ውድ ባለቅኔዎች ዓለምን በጥበብ ሲያጠምቁ የነበሩት፡፡
*****
   የጥንቷ ኢራን እንዲህ እንደ አሁኑ አልነበረችም፡፡ ዛሬ አፍጋኒስታን፣ ቱርክሜኒስታን እና አዘርባይጃን የሚባሉ ሀገራት ለብዙ ክፍለ ዘመናት የርሷ ግዛቶች ነበሩ፡፡ የዛሬው እንግዳችንም በአሁኗ አፍጋኒስታን፣ በበልኽ አውራጃ፣ “ሩማ” በምትባል ከተማ ነው የተወለደው፡፡ እውነተኛ ስሙ ጀላሉዲን ሙሐመድ ወለድ ነው፡፡ ብዙዎች እርሱን የሚጠሩት ግን በትውልድ ከተማው ስም “ሩሚ” በማለት ነው፡፡
የሩሚ አባት የታወቁ ሼኽ እና ቃዲ ነበሩ፡፡ ሩሚም መደበኛ ትምህርቱን እዚያው በአባቱ ስር መማር ጀመረ፡፡ ነገር ግን በአስራ አንድ ዓመቱ መጥፎ እጣ ገጠመው፡፡ በዘመኑ መካከለኛው እስያን ደም በደም አድርገው የነበሩት የሞንጎል ወራሪዎች ወደ “በልኽ” እየተቃረቡ መሆናቸው ተሰማ፡፡ ስለዚህ የሩሚ አባት ቤተሰቡን ይዞ በምዕራብ አቅጣጫ ተሰደደ፡፡ “ኒሻፑር” ከምትባለው ጥንታዊት የኢራን ከተማ ሲደርሱም ከዘመኑ ዝነኛ ገጣሚ ፈሪዱዲን አጣር ጋር ተገናኙ፡፡ አጣር በሩሚ ነገሮችን የማስተዋል ችሎታ ተደንቆ “ይህ ልጅ ለወደፊቱ ትልቅ ባለቅኔ የመሆን ተስፋ አለው” የሚል ትንቢት ተናገረ ይባላል፡፡
ከሞንጎል የሸሸው የሼኽ ሙሐመድ ባሀኡዲን ወለድ (የሩሚ አባት) ቤተሰብ በመጨረሻ “ኮኒያ” ከምትባለው የቱርክ ከተማ ደረሰ፡፡ ሼኽ ባሃኡዲን እዚያ ካለው መድረሳ ማስተማር ጀመሩ፡፡ እርሳቸው ከሞቱ በኋላ ደግሞ የማስተማሩ ተግባር አንጋፋ ልጃቸው ለሆነው ለሩሚ ተላለፈ፡፡ ይሁንና ልጁ በማስተማሩ ላይ ሊያተኩር አልቻለም፡፡ ተፈጥሮንና ኑሮን እያየ ይህንን ግልብጥብጥ ዓለም የፈጠረውን ፈጣሪ አፈቀረ፡፡ ለርሱ የሙገሳ ቃላትን በግጥም መደርደር ጀመረ፡፡ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ግን አንድ ያልተጠበቀ እንግዳ ወደ ሩሚ መንደር ብቅ አለ፡፡
ሙላህ ሸምሱዲን ይባላል፡፡ የጠብሪዝ ተወላጅ ነው፡፡ ኢራናዊያን “ሸምስ-ኢ-ጠብሪዚ” ይሉታል፡፡ ሩሚ በሸምሱ-ጠበሪዝ ላይ ባየው መንፈሳዊ ልቅና ተመሰጠ፡፡ እንደ መምህሩም ቆጠረው፡፡ ቤተሰቡንና ስራውን ሁሉ ትቶ ከርሱ ጥበብን መቅሰም ጀመረ፡፡ አንድ ቀን ግን ሸምስ ጠብሪዝ እዚህ ነኝ ሳይል ጠፋ፡፡ በዚህም የተነሳ ሩሚ የመምህሩን ፍቅር ተራበ፡፡ ፍቅሩ እያቃጠለው “መደድ” (የፍቅር የመጨረሻ ደረጃ) ውስጥ አስገባው፡፡  ከዚያማ ማን ይቻለው! ከመምህሩ የተማረውን በራሱ ቋንቋ ጻፈው፡፡ 30,000 “ገዛል” እና ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ “ሩባኢያት”ን ከተበ፡፡ እነዚህም ግጥሞች “ዲዋን-ኢ-ሸምሹ-ጠብሪዝ” በተሰኘ መጽሐፍ በአንድ ላይ ተሰበሰቡ (“ገዛል” የሚባለው ግጥም “ዜማ” ጭምር እንዳለው ልብ በሉ)፡፡
*****
የሩሚ የጥበብ ፍቅር አላበቃም፡፡ በሸምስ ጠበሪዝ መጥፋት የተከፋችው ነፍስ ሌላ መምህር ፍለጋ አላቆመችም፡፡ ታዲያ ሩሚ ብዙም አልተጓዘም እዚያው “ኮኒያ” ከተማ ውስጥ ተማሪው የነበረ ልጅ መምህሩ ሆኖ ተገኘ፡፡
 ሑሳሙዲን ይባላል፡፡፡ ሑሳሙዲን ከሩሚ ግጥሞች ሌላ የነ ፈሪዱዲን አጣርን፣ የነ ሰነኢንና የሌሎች ታላላቅ የፋርስ ባለቅኔዎችን ስራ አጥንቷል፡፡ እናም አንድ ቀን ሩሚን እንዲህ አለው፡፡ “መምህር! የርስዎ ግጥሞች ጉድለት ይታይባቸዋል፤ የራስዎትን ስሜት ብቻ እየተከተሉ ስለሚጽፉ በሌላው ውስጥ ጠልቆ የመግባት ሀይል ያጥራቸዋል፤ ለምን እንደ አጣርና እንደ ሰነኢ አይጽፉም” አለው፡፡
 ሩሚም “እስቲ እንዴት አድርጌ ልጻፍ?” በማለት ጠየቀው፡፡
 ሑሳሙዲንም “ከልዩ ልዩ ምንጮች የተገኙ እውነተኛ ታሪኮችን፣ ተረቶችን፣ ምሳሌዎችን፣ ተምሳሌቶችን፣ ወዘተ… እያሰናሰሉ ቢቀላቅሉባቸውና የግጥሞቹ አካላት ቢያደርጓቸው የምን ጊዜም ተወዳጅ ይሆናሉ” ብሎ መለሰለት፡፡
 የሑሳሙዲን ምክር በሩሚ ልብ ውስጥ ጠልቆ ገባ፡፡ ከዚያም ቅኔ ሲመጣለት መቀኘት ጀመረ፡፡ ሑሳሙዲንም ከሩሚ አንደበት የሚወጣውን መጻፉን ተያያዘው፡፡ ሁለቱ ሰዎች እንዲህ እያደረጉ ዛሬ ዓለም በሙሉ የሚደመምበትን “መስነቪ”ን አስገኙ (የመጽሐፉ ትክክለኛ ስም “መሥነዊ” ነበር፤ ይህም “መሥን” ከተሰኘው የዐረብኛ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ነገር ግን የ“ሠ” እና የ“ወ” ድምጾች በፋርሲ ቋንቋ ውስጥ ስለሌሉ ኢራናዊያን “መስነቪ” እያሉ ይጠሩታል፤ የዓለም ህዝብም የነርሱን ፈለግ በመከተል “መስነቪ” ይለዋል)፡፡
*****
ሩሚ “መስነቪ”ን የደረሰው ከዛሬ 800 ዓመት በፊት ነው፡፡ ይሁንና ዛሬም ድረስ የህዝብ ፍቅር ሳይነፈገው እንደተወደደ አለ፡፡ በዘመናችን “ሩሚ”ን እጅግ ተነባቢ ከሆኑ አስር ምርጥ ገጣሚዎች ተርታ ያሰለፈውም “መስነቪ” ነው፡፡ ይህ ዝነኛ የግጥም ድርሳን ለዓለም ስነ-ጽሑፍ መዳበር ያደረገውን አስተዋጽኦ በመመዘን የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት የአውሮፓዊያኑ 2007 በዓለም አቀፍ ደረጃ የሩሚ ዓመት ተብሎ እንዲጠራ ወስኗል፡፡ በዚያው ዓመት ሩሚ የተወለደበት ስምንት መቶኛ ዓመት ተከብሯል፡፡
የመስነቪ ይዘት ሰፊ ነው፡፡ የሰውን ልጅ አዕምሮ ያመራምራል፡፡ በዚህ ትንሽ መጣጥፍ ስለርሱ ብዙ ማውራት አይቻልም፡፡ ዳሩ ግን ከመስነቪ የተቀዳ አንድ ውብ ታሪክ ላካፍላችሁ እችላለሁ፡፡ ሩሚ ታሪኩን በግጥም ነው የጻፈው፡፡ ነገር ግን ተርጓሚው በስድ-ንባብ መልሶ ጽፎታል፡፡ እኔም በስድ ንባብ የተጻፈውን ታሪክ ነው የምጋብዛችሁ፡፡
===አራቱ ሰዎችና መንገደኛው===
  አራት ሰዎች ነበሩ፡፡ እነዚያም ሰዎች ግሪክ፣ ፋርሲ (ኢራናዊ)፣ ዐረብ እና ቱርክ ነበሩ፡፡ የሚፈልጉትን ነገር ይገዙበትም ዘንድ የተወሰነ ገንዘብ ተሰጣቸው፡፡ ግሪኩ “እኔ ስታፊል አምሮኛል፤ ስታፊል ግዙልንና እንብላው” አለ፡፡
ፋርሲው “የምን ስታፊል? ኡዙም ግዙልን እንጂ ሰዎች” አለ፡፡
ዐረቡ “አረ ወደዚያ! ኢነብ ነው የምንገዛው፤ ኢነብ መግዛት አለብን” በማለት ተናገረ፡፡
ቱርኩ “እንዴ! አንጉር ነው መግዛት ያለብን፤ አንጉር እንጂ ሌላ ነገር አትግዙብን” አለ፡፡
    አራቱ ሰዎች ተከራከሩ፡፡ ተነታረኩ፡፡ በጭራሽ ሊግባቡ አልቻሉም፡፡ እንዲህ እየተወዛገቡ ሳለም አንድ መንገደኛ መጣ፡፡ “ምንድነው የሚያጨቃጭቃችሁ?” በማለት ጠየቃቸው፡፡ ጉዳዩን ነገሩት፡፡ ሰውየውም “በዚህ ፍራንክ የሁላችሁንም ፍላጎት ማሟላት ይቻላል” አላቸው፡፡ ሰዎቹም “እንዴት?” በማለት ጠየቁት፡፡ ሰውዬም ገንዘቡን እንዲሰጡት ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም እንደተባለው አደረጉ፡፡
መንገደኛው ሰውዬ በአካባቢው ከነበረ የፍራፍሬ መሸጫ ገብቶ አንዱን የፍራፍሬ ዓይነት ገዝቶ ሲወጣ አራቱ ሰዎች ተያዩ፡፡ በዚያው በሳቅ ፈረሱ፡፡ ለካስ አራቱም የአንዱን ፈራፍሬ ስም በየቋንቋቸው እየጠሩት ነበር? አራቱም “ወይን እፈልጋለሁ” እያሉ ነበር የሚከራከሩት::
*****
የታሪኩን “ማዕና” (መልዕክት) አገኛችሁት አይደል? ለኛም እንደ መንገደኛው ሰውዬ ያለ አስታራቂ ይላክልን፡፡ አንድ ውጥንና ግብ ያላቸው ሰዎች ዕድሜ ልካቸውን በአተገባበር ላይ ሲጣሉ ማየትን የመሰለ አሰቃቂ ህመም የለም፡፡ ሁሉም እይታውን ቢያስተካክል መግባባት ይቻላል፡፡ ሩሚ ይህንን ነው የመከረን፡፡
ብራቮ ጀላሉዲን ሩሚ! ብራቮ መሥነቪ!
*****
የካቲት 24/2006
*****
Afendi Muteki is a researcher and author of the ethnography and history with special focus on the peoples of East Ethiopia. You may follow him on his blog and his facebook page by clicking the following links

ኢትዮጵያ ውስጥ በልማትና አገልግሎት ላይ የተሠማሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ዕድገት ሲያሳዩ በመብቶች ጉዳዮች ላይ ሲሠሩ የነበሩት ግን መዳከማቸውን አንድ ጥናት አመልክቷል፡፡

በሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች አማካይነት በዚህ ዓመት ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል፡፡

ወደ 20 ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን ተጠቃሚ ሆነዋል – ተብሎም ተገምቷል፡፡
የዘገባውን ዝርዝር ከዚህ ያድምጡ፤

 

ሕዝብን ያላስከተለ ትግል ዉጤት አያመጣም – ግርማ ካሳ

“ምርጫው ላይ ለመሳተፍ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠናል።በምርጫው ልንሳተፍም ሆነ ላንሳተፍ ውሳኔ የምናሳልፈው እኛ ሳንሆን ሂደቱ ነው” ብለዋል። ” እኛ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጥነው ምርጫ ላይ ሳይሆን የምርጫ ሂደቱ ላይ ነው” ሲሉ ደግሞ አቶ ግርማ በቀለ የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፀኃፊ፣ ቀደም ሲል ለምርጫው ቅድመ ሁኔታ አላቀመጥንም የሚለው ለማሻሻል ሞክረዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የትብብሩ አመራሮች መልስ ለመስጠት የተቸገሩ፣ እርስ በርሳቸዉም አንድ አቋም ያልያዙ መሰለኝ። አቶ ዮናትን ቅድመ ሁኔታ ለምርጫው አስቀምጥናል እያሉ፣ የትብብሩ ዋና ጸሃፊ ለምርጫው ቅድመ ሁኔታ አላስቀመጥንም የሚሉ ከሆነ የቱ ነው ትክክለኛ የትብብሩ አቋም ? ? ? አቶ ዮናትን ወይስ አቶ ግርማ በቀለ ያሉት። በዚህ ጥያቄ ላይ “Honesty is the best policy” ይላሉ ፈረንጆች። ሰማያዊም ሆነ ትብብር በዚህ ረገድ አቋማችሁን በግልጽ ማስቀመጥ አለባችሁ። መቃረን የለባችሁም።

ሌላው ወደ ምርጫ ለመግባት ሂደቱ ይወስነዋል ይላሉ አቶ ዮናታን። ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠዋል። አንዱ ቅድመ ሁኔታ ይመስለኛል የምርጫ ቦርድ ነጻ መሆን አለበት የሚል ነው። በዚህ ረገድ አሁን ባለው ሁኔታ ገዢው ፓርቲ ፈቀቅ ያለበት ሁኔታ የለም። ካልተገደደ በቀር አሁን ያለው ምርጫ ቦርድ ነው የሚቀጥለው።

ትዝ ይለኛል ከምርጫ ቦርድ ሰብሰባ ሰማያዎች ረግጠው ወጥተው ነበር …ምርጫ ቦርድ ግን ኢግኖር ነው ያደረጋቸው። ስራዉንም ቀጥሏል። የአንድ ወር መርሃ ግብር ብለዉም ከፖሊሶች ጋር ተጋጩ፥ ብዙዎች ለሁለት ሶስት ቀናት ታሰሩ። አሁንም ምንም ለዉጥ የለም በምርጫ ቦርድ አካባቢ።

ሁለት ሶስት መቶ ሰዎች ይዞ ሰልፍ መዉጣት አገዛዙን አያስገድድም። ይልቅ መቶ ሺሆች፣ ሚሊዮን ሕዝብ እንዲወጣና ለመብቱ እንዲጮህ ነው ማድረግ የሚያስፈለገው። ለዚህም በጋራና በትብብር መስራት ያስፈልጋል። ጠንካራ ከሚባሉ ድርጅቶች ጋር ከነ አንድነት፣ መድረክ ጋር አብራችሁ ሰላማዊ ሰልፎችን ሰማያዎች ቢጠሩ፣ አብረው መሰረታዊ የዲሞክራሲ ጥያቄዎችን ቢያነሱ ብስለትና እውቀት ባለበት መልኩ ቢንቀሳቀሱ፣ ትልቅ ቫይብሬሽን መፍጠር ይቻል ነበር።

እርግጥ ነው እዚህ በዉጭ ያሉ እንዳንድ ጽንፈኞቹ ከረን አፌር ክፍል ያሉ ሰማያዎችን ፣ ሆይ ሆይ እያሏቸው ነው። ምናልባት ሁለት፣ ሶስት ቀናት በመታሰራችሁ “ጀግኖች፣ አንበሶች” ሲሏቸው፣ ያለ እነርሱ ሰው የሌለ ሊመስላቸው ይችላል።

ሆኖም ግን እዚህ በዉጭ ያሉ ጽንፈኖች ችግር ዉስጥ ነው ሰማያዎዎችን የሚከቷችሁ። አዎ ከዉጭ ድጋፍ ማግኘት ጥሩ ነው። ዉጭ ያለው ወገን የትግሉም አካል ነው። ሆኖም ዉጭ ያለው ማህበረሰብ የሚፈልገውን ሳይሆን በአገር ቤት ያለው ሕዝብ የሚፈለገውን በማዳመጥ ነው መንቀሳቀስ የሚገባው። የሰላማዊ ትግል የራሱ የሆነ ሰራዊት አለው። እርሱም ሕዝብ ነው። ሕዝብን ያላሰለፈና ያላንቀሳቀሰ ትግል ዋጋ አይኖረዉም።

አንድ ነገር ብዬህ ላቁም። ከአንድ አመት በፊት ሰማያዊ ሰልፍ ሲጠራ ወደ 70 ሺህ ሕዝብ ተገኝቶ ነበር። ከሶስት ወራት በኋላ ሰልፍ አንድነት ሲጠራ አብረው አእንዲያደረጉ ትልቅ ተማጽኖ ቢቀርብላቸውም፣ እምቢ ብለው፣ ተሽቀዳድመው ሰልፍ ጠሩ። ሰልፉ ጃን ሜዳ ነበር ግን መስቀል አደባባይ መሄድ አለብን ሲሉ ከፖሊስ ጋር ዉዝግብ ፈጠሩ። ጥቂት ፖሊሶች አፈኗችሁ።

ስድስት ወራት በኋላ፣ ሚያዚያ ላይ አንድነት ሰልፍ ጠርቶ ከአስተዳደሩ ጋር እየተነጋገረ ባለበት ጊዜ ፣ እንደ ጎህ ዝንብ ጣልቃ ገብተው፣ ሰልፍ ጠሩ። ለአንድነት አይሆንም በተባለ ቀን፣ እውቅና አገኙ። ለሰልፉም ቅስቀሳ አደረጉ። የተገኘላችሁ ሰው ሶስት መቶ አካባቢ ብቻ ነበር። ከሰባ ሺህ ወደ ሶስት መቶ መዉረድ ማለት ትልቅ የፖለቲካ ኪሳራ ነው። የአዲስ አበባ ህዝብ የሰማያዊን ስትራቴጂ እንደማያደገፍ ሰልፉ ላይ ባለመገኘት ገለጸ።

ለምንድን ነው ይሄ የሆነው ብለው መጠየቅ አልቻሉም። አሁን በአንድ ወር መርሃ ግብር እንቅስቃሴያቸውም የተለየ ነገር አላየንም። እንደ ኢሳት ባሉ ሜዲያዎች ሁሉ ሳይቀር ለሌለ ማንም ድርጅት ያልተደረገ ትልቅ ቅስቀሳ ተደረገላቸው። በሶሻል ሜዲያዉም እንደዚሁም። ከአምስት ሚሊዮን የአዲስ አበባ ህዝብ፣ መቶ አይሞላም የወጣላቸው። ለምን የአዲስ አበባ ህዝብ ጥሪያቸዉን ሰምቶ እንቅስቃሴያቸዉን አልተቀላቀለም ? ይሄ መመለስ ያለበት መሰረታዊ ጥያቄ ነው።

ገዢው ፓርቲን ማስገደድ የሚቻለው ህዝቡ በነቂስ ሲወጣ ብቻ ነው። ሰማያዊቾ ትኩረት ሰጥተው መንቀሳቀስ የነበረባቸው ሕዝቡ እንዲወጣ ማድረግ የሚቻልበትን ስትራቴጂ በመንደፍ ላይ መሆን ነበረበት። ደግሜ እላለሁ ….ሰማያዊች የያዙት መስመር በጣም አደገኛና ትግሉን የሚጎዳ ነው። አላስፈላጊ ኮንፍሮንቴሽን አስወግደው፣ ሕዝቡን በማደራጀት ላይ፣ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር አብሮ በመስራት ላይ ቢያተኩሩ ጥሩ የሚሆን ይመስለኛል። አለበለዚያ የሁለተኛ መርሃ ግብር ብለዉም የሚያወጡት ከአንደኛው የሚለይ አይሆንም።

የአንድነት ፓርቲ በፖለቲካ ፕሮግራም ተመሳሳይነት ካላቸው ጋር ፣ ሰማያዊን ጨምሮ፣ ያለ አንዳንች ቅድመ ሁኔታ በጋራ ለመስራት ዝግጁ እንደሆነ እየገለጸ ነው። ሆኖም የሰማያዊ አመራሮች ከአንድነት ጋር ለመስራት አለርጂክ ለምን እንደሆነባቸው ደጋፊዎቻቸው መጠየቅ ያለባቸው መስለኝ።

የሰማያዊ አቅጣጫ ስህተትና የማይጠቅም ነው – ግርማ ካሳ

አቶ እያስፔድ ተስፋዬ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ አባልና የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ ናቸው። “አቧራን ለማጥራት – ነጻነት ለምርጫ ቅድመ ሁኔታ ነው” በሚል ርእስ አንጹ ጽሁፍ አቅርበዋል። በሚከተለው ሊንክ ያገኙታል። የእኝህ ወጣት አቀራረብ በጣም ተመችቶኛል። በነጻነት ነጥባቸውን በማስቀመጥ ለምርጫ ከመገባቱ በፊት መሟላት ያለበት ቅድመ ሁኔታ እንዳለ ይከራከራሉ።

viewtopic.php?f=2&t=90558

የድርጅት አባል ባልሆነም፣ የምደገፈው ድርጅት አለ። እርሱም የአንድነት ፓርቲ ነው። ይህ ፓርቲ፣ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለምርጫ እንደሚሳተፍ በይፋ ለህዝብ አሳዉቆ፣ «2007 ለለውጥ»፣ «ተደራጅ ለምርጫ» በሚል መርህዎች በአገሪቷ ሁሉ መጠነ ሰፊ የምርጫ እንቅስቃሴ ጀመሯል።

የአንድነት አቋም ለምን ትክክለኛ እንደሆነ፣ በአንጻሩም ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ አቋም ለምን የወቅቱን ሁኔታ ያላመዛዘነ የተሳሳተና በ እወቀት ሳይሆን በስሜት ላይ የተመሰረተ አቋም እንደሆነ ለማሳየት እሞክራለሁ። የአንድነት አባል እንዳለመሆኔ፣ ከዚህ በታች የምጽፈው የግል አስተያየቴ እንደሆነ ከወዲሁ ለአንባቢያን አሳውቃለሁ።

ብዙዎቻችን በምርጫ በመግባትና ባለመግባት ዙሪያ የሚደረገው ዉይይት አካል ሆነን ሐሳቦችን ሰንዝረናል። አሁን ባለው ሁኔታ ምርጫ መገባት የለበትም የሚሉ ወገኖች ፣ ከምን ተነስተው እንደዚያ እንደሚሉ እረዳለሁ። ሆኖም የነርሱን አቋም ተቃዉሜ ስጽፍ፣ ምርጫ ባለመግባት የሚገኝን ጥቅም ሊያሳዩን ባለመቻላቸው ነው።

እዚህ ዉጭ አገር ያሉ አንዳንድ በጠመንጃ ትግል እናምናለን የሚሉ ቡድኖች፣ ምርጫ እንዲገባ አይፈልጉም። (እነርሱ ዉጊያቸውን ትተው ለምን በሰላማዊ ታጋዮች ዙሪያ እንደሚጨነቁ ባይገባኝም) ምናልባት ምርጫ ከተደረገና አንጻራዊ መሻሻል ከመጣ የነርሱ ፖለቲካ ዜሮ ስለሚገባ ሊሆን ይችላል ምርጫዉን የሚቃወሙት። በመሆኑም ከነዚህ ቡድኖች በምርጫ ዘመቻ ላይ ተቃውሞ ቢሰማ ልንገረም አይገባም።

አገር ቤት በሰላም የሚታገሉ ወገኖች ግን ፣ ምርጫዉን ቦይኮት ሲያደርጉ ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ደርጅታቸውን ወይንም ሕዝቡን የሚጠቅም መሆኑን በማስላት መወሰን ያለባቸው መሰለኝ። ይሄን ካደረጉ የቦይኮት ጥሪው ችግር ይኖረዋል ብዬ አላስብም። ነገር ግን ትንሽ ያልተመቸኝ ፣ እነ አቶ እስያስፔድ እንዲያስረዱን የምፈልገው ፣ ቦይኮት ማድረጉ ምን ጥቅም ለትግሉም ሆነ ለሰማያዊ ፓርቲ እንደሚያስገኝ ነው። ቦይኮት ተደረገ፤ ከዚያስ ? ? ትልቅ መመለስ ያለበት ጥያቄ።

እስከሚገባኝ ድረስ የሰማያዊ ፓርቲ ሆነ ትብብር በቀዳሚነት አቋማቸው በግልጽ አይታወቅም። አንዳንድ አመራሮች ያለ ቅድመ ሁኔታ ወደ ምርጫው እንገባለን ይላሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ ተቃራኒዉን ይናገራሉ። ስለዚህ በቅድሚያ የሰማያዊም ሆነ ትብብሩ አቋም ግልጽ መሆን አለበት። አንድ የአመራር አባል ፌስ ቡክ ላይ በመጻፉ ሳይሆን፣ ደርጅቶቹ በኦፊሴል ለሕዝብ አቋማቸዉን ግልጽ ማድረግ አለባቸው።

ለዉይይት ያህል.፣ ቅድመ ሁኔታ ሳይሟላ ወደ ምርጫው አይገባም ከተባለ፣ ቀጣዩ ጥያቄ የሚሆነው ቅድመ ሁኔታዎቹ ምንድን ናቸው የሚል ነው። ከዚያ ገዚው ፓርቲ ቅድመ ሁኔታዎችን እንዲያሟላ ምን እየተደረገ ነው ? የተደረገውስ ምን ዉጤት አመጣ ? የሚሉ ጥያቄዎች ይነሳሉ።

የሰማያዊ ፓርቲ አገዛዙ ቅድመ ሁኔታዎችን እንዲያሟላ፣ ጫና ለማድረግ የአንድ ወር መርሃ ግብር አጠናቋል። ዉጤቱን ሁላችንም የምናወቀው ነው። ካለፈው የአንድ ወር መርሃ ግብር የተለየ ነገር በሚቀጥሉት መርሃ ግብሮች ምን ሊፈጠር እንደሚችል በርግጠኝነት መናገር ቢያስቸግረም፣ መገመቱ ግን ይከበዳል ብዬ አላስብም።

የሰማያዊ ፓርቲ ቅድመ ሁኔታዎች አልተሟሉም ብሎ ከምርጫው ቢወጣ፣ ገዢው ፓርቲ የሚፈራው ወይም የሚጎዳበት ሁኔታ የሚፈጥር ቢሆን ኖሮ «ቦይኮት አደርጋለሁ» በሚል ማስፈራራትና ቅድመ ሁኔታዎች ማስቀመጥ ያስኬዳል ብዬ ልቀበል እችል ነበር። ሆኖም ያደረች ባቄላ እንደሚባል፣ ገዢው ፓርቲ ሰማያዊ ምርጫ ዉስጥ ገባ፣ አልገባ ግድ አይሰጠዉም። የሰማያዊ ምርጫውን አለመሳተፍ ለነርሱ ኢንሲግኒፊካንት ነው። በመሆኑም ምርጫ አንገባም ማለት ፖለቲካ ፋይዳ አይኖረዉም።

ሌላው ቦይኮት በሚደረግበት ጊዜ ፣ ሕዝቡም ቦይኮት እንዲያደርግ ማስተባበር ያስፈልጋል። ህዝቡ ወደ ምርጫ ሄዶ ፣ ሰማያዊ ግን ብቻዋን ቦይኮት ቢያደረግ፣ እንደ ቢራቢሮ አየር ላይ የሚንሳፈፍ ድርጅት ነው የሚሆነው። ድርጅቶች በሙሉ ተባብረው፣ ተነጋግረው፣ በተቀናጀ መልኩ ቦይኮት እንዲደረግ ዘመቻ ቢያደርጉ፣ ህዝቡም የቦይኮቱ አካል እንዲሆን ቢያደራጁ፣ ከቦይኮቱ ጎን ለጎን ሰላማዊ ሰልፎችን የሥራ ማቆም አድማዎችን ቢጠሩ …ቦይኮት ሊሰራ ይችላል። ከዚያ ዉጭ ግን ቦይኮት የሚያመጣዉ አንዳች ፋይዳ አይኖርም። (እስከሚገባኝ ድረስ የሰማያዊ ፓርቲ ከነ አንድነት ፓርቲ ጋር አብሮ መስራቱ እንደ አለርጂክ እየሆነበት ነው። ከተመሰረቱ ጊዜ ጀመሮ ከአንድነት ጋር ፉክክር እንጂ የያዙት፣ በቁም ነገር፣ «በአንድ ላይ መሰባሰባች የአገርና የሕዝብ ጥያቄ ነዉ» በሚል ሂሳብ ለመንቀሳቀስ ሲሞክሩ አይታዩም)

በመጨረሻ የማነሳው ነጥብ የፕራክቲካሊቲ ነጥብ ነው። ሰማያዊ «አገዛዙ ላይ ጫና አሳድሬ፣ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሟሉ አደርጋለሁ» ይላል። በአራት ወራት ጊዜ ዉስጥ ምን ያህ ይሄ ግብ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል ? እዉነት እንነጋገርና በአራት ወራት ዉስጥ አገዛዙ ምርጫ ቦርድን ይለውጣልን ? ለነዚህ ጥያቄዎች መልሱ « አይችልም፣ አይሆንም» የሚል ነው።

ምርጫ ቦርድ ላይ በየምርጫ ጣቢያ ጫና ሊያደረግ የሚችለዉን ህዝብ፣ ድምጹን እንዲያስከበር ከማደራጀትና በየሜዳው ሄዶ ከመንቀሳቀስ ዉጭ ሌላ አማራጭ አይኖርም። የሰላማዊ ትግል ሰራዊት ሕዝቡ ነው። ወታደሮች ከኋላው ያላሰለፈ ጀነራል የትም እንደማይደርስ፣ ህዝቡን ከበስተኋላ ያላሰፈ የሰላማዊ ትግል መሪም ሆነ ድርጅት ሩጫ ከንቱ ነው።

«አንድነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በምርጫው እሳተፋለሁ» ብሎ መግለጫ መስጠቱን አልቃወምም፡፡ አባላቶቼን ከወዲሁ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ይረዳኛል ብሎ ይሆናልና፡፡ ልክ እንደዚሁም ሁሉ ሌላውም የእኛን አቋም እንዲያከብርልን እሻለሁ፡፡» ሲሉም አቶ እያስፔድ ጽሁፋቸውን ያጠቃልላሉ። በመርህ ደረጃ ትክክል ናቸው። ሆኖም በዚህ ወሳኝ ወቅት የሰማያዊና የአንድነት ስትራቴጂዎች የተለያዩ በመሆናቸው ሕዝቡን የማደናገር ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። አንድነት በአንድ በኩል ለምርጫ ተመዝገቡ እያለ ለምርጫ ሲቀሰቀስ፣ ሰማያዊ ደግሞ በሌላ በኩል ቦይኮት ይደረግ እያለ የሚቀሰቅስ ከሆነ፣ በተቃራኒ ወገን ቆሙ ማለት ነው። የግድ አንድነቶች የሰማያዊ አማራጭ ትክክል እንዳለሆነ የማስተማርና የመቀስቀስ፣ በሐሳብ የማሸነፈ ሃላፊነት ይኖርባቸዋል።

ስለዚህ መከባበሩ፣ እንደተጠበቀ፣ ቢቻል ሁለቱም ወደ አንድ አቋም እንዲመጡ ቢነጋገሩና በጋራ ቢሰሩ፣ ካልሆነም ግን የግድ አንዱ ሐሳብ አሸናፊ ሆኖ መውጣት ስላለበት የፖለቲካ ክርክሮቹ በሰለጠነ፣ ከስሜትና ከስድብ በጸዳ መልኩ ቢደረጉ ጥሩ ሊሆን ይችላል።

ከዚህ በፊት እንደጻፍኩት፣ ሰማያዊ የወሰደው ቅድመ ሁኔታ የማስቀመጣ ፖለቲካና አቋም ስህተተ ነው ብዬ ነው የማምነው። አንዳንዶች በምርጫው መሳተፉን «ተለጣፊ» እንደመሆን እና ለአገዛዙ ሌጂቲመሲ(እውቅና) እንደመስጠት አድርገው የሚቆጥሩ አሉ። እነዚህ ወገኖች አንድነት ወደ ምርጫ በመግባቱ «ተለጣፊ» ሆኗል የሚል አስተሳሰብ ካላቸው፣ መለስ ብለው የሚሊዮኖችን ንቅናቄ እንዲመለከቱ እጋብዛቸዋለው። በአሁኑ ጊዜ የሕዝብን ትርታ የያዘ፣ በሆያ ሆዬ ላይ ሳይሆን፣ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ የሚያራምድ ፣ በሁሉም ክልሎች መዋቅር ያለው የፖለቲካ ድርጅት አንድነት ብቻ ነው። ሂዱ አርባ ምንጭ፣ ሂዱ ጂንክ፣ ሂዱ ወሊሶ፣ ሂዱ ጊምቢ፣ ሂዲ ጎንደር፣ ሂዱ አሳሶ፣ ሂዱ አዳማ፣ ሂዲ ሶዶ፣ ሂዱ ደሴ …አንድነትን በዚያ ታገኛላችሁ።

ለአገዛዙ ሌጂቲመሲ መስጠት ነው ለሚሉት ደግሞ ሌጂቲመሲ ሰጭው ማን እንደሆነ ቢነገሩን ጥሩ ነበር። በዉጭ ኃይሎች ዘንድ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ሌጂቲሚስ ያገኛል የሚል ፍርሃት ከሆነ ያላቸው፣ በጣም የዲፕሎማሲ እወቀት ዴፊሸንሲ አለባቸው ማለት ነው። እነአሜሪካ፣ ሕወሃት/ኢሕአዴጎች አምባገነን፣ በሕዝብ ያልተመረጡ፣ ድምጽ ሰርቀው ስልጣን ላይ ጠመንጃ ስለያዙ ብቻ፣ እየገደሉና እያሰሩ እንደሚገዙ ያውቃሉ። ሆኖም እውቅና ሰጥተዋቸው ዋይት ሃዉስ ድረስ ጠርተው እያስተናገዷቸው ነው። ለምን ሌላ፣ የተሻለ፣ ጥቅማቸውን የሚያስጤብቅ ኃይል ስለሌለ። እቅጩን እንወቅ፣ ቦይኮት ተደረገም አልተደረገም፣ ምርጫ ተገባም አልተገባም፣ አሜሪካም ሆነ አዉሮፓዉያን በአገዛዙ ላይ ያላቸውን አቋም አይለዉጥም። እነ አሜሪካ የፖሊሲ ለዉጥ የሚያደርጉት፣ ፊታቸውን ከሕወሃት/ኢሕአዴግ የሚያዞሩት፣ ተቃዋሚዎች ምርጫዉን ቦይኮት በማድረጋቸው ሳይሆን፣ ሕዝቡን አደራጅተው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ማነቃነቅ ከጀመሩ ብቻ ነው። ለዚህም ነው ምርጫ ከተገባ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ሌጂቲማሲ እንዲያገኝ እናደርገዋለን የሚለው አስተያየት ዉህ የማይቋጥርና በእወቅት ላይ ያልተመሰረተ ነው የምለው።

ለጊዜው አበቃሁ !

* የገቡት ይወጣሉ ፣ የወጡት ተመልሰው ይመጣሉ * የሳውዲ መንግስት “ህገ ወጦችን” የማጽዳቱ ዘመቻ ቀጥሏል * ስፍር ቁጥር የሌላቸው ዜጎች ከሞት ጋር ተፋጠው እየተሰደዱ ነው * የሳውዲ መንግስት ማስጠንቀቂያና እርምጃ … የሳውዲ መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውንና ህጉ በማይፈቅደው መንገድ የመኖሪያ ፈቃዳቸው ካለው ሙያ ውጭ የሚሰሩ የማናቸውንም ሀገር ዜጎች በመላ ሀገሪቱ ለማጽዳት የተደራጀ ዘመቻ ከተጀመረ ወር […]

አዲስ አበባ ህዳር 26/2007 አዲሱ የአዋሽ ወንዝ ድልድይ ግንባታ በመጠናቀቁ ዛሬ ለትራፊክ ክፍት መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ።

የኢትዮ-ጅቡቲ መስመር 90 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ገቢና ወጪ ንግድ የሚስተናገድበት መንገድ ሲሆን በቀን ከ20 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎችንም…

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሰማያዊ ፓርቲ እና ሌሎች በትብብሩ ውስጥ የታቀፉ ፓርቲዎች በጠሩት የአዳር ሰልፍ ላይ የወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተወሰደውን አሳፋሪ እርምጃ ሰምቻለሁ፡፡ እርምጃው ሁለት ነገሮችን በጉልህ ያሳዬ ነበር፡፡ አንደኛ የኢህአዴግ መራሹ መንግስት ሽንፍትን ያሳየ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ ሰላማዊ ትግሉ እየተጠናከረ መምጣቱን ያመላከተ ነው፡፡ አንተ ባዶ እጅህን መብትህን ለመጠየቅ ስትንቀሳቀስ፣ መሳሪያ ወደታጠቀ አካል በሰላም ስትገሰግስ […]

ታኀሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከፍተኛ ዝግጅት ይከበራል የተባለው የህወሃት 40ኛ አመት በአል ወጪ የሚሸፈነው ከመንግስት ካዝና መሆኑ በአባል ድርጅቶች መካከል መነጋገሪያ አጀንዳ እየሆነ መምጣቱን የሚናገሩት የኢህአዴግ ምንጮች፣ ከመንግስት ካዝና ለሚወጣው ገንዘብ የተሰጠው ሰበብ  ገጽታ ግንባታ የሚል መሆኑን ገልጸዋል። ህወሃት በአሉን ከድርጅቱ ካዝና በተለይም የአገሪቱን ሲሶ ሃብት ከተቆጣጠረው ኢፈርት ካዝና መጠቀም እየቻለ፣ ወጪውን …

ታኀሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ መንግስት የሃማኖት፣ የእድር፣ የአፎቻ መሪዎችን፣ የአገር ሽማግሌዎችንና ታዋቂ ግለሰቦችን በራስ መኮንን የህዝብ አዳራሽ ታህሳስ 5 ቀን 2007 ዓም ሰብስቦ ባወያየበት ወቅት ፣ ከ1990-2004 ዓም ባለው ጊዜ ውስጥ የተሰሩ ቤቶች በሰነድ አልባ ቤትነት የተመዘገቡ እና ከከተማው ማስተር ፕላን ጋር የማይጋጩ ከሆነ ህጋዊ ይደረጋሉ፣ ከ2004 ዓም እስካሁን ካርታና ፕላን …