ወያኔ የሻእቢያ ተቃዋሚ የሆኑ ፓርቲዎችን በአዲስ አበባ ደሳለኝ ሆቴል ሊሰበስብ ነው::-በወያኔ እና በአልሸባብ መካከል ተጋግሎ የቀጠለው ጦርነት የኦባማና ባለስልጣኖቻቸውን አትኩሮት ለመሳብ ነው::Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)​-የወያኔው ጉጅሌ አገዛዝ የሻእቢያ ተቃዋሚ የሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶችን በማስታጠቅ እና በማደራጀት ዙሪያ በደሳለኝ ሆቴል ሊሰበስባቸው መሆኑ …

ወያኔ የሻእቢያ ተቃዋሚ የሆኑ ፓርቲዎችን በአዲስ አበባ ደሳለኝ ሆቴል ሊሰበስብ ነው:: – በወያኔ እና በአልሸባብ መካከል ተጋግሎ የቀጠለው ጦርነት የኦባማና ባለስልጣኖቻቸውን አትኩሮት ለመሳብ ነው:: Read more »

«ከዓመት በላይ እስር ላይ ከቆዩት ጋዜጠኞችና አምደኞች የከፊሉ መፈታት እርግጥ ከፕሬዝዳንት ኦባማ ጉብኝት ጋር የተያያዘ ነው። ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ከ15 ቀናት በፊት አሸባሪዎች ሲሏቸው ኅዝቡ ግን “አቶ ደሳለኝ ሊፈቱ መሆኑን አያውቁም ነበር። ከእኛው እኩል ሰሙ” ነው ያለው።» ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ።

የባራክ ኦባማ ምስራቅ አፍሪካ ላይ ኬንያን እና ኢትዮጵያን መጎብኘት የሰሞነኛ አዲስ ዜና ሲሆን ባራክ ኦባማ የሃያላኗ አገር መሪ በመሆናቸው የጉዞው ዜና ሰፊ ሽፋን አግኝቶ አለምን እያስተጋባ ይገኛል::ባራክ ኦባማ በርግጥ ከአፍሪካዊ አባት መገኘታቸው እንዲሁም የሃያላኗ አሜሪካ የመጀመሪያው ጥቁር መሪ መሆናቸው ለየት …

ለእኛ የሚበጀን በትግላችን ነጻነታችንን ማረጋገጥ እንጂ የኦባማ መግባት እና መውጣት አይደለም:: ምንሊክ ሳልሳዊ Read more »

ኢሳት ዜና (ሃምሌ 16, 2007) የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ወደ አዲስ አበባ ከተማ በሚገቡ ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ተንቀሳቅሳችኋል ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች በእስር ቤት ድብደባ እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ለፍርድ ቤት ገለጹ። ሐሙስ እለት በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት አቶ መርከቡ ሀይሌና አቶ አበበ ቁምላቸው ፕሬዘዳንት ኦባማ ወደ ሀገሪቱ በሚመጡ ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ …

ምርጫ 97 ላይ ድምፅ ሲሰርቅ እጅ ከፍንጅ የተያዘው፣ ከዛም የሌባ አይነ ደረቅ ሆኖ እኔ ነኝ አሸናፊ ያለው ህወሓት/ኢህአዴግ የተቀየመውን ህዝብን ትኩረት ለማስቀየስ አንዳች ዘመቻ ያስፈልገው ነበር፡፡ የእስልምና ፍርድ ቤቶች ህብረት ሶማሊያ ውስጥ ቡራከረዩ ሲል የነበረበት ወቅት ነው፡፡ ለህወሓት/ኢህአዴግ ጥሩ አጋጣሚ …

አሁንም አልሸባብ! – ጌታቸው ሽፈራው Read more »

የፀረ ሽብር ግብረሀይል ነኝ ብሎ የሚጠራው ቡድን አንድ ሰሞን የብሄር እና የፖርቲ ተዎፆ ያማከለ በሚመስል መልኩ ጠንካሪ የተባሉ የፖርቲ አመራርና ንፁሀን ሀሳብ ያላቸውን ግለሰቦች ከየአሉበት ሀገር ሆነ አዲስ አበባ ጨምሮ በገፍ ያስራል ህውሀት ። ይሄን የተመለከተ የአንድ ፖርቲ ብሄራዊ ም/ቤት …

“እንደ ሰው ካሰብክ ትፈለጋለህ ” ጥላዬ ታረቀኝ Read more »

ዛሬ ማምሻውን ኬንያ ይገባሉ ተብለው ለሚጠበቁት ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አቀባበል ከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ በመደረግ ላይ መሆኑን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት AFP አስታወቀ። እጅግ ብዙ ፀጥታ አስከባሪዎች በዋና ከተማይቱ ናይሮቢ ለጥበቃ ተሰማርተዋል ። አንዳንድ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ አውሮፕላኖችም ከተማዋን ከአየር …

ዶይቸ ቬለ – የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የኬንያ ጉብኝት Read more »

የቀድሞዋ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርግሬት ታቸር በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም የሚመራዉን መንግሥት ለመጣል ተጠቅመዉበታል የተባለ የከፍተኛዉ ምሥጢር ማስታወሻ ሰነድ በቅርቡ ይፋ ሆነ። Listen 1203

ሐምሌ ፲፸ (አስራሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግንባሩ ባወጣው መግለጫ “በሕዝባዊ ኃይሎች ላይ ሊወስድ ያሰበው እርምጃ ተቀባይነት እንዲያገኝለት የሽብር ተግባር ፈጽሞ በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ ለማላከክ ወስኗል።” ብሎአል። አርበኞች ግንቦት 7 “በቅርቡ የጀመረው የነፃነት ትግል የፈጠረበት መደናገጥ ለመሸፈንና ንቅናቄውን በኢትዮጵያ ሕዝብና በዓለም ዓቀፍ ማኅበረሰብ ለማስወገዝ ያግዘኛል ብሎ ያመነበት ይህን ዘግናኝ ሴራ ከሳምንት በፊት …

ሐምሌ ፲፸ (አስራሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ ፈንታሁን ታደሰና ሌሎች 6 እስረኞች ለ5 ወራት ያህል ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። በፖሊስ የካቲት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. የታሰሩት እነ አቶ ፈንታሁን በወቅቱ የጉሃላ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ወስዷቸው የነበር ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ”እኛ ይህን ጉዳይ አናይም! ከፈለጋችሁ ወደ ዞን ፍርድ ቤት ወስዳችሁ …

ሐምሌ ፲፸ (አስራሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የድርጅቱ የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሚስ ሌስሊ ሌፍኮ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ የሚታየው የሰብአዊ መብት ጥሰት የፕሬዚዳንቱ አንድ አጀንዳ ይሆናል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ። ፕ/ት ኦባማ ኢትዮጵያን መጎብኘት አልነበረባቸውም የሚለው አስተያየት ዋናው ጉዳይ አለመሆኑን የገለጹት ሌፍኮው፣ ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ምን ምን ጉዳዮችን አነሱ የሚለው ጥያቄ ዋናው …

ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ሴነተር ማርኮ ሩቢዮ ፕሬዝዳንት ኦባማ ኢትዮጵያን በሚጎበኙበት ጊዜ ሰብዓዊ መብት ቀዳሚ አጀንዳቸው እንዲያደርጉ አሳስበዋል:: ሴነተሩ ለፕሬዝዳንት ኦባማ በጻፉ ደብዳቤ “ምንም እንኳን አሜሪካና ኢትዮጵያ አሸባሪነት በመዋጋትና አካባቢዉ የተረጋጋ በማድረግ የጋራ ጥቅሞች ቢኖሯቸውም: አሜሪካ ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶችን ስትጥስ እንዳላየች ማለፍ የለባትም” ብለዋል:: አስከትለውም “አማራጭ ሃሳቦችን የማንሸራሸሪያ ጎዳናዎችን በፖለቲካ ሂደቱ: በሲቭል ሶሳይቲውና: በሚዲያ […]

ዘረኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝ፣ በሕዝባዊ ኃይሎች ላይ ሊወስድ ያሰበው እርምጃ ተቀባይነት እንዲያገኝለት የሽብር ተግባር ፈጽሞ በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ ለማላከክ ወስኗል። እንዲህ ዓይነቱ እኩይ ተግባር ህወሓት ስልጣን ከመያዙ በፊትም በኋላም ሲያደርገው የነበረ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ህወሓት እንዲህ ዓይነቱ ኢሰብዓዊና ዘግናኝ ተግባር ለመፈፀም የሚያስችሉ እኩይ ስለልቦና እና ልምድ አለው። አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ በቅርቡ […]

ሐምሌ ፲፮ (አስራስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጥያቄውን ያቀረቡት በአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳዮች ግንኙነት የተዘዋዋሪ ወንጀሎችና የሕዝብ ደሕንነት ሊቀመንበር የሆኑት ሴናተር ማርኮ ሩቢዮ ናቸው። ዴሞክራሲ፣የሰብዓዊ መብትና ዓለምአቀፍ የሴቶች ጉዳይ፣ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ወቅት ቅድሚያ ሊሰጡባቸው የሚገቡ አንገብጋቢ ጉዳዮች መሆናቸውን ሴናተሩ ጠቅሰዋል። ሴናተር ማርኮ ሩቢዮ ”ኢትዮጵያና አሜሪካ ሽብርተኝነትን በመዋጋት በአካባቢው መረጋጋትን …

ሐምሌ ፲፮ (አስራስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብርተኝነት ተከሶ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኘው በአርባ ምንጭ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ ዋና ፀኃፊ አቶ በፍቃዱ አበበ በትናንትናው ዕለት ሀምሌ 15 ቀን 2007 ዓ.ም በልደታ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት የመከላከያ ምስክሮቹን አሰምቷል፡፡ ከአምስቱ የመከላከያ ምስክሮች መካከል አራቱ ፣ የአርባ ምንጭ ፖሊስና ደህንነቶች በፍቃዱ አበበ ላይ በሀሰት …

ሐምሌ ፲፮ (አስራስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በክልሉ በሚገኙ በሁሉም አካባቢዎች 38 ብር ይሸጥ የነበረው አንድ ኪሎ በርበሬ ፣ 185 ብር በመሸጥ ላይ ሲሆን፣ 26 ብር በኪሎ ይሸጥ የነበረው ምስር ደግሞ ከ50 ብር በላይ እየተሸጠ ነው። በተፈጠረው የዋጋ ንረት የክልሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው። ክልሉ በበልግ ወራት የተጠበቀው የምስር ምርት ባለመገኘቱ የተፈጠረ ነው …

ሐምሌ ፲፮ (አስራስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በማላዊ ካሮንጎ ከተማ አቅራቢያ 34 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ማንነቱ ያልታወቀ ማላዋዊ ሕገወጥ ስደተኞችን አስተላላፊ ግለሰብ ”በሙያው የካበተ ልምድ አለኝ፤ከዚህ በፊት ከማላዊ፣ዛምቢያ፣ሞዛምቢክና ዝምባቢዌ ስደተኞችን አሸጋግራለሁ።” በማለት ስደተኞችን አጭበርብሮ በማሳመን 3 ሚልዮን የማላዊ ክዋቻ ተቀብሏቸዋል።የካሮንጋ የስደተኞች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ …

ፍትህ ካለ ሰላም አለ::ፍትህ ካለ እድገት አለ:;ፍትህ ካለ እስር ቤቶች በንጹሃን አይሞሉም:: ፍትህ ካለ ነጻነት እና መብት አለ:; ፍትህ ካለ የሚሸማቀቅ አይኖርም::ፍትህ ከተረጋገጠ ሕጎች ሁሉ በበላይነት የሕዝብ ይሆናሉ::ይህ ሁሉ የሚረጋገጠው በኛ ለኛ ከኛ ነው::እኛ አዎ እኛ በአሁን ወቅት እና ጊዜ …

የሕግ የበላይነት አለመከበሩን ካወቅን የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ወገባችንን አጥብቀን እንታገል:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

የማንዴላን ፎቶ ሰቅሎ መብላትና መጠጣት ሆድ ከመሙላት የዘለለ ምንም ፋይዳ የለውም። ስንቱን ኢትዮጵያዊ ማንዴላ በየእስር ቤቱ አጉረው እያሰቃዩና እየገረፍ፣ የተረፈውን ለስደትና ሞት እየዳረጉ የማንዴላ ቀን በድግስ ማክበር የቆመለት አላማ ምን እንደ ነበር መዘንጋት ብቻ ሳይሆን የለየለት አስመሳይነት ነው። ማንዴላ መስዋነትነት …

ህወሃቶች “የማንዴላን ቀን” ለማክበር ሽርጉድ ሲሉ አለማፈራቸው ባይገርምም ያሳዝናል። አበበ ገላው Read more »

የቡናን ዘርፍን በበላይነት እንዲመራ የሚቋቋመው የኢትዮጵያ የቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ባለሥልጣን፣ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እንዲሆን ጥያቄ ቀረበ፡፡  ባለሥልጣኑን ለማቋቋም የተዘጋጀው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ እንደሚለው ባለሥልጣኑ ተጠሪነቱ ለግብርና ሚኒስቴር ነው፡፡ ሰሞኑን የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማኅበር በረቂቅ ደንቡ …

የቡና ባለሥልጣን ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሆን ተጠየቀ Read more »

በሽብርተኝነት ተከሶ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ ፀኃፊ አቶ በፍቃዱ አበበ በትናንት ሀምሌ 15/2007 ዓ.ም በልደታ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት የመከላከያ ምስክሮቹን አሰምቷል፡፡ ከአምስቱ የመከላከያ ምስክሮች መካከል አራቱ የአርባ ምንጭ ፖሊስና ደህንነቶች በፍቃዱ አበበ ላይ በሀሰት ከመሰከሩ የተሻለ ጥቅም እንደሚሰጣቸው ቃል ገብተውላቸው እንደነበር ገልጸው መስክረዋል፡፡ ከአመት በፊት አንድነት ፓርቲ በአርባምንጭ ያደርገው […]

የፕሬስ ነፃነትን በማፈንና የሰብአዊ መብትን በመርገጥ የሚታወቀው የኢህአዴግ መንግስት የፈፀመብኝን እስር በመቃወምና በማውገዝ እንዲሁም ያለቅድመ ሁኔታ እፈታ ዘንድ በመጠየቅ ከጎኔ ለነበራችሁ በሙሉ ምስጋናዬን የማቀርበው በታላቅ ትህትናና አድናቆት ነው፡፡ በነዚያ የጨለማ ቀናት አብሮነታችሁ ያልተለየኝ አለምአቀፍና ሀገር አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡ ዩኔስኮ፣ አለምአቀፍ የሴቶች ሚዲያ ፋውንዴሽን፣ ሚዲያ ሌጋል ዲፈንስ ኢንሼቲቭ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂዩማን ራይትስዎች፣ ሲፒጄ፣ ፔን […]

ወያኔ እንደለመደዉ ከተቃዋሚዎች ጋር ለማገናኘት እየጣረ ነዉ የደርባን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ሳሙኤል በዘራፊዎች በተተኮሰ ጥይት ተመተው ህይወታቸው አለፈች ፡፡ አዎ ይህንን በተንተራሰ መልኩ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘዉ የወያኔ ስራ አስፈጻሚ መስሪያ ቤ/ት የህወሃት ቀኝ እጅ የኢቶፕያ ኢንባሲ በደቡብ አፍሪካ ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የወያኔ ደጋፊዎችን ” የናንተም እጣ ፋንታ ይህዉ ነዉ ” ። […]

“የማንዴላ ቀን” ህወሃቶች “የማንዴላን ቀን” ለማክበር ሽርጉድ ሲሉ አለማፈራቸው ባይገርምም ያሳዝናል። የማንዴላን ፎቶ ሰቅሎ መብላትና መጠጣት ሆድ ከመሙላት የዘለለ ምንም ፋይዳ የለውም። ስንቱን ኢትዮጵያዊ ማንዴላ በየእስር ቤቱ አጉረው እያሰቃዩና እየገረፍ፣ የተረፈውን ለስደትና ሞት እየዳረጉ የማንዴላ ቀን በድግስ ማክበር የቆመለት አላማ ምን እንደ ነበር መዘንጋት ብቻ ሳይሆን የለየለት አስመሳይነት ነው። ማንዴላ መስዋነትነት የከፈለው ህወሃት በኢትዮጵያ ህዝብ […]

ህወሓት ጥቂት አባላትና ደጋፊዎች ይዞ ታላቂቷን ኢትዮጵያ ለማንበርከክ እና ሀብቷን ለመመዝበር  እናንተን መጠቀሚያ ያደረጋችሁ መሆኑን የምታውቁት ነው። እናንተ አባል የሆናችሁባቸው ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴድ የተባሉ ድርጅቶች የራሳቸው ድርጅታዊ ነፃነት የሌላቸው የህወሓት አገልጋዮች መሆናቸው እነሱ ራሳቸው የሚነግሯችሁ ከመሆኑም በላይ እናንተም በዕለት ተዕለት ተግባራችሁ የምትታዘቡት ሀቅ ነው። እነዚህ ድርጅቶች ህወሓትን ለማስደሰት ሲሉ የራሳቸውን ሕዝብ የሚያስሩ፣ የሚገድሉ፣ የሚዘርፉ፣ ከቀየው […]

–ባለሥልጣኑ በጣቢያውና በኢትዮፒካሊንክ ላይ ያሳለፈው ውሳኔ ውድቅ ተደርጓል የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን በዛሚ 90.7 ኤፍኤም ራዲዮ ጣቢያ በሚተላለፈው ኢትዮፒካሊንክ ፕሮግራም ላይ የቀረበን አቤቱታ ምክንያት በማድረግ ሰኔ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ለሬዲዮ ጣቢያው የጻፈው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያና ኢትዮፒካሊንክ የተባለው ፕሮግራም ላይ የሰጠው ዕግድ …

ብሮድካስት ባለሥልጣንና ዛሚ ራዲዮ የፈጠሩት ውዝግብ በባለሥልጣኑ ቦርድ ውሳኔ ተፈታ Read more »

ልደት እና ትምህርት ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ሊቀ ጳጳስ ከአባታቸው ከመምህር ሀብተ ማርያም ደስታ ተክሌ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ በስሙ ቸርነት ታኅሣሥ 19 ቀን 1925 ዓ.ም. በድሮው አጠራር ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እየተባለ ይጠራ በነበረው እንሳሮ ወረዳ በአኹኑ አጠራር በሰላሌ አውራጃ በውጫሌ ወረዳ ልዩ ስሙ በርጋፈት ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ተወለዱ፡፡ ዕድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ በታላቁ …

ኢሳት ዜና (ሃምሌ 13 2007 አም) የበክኔል ዩኒቭርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑትና በቅርቡ ከዚሁ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማእረግ የተቀበሉት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በሳምንቱ መጨረሻ ኤርትራ መግባታቸው በኢትዮጵያውያን ዘንድ አብይ መነጋገሪያ ሆኖ ወጥቷል ፤ የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የመሪውን ትግል ቦታ መሄድ ይፋ በማድረግ ኢትዮጵያውያን በአቅማቸው መጠን በትግሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል። “እነሆ የአርበኞች ግንቦት ሰባት …

Magdalaወለላዬ ከስዊድን

አፄ ቴዎድሮስ ያሠሩትን መድፍ (ሴባስቶፖል) ወደ ተራራው አናት ለማውጣት እየተጣደፉ ነው። እሳቸው ጭምር በጉልበት እያገዙ ሲገፋ ውለው ረፋዱ ላይ ከሰፈር ደርሰው ሲመለሱ አንዱ መድፉን ከሚገፉት ተለይቶ ወደ ሰፈር ሲወርድ መንገድ ያገኙትና ቆም ብለው ወዴት ነው ሥራ ትተህ የምትሄድ? ብለው ይጠይቁታል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሐምሌ ፲፭ (አስራአምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ድርጅቶቹ ለፕ/ት ኦባማ በጻፉት ደብዳቤ ኬንያና ኢትዮጵያ በብሄራዊ ደህንነት ስም የሚያደርሱት የሰብአዊ መብት ረገጣ ፣ አለማቀፍ ህግጋትን መጣስ ብቻ ሳይሆን፣ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የሚደረገውን ጥረት አደጋ ውስጥ እንደሚጥለው ገልጸዋል። ደብዳቤውን የጻፉት፣ አትላንታ ካውንስል፣ ካውንስል ኦን ፎሬን ሪሌሽን፣ ሂውማን ራይትስ ፈርስት፣ ከኒይ ግራጅዌት ሴንተር እና ሲቲ ኮሌጅ ኦፍ …

ሐምሌ ፲፭ (አስራአምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲቀርቡ ሲል የልደታ ፍርድ ቤት 19 ኛው የወንጀል ችሎት ወሰነ፡፡የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በምስክርነት እንዲያቀርብ ሲል ፍርድ ቤቱ ለሀምሌ 29 ቀን 2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥትዋል። አቶ አንዳርጋቸው …

ሐምሌ ፲፭ (አስራአምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይ ኦ ኤም በየመን አድርገው በሕገወጥ መንገድ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ለመግባት ሲሞክሩ በሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች ታግተው የአካልና የሞራል ጉዳት የደረሰባቸውን ቁጥራቸው 3 ሺ 478 የሚሆኑ በጎፈቃደኛ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው መመለሱን አስታውቀዋል። የ18 ዓመቱ ወጣት አልማይ ፍፁም ”በመኪና ተጭነን ወደ ሳዑዲ ድንበር እንደተቃረብን …

ሐምሌ ፲፭ (አስራአምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉት አቶ ጌታሁን ካሳ ”የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት ተቋም ሚናውና የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ላይ ይጋጠሙት ፈተናዎች” በተሰኘ ጥናታዊ የምርምር ሥራቸው ላይ እንደገለፁት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተቋም ነፃና ገለልተኛ ሆኖ፣ የሕግ የበላይነትን ከማረጋገጥ አኳያ ውጤታማ ሥራ ሠርቷል ማለት እንደማይቻል አመልክተዋል፡፡አቶ …

ከአርበኞች ግንባር ጋር የተዋሀደዉ የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶክተር ብርሃኑ ነጋና እና የፓርቲያቸዉ ከፍተኛ የአመራር አባላት ወታደራዊ ትግል ለማካሄድ ወደሚንቀሳቀሱባት ኤርትራ ጠቅልለዉ መሄዳቸዉን አንድ የንቅናቄዉ አመራር አባል አስታወቁ። ቁጥራቸዉ ይፋ ያልተደረገዉ የአርበኞች ግንቦስ ሰባት የአመራር አባላትን ይዘዉ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ወደኤርትራ …

ዶክተር ብርሃኑና የፓርቲያቸዉ አመራሮች የትግል ርምጃ – ዶይቸ ቬለ Read more »

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በርስ በርስ ጦርነት በምትታመሰው የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን እየመለሰ መሆኑን አስታወቀ። እስካሁን ድረስ 1,429 በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት 4,442 በኢትዮጵያ መንግስት ስደተኞች መመለሳቸውን ድርጅቱ አስታውቋል። በተጨማሪም በሚቀጥለው ሳምንት 284 ኢትዮጵያውያን በጀልባ ወደ ጅቡቲ ለማጓዝ አቅዷል … Listen

  ሮናልዶ እንዲህ ይላል… “ለኔ ለዚህ ስኬት መድረስ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረገልኝን የልጅነት ጓደኛዬን አልበርት ፎንትራኦን አመሰግነዋለሁ! በጊዜዉ እኔና እሱ ከ18 አመት በታች ለታዳጊ ሻምፕዮና በአንድ ክለብ አብረን እንጫወት ነበር…አንድ ቀን የሊዝበን አሰልጣኝ ወደ እኛ መጣና እንዲህ አለን:- “ዛሬ ብዙ ጎል ያስቆጠረ ወደ እኛ አካዳሚ ይገባል” አለን! በእለቱም ጨዋታውን 3ለ0 ስናሸንፍ ጎሎቹንም የመጀመሪያውን እኔ 2ኛውን ደግሞ […]

Sur Construction Ethiopiaየአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት ጋዜጣዊ መግለጫ:- የአርበኞች ግንቦት 7 ጀግና የነፃነት ፋኖዎች በኢትዮጵያ መሬት ላይ በህዝቡ ጉያ ውስጥ ሆነው በወልቃይት የጀመሩትን ወታደራዊ ጥቃት አሁንም አጠናክረው በመቀጠል የህወሓትን አገዛዝ እያሽመደመዱት ነው፡፡ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የተባለውን በቁሙ ደርቆ የበሰበሰ ዛፍ ከስሩ ገዝግዞ ለመቁረጥ የተጀመረው ትግል ሰሞኑን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ልዩ ልዩ አካባቢዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ከወታደራዊ ጥቅምና ደህንነት አንፃር ስማቸውን ለመግለፅ በማይቻልባቸው የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ልዩ ልዩ አካባቢዎች ላይ በሚንቀሳቀሰው የህወሓት ፀረ-ሽምቅና ሚሊሻ ኃይል ላይ ደፈጣ በመጣል ደምስሰውታል፡፡

በአዘዞ እና ጠዳ ከተሞች መካከል ከሚገኘው መገጭ ወንዝ አጠገብ በግንባታ ስራ ላይ የነበረው የሱር ኮንስትራክሽን የድንጋይ መፍጫ ማሽነሪዎች እና ሌሎችን የግንባታ ቁሳቁሶች በአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች ሙሉ በሙሉ በመውደሙ ስራውን አቁሞ እንዲሸሽ ተገዷል፡፡ ሱር ኮንስትራክሽን የህወሓቶች የግል ንብረት የሆነው ኤፈርት በስሩ ካሉት ከ60 በላይ የንግድ ኩባንያዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ሱር ኮንስትራክሽን ውድመት በደረሰበት አካባቢ የግንባታ ስራውን በብቸኝነት የያዘው እንደተለመደው ያልምንም ጨረታ ነው፡፡ በተያያዘ ዜና ከዚያው ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ውስጥ የሚኖር አቶ ጎሸ ሽባባው የተባለ ገበሬ ለአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች ስንቅ አቀብለሃል በሚል በህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ውሎ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞበታል፡፡ አቶ ጎሸ ሽባባው አሁን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝት እስር ቤት ውስጥ ይገኛል፡፡

በላይ አርማጭሆ አንገረባ ቀበሌ የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች እና የህወሓት ጸረ-ሽምቅ ኃይል ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ጦርነት አድርገዋል፡፡ ጦርነቱም የተካሄደው ሀምሌ 11 2007 ዓ.ም ሲሆን በአካባቢው ለአሰሳ ሲንቀሳቀስ የነበረውን የህወሓት ፀረ-ሽምቅ ኃይል በውስጥ አርበኞች የተከፈተበትን ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት መቋቋም ስላልቻለ አንድ ሰዓት ከፈጀ የተኩስ ልውውጥ በኋላ ለጊዜው ቁጥራቸው በትክክል ያልታወቁ በርካታ አባላቱ ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል፡፡ የሱዳን መከላከያ ኃይል የኢትዮጵያን ወሰን ጥሶ ገብቶ ከሆር ሁመር ገበሬዎች ጋር መታኮሱ ታውቋል፡፡ በተደረገው የተኩስ ልውውጥ 2 ገበሬዎች ለሞት ተዳርገዋል፡፡ በአካባቢው ሰፍሮ የሚገኘው ህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት የሱዳን መከላከያ ኃይል ድንበር ሰብሮ ገብቶ በገሬው ህዝብ ላይ የጦር ጥቃት ሲያደርስ እየተመለከተ እንዳላየ በዝምታ አልፎታል፡፡

ህወሓት በጠመንጃና ዱላ ብቻ የተንጠለጠለ ስልጣ ይዛ እንድትቀር፣ በ2007 ዓ/ም ምርጫ ተሸንፎ ቅስሙ እንዲ ሰበር ያደረግነው የተሻለ ኣማራጭ ፓሊሲ፣ የበለጠ ዲሞክራሲያዊ ባህሪ፣ የነጠረ ሃገራዊ ራኢ፣ ህዝባዊነት የተላበሱና ከሂወት መስዋእትነት ጀምረው የኣካል መጉደል፣ የስራ መፈናቀል፣ የቤተሰብ መበተንና ከትዳር መፈናቀል፣ ከማህበራዊ ግንኝነቶች …

ህወሓት ዱላዋ ኣስቀምጣ ትግጠመን…! አምዶም ገ/ስላሴ Read more »

ከአርበኞች ግንቦት 7 የጥቃት ማግስት ጀምሮ የተለያዩ የነጻነት ሐይሎች ጦርነት እያካሄዱ እንደሚገኙ ከወያኔ ወታደራዊ ግንኙነት ክፍል የወጣ መረጃ አመለከተ። መረጃዉ እንደሚጠቁመዉ ኦነግና የኦጋዴን ነጻ አዉጪ ሀይሎችም ተመሳሳይ የሆነ ሽምቅ ዉጊያ ተያይዘዉታል። የአሜሪካዉ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማን መምጣት ምክንያት ባደረገ መልኩ ኢትዮጵያ ምንም አይነት የጦርነት አዋጅ እንደማታዉጅ ወታደራዊ ደህንነቱ ለየ እዝ ባለስልጣናቱ ሚስጢራዊ ትዕዛዝ በማሳለፉ የእዝ አመራሮችን […]

  አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ የወሰነው የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በምስክርነት እንዲያቀርብ ለሀምሌ 29/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጠ፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሀምሌ 13/2007 ዓ.ም ልደታ ፍርድ ቤት ቀርበው የመከላከያ ምስክር እንዲሆኑ ፍርድ ቤቱ ወስኖ የነበር […]

የኦነግ አባላትን ለማደን ጋራሙለታ የዘለቀው የሕወሓት የደሕንነት ሃይል የኦሕዴድ ካድሬዎችን ፈጃቸው:: Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከባሌ ክፍለሃገር ተነስተው አዳዲስ ተዋጊ አባላትን ለመመልመል ወደ ሃረርጌ ጋላሙለታ ዘልቀዋል የተባሉትን የኦነግ አባላት በደረሰው መረጃ መሰረት አድኖ ለመያዝ አሊያም የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ በሚል …

የኦነግ አባላትን ለማደን ጋራሙለታ የዘለቀው የሕወሓት የደሕንነት ሃይል የኦሕዴድ ካድሬዎችን ፈጃቸው:: Read more »

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ተኛው ወንጀል ችሎት በሽብር ከተከሰሱት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች መካከል አብዛኛቹ በአቃቤ ሕግ ማስረጃ ላይ ያቀረቡትን መቃወሚያ ውድቅ አደረገ። ካሁን ቀደም በዋለው ችሎት ሰባት ተከሳሾች አቃቤ ሕግ ያቀረባቸዉን የክስ ማስረጃዎች ተቃውመዉ ፍርድ ቤቱ ከመዝገቡ እንዲያስወጣላቸዉ በጠበቃቸው አማካይነት …

በእስር ላይ ያሉ የተቃዋሚ መሪዎች “ተቀባይነት የሌላቸው” ያሏቸው ማስረጃዎች ይነሱልን ጥያቄ – VOA Read more »

ሐምሌ ፲፬ (አስራአራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት እንደ አዲስ ባገረሸው የምስራቅ እዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና የሃረሪ ክልል ፖሊሶች ግጭት 4 ፖሊሶች በመከላከያ አባላት ታፍነው መወደሳቸውንና እስካሁን የደረሱበት አለመታወቅን የሃረር ወኪላችን ገልጿል። የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ከሁለቱ ሃይሎች የተውጣጡ መሪዎችን ለማነጋገር ሙከራ ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም። በሃረሪ ፖሊስና በምስራቅ እዝ የፖሊስ አባላት መካከል ያለው ግጭት …

ሐምሌ ፲፬ (አስራአራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርባምንጭ ምንጮች እንደገለጹት ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፌደራል ፖሊስ አባላት በየአንዳንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ፍተሻ ሲያደርጉ የታየ ሲሆን፣ አንዳንድ ሰዎች ላቀረቡት ጥያቄ የተሰጣቸው መልስ ” ግንቦት7″ ከተማው ውስጥ ገብቷል የሚል ነው። በከተማውና በዙሪያ ወራዳዎች የሚታየው ፍተሻና ቁጥጥር መጨመሩን ፣ ህዝቡም ግራ ተጋብቶ እንደሚገን ምንጮች …