በአዲስ አበባ በኑር (በኒ) መስጅድ ህዝበ ሙስሊሙ ድንገተኛ ተቃውሞ በማድረግ አስገራሚ ተቃውሞውን ገልጽዋል (photos and video)

የተለያዩ መፈክሮችን የያዙ ፊኛዎች ወደ ተውለብለበዋል :: ፊኛዎቹ የተለያዩ መፈክሮች የተጻፈባቸው ሲሆን ከነዚህም መካከል : – ትግሉ ይቀጥላል ፍትህ ነጥፏል ፤ሂጃብ መለያችን፤ኒቃብ ውበታችን ፤ትግላችን ቀጥሏል
ፍትህን ማዘግየት ፍትህን መንፈግ ነው ፤ትግላችን እንደቀጠለ ነው ::
ፍትህ ፍትህ ፍትህ ;We Need Justice ፤Hijab Is Beauty ፤ justice Is Denied የሚሉት መፈክሮች ይገኙበታል፡፡ በርካታ ፊኛዎች የተውለበለቡና ወደ ሰማይ የተለቀቁ ሲሆን ተቃውሞው በከፍተኛ ድምቀት ተከናውኗል፡፡ መንግስት በሴኩላሪዝም ሽፋን እየፈጸመ ያለውን የሂጃብ ገፈፋ የሚያወግዝ ሲሆን በተጨማሪም በህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ እጸፈጸመ ያለውን የፍትህ መዛባት ፤ በማረሚያ ቤቱ የሚፈጸሙ ግፎችን ለማውገዝ ነው፡፡ መንግስት ሙሉ በሙሉ ተቋሞውን በሃይል አስቁሚያለሁ ሲል የነበረ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙ ግን ድንገተኛ ተቃውሞ በማድረግ አስገራሚ ተቃውሞውን ገልጽዋል፡፡
Please wait, video is loading…