የአሜሪካ የጥቁሮች ሰብዓዊ መብት ታጋይ የነበሩት ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ታዋቂዉ ንግግራቸዉን ያደረጉበት 50ኛ ዓመት ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ እየተከበረ ይገኛል።

አራት መቶ የሚሆኑ ቤተ እስራኤላዉያን ለዓመታት ሲያልሟት ወደነበረችዉ ምድር በዛሬዉ ዕለት ተሸንተዋል። ቀሪዎቹን ደግሞ ይህ ጉዞ የመጨረሻዉ ነዉ መባሉ እንዳሳዘናቸዉ የቤተ እስራኤላዉያን ማኅበር ገልጿል።

ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት ባዘጋጀው በሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ” የአገሪቱ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአክራሪዎችንና የአሸባሪዎችን እንቅስቃሴዎች ከመደገፍ ካልተቆጠቡ ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት እርምጃ እንወስዳለን” ብለዋል። ማንኛውም ጸረ ሰላም እንቅስቃሴ በሚያደርጉትም ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የገለጡት አቶ ሐይለማርያም፣ የጥፋት ሀይሎችን ለማምከን የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል። …

ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰማያዊ ፓርቲ ቀደም ካሉት ጊዜያት ጀምሮ ለነሐሴ 26 ቀን 2013 ዓመተምህረት ሰልፍ እንደሚጠራ አስታውቆ የቅስቀሳ ሥራ መሥራት በጀመረበት ጊዜ፤ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ሰሞኑን  በዚያው ቀን ሰልፍ ለማድረግ ጥሪ ማቅረቡ ያታወቃል። በተለይ በኢህአዴግ የሰልፍ ጥሪ  የሴትና ወጣት ማህበራት፣የመንግስት ሠራተኞች፣ የሀይማኖት ተቋማትና  ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጭምር በግዳጅ …

ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተለያዩ የአማራ አካባቢዎች ተያዙ የተባሉ 10 ሰዎች ዛሬ በአቃቂ 4ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል። ዘመኑ ካሴ ከተባለው ሰው በስተቀር ሌሎች 9ኙ ተከሳሾች ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ለህዳር 2 ቀን፣2006 ዓ/ም ቀጠሮ ተሰጥቶአቸዋል። ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል የባህርዳር ከተማና ዙሪያዋ ነዋሪዎች የሆኑት አሸናፊ አካሉ፣ ደህናሁን ቤዛ፣ ምንዳየ ለማ፣ አንሙት …

ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ፓዊ እና አልሙ የከተማ እና የገጠር አካባቢዎች እንዲሁም በአማራ ክልል ቻግኒ እና አካባቢው መብራት ለተከታታይ ሳምንታት መቆረጡን ኑዋሪዎች ተናገሩ፤ ነዋሪዎች ለኢሳት ባደረሱት መረጃ እንዳሉት በመብራት እጦት በከፍተኛ ሁኔታ ተሰቃይተናል ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ የኢትዩጵያ መብራት ሃይል ኮርፖሬሺ ከአቅም በላይ ሁኖብኛል ሲል ተናግሮዋል፡፡ ድሃ …

በኢትዮጵያና በኬንያ የድንበር አካባቢዎች ከከትናንት በስተያው ቅዳሜ ወዲህ በተፈጠሩ የጎሣዎች ግጭቶች ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን አንድ የኬንያ ራዲዮ ጣቢያ ዘገበ፡፡

ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ማብራሪያ የሚሊየኖች ድምፅ ለነፃነት ንቅናቄ በአራቱም የኢትዮጵያ ማዕዘናት የነፃነት ድምፅ ማስተጋባት ከጀመረ እንሆ ዛሬ ስልሳ ሰባተኛ(67) ቀኑን ይዟል፡፡ ፓርቲያችን በእዚህ ታላቅ ሕዝባዊ የነፃነት ንቅናቄ መሪር የሆነ ውድ ዋጋ እየከፈለ ድምፅ አልባ ለሆኑት ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ድምፅ በመሆኑ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡ ላለፋት ስምንት ዓመታት ሰቆቃ እና ግፍ በገዢዎቻችን ሲፈፀምበት የኖረው የገጠሩም […]

ለተከበሩ ኢንጂነር ይልቃል፣ ለክቡራን ከፍተኛ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት፣ በቅድሚያ ሰላምታዬ ባላችሁበት ቦታ ይድረሳችሁ! ጤና ይስጥልኝ። ለሰማያዊ ፓርቲ አድናቆት አለኝ። የግራዚያኒ ሃዉልትን በመቃወም ያደረጋችሁት ሰልፍን ተከታትያለሁ። በብዛት ግን ሰው ያወቃችሁ፣ በአዲስ አበባ በጠራችሁት ሰላማዊ ሰልፍ ነዉ። ያኔ ትልቅ ሥራ ነው የሰራችሁት። አኩርታችሁኛል። ብዙ ደጋፊዎችም በአጭር ጊዜ ዉስጥ አግኝታቹሃል። ያኔ የጠራችሁትን ሰልፍ አብዛኞቻችን ብንደግፈውም፣ ሌሎች ድርጅቶችን […]

የአገሬ ሰው “ነገሩ ነው እንጂ ጩቤ ሰው አይጎዳም”የምትል አባባል ነበረችው።ግፍ በተለያየ ምክንያት ሊውልብህ ቢችልም የግፉ ደራሲ ግፉን ሲፈጽምብህ ወይም እየፈጸመብህ መርዘኛ በሆነ ፀያፍ አነጋገር በሕሊናህም ላይ ጠባሳ ካልተወ በጊዜ ብዛት የደረሰብህን ግፍ ችላ ልትል፤ ከቶውንም ግፈኛውንም ይቅር ልትል እንደምትችል ለማመላከት ይመስለኛል። “ስልጣን ያባልጋል፤ፍፁም ስልጣን ደግሞ ፍፁም ያባልጋል” የሚለው አባባል ደጋግሞ በታሪክ እንዳሳየን አምባገነኖችና ጀሌዎቻቸው ግፍ […]

  ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

የግብፅ ጦር ሐይል በሐገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሕዝብ የተመረጡትን ፕሬዝዳትን ከሥልጣን ማስወገዱ፥ መፈንቅለ መንግሥቱን የሚቃወሙ ወገኖችን መግደል፥ ማሰሩ ብዙ ሲያነጋግር፥ሕዝባዊ አብዮት ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀጣጠለባት አምባገናናዊዉን ሥርዓት በምርጫ የተኩት የቱኒዚያ ፖለቲከኞች እርስ በርስ እየተወዛገቡባት ነዉ

ባለፈዉ ሳምንት ደማስቆ ዉስጥ ደርሷል ለተባለዉ የአደገኛ ኬሚካል መሳሪያ ጥቃት የአረብ ሊግ የሶርያ መንግስትን ተጠያቂ አደረገ። በመቶዎች የተገመቱ ሰዎችን ሕይወት ያሳለፈዉ የኬሚካል መሳሪያ ጥቃት ተጠያቂዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ ድርጅቱ ጠይቋል።

የፊታችን መስከረም ለሚካሄደው የጀርመን አጠቃላይ ምርጫ የሚፎካከሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ዘመቻ ላይ ናቸው። ፓርቲዎቹ ዓላማቸውን ከግብ ለማድረስ ይረዳል ባሉት መንገድ የመራጩን ህዝብ ቀለብ ለመሳብ እየጣሩ ነው።

ችግሩ የውጭ ግንኙነት መምሪያውን አፋጣኝ ትኩረት ይሻል የመላው አፍሪቃ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በኾኑት ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ አስተዳደር ላይ በወጣው ዘገባ ዙርያ ከሚደርሱን አስተያየቶችና ትችቶች የሚበዙት ከደቡብ አፍሪቃ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን ምእመናንና አገልጋዮች የሚላኩልን ናቸው፡፡ ብፁዕነታቸው በኤጲስ ቆጶስነት ከተሾሙበት ፲፱፻፺፯ ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ ለስምንት ዓመታት የቆዩበት ደቡብ አፍሪቃ መንበረ ሊቀ ጵጵስናው እና የአህጉረ …

በጎርጎሪዮሳዊዉ 2010ዓ,ም በዓለም ዙሪያ በወባ በሽታ 660 ሺ ሰዎች ማለቃቸዉን የዓለም የጤና ድርጅት ያመለክታል። ከእነዚህ መካከል አብዛኛዎቹ ማለትም 90 በመቶ የሚሆኑት የሚገኙት ደግሞ አፍሪቃ ዉስጥ ነዉ። የዛሬ ሶስት ዓመት በወባ በሽታ 220 ሚሊዮን ሰዎች ተይዘዉ እንደነበር የዓለም የጤና ድርጅት መረጃዎች ያመለክታሉ።

አሁን አብዛኛው አውስትራልያ የገባ ኢትዮጵያዊ በሚገኝባት የሜልበርን ከተማ ውስጥ አበሻው ሰብሰብ ብሎ በሚኖርባትና በሚሠራባት ፉትስክሬይ በተባለችው መንደር እንገኛለን፡፡ ይህች የሜልበርን ምዕራባዊ ቀበሌ የሆነች መንደር ጥንት የኤስያውያን መናኸርያ ነበረች ይባላል፡፡ ዛሬ ግን ዋናዋ የአፍሪካውያን ስደተኞች መሰባሰቢያ ናት፡፡ በዚህች ከ74000 ትንሽ ከፍ የሚል ሕዝብ በሚኖርባት መንደር ውስጥ ከ135 ሀገሮች የመጡ ስደተኞች ይኖሩባታል፤ ከ85 ቋንቋ በላይ ይነገርባታል፡፡ እንዴው መርካቶ በሏት፡፡

በአውስትራልያ ታሪክ የመጀመሪያው የእንጀራ መሸጫ ሱቅ የተከፈተው እዚህ ነው፡፡ በነገራችን ላይ እዚህ ሀገር እንጀራ በዋናነት ከስንዴ ወይም ከሩዝ ዱቄት ተቦክቶ የማሽላ ዱቄት ይቀላቀልበታል፡፡ የታደሉት ደግሞ ከሀገር ቤት የመጣ የጤፍ ዱቄት ለአመል ይጨምሩበታል፡፡ ስፋቱ የአገር ቤት እንጎቻ የሚያህል ሲሆን ውፍረቱ የሰንበት ቂጣ ታናሽ ወንድም ነው፡፡ ኮከብ የመሰለ ዓይን ባያገኝም፣ ሞጭሟጫ ከመባል ለጥቂት ይተርፋል፡፡ በብዛት የሚጋገረው ከብረት በተሠራ ምጣድ ነው፡፡ አልፎ አልፎ ግን ከሀገር ቤት የሸክላ ምጣድ የሚያመጡ አሉ፡፡ ሳይሰበር ከደረሰላቸው፡፡

በፉት ስክሬይ ከደርዘን በላይ የኢትዮጵያውያን ሱቆች፣ ከአምስት በላይ ምግብ ቤቶች እንዳሉ ይነገራል፡፡ በአካባቢው ስትዘዋወሩ ቢያነጥሳችሁ ‹ይማርህ› የሚል አታጡም ይባላል፡፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን እናቶችና አባቶች ስለሚዘዋወሩበት፡፡ በርግጥ ወጣቶቹና ጎልማሶቹ እንዲህ ያለ ነገር አያውቁም፡፡ የሚገርማችሁ እንዲያውም እዚህ አካባቢ አበሻና አበሻ ሲገናኝ ቁጣ እንጂ ሰላምታ አይሰጣጥም፡፡ ሁለቱም ፊታቸውን ኮስተር አድርገው ነው የሚተላለፉት፡፡ እኔ እንዲያውም ‹እዚህ ሀገር የመጣው ያኮረፈው ተመርጦ ነው እንዴ› ብዬ ነበር፡፡

በፉት ስክሬይ የሚጠፋ ቅመማ ቅመም የለም፡፡ በተለይም ሕንድ ሱቅ ውስጥ በሀገራችን የጠፋው ቅመም ሁሉ ይገኛል፡፡ ሞያ በሜልበርን በሽ በሽ ነው፡፡ በርበሬ ከሀገር ቤት ለማስመጣት የአውስትራልያ የምግብ ሕግ ሲያስቸግር እዚሁ ሌላ በርበሬ ተፈጥሯል፡፡ ከሕንዶች ሱቅ የሚገዛ የሚያቃጥል ቀይ ቃሪያ አለ፡፡ እርሱን በኮረሪማ መፍጫ መፍጨት ነው፡፡ ከዚያ ደግሞ ቅመማ ቅመሙን ለብቻ ፈጭቶ መጨመር፡፡ በመጨረሻም አውስትራልያ ሠራሽ ምርጥ ድልህ ይሆንላችኋል፡፡

 አንድ ወዳጃችን ‹ሽሮ እኛን ስላሳደገች በክብር ጡረታ ወጥታ ትቀመጥ› ቢልም ከሀገር ሲወጡ አንዱ የሚናፍቀው ግን ሽሮ ነው፡፡ በአውስትራልያ ልዩ የሆነ የሽሮ አዘገጃጀት ተፈጥሯል፡፡ የባቄላው ዱቄት ከሕንድ ሱቅ ይገዛል፡፡ ከዚያም አመስ አመስ ይደረጋል፡፡ ለቅመማው አስፈላጊ የሆነውን ቅመምም ሕንዶቹ ያመጡታል፡፡ እርሱንም በቡና መፍጫ ፈጭቶ በመጠኑ ማመስ ነው፡፡ ከዚያም ሁለቱን በባለሞያ እጅ ደባልቆ ምርጥ የውጭ ሀገር ሽሮ ማግኘት፡፡ ችግር ብልሃትን ይፈጥር የለ፡፡

   ለኢትዮጵያውያን እዚህ አንዱ ፈተና ከሀገር ቤት ባህላዊ ምግቦችን ማስመጣት ነው፡፡ የሀገሩ ሕግ ጥብቅ ስለሆነ፡፡ ሳይደግስ አይጣላም እንዲሉ ግን እንደ ካልዲ(የቡናን ፍሬ ያገኘው እረኛ) አዳዲስ ቅጠላ ቅጠሎችን የሚያገኙ ኢትዮጵያውያን እዚህ ሞልተዋል፡፡ አንድ ቀን ነው አሉ፡፡ መቼም እኛ ታሪክን በጊዜና በሰዓት የመመዝገብ ችግር አለብን፡፡ (ተረቱም ታሪኩም ከዕለታት በአንድ ቀን ብሎ ነው የሚጀምረው) አንዲት የሀገሬ ሰው በግቢዋ ውስጥ ስትዘዋወር አንድ የምታውቀውን ቅጠል የሚመስል ነገር ታያለች፡፡ ጠጋ ብላ ቆረጠችውና መዳፏ ላይ አሸችው፡፡ ልክ ነው፤ እርሱ ነው፡፡ ወስዳ ለጓደኛዋ አሳየቻት፡፡ ሁለቱም ርግጠኞች ሆኑ፡፡ ጉዳዩን ወደ ልጅቱ እናት ‹ሪፈር› አደረጉት፡፡ እርሳቸውም እየተገረሙ ‹እርሱ ነው› አሉ፡፡ ለካስ ጌሾ ኖሯል፡፡ ጠላ ለመጥመቅ ችግር የነበረው ጌሾ በአውስትራልያ ምድር በቅሎ ተገኘ፡፡ ዛሬ በብዙ ኢትዮጵያውያን ግቢ ውስጥ ጌሾ በቅሎ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡

በዚህች ምድር በቅሎ የተገኘው ግን ጌሾ ብቻ አይደለም፡፡ መቼም አገር ደግ ነገር ብቻ አታበቅል፡፡ አንድ ወዳጃችን ሁል ጊዜ አንድ ቦታ እየሄደ ቅጠል ሸምጥጦ ሲወጣ ይታያል አሉ፡፡ መጀመሪያ አካባቢ ማንም ከቁም ነገር አልወሰደውም ነበር፡፡ በኋላ ግን ሸምጣጩ በዛ፡፡ የአካባቢው ሰዎችም ግራ ገባቸው፡፡ በከተማዋ ውስጥም ወሬው ተባዛ፡፡ የሚሸመጠጥበት ቦታም በአንዳንድ ሰዎች መዘውተር ጀመረ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ከሥሩ እየነቀሉ ወስደው በጓሯቸው ተከሉት፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የአውስትራልያ ፖሊሶች ጉዳዩን ሰሙትና ክትትል አደረጉ፡፡ ለካስ ያ በወፍ ዘራሽ በቅሎ አገር እየተራኮተ የሚሸመጥጠው ጫት ኖሯል፡፡ ፖሊሶቹ እዚያ ቦታ የነበረውን መድምደው አጠፉት፡፡ ችግሩ ግን እነርሱ ሳይደርሱ በፊት በየግቢው ተዛምቷል፡፡ አንዳንድ ቤት ስትሄዱ ጫት በኩራት በቅሎ ታዩታላችሁ፡፡

ፉት ስክሬይ በአበሾች ዘንድ ከምትታወቅበት ሀብቷ አንዱ ምርጥ የሆነ ቁርጥ ሥጋ መሸጫ ስለሆነች ነው፡፡ መቼም ቁርጥ እየበላን ቁርጥ ነገር አለመቻላችን የሚገርም ቢሆንም የሀገሬ ሰው የትም ቦታ ቢሄድ፣ ምንም ዓይነት ትምህርት ቢማር ሊያጣው የማይፈልገው ነገር ቢኖር ቁርጥ ሥጋ ነው፡፡ ከነአባባሉም ‹የተማረ ሰውና የተሳለ ቢላዋ ሥጋ አያጣም› አይደል የሚባለው፡፡ እዚህ ከተማ በጥሬ ሥጋ ሻጭነታቸው የታወቁ ቤቶች አሉ፡፡ ነጭ፣ ቀይ፣ ጎድን፣ ዳቢት፣ ሻኛ፣ ለቁርጥ፣ ለወጥ እያሉ የሚያስተናግዱ፡፡ እነርሱ ጋ ገብቶ አለበለዚያም ደግሞ ሰፈር ይዞ መጥቶ ቁርጥ በኅብረት መብላት እዚህ የተለመደ ነው፡፡ ከአውሮፓና ከአሜሪካ ወደ አውስትራልያ ዘመድ ለመጠየቅም ሆነ ለመዝናናት የሚመጡ ኢትዮጵያውያን በአውስትራልያ ቁርጥ ፍቅር ተነድፈው ነው የሚመለሱት፡፡ አንዳንድ የአውሮፓና የአሜሪካ ወዳጆቼ ጋር ስንጻጻፍ እንዲያውም ‹የአውስትራልያን ቁርጥ ሳትበላ እንዳትመጣ› ይሉኛል፡፡ እስቲ ቀምሼ እመሰክርለታለሁ፡፡

‹አይ እኔ ማን እንደነካው የማይታወቅ ሥጋ አልበላም› ለሚሉ አለያም ደግሞ ‹የተሸረፈ ጥርስ፣ ደልደል ያለም ላት አይቶ መርጦ ተከራክሮ መግዛት› ለሚያምራቸው ወደ ገጠሩ ክፍል ወጣ ማለት ነው፡፡ ከበግ አርቢ ገበሬዎች ጋር ምን የመሰለ የደብረ ብርሃን በግ ይገኛል፡፡ ማረዱን ባይፈቅዱላችሁም መባረኩን ይፈቅዱላችኋል፡፡ እነርሱ ደግሞ ገፍፈውና ቆራርጠው ይሰጧችኋል፡፡ ከዚያ በኋላማ ‹አቤት ባለፈው ለፋሲካ የገዛሁት ምን የመሰለ በግ› እያላችሁ ሾላ ገበያ የሄዳችሁ ማስመሰል ነው፡፡ 

ሜልበርን አውስትራልያ፡፡

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በፍቼ ከተማ እሁድ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፈ ላይ የገዢው ፓርቲ አፈና በግልጽ የተነጸባረቀበት እንደነበር የፓርቲው የምክርቤት አባል አቶ አበበ አካሉ ገልጸዋል በባሌ ሮቤ ሊካሄድ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ገዢው ሀይል የሀይል እርምጃ ለመውሰድ በማቀዱ ሳይሳካ መቅረቱን በስፍራው የተገኙት የፓርቲው የምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሀን እንደገለጹት ገዢው ፓርቲ በተቃውሞው ላይ …

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጽያ ሃይማኖቶች ተቋማት ጉባዔ ዛሬ ከቀትር በሁዋላ በአ/አ አምባሳደር ቲያትር አካባቢ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አክራሪነትን ለመቃወም የፊታችን እሁድ ነሃሴ 26 ቀን በመስቀል አደባባይ ሰልፍ መጥራቱን አስታወቀ፡፡ በዕለቱ ሰማያዊ ፓርቲ ሁለተኛ ሰልፉን በመስቀል አደባባይ ለማድረግ በይፋ ለአስተዳደሩ አሳውቆ ምላሽ እየተጠባበቀ የሚገኝ ሲሆን ምናልባት የሃይማኖት ተቋማቱ ሰልፍ ለማካሄድ …

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለኦሮሞ ህዝብ መብት በመታገል ላይ የነበረው የ37 ዓመቱ ወጣት ኢ/ር ተስፋሁን ጨመዳ ቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ እንዳለ መሞቱ ታውቋል። ኢ/ሩ በምን ምክንያት እንደሞተ ግን አልታወቀም።  ከጓደኞቹ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ኢ/ር ተስፋሁን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ከነበረበት ጌዜ ጀምሮ ገዢውን ፓርቲ ይቃወም ነበር። ኢ/ር ተስፋሁን ኬንያ በነበረበት ወቅት ምንም …

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከአባይ በፊት ዘረኝነት የወገድ በማለት መቃወማቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የመንግስት ወኪሎች ተቃውሞውን በመፍራት ሊሰበሰቡበት ተከራይተውት የነበረውን አዳራሽ በመተው በሰዎች ቤት ስብሰባውን በግለሰቦች ቤት ለማድረግ ተገደዋል። በስፍራው ለተገኙት አንዳንድ አረጋውያን ለአባይ ቦንድ የሚገዙ ከሆነ የቤት መስሪያ ቦታ እንደሚሰጠቻው በስበሰባው መሪዎች ተነግሮአቸዋል። መንግስት በውጭ አገራት የሚያደርገው …

የርምጃውን ጅምር የወሰደው የአ/አ መካነ ሰማዕት ቅ/ቂርቆስ ደብር ሰበካ ጉባኤ ነው፡፡ የደብሩ የስብከተ ወንጌል ክፍል ጥብቅ ክትትል እንዲያደርግ ማሳሰቢያ ተሰጥቶታል፡፡ ለሰ/ጉባኤው የእግድ ውሳኔ ዝርዝር መረጃ የሰጠው የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ነው፡፡ ሰንበት ት/ቤቱ ከአምስት ዓመት በፊት ከመናፍቃን ኅትመቶች ገልብጦ ባዘጋጀው በራሪ ወረቀት ምክንያት ከማንኛውም አገልግሎት አግዶ ክትትልና ማጣራት ሲያደርግበት ቆይቷል፡፡ ዲ/ን ኀይሉ በነገሌ ቦረና የሀ/ስብከቱ ስብከተ …

ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ ወኅኒ ውስጥ አረፉ
የሽብር ክሥ ተመሥርቶባቸው የዕድሜ ልክ እሥራት የተፈረደባቸው ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ ለሰባት ዓመታት እሥር ላይ ከቆዩ በኋላ እዚያው ወኅኒ ውስጥ ማረፋቸውን ቤተሰቦቻቸው ለቪኦኤ ገለፀዋል፡፡

ፖሊስ የሰጠውን ማስረጃ አይተናል ያሉት እስከፍርዱ ድረስ ከይግባኝ በፊት ቆመውላቸው የነበሩት ጠበቃ አቶ ጥላሁን ታደሰ ኢንጂነር ተስፋሁን ያረፉት ባለፈው ዓርብ ሌሊት መሆኑን አመልክተው የፖሊሱ መረጀ እራሣቸውን ማጥፋታቸውን እንደሚጠቁም ጠቁመዋል፡፡

ኢንጂነር ተስፋሁን እራሣቸውን አጥፍተዋል የሚለውን መግለጫ ለማመን እንደሚቸገሩ የሚናገሩት አቶ ጥላሁን ታደሰ ሕክምና እንዲደረግላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ እንደነበረና የጠየቁትን አለማግኘታቸውን እንደሚያውቁ፤ ከእህታቸው ጋርም በማግስቱ ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘው እንደነበረ ቤተሰብ እንደነገራቸው …

መጠለያ ​​
ኢትዮጵያ በምሥራቅ ተከሰተ የተባለውን ፖሊዮ እያጠናች ነው
ኢትዮጵያ እአአ ከ 2008 አም አንስቶ ማለት በአምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በፖልዮ ማለትም በልጅነት ልምሻ የተያዘ ሰው እንደተገኘ ማስታወቋን የአሜሪካ ድምጽ ሬደዮ ዘጋቢ ሜሪ አሊስ ሳሊናስ ያነጋገረቻቸው የሮተሪ-ኢንተርናሽናል ፖሊዮን የማጥፋት ዓለምአቀፍ ዘመቻ አባል ካሮል ፓንዳክ መግለፃቸውን ዘግበናል፡፡

የታመችው ያልተከተበች የአንድ ዓመት ተኩል ሕፃን መሆኗን ያስታወቁት ፓንዳክ ሶማልያ ውስጥ አንድ መቶ የሚሆኑ፣ በሰሜን ኬንያ ደግሞ ከአሥር በላይ የሚሆኑ የፖልዮ ህሙማን እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ በምሥራቅ ተከሰተ የተባለውን ፖሊዮ እያጠናች ነው ​​
“አካባቢው ለሶማሊያ ቅርበት ያለው በመሆኑ የቫይረሱ ወደዚያ መዛመት የሚደንቅ አይደለም፡፡ ይህ በኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ ውስጥ …

መሠረት ደፋር በስቶክሆልም ዳያመንድ ሊግ በ 3 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር የዓመቱን የዓለም ፈጣን ጊዜ በማስመዝገብ አሸንፋለች። በሉዥኒኪ ሞስኩ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ 5 ሺህ የወርቅ ሜዳልያ ከወሰደች ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ መሆኑ ነው መሠረት ይህን ድል የተቀዳጀችው።

በሐሙሱ የዳያመንድ ሊግ 3 ሺህ ሜትር አዲሱ የመሠረት ደፋር የዓመቱ ፈጣን ጊዜ 8 ደቂቃ ከ 30 ነጥብ 29 ሴኮንድ ነው።

ሌላዋ የኢትዮጵያ አትሌት ሲፋን ሐሰን የግሏን ፈጣን ጊዜ አስመዝግባ በሦስተኝነት ጨርሳለች።

መርሲ ቼሮኖ ከኬንያ የብሩን ሜዳልያ አጥልቃለች።

  ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

ሄሊኮፕተሮቹ አገልግሎት እንዲሰጡ ለታሰበው ተግባር አመቺ እንዳልሆኑና የጥራት ደረጃቸውም ከጊዜው ጋር አብሮ የሚሄድ እንዳይደለ ዛሬ ታትሞ የወጣው ፍራንክፉርተር አልገማይነ የተባለው የጀርመን ጋዜጣ ዘግቧል ።

ሠፊዉ ዓለም የግብፅን እልቂት ፍጅት፤ የሌላዉን ዓለም አፀፋ በቅጡ ለማስተንተን እንደገና ጊዜ አልነበረዉም።ወይም የሰዉ ደም ጠጥቶ ደም የሚጠማዉ ምድር ለሌላ ጥማቱ እርካታ ሶሪያን በመርዝ ጋዝ ሲያጥናት ትልቁም፥ ትንሹም፥ ምሥራቁም ምዕራቡም ቱጃሩም፥ ሐያሉም በሶሪያ የእልቂት ዜማ ያንጎራጉር ሌላዉ ይፎክር-ይዝት ገባ።

የድርጅቱ አመራር አባላት አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ የኤርትራ መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት በሚወስዳቸው እርምጃዎች የቀይ ባህር አፋሮችን እንደሚገድል እንደሚያስርና ከቀያቸው እንዲሰደዱ እንደሚያደርግ ተናግረዋል ።

ለስድስት አመት ኤፈርትን ሲመሩ የቆዩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከሃላፊነት መነሳት ተከትሎ በሕወሐት ውስጥ ውጥረት መንገሱን ምንጮች አመለከቱ። የኤፈርት ቦርድ ሰብሳቢ በነበሩት ባለቤታቸው አቶ መለስ አማካይነት ዳይሬክተር ተደርገው አዜብ መሾማቸውን ያስታወሱት ምንጮች፣ ከመለስ ሕልፈት በኋላ ቦታውን የተረከቡት ኤርትራዊው ቴዎድሮስ ሃጎስ መሆናቸውን፣ እንዲሁም ዳይሬክተር የመሾምና የመሻር ስልጣኑ የቦርዱ መሆኑን ያስረዳሉ። አዜብ ከኤፈርት እንዲወገዱ የተደረገው ግን በነቴዎድሮስ ሃጎስ […]

በጥቅመኝነት ላይ የተመሠረተ የአገልጋዮች ምደባና ስምሪት፣ ለምእመናን ወቅታዊ ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ አለመስጠት፣ በዕቅበተ እምነት ሊቀ ጳጳሱ ይታይባቸዋል የሚባለው ቸልተኝነት እና የጎጠኝነት ዝንባሌ በዋናነት ተጠቅሰዋል፡፡ *       *      * ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በቅርቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሥራች አባል ለኾነችበት ለመላው አፍሪቃ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ በምክትል ፕሬዝዳንትነት መመረጣቸው ለውጭ ግንኙነታችን መልካም ዜና ነው፡፡ ከጉባኤው …

የቀድሞው ጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ፣ አምና ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ ወዲህ የአገሪቱ ፖለቲካዊ ፣ ኤኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ገጽ ምን ይመስላል?

አባይ የህዝብ እንጂ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም!

Ethiopia Zare (እሁድ ነኀሴ 19  ቀን 2004 ዓ.ም. August 25, 2013)የአባይ ግድብ ሂደት ግልጻማነት የጎደለውና ኢትዮጵያዊያን ያልመከሩበት አገዛዙ የፈጠረው የፖለቲካ መጠቀሚያ ነው የሚሉ ኢትዮጵያዊያን በቫንኩቨር ካናዳ የተጠራውን የግድብ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ምሽት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አንድነት ታርቲ ዛሬ በባሌ ሮቤ የሚያደርገውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በኦህዴድ ባለስልጣናትና በደህንነት ሀይሎች አፈና ተፈፀመበት፡፡ ሰልፉን ለማደናቀፍ የአካባቢው ባለስልጣናት ትላንት ምሽት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ካረፉበት ታይታኒክ ሆቴል ንብረታቸውን ሳይዙ በግዳጅ እንዲወጡ ከመደረጉም በላይ አብዛኞቹ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና የቅስቀሳ ቡድን አባላት ታግተዋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና የቅስቀሳ ቡድን አባላት ደህንነት አደጋ ላይ እንደሆነም ከስፍራው […]

አንድነት ሰላማዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነዉ። አገዛዙ ግን ሕገ መንግስቱን በመርገጥ የሰለጠነን ሳይሆን፣ የዛቻን ፖለቲካ እያራገበ ነዉ። «በሮቢ ደም ሊፈስ ይችላል» በማለት ማስፈራሪያዊች እየቀረቡ ሲሆን፣ ፖሊሲስ ሰልፍን የምታደርጉ ከሆነ እርምጃ እንደሚወስድ አሳዉቀዋል። የሮቢ የአገዛዙ አስተዳዳሪዎች፣ 20 ሰዎች የሚገኙበት የ«ሽማግሌዎች» ቡድን አቋቁመዋል። ይሀ ቡድን ከጥቂት ሰዓት በኋላ ከሚሊየነም ድምጽ ለነጻነት ግብረ ኃይል ጋር ዉይይት ያደርጋል። ኮምቴዉ፣ ስብሰባው […]