ግብፅ (ምስር) እንደሃገር ከምትታውቅበት ማለትም ከፈሮኦኖች ዘመን ጀምሮ ፤ የታሪኳም ሆነ የህልውናዋ መሰረት አባይ ነው። አባይ ባይኖር የግብፅ የቆየና ጥንታዊ ታሪኳ የለም ፤ የፈርኦኖች ታሪክ የለም፤ አባይ ባይኖር የክሊዮፓትራ ታሪክ የለም ። ባጠቃላይ አባይ ባይኖር ግብፅም ታሪኳም፤ ጥንታዊ ስልጣኔዋም፤ የአለማችንን …

የግብፅና ኢትዮጵያ መጪው ዘመን ምን ሊመስል ይችል ይሆን? Read more »

በማዳጋስካር ከአራት ዓመት ተኩል በፊት መፈንቅለ መንግሥት ከተካሄደ ወዲህ ደሴቲቱ እከፋ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች። በሀገሪቱ ይካሄዳል የተባለው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በተደጋጋሚ መተላለፉ የሚታወስ ነው።

የዛሬው የሙዚቃ ቃና ፕሮግራም ስለ Martin Luther King, I have a dream ንግግር 50ኛ አመት በአል የሚዘክሩ ዜማዎችን እና ሙዚቃ ነክ ዜናዎችን ያስተናግዳል፡፡

የአንድነት ፓርቲ የቅስቀሳ ቡድን አባላት የሚደርስባቸውን ጫና ተቋቁመው በባሌ ሮቤ የተሳካ ቅስቀሳ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ የቅስቀሳ ቡድኑ አባላት “የህዝቡ አቀባበል መንግስት የሚያደርስብንን ጫና ተቋቁመን ስራችንን እንድናከናውን ረድቶናል” ብለዋል፡፡ በባሌ ሮቤ ከንቲባ ጽ/ቤት አራት የአንድነት ፓርቲ ተወካዮች ለውይይት ተጠርተው ታግተው የነበሩ ሲሆን እነዚሁ የአንድነት ፓርቲ ተወካዮችና የቅስቀሳ ብድን አባላት አሁን የተለቀቁ ቢሆንም በሁለት መኪኖች የተጀመረውን ቅስቀሳ […]

የአንድነት ፓርቲ የቅስቀሳ ቡድን መኪናና በባጃጆችን በመጠቀም የተቀናጀ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የፍቼ ከተማ የኢህአዴግ ካድሬዎችና የመንግስት ሹመኞች ህዝቡ ለነገው ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይወጣ ቤት ለቤት በመሄድ በማስፈራራት ላይ ቢገኙም ህዝቡ በነገው የተቃውሞ ሰልፍ ብሶቱን ለመግለፅ ተዘጋጅቷል፡፡ ዘግይቶ በደረሰን ዜና በፍቼ ከተማ የሚገኘውን የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት የመንግስት የደህንነት ሀይሎች ሰብረው በመግባት በቢሮው ውስት ያሉትን አባላት ቢያባርሩም […]

  ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

ነሃሴ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአዲስ አበባ ወደ ወልድያ ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ አውቶቡስ ደሴ አካባቢ ሲደርስ በመገልበጡ የ21 ሰዎች ህይወት ጠፋ፣ የዛሬውን ጨምሮ በአንድ ሳምንት ውስጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 66 ደርሶአል። የአደጋው  መንስኤ ጥራት የሌለው የአስፓልት መንገድ በጎርፍ በመቆረጡ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የወልድያ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ለኢሳት እንደገለጸው ደግሞ የአደጋውን መንስኤ …

ነሃሴ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ በአንዋር መስጂድ የጁምአ ሰላታቸውን በመስገድ ላይ የነበሩ ሙስሊም ሴቶች በፖሊስ መደብደባቸውን የ ኢሳት ወኪል ከስፍራው ዘግቧል። በጁምአ ሰላት ላይ የነበሩት ሙስሊም ሴቶች የተደበደቡት፤ “ሶላት መስገድ የምትችሉት በግቢ ውስጥ እንጂ ከግቢ ውጪ አንጥፋችሁ አትሰግዱም” ተብለው በውጪ እንዳይሰግዱ በፖሊሶች መከልከላቸውን ተከትሎ በተፈጠረ አለመግባባት ነው። ሙስሊም ሴቶቹ ሁልጊዜ እንደሚያደርጉት …

በመጪው እሁድ ነሃሴ 19 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚገኘው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መ.ኢ.አ.ድ/ ዋና ጽ/ቤት 33ቱ ፓርቲዎች ለጠሩት ህዝባዊ ውይይት የመኪና ላይ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ የፓርቲዎቹ አባላት በህገወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡ አቶ ደመላሽ፣ አቶ አብርሃም ፣ አቶ አታላይ በለው፣ አቶ እዮብዘርና አቶ መላኩ መሰለ የተባሉት አባላት የቅስቀሳ መከናውን ከያዘው ሹፌርና ረዳት ጋር ታስረዋል፡፡ የፓርቲዎቹ አመራሮች […]

ነሃሴ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከባህርዳር የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው ኢህአዴግ ለከተማው ነዋሪዎች አዲስ የአባልነትና አንድ ለአምስት አባልነት መለያ ወረቀት ያዘጋጀ ሲሆን፣ ይህንን ወረቀት ያላሳየ ሰው በመንግስት የሚከፋፈለውን ስኳር አያገኝም። አንዳንድ ነዋሪዎች ችግራቸውን በኤፍ ኤም ራዲዮ ላይ ቢናገሩም ምንም መፍትሄ እንደሌለው እንዳወቁ ለኢሳት ተናግረዋል። በጉዳዩ ዙሪያ የክልሉን ህዝብ ግንኙነት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። …

ነሃሴ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አለም የጤና ድርጅት እንደገለጸው በያዝነው ወር በጣለው ዝናብ ከ50 በላይ ሰዎች ሞተው፣ ከ300 ሺ ያላነሱት ደግሞ ተፈናቅለዋል። በተለይ በዋና ከተማዋ ካርቱም ላለፉት 25 አመታት ያልታየ ጎርፍ መታየቱን ድርጅቱ አስታውቋል። በአገሪቱ ካሉ 18 ግዛቶች መካከል በ14 ላይ ከፍተኛ የንብረት መውደምም ተከስታል።

በመጪው እሁድ ነሃሴ 19 ቀን 2005 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ሊያደርግ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ወደ ጷጉሜ 3 መዘዋወሩን የአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረ ኃይል ማምሻውን አስታወቀ፡፡ ግብረኃይሉ እንዳስታወቀው የአዳማ ከተማ አስተዳደር ለአንድነት ፓርቲ በፃፈው ደብዳቤ ነሃሴ 19 በከተማው ስብሰባ በመኖሩና የሀይል እጥረትም ስላለበት አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን እንዲያስተላልፍ ጠይቋል፡፡ አንድነት ፓርቲም የቀረበለትን ጥያቄ ከግምት በማስገባት ሰልፉን […]

ሀሙስ ነሃሴ 16 ቀን 2005 ዓ.ም የአንድነት ፓርቲ ተወካዮች ከሮቤ ከተማ ከንቲባ፣ ምክትል ከንቲባ፣ የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊና ከከተማው ካቢኔዎች ጋር 3 ሰዓት የፈጀ ውይይት አድርገዋል፡፡ ባለስልጣናቱ “አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን ማድረግ አይችልም፤ እኛ ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ስጋት አለብን፡፡ የቀድሞው ጠ/ሚር መለስ በፓርላማ እንደተናገሩት በአካባቢያችን የአልቃይዳ ክንፍ አለ” ብለዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ተወካዮች በበኩላቸው “በባሌ አካባቢ ያለውን የፀጥታ […]

ጠጋ ብለው ሳያውቁ፤ የቀኝ ጽንፈኛ አመለካከታቸውን ብቻ በማንጸባረቅ፤ የውጭ ተወላጆችን፣ በጭፍን የሚጠሉ ፣ የሚያጥላሉ አካራሪ ጀርመናውያን በየጊዜው ነው ተቃውሞአቸውን የሚያሰሙት።

በምርጫ ሥልጣን የያዙት መሀመድ ሙርሲ በጦር ኃይሉ ከሥልጣን ተነስተው በታሰሩ በ7 ሳምንታቸው ሙባረክ ከእስር ቤት መውጣታቸው በሙባረክ ተቃዋሚዎች ዘንድ የግብፅ ህዝባዊ ንቅናቄ የመቀልበሱ ምልክት ተደርጎ ተወስዷል ።

ያኒንግ እንደሚያምኑት የአሜሪካ ጦር ሶሪያ ከዘመተ የደማስቆ መንግሥትን የምትደግፈዉ ኢራን አሜሪካኖች ነገር እንደፈለጓት ነዉ የምትቆጥረዉ።የእስራኤል ደሕንነትም ላደጋ መጋለጡ አይቀርም።«ከዚሕም በተጨማሪ» ይላሉ ያኒንግ አሜሪካኖች «ጣልቃ መግባት» መጀመሪያዉ እንጂ ፍፃሜዉ እንደማይታወቅ ካለፈዉ አስር ዓመት ልምዳቸዉ በቅጡ መማር አለባቸዉ።

መሐመድ አማን ​​
አዲስ አበበ ቢቂላ፣ አዲስ ምሩፅ ይፍጠር፣ አዲስ መሐመድ አማን
“ከአሁን በኋላ በዓለም አቀፍ ትራኮች የአጭር ርቀት ሩጫ አሸናፊነት በር ለኢትዮጵያዊያን አትሌቶችም ተከፍቷል” ሲል በርቀቱ በአገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን ወርቅ በስምንት መቶ ሜትር ያገኘው መሃመድ አማን አስታወቀ።

“መሃመድ አማን የዚህ ዘመን አበበ ቢቂላና ምሩፅ ይፍጠር ነው” ሲሉ የተናገሩት ደግሞ አሰልጣኙ ንጉሴ ጊቻሞ ናቸው።

መሃመድ አማን ዛሬ ለጋዜጠኞች የሰጠውን መግለጫ የተከታተለውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡
መሐመድ አማን ​​

  ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

በጥንቱ ስርዓት፣ አንድ ሰው ከአራቱ በአንዱ መንገድ ባሪያ ይሆናል። የመጀመሪያው በጦርነት ተሸንፎ ከተማረከ ፣ ሌላው እዳውን መክፈል አልችል ብሎ በእዳ ከተያዘ ፣ ሶስተኛው ከባሪያ ቤተሰብ የተወለደ ከሆነ በውርስ፣ አራተኛው ደግሞ ባሪያ ፈንጋዮች ይዘው ከሸጡት ነው። በዚህ ዘመን የባሪያ ንግድ ቢጠፋም፣ ባርነት ግን አልጠፋም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንዲያውም አምስተኛውን የባርነት መንገድ እያየን ነው፤ ይሄ ባርነት በባህሪው […]

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 60 የሚጠጉ የወረዳዋ ሽማግሌዎች በዛሬው እለት ለ7ኛ ጊዜ በጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጽሀፈት ቤት ቢገኙም ጠ/ሚኒስትሩን ሊያገኙዋቸው እንዳልቻሉና በተወካያቸው በአቶ ወርቁ በኩል መንግስት ጉዳዩን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያሳውቃል የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ለኢሳት ገልጸዋል። በመንግስት መልስ ደስተኞች ያለሆኑት የአገር ሽማግሌዎች፣ እንደገና ተመልሰው ወደ ክልሉ ዋና ከተማ አዋሳ ማቅናታቸው ታውቋል። …

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከንቲባ ድሪባ ኩማ የሚመራው አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ረቂቅ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ የኮንዶሚየም ቤት ፈላጊዎችን ለማስተናገድ ከ20 ዓመታት በላይ ጊዜ እንደሚወስድ ጠቆሟል። አስተዳደሩ ለኮንዶሚየም ቤቶች ብቻ ከ800ሺ በላይ ዜጎችን ቢመዘግብም በቀጣይ አምስት ዓመት ለመስራት ያቀደው 178 ሺ ቤቶችን ብቻ ነው፡፡ አስተዳደሩ ከ2006 …

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የ33ቱ ፓርቲዎች የትብብር መድረክ -ሰማያዊ ፓርቲን ያሰናበተው፤የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ሰሞኑን ለ ሰንደቅ ጋዜጣ የሰጡት ቃለምልልስ የሌሎች ፓርቲዎችን ክብር የነፈገ ነው በሚል ነው። በዚህም መሰረት ፓርቲዎቹ ባደረጉት ስብሰባ ሰማያዊ ፓርቲ ከስብስቡ እንዲወጣ መወሰናቸውን የቪኦኤ ዘገባ ያስረዳል። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፀሀፊ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ ውሳኔው የተላለፈው …

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአካባቢው በሚጥለው ከባድ ዝናም የተነሳ በክልሉ በሚገኘው ኦሮሚያ ዞን ባለፈው ሳምንት ከ30 ያላነሱ ሰዎች የተገደሉበትን ክስተት ጨምሮ ፣ በደቡብ ወሎ ዞን በአንባሰል ወረዳ አንዲት ሚኒ ባስ በጎርፍ በመወሰዷ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል። በጎርፍ የተወሰዱ ሰዎችን አስከሬን ለማግኘት በተደረገ ጥረት የ14 ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል። የአካባቢውን ፖሊስ አዛዥ ለማግኘት …

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከእስር ተፈተው በሄሊኮፕተር ወደ ጦሩ ሆስፒታል ለምርመራ ተወስደዋል፣ ጊዚያዊው መንግስት ከቤታቸው እንደማይወጡ አስታውቋል። ፕሬዚዳንቱ ከቀረረበባቸው የሙስና ክስ ነጻ በመሆናቸው መፈታታቸው ተገልጿል። ይሁን እንጅ ከሁለት አመት በፊት በግብጽ ከተካሄደው አብዮት ጋር በተያያዘ አሁንም ሌሎች ክሶች ቀርበውባቸዋል። ደጋፊዎቸቻቸው ደስታቸውን ቢገልጹም፣ የሙስሊም ብራዘርሁድ ደጋፊዎች ደግሞ …

በግብጹ ግጭት መንስኤ አስቸኳይ ጉባኤ ያካሄዱት የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባሳለፉት ውሳኔ መሰረት ሕብረቱ ለግብፅ ጦር የሚውሉ የጦር መሣሪያዎችና ወታደራዊ ቁሳቁሶች ሽያጭ አግዷል ። «በሀገር ውስጥ ህዝብን ለመጨቆን የሚውል የማንኛቸውም የጦር መሣሪያዎች የውጭ ንግድ ፈቃዶች» ታግደዋል ።

ምሥራቅ አፍሪቃዊቷ ሀገር ታንዛንያ በተለይ በአገር ጎብኚዎች ዘንድ ፣ እንጎሮንጎሮ እና ሴሬንጌቲ በተባሉት ቦታዎች በሚገኙት የዱር እንስሳትና ዓራዊት ክልሎች ትታወቃለች። ከዛ ባለፈስ የታንዛንያን ባህል ምን ይመስላል?

7, 617, 930 ስኩዌር ኪሎ ሜትር በምታካልለው ሰባተኛ አህጉር፣ በስፋቷ የዓለማችን ስድስተኛ ሀገር በሆነችው አውስትራልያ ውስጥ እገኛለሁ፡፡  አንድ አህጉር አንድ ሀገር ሲሆን አውስትራልያ በዓለማችን ብቸኛዋ ትመስለኛለች፡፡ የሚገርመው ግን ይህንን የሚያህል ሰፊ ሀገር ውስጥ የሚኖሩት ሃያ ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ብቻ መሆናቸው ነው፡፡ ‹አይሆንም እንጂ ቢሆንማ› እንደሚባለው ቢቻል ኖሮ ከአውስትራልያ ይዤ ወደ ሀገሬ የምገባው የቤት መሥሪያ መሬት ነበር፡፡ እዚያ የወባ ክኒን የምታክል መሬት ለማግኘት የቀበሌ መታወቂያ፣ 10/90፣ 20/80፣ ባንክ ቤት፣ ወረፋ፣ ምዝገባ፣ ዕጣ፣ መከራ እያሳየን እዚህ መሬት የካንጋሮ መጨዋቻ ሆኖላችኋል፡፡ ‹አስወስጄ መጣሁ አስወስጄ› የሚለው ዘፈን ባህል ነውና እኛ የባሕር በራችንን አስወስደን ትንሷን ጅቡቲ ስንለማማጥ እንኖራለን፤ የዓለማችን ትልቋ ደሴት የምትባለው አውስትራልያ 34,218 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የባሕር ጠረፍ ባለቤት ናት፡፡ አውስትራልያ የሚለው ስም ከላቲኑ ‹‹አውስትራሊስ› የመጣ መሆኑንና ትርጉሙም ‹ደቡባዊ› ማለት እንደሆነ ይነገራል፡፡

በስድስት ክልሎችና በሁለት ልዩ ግዛቶች የተመሠረተችው ይህች ፌዴራላዊት ሀገር ራሳቸውን ‹አውሴ› ብለው የሚጠሩት የዛሬ ዋነኛ ነዋሪዎቿ ከመምጣታቸው በፊት ‹አቦርጅን›[አዳሙ ተፈራ የሚባል አውስትራልያ የሚኖር ደራሲ – ‹ኑር ተገኝ› ብሎ ጠርቷቸዋል፡፡] የተባሉ ጥንታውያን ሕዝቦች ይኖሩባት የነበረች ሀገር ናት፡፡ እነዚህ ከእስያ መጥተው ከብዙ ሺ ዓመታት በፊት የኖሩት ባላገሮቹ ዛሬ በሰሜናዊ አውስትራልያ በሚገኘው ‹የሰሜን ግዛት› በሚባለው ልዩ ክልል ውስጥ በብዛት ይገኛሉ፡፡ እንግሊዞች ወደዚች ሀገር ሲመጡ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ቁጥር ነበራቸው የሚባሉት አቦርጅኖች በደረሰባቸው ግፍና መከራ የተነሣ ቁጥራቸው መንምኗል፡፡ ለመሬታቸው ሲባል ተሰድደው፣ ተገድለውና በበሽታ እንዲያልቁ ተደርገው ሀገራቸውን አጥተዋል፡፡ በ1787 ዓም የተነሣውና መጤዎቹ ሆን ብለው ወደ አቦርጅኖች እንዲደርስ አድርገውታል የሚባለው ፈንጣጣ ብቻ ‹ዳሩግ› ከሚባሉት የአቦርጅን ጎሳዎች መካከል ዘጠና በመቶውን ፈጅቷቸዋል፡፡ [የኡጋንዳው ዩዌሪ ሙሴቪኒ ነጮች በአፍሪካ ላይ በመድኃኒት ጥቁሮችን እንዳይጨርሱ ያደረጋቸው ከብት አርቢ መሆናችን ነው፡፡ ብዙውን በሽታ ከብቶቹ ወስደውታል፡፡ ከከብት ጋር በመኖራችንም የመቋቋም ውሳጣዊ ዐቅም ገንብተናል ብለው ነበር፡፡] ልጆቻቸውን ለጉልበት ሥራ አስገድዶ በመውሰድ፣ እንዳይወልዱ የማምከኛ መድኃኒት በመስጠት፣ የመጠጥ ሱሰኞች ሆነው እንዲቀሩ በማድረግ አቦርጅኖች ከሀገር እንዲጠፉና ቁጥራቸው እንዲቀንስ ተደርጓል፡፡ በዚህ ምክንያት በሁለት መቶ ዓመታት ውስጥ እየጠፉ መጥተው በ1900 ዓም አካባቢ ቁጥራቸው ወደ 96 ሺ ወርዶ ነበር፡፡ አሁን ከጠቅላላው ሕዝብ 2 በመቶ ብቻ ናቸው፡፡ እሥር ቤት ስሄዱ ግን 25% እሥረኞች እነርሱ ሆነው ታገኛላችሁ፡፡ ልክ በአሜሪካ አፍሪካ አሜሪካውያን ከጠቅላላ ሕዝቡ 30 በመቶ ቢሆኑም እሥር ቤት ግን 60 ከመቶ እንደሆኑት ዓይነት ማለት ነው፡፡ 

አንዳንድ ጊዜ ለነጻነታችን ለተዋጉት አርበኞች ክብር የምትሰጡት ይህን መሰል የመከራ ታሪኮችን ስትሰሙ ነው፡፡ ‹በኋላ የመጣ ቀንድ በፊት የመጣን ጆሮ በለጠው› እንደተባለ በኋላ ሀገር የወሰዱት ዜጎች ክብሩንም፣ ነጻነቱንም፣ ኢኮኖሚውንም፣ ሥልጣኑንም ነጥቀውት ባላገሩን ሁለተኛ ዜጋ ሲያደርጉት ስታዩ ‹ነጻነት ሆይ ዋጋሽ ምን ያህል ነው?› ትላላችሁ፡፡ አንዳንድ ወገኖቼ ‹ጥቂት ቅኝ ብንገዛ ኖሮ እንሠለጥን ነበር፣ እናድግም ነበር› ብለው ይቆጫሉ፡፡ በእሳት የሚጫወት የአበራሽን ጠባሳ ያላየ ብቻ ነው፡፡ ባይሆን እኛ ‹ነጻነትን አላግባብ በመጠቀም ወንጀል›› ልንቀጣ የሚገባን ሕዝቦች ነን፡፡ ነጻነታችንን ለዕድገትና አንድነት፣ ለብልጽግናና ለመልካም አስተዳደር ከመጠቀም ይልቅ ለጦርነት ተጠቅመንበታል፡፡ የውጭ ወራሪዎችን ተከላክለን ራሳችን በራሳችን ስንዋረር ኖረናል፡፡ ነጻነትን ለጦርነት የመጠቀም ልማዱ አልለቀን ስላለም በአንጻራዊነት የመብት ነጻነት ተከብሮባቸዋል ወደሚባሉት ሀገሮች ስንገባ እንኳን ‹የዘሬን ያንዘርዝረኝ› ብለን ጦርነቱን ቀጥለነዋል፡፡ በሀገር ቤትም ሆነ በውጭው ዓለም ያሉ የፓርቲና የኮሙኒቲ፣ የሚዲያና የኪነ ጥበብ፣ የቤተ እምነትና የማኅበራዊ ተቋማት አደረጃጀቶቻችን ሁሉ የጦርነት አደረጃጀቶች ናቸው፡፡ የህልውናችን መሠረቱ ጠላት ነው፡፡፡ ያለ ጠላት ህልው መሆን ስለማንችል ጠላት ካጣን ጠላት እንፈጥራለን፡፡

‹እንግዳ ሆነሽ ትመጭ ባለቤት ሆነሽ ትቆጭ› እንደሚባለው በኋላ ዘመን የመጡትና ባለቤትነቱን የወሰዱት እንግሊዞች እነዚህን ነባር ሕዝቦች እንዳይድኑ አድርገው ሰብረዋቸዋል፡፡ ዛሬ ምንም እንኳን ችግሩ የተቀረፈ፣ መንግሥትም ለተፈጸመው ግፍ ይቅርታ የጠየቀ፣ እነርሱን የሚደግፍ ሕግም ያወጣ ቢሆን አካላዊ፣ ባህላዊና ሞራላዊ ህልውናቸውን እንዲያጡ በመደረጉ የተነሣ ወደ ጥንቱ ክብራቸው ለመመለስ አልቻሉም፡፡ እንግሊዞቹ እነዚህን ሕዝቦች ከምቹ የመኖርያ ሥፍራዎች በማስለቀቅ ወደ በረሃማውና ለኑሮ አስቸጋሪ ወደሆነው አካባቢ ገፍተዋቸዋል፡፡ ለብዙ ዘመናት ትምህርትና ሥልጣኔ እንዳይቋደሱ ተደርጓል፡፡ ከዚህ ይልቅ መጠጥና አደንዛዥ ዕጽ በአካባቢያቸው እንዲስፋፋ አድርገዋል፡፡ የቤተሰብን ማኅበራዊነት በመበተን ወላጆችና ልጆች እንዲለያዩ አድርገዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ ተደምረው ዛሬም የአውስትራልያ አቦርጅኖች በሀገራቸው ሙሉ በሙሉ የሚያዝዙ አልሆኑም፡፡

ከአውሮፓውያን መካከል አውስትራልያን ለመጀመሪያ ጊዜ የጎበኛት ሆላንዳዊው አሳሽ ዊልያም ጃንስዘን ነው፡፡ ዊልያምስ በሰሜን አውስትራልያ የረገጠውን መሬት ‹አዲሲቷ ሆላንድ› ብሎ ሰየመና የሀገሩ ግዛት አደረጋት፡፡ እርሱን ተከትሎ ወዲያው የመጣ አውሮፓዊ ሠፋሪ ግን አልነበረም፡፡ ከእርሱ በኋላ ዊልያም ዳምፐር የተባለ እንግሊዛዊ በሰሜናዊ ምዕራብ አውስትራልያ በ1688 ደረሰ፡፡ እንግሊዞች ወደ አውስትራልያ እግራቸውን መስደድ የጀመሩት ከዚያ ጊዜ በኋላ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ በ1770 ጄምስ ኩክ በተባለ መቶ አለቃ አማካይነት ወደ ምሥራቃዊው አውስትራልያ ክልል በመምጣት በእንግሊዙ ንጉሥ ጆርጅ ሦስተኛ ስም አካባቢውን ያዙና ‹ኒው ሳውዝ ዌልስ› ብለው ጠሩት፡፡

እንግሊዞች ወደ አውስትራልያ ፊታቸውን እንዲያቀኑ ያደረጓቸው ብዙ ምክንያቶች ነበሩ፡፡ በአንድ በኩል የአሜሪካ ግዛታቸው ነጻ መውጣት የእርሻ ቦታቸውን ነጥቋቸዋል፡፡ ስለዚህም ሌላ ቦታ በማፈላለግ ላይ ነበሩ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ወንጀለኞቻቸውን ያሥሩባት የነበረችው አሜሪካ ነጻ መውጣቷ ሌላ የወንጀለኞች ማሠሪያ እንዲያፈላልጉ አስገድዷቸው ነበር፡፡

እንግሊዞች ወታደሮቻቸውንና ወንጀለኞችን ይዘው በ1788 ዓም ወደ አውስትራልያ በመምጣት በሲድኒ በኩል አካባቢውን እያጸዱ መቆጣጠር ጀመሩ፡፡ በአሜሪካ የባሮችን ጉልበት ያጡት እንግሊዞች በአውስትራልያ የእሥረኞችን ጉልበት መጠቀም ጀመሩ፡፡ እየቆዩም ከተለያዩ ሀገሮች የመጡ ስደተኞች ተቀላቀሏቸው፡፡  

ዛሬ በአውስትራልያ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከ220 በላይ ሀገር ሰዎች ይኖሩባታል፡፡ ምንም እንኳን ዋናው ኦፊሴልዊ ቋንቋዋ እንግሊዝኛ ቢሆን ከ224 ቋንቋዎች በላይም ይነገሩባታል፡፡ የፌዴራል ሥርዓት የምትከተለው አውስትራልያ የሀገሪቱ ርእሰ ብሔር የእንግሊዟ ንግሥት ናት፡፡ (በነገራችን ላይ ንግሥቲቱ ካናዳን ጨምሮ የ16 ሀገሮች ርእሰ ብሔር ናት) የ2006 ዓም የሀገሪቱ የቆጠራ ውጤት እንደሚገልጠው ከሕዝቡ ቁጥር ሩብ ያህሉ ከተለያየ ሥፍራ መጥቶ የሚኖር ነው፡፡ ጣልያኖች፣ ቻይናዎች፣ ቬትናሞች፣ ሕንዶችና ፊሊፒኖች ከስደተኞቹ መካከል ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ፡፡ ከአፍሪካ አህጉር ብቻ ከ48 ሀገሮች የመጡ ስደተኛ ነዋሪዎች በአውስትራልያ ይገኛሉ፡፡

በ2006 ዓም የተደረገው የአውስትራልያ ሕዝብ ቆጠራ በሀገሪቱ 7516 ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩ ይገልጣል፡፡ ነባር ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ግን ቁጥሩን የዚህ ሦስት እጥፍ አካባቢ ያደርጉታል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ለቆጠራው ቅጽ ትኩረት ባለመስጠታቸው እንደማይሞሉት፣ አንዳንዶቹም የቋንቋው ችግር ሳይረዱት እንዲቀሩ እንደሚያደርጋቸው፣ ሌሎቹም ከቆጠራው በኋላ በብዛት መምጣታቸውን እንደ ምክንያት በመውሰድ የኢትዮጵያዊውን ቁጥር እስከ ሃያ ሺ ያደርሱታል፡፡ የአውስትራልያ መንግሥት ቆጠራ እንደሚያሳየው 26 በመቶዎቹ የሀገሬ ልጆች በሹፍርናና ማሽኖችን በማንቀሳቀስ፣ 24.3 በመቶዎቹ በጉልበት ሥራ፣ 16.3 በመቶዎቹ በአገልግሎት ዘርፍ፣ 33.5 በመቶዎቹ ደግሞ በአስተዳደር፣ በጸሐፊነት፣ በቴክኒክ ሥራ፣ እንዲሁም በሌላ ሞያ ነክ ሥራ መሠማራታቸውን ያሳያል፡፡ በሀገሪቱ ከሚኖሩት ኢትዮጵያውያን መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት እዚህ እኔ ያለሁበት ቪክቶርያ ግዛት፣ ሜልበርን ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ናቸው፡፡

አዳሙ ተፈራ ‹ገመናችን በሰው ሀገር› ብለው በጻፉት መጽሐፍ ላይ እንደገለጡት ወደ አውስትራልያ ለመጀመሪያ ጊዜ የገቡት ኢትዮጵያዊ አቶ አዲስ ታምሩ ይባላሉ፡፡ እኒህ በ1965 ዓም ወደ አውስትራልያ የገቡት የኢትዮጵያ አየር ኃይል ባልደረባ ለትምህርት መጥተው ነው በዚሁ የቀሩት፡፡ ዛሬ ከሀገሩ ነባር ነዋሪ (አቦርጅን) ጋር ተጋብተው ይኖራሉ፡፡

እዚህ የሚኖሩ የሀገሬ ልጆች ብዙ አስገራሚ፣ ብዙ አስቂኝ፣ ብዙም አሳዛኝ ገጠመኝ አላቸው፡፡ እድሜና ጤና ከሰጠን አብረናቸው እናዝናለን፣ እንስቃለን፣ እንሳቀቃለንም፡፡

ሜልበርን፣ አውስትራልያ

በትናንትናው እለት ሁለት የአንድነት ፓርቲ የእስቀሳ ቡድን አባላት ፍቼ ከተማውስጥ ከፍተኛ ድብደባ እንደተተፈፀመባቸው መግለጻችን ይታወሳል፡፡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል ሶስት ከተሞች “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ለቅስቀሳ ወደ ፍቼ ካቀኑት የፓርቲው አመራሮችና አባላት መካከል ትላንት ነሃሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ በከተማው የፀጥታ ዘርፍ ምክትል ሀላፊ […]

የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መርህ የአንድነት ፓርቲ የሚያደርጋቸዉን፣ አገረ ሰፊ ሰላማዊ እንቅስቃሴዎቹን በስፋት ገፍቶበታል። በኦሮሚያ በሚገኙ ሶስት ታላላቅ ከተሞች፣ አዳማ/ናዝሬት፣ ባሌ ሮቢና ፍቼ ሰላማዊ ሰልፎች እንደሚያደርግ፣ ለከተሞቹ ባለስልጣናት ያሳወቀ ሲሆን ፣ ቅስቀሳዎችንም በስፋት አያደረገ ነዉ። ከጥቂት ሰዓታት በፊት ፣ ሰላማዊ ሰልፉን ለማስተባበር ወደ ፍቼ ያቀኑ ሁለት የአንድነት ፓርቲ አሰተባባሪዎች በአገዛዙ ካድሬዎች ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው ሲሆን፣ […]

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢሳት የወረዳው ምንጮች እንደገለጹት ከተባረሩት ሰራተኞች መካከል 2 አቃቢ ህጎች፣ 2 ዳኞች ፣ 1 ፍርድ ቤት ሬስጅስትራርና አንድ ፖሊስ ይገኙበታል። 8 ሰዎች ደግሞ ከስራ ገበታቸው ላይ ለቅቀው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተሰደዋል። የሚታሰሩ ሰዎች እየተበራከቱ መምጣቱን የሚናገሩት ምንጮች፣ 16 ሰዎች ሰሞኑን ተይዘው ታስረዋል። ካለፈው ወር ጀምሮ በቁጥጥር ስር …

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቡሬ ግንባር የሰፈረው የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተለያዩ ጊዜያት የአፋር ሴቶችን አስገድደው እንደሚደፍሩ ከስፍራው ደረሰን መረጃ አመለከተ። የሰራዊቱ አባላት ለቅኝት ወይም ለተለያዩ ስራዎች በሚወጡበት ጊዜ ግመል እና ፍየል የሚጠብቁ ሴቶች ሲያገኙ በሀይል ይድፍራሉ። ነሀሴ 3 ቀን 2005 ዓም አንዳባ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ሀሊማ አህመድ የሱፍ የተባለች እድሜዋ ከ45 …

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለሳምንታት መብራት የተቋረጠባቸውን አካባቢዎች በማስመልከት ዘገባውን ያጠናከረው ዘጋቢያችን እንደሚለው በየጊዜው እየሄደ ሳይታሰብ የሚመጣው የኤሌክትሪክ ሀይል፣ መንግስት ላለፉት 21 ዓመታት ገነባሁት የሚላቸው የሀይል ማመንጫዎች የት እንደደረሱ ጥያቄ የሚፈጥር ነው። ያለምንም መብራት መቋረጥ አንድ ሳምንት መድፈን ብርቅ ነው የሚለው ዘጋቢያችን፣ በተለይ የህክምና መስጫ ተቋማት ከመብራት …

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰንደቅ እንደዘገበው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አንዳንድ ሰራተኞች የኢህአዴግ የ2006 እቅድ መስሪያ ቤቱ ካለበት መደበኛ ስራ ውጪ የገዢውን ፓርቲ ድርጅታዊ ስራ በልዩ ሁኔታ እንዲያስፈፅም ማስገደዱን እየተቃወሙ ነው።አብዛኛዎቹ ሰራተኞች ሚኒስቴሩ በ2006 ዓ.ም ድርጅታዊ ስራን ትኩረት ሰጥቶ እንዲተገብር መድረጉ ሰራተኛው ያለፍላጎቱ የመንግስትንና የድርጅትን ስራ ቀይጦ እንዲሰራ የሚያስገድድ ነው ብለዋል። ለጋዜጣው …

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሲኤን ኤን፣ ቢቢሲ እና ሌሎችም ታዋቂ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን የተለያዩ የፖለቲካ ተንታኞችን በማነጋገር እንደዘገቡት የቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከእስር መፈታት ግብጽን በድጋሜ ከሁለት ሊከፍላት ይችላል። አንዳንድ ተንታኞች እንደሚሉት ሙባረክን ለማውረድ የታገሉ ወጣቶች ምናልባትም ራሳቸውን ከሙስሊም ብራዘርሁድ ጋር በማቀናጀት በስልጣን ላይ ባለው መንግስት ላይ ሊዘምቱ ይችላል። ይሁን …

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወጣቱ ዙከርበርግ እንደገለጸው ድርጅቱ ከኤሪክሰን፣ ኖክያ፣ ኦፔራ፣ ኳልኮም እና ሳምሰንግ ጋር በመተባበር በሞባይል መረጃ ላይ የሚጠየቀው ክፍያ እንዲቀነስ ያደርጋል። በማደግ ላይ ያሉ አገሮች የኢንተርኔት አግልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ ለማመቻቸት እንደሚሰራ ዙከርበርግ ተናግሯል። አንዳንድ ባለሙያዎች በበኩላቸው የአፍሪካውያን ችግር የኔትወርክ እና የሀይል አቅርቦት ችግር መሆኑን በመጥቀስ በዚህ በኩል ቅድሚያ …