ሰበር ዜና ከባሌ ሮቤ – የባሌ ሮቤው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ አፈና ተፈፀመበት – ፍኖተ ነጻነት
አንድነት ታርቲ ዛሬ በባሌ ሮቤ የሚያደርገውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በኦህዴድ ባለስልጣናትና በደህንነት ሀይሎች አፈና ተፈፀመበት፡፡ ሰልፉን ለማደናቀፍ የአካባቢው ባለስልጣናት ትላንት ምሽት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ካረፉበት ታይታኒክ ሆቴል ንብረታቸውን ሳይዙ በግዳጅ እንዲወጡ ከመደረጉም በላይ አብዛኞቹ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና የቅስቀሳ ቡድን አባላት ታግተዋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና የቅስቀሳ ቡድን አባላት ደህንነት አደጋ ላይ እንደሆነም ከስፍራው የተገኙ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው፡፡ በባሌ ሮቤው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ መንግስት ያደራጃቸው ሀይሎች ሁከት ለመፍጠር መዘጋጀታቸው በመታወቁ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረኃይል ሰልፉ እንዲሰረዝ ወስኗል፡፡ እስካሁን ድረስ ባለን መረጃ የአንድነት ፓርቲ የባሌ ዞን አመራሮች በባሌ ሮቤ ከሚገኙ የአንድነት ፓርቲ ተወካዮች ጋር መገናኘት አልቻሉም፤ በመንግስት ሀይሎች ታፍነው ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡ #Millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ