መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት _IOM ባወጣው ዘገባ ህይወታቸው በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 131 ኢትዮጵያውያንን ከጅቡቲ ወደ አገራቸው መልሷቸዋል። ከተመላሾቹ መካከል 100 ያህሉ ኢትዮጵያውያ ወደ የመን ለመጓዝ በዝግጅት ላይ እንደነበሩ ድርጅቱ አስታውቋል። 28 ኢትዮጵያውያን ደግሞ ከየመን ወደ ጅቡቲ በባህር ላይ ጉዞ አድርገው የደረሱ ናቸው። በሰላም ወደ አገራቸው ከተመሰሉት መካከል …

መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን በአለፋ ጣቁሳ ወረዳ በሻውራ ከተማ የከተማዋ ነዋሪዎች ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ ውሃ በማጣታቸው መቸገራቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። አንድ ጀሪካን ውሃ እስከ 20 ብር ለመግዛት ተገደናል የሚሉት ነዋሪዎች ምክንያቱም ሙስና ነው ይላሉ። የወረዳው መስተዳደር 300 ሺ ብር የተገዛውን ጄኔረተር 800 ሺ ብር እንደተገዛ አድርጎ ማቅረቡን የሚናገሩት …

መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሱዳን ትሪቢውን የግንባሩን ሊቀመንበር ተዋት ፖል ቻይን ጠቅሶ እንደዘገበው ፣ የደቡብ ሱዳን አማጽያን፣ የሳልቫኪር መንግስት ለኢትዮጵያ አርበኞች አንድነት ግንባር ወታደራዊ ስልጠና፣ የገንዘብ እንዲሁም የሎጅስቲክ ድጋፍ ያገኛል በሚል ያቀረበው ወቀሳ ተቀባይነት የሌለው ነው። አማጽያኑ የፖል ቻይ ጦር ወደ ጋምቤላ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም አስቧል በማለት ክስ አሰምተው ነበር። ፖል …

መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እንድ ራዲዮው ዘገባ  ትናንትና አንዲት ወጣት አይነስውር ድልድዩን ስትሻገር ገደል ውስጥ ገብታ ህይወቷ አልፏል። ይህ  ቀጭኔ መድህኒ ዓለም አካባቢ ያለው ድልድይ በቀኝና በግራ በኩል አደጋ መከላከያ ድጋፍ የሌለው በመኾኑ ለሰዎች መጥፋት ምክንያት እየሆነ መምወጣቱን የ አካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። አካል ጉዳተኞችን ለአደጋ የሚያጋልጡ ከደረጃ በታች የሆኑ ድልድዮች  በከተማው …

(በቴክኖሎጂስት ዳንኤል አማረ)

መነሻው ምን እንደሆነ በዉል ሳያዉቁት በጀርባ ህመም ተሰቃይተዋል? የጀርባ ህመም በአደጋ ብቻ ላይከሰት ይችላል የአቀማመጥ ሁኔታ፣ የሚጠቀሙት ጫማ፣ ከመጠን ያለፈ ዉፍርትና ከባድ ነገሮችን ማንሳት የላይኛዉና ታችኛው ጀርባ ህመም ያስከትላል።
በሴቶችና ወንዶች ላይ የጀርባ ህመም የሚያስከትሉ መነሻ ምክንያቶችን በዝርዝር እንመልከታቸው፦
1. የቢሮ ወንበር

የቢሮ ወንበርዎ ለጀርባ ህመም ከፍተኛ…

ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ 4002 Blacksmith Drive, Garland, TX 75044; Tel: (214)703 9022  www.globalallianceforethiopia.org; E-mail: [email protected] ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚታወቀው፤ “የኢትዮጵያ ጨፍጫፊ” በመባል ለሚታወቀው ለሮዶልፎ ግራዚያኒ፤ አፊሌ በምትሰኝ የኢጣልያ ከተማ አንድ የመታሰቢያ ኃውልትና መናፈሻ ተቋቁሞለት፤ የቫቲካን ተወካይ በተገኙበት፤ …

ጋዜጣዊ መግለጫ – የፋሺሽቱ የግራዚያኒ ኃውልት ስያሜ መወገድ Read more »

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

አቡበከር አህመድ  መንግስት በሴኩላሪዝም ስም ህብረተሰቡን በተለይ ሙስሊሙን ማህበረሰብ ከእምነቱ ለማስወጣት የሚያደርጋችውን ጥረቶች አጠናከሮ የቀጠለ ሲሆን የዚህ እቅድ አንደ አካል የሆነወን ድርጊቱን ማንኛዉም አይነት የእምነት አዲስ ተቋማት በአድስ አበባ ከተማ ዉስጥ እንዳየገነቡ በሚል መመራያ ማዉጣቱን ምንጮች አስታዉቀዋል። በየትኛዉ እምነት አማኞች ፈጣሪያቸውን በአንድነት የሚያመልኩበት ቦታና የእምነቶቻቸውን ጥሪ የሚያደርጉበት ቦታ የእምነት የእምነት ተቋማቸዉ ሆኖ እያለ ከተማዋ እጅጉን […]

የኢትዮጵያ መንግስትን በጦር ሀይል ለመጣል ሚታገሉት “የኢትዮጵያ የተባበሩት አርበኞች ግንባር” በደቡብ ሱዳን ግጭት ውስጥ ከፕሬዘዳንት ሳልቫኪር ሀይል ጎን ተሰልፎ የተቃዋሚውን የሪክ ማቻርን ሀይሎች ይወጋል በሚል የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ አደረጉ. በሪክ ማቻር የሚመሩት የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚዎች በቅርቡ እንዳስታወቁት ከሆነ በምእራብ ኢትዮጵያ ጋምቤላ ክልል ሚንቀሳቀሰውና በቀድሞው የአካባቢው አስተዳዳሪ በሆኑት በቶዋት ፓልቻይ የሚመራው የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ኢትዮጵያን ለመውጋት […]

The post የኢትዮጵያ አማጺያን በደቡብ ሱዳን ተቃዋሚዎች የቀረበባቸውን ክስ አጣጣሉ appeared first on ሳተናው .

በቨርጂኒያ ሀገረ ግዛት ፣ በሬገን ብሄራዊ የአየር ማረፊያ ተርሚናል ውስጥ አብርሀም ዘመድአገኘሁ የተባለ፣ መስማት የተሳነው እና የጎዳና ተዳደሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ወንድማችን ምንም በማያውቀው እና ባልፈፀመው ወንጀል አይፓድ ሰርቀሀል በሚል በፖሊስ ተይዞ ለስድስ ሳምንታት በወይህኒ ቤት አሳልፏል። አብርሀም ከተያዘበት ሰአት ጀምሮ ለሀያ አራት ሰዓታት በምን ምክንያት እንደታሰረ ካለማወቁም በተጨማሪ ያረፈበት የእስር ቦታ ( jail ) መስማት […]

የኬንያ መንግስት የዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያን ሊዘጋ መሆኑን የጀርመን የዜና ወኪል ዘገበ። በጣቢያው የሚገኙ ከ500 ሺ በላይ የሶማሊያ ስደተኞች የአሸባብ ታጣቂ ቡድን ወደ ማይገኝባቸው የሶማሊያ ግዛቶች እንዲመለሱ ይደረጋል ተብሏል። የኬንያ መንግስት ከዚህ ውሳኔ የደረሰው በጋሪሳ ከተፈጸመው ጥቃት በኃላ መሆኑን የዜና ወኪሉ ጨምሮ ዘግቧል።

በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በተመላሽነት ለመመዝገብ ፓስፖርት ወይም መታወቂያ ያስፈልጋል ተባለ። ኢትዮጵያ በየመን የሚገኙ ዜጎቿን ለመመለስ የምታደርገው ጥረት ግን አዝጋሚ ነው ተብሏል።

የጀርመን የመጀመሪያው መራኄ መንግሥት የኦቶ ፎን ቢስማርክ 200ኛ ዓመት የልደት በዓል ባለፈው ሳምንት ታስቧል ። ከ200 ዓመት በኋላ አሁንም ጀርመናውያን ስለ ቢስማርክ የሚሰጡት አስተያየት በሁለት የተከፈለ ነው ። ቢስማርክ ማንናቸው ?

የዓለም የጤና ቀን በየዓመቱ በጎርጎሪዮሳዊዉ የዘመን ቀመር ሚያዝያ ሰባት ቀን ይታሰባል። የዓለም የጤና ድርጅት የዘንድሮዉን የዓለም የጤና ቀን ያሰበዉ «የሚመገቡት ምግብ ምን ያህል ለጤና ተስማሚ ነዉ» በሚል መሪ ቃል ላይ ተመስርቶ ነዉ።

ክቡር አቶ አባይ ፀሐዬ የህ.ወ.ሓ.ት/ኢህአዴግ መስራች አባል ታጋይና በአሁኑ ግዜ በሚኒስትር ማአርግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማእከል ዋና ዳይርክተር ናቸው፡፡ ከጋዜጠኛ ዘርአይ ሀ/ማርያም በኦህዴድ ታሪክና የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳዮች ቆይታ አድርገዋል፡፡ ሙሉ ቃለ-ምልልሱ ከዚህ በታች በጽሑፍ የቀረበ ሲሆን፤ ቪዲዮውን ደግሞ ከታች መመልከት ይችላሉ፡፡ —— ዘርአይ ኃ/ማርያም:- በትጥቅ ትግሉ ዘመን ኦህዴድ የኢህአዴግ አንድ አባል ድርጅት ሆኖ መቆሙ የነበረው ፋይዳ ምን ነበር? አቶ አባይ ፀሐዬ፡- የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ አንድ የኢህአዴግ አባል ድርጅት ሆኖ መደራጀቱ በመጋቢት 1982 ዓ.ም ፋይዳው ከዛ በፊት የኦሮሞ ህዝብ በዴሞክራሲያዊ አላማ ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝብ አስተሳስሮ የሚያታግለውና የሚመራው ዴሞክራሲያዊ ድርጅት በማጣቱ የተፈጠረ ድርጅት ነው፡፡ ከዛ በፊት የነበረ የኦሮሞ ህዝብ ትግል የብሄር ጭቆናው የሌላው በደልንም ከተጀመረበት /ከተፈጠረበት ግዜ ጀምሮ ሲታገል የቆየ ህዝብ ነው፡፡ በብሄራዊ መብቱም ለአጠቃላይ የኢኮኖሚያዊና ዴሞክራሲያዊ አጠቃላይ መብትም፡፡ ግን ከዛ በፊት የነበሩ ድርጅቶች የተለያዩ በኦሮሞ ህዝብ ስም የተደራጁ ድርጅቶች ቢኖሩም አንደኛ ጠንካራ የህዝብ ድጋፍ እና ጠንካራ የህዝብ ማደራጀት ስራ አልነበረባቸውም፡፡ ወደ ህዝብ ገብተው ህዝቡን አደራጅተው ከህዝቡ ጋር ሆኖ የህዝቡን ስሜት አዳምጠው ሀይል የፈጠሩ አቅም የፈጠሩ ጠንካራ ድርጅቶች ጠንካራ የትጥቅ ትግል ሰራዊት የፈጠሩ አልነበሩም፡፡ ስለዚህ እየተደነቃቀፉ እየተኳላሹ ወደ አጎራባች ሀገሮች ወጣገባ እያሉ ነው ግዚያቸውን ያሳለፉትበአብዛኛው፡፡ ሁለተኛ መላውን የአማራ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝብ እንደጠላት የሚወስዱ ናቸው የነበሩ፡፡ ይህ ደግሞ የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎትና ጥያቄ አልነበረም፡፡ የህዝቡ ጥያቄ የፖለቲካ ዲሞክራሲ የማንነትና የኢኮኖሚ […]

የኢትዮጵያ መንግስትን በጦር ሀይል ለመጣል ሚታገሉት “የኢትዮጵያ የተባበሩት አርበኞች ግንባር” በደቡብ ሱዳን ግጭት ውስጥ ከፕሬዘዳንት ሳልቫኪር ሀይል ጎን ተሰልፎ የተቃዋሚውን የሪክ ማቻርን ሀይሎች ይወጋል በሚል የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ አደረጉ. በሪክ ማቻር የሚመሩት የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚዎች በቅርቡ እንዳስታወቁት ከሆነ በምእራብ ኢትዮጵያ ጋምቤላ ክልል ሚንቀሳቀሰውና በቀድሞው የአካባቢው አስተዳዳሪ በሆኑት በቶዋት ፓልቻይ የሚመራው የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ኢትዮጵያን ለመውጋት […]

ባሳለፍነው ሐሙስ በሰሜን ኬንያ በሚገኘው ጋሪሳ ዩኒቨርስቲ ሰቅጣጭ ዜና የሰማንበትን ድርጊት የመራው የቀድሞው የናይሮቢ ዩኒቨርስቲ የህግ ተማሪ የነበረው የ24 ዓመቱ ሞሀመድ አብድራሂም አብዱላሂ መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
የሙሀመድ ወላጅ አባት አብዱላሂ ዳቃሪ የመንግስት ከፍተኛ ስልጣን የያዙና በጃምሁሪ አካባቢ የሚገኘውን ማንዴራ የተሰኘ ክልል የሚያስተዳድሩ መሆናቸውም ነገሩን አወዛጋቢ አድርጎታል፡፡
በናይሮቢ ዩኒቨርስቲ የህግ ዲፓርትመንት ቆይታው በጓደኞቹ አባብሞ እየተባለ ይጠራ የነበረው ሞሀመድ ዘናጭ ውድ ሱፎችን የሚያዘወትርና ፑል መጫወት የሚያዝናናው ነበር፡፡
በዩኒቨርስቲው የሚተኛበት ክፍል ቢኖረውም ዶርሙን የተጠቀመው በጣት ለሚቆጠሩ ቀናቶች ብቻ ነበር፡፡ለምግብ ማብሰያ የሚሆን ጋዝ በኢስትሌይ አካባቢ በመሸጥ ይተዳደር ስለነበርም በዶርም ለማይቆይባቸው ጊዜያቶች ስራውን እንደምክንያት ያቀርብ ነበር፡፡የክፍል ጓደኞቹም ከእነርሱ የተሻለ ገንዘብ የሚያገኘው ከስራው የተነሳ እንደሆነ ያምናሉ፡፡
በዩኒቨርስቲው ከሙሃመድ ጋ ፑል የተጫወተው ዴዳን ዋቼራ ‹‹በአንድ ወቅት ጠይቄው ነበር፡፡ነገር ግን የምሩን ይሁን እየቀለደ ባይገባኝም የሚለብሳቸው ሱፎች ዋጋ 16.000የኬንያ ሽልንግ (160ዶላር)መሆናቸውን ነግሮኝ ነበር፡፡ነገር ግን ሱፎቹ በጣም ውድ ይመስሉ ነበር፡፡በእርግጥ የእኔን ሱፍ አዘጋጅ ለመጀመሪያ ግዜ ያስተዋወቀኝ እርሱ ነው፡፡››
ዋቼራ የቀድሞ ጓደኛውን ሲገልጸው ‹‹ጥሩ ተናጋሪ፣በህግ ክፍል በሚደረጉ ክርክሮች የሚሰማውን ለመናገር የማይፈራ ››ብሎታል፡፡ነገር ግን ከሚለብሰው ሱፍ ስር የሚገኘው ልቡ በጥላቻ የተሞላና በሃይማኖት አክራሪነት የናወዘ መሆኑን ማንም ሳያውቅለት እስከ ሀሙሱ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ድረስ ቆይቷል፡፡

አይ ሲ አይ ሲን የመቀላቀል ህልሙ
ጦማሪና ጋዜጠኛ የሆነው ያሲን ጁማ በግል ድረ ገጹ አብዲራሂም መኖሪያ ቀዬውን ከለቀቀ በእርግጠኝነት አል ሻባብን ወይም አይ ሲ አይ ሲን ለመቀላቀል እንደሚሆን አትቷል፡፡እንደ ጦማሪው ከሆነ የአብዲራሂም የመጀመሪያ ፍላጎት አይ ሲ አይ ሲን መቀላቀል ነበር፡፡ነገር ግን ፓስፖርት ስላልነበረው ወደ ኢራቅ ወይም ሶሪያ ማምራት አልቻለም፡፡

ጦማሪው የአብዲራሂም ከየሁለተኛ ደረጃ ጀምሮ የክፍል ጓደኛ የነበረው ዋሚ ወደ ቱርክ በማምራት ወደ ሶሪያ በመሻገር አይ ሲ አይ ሲን ተቀላቅሏል፡፡ነገር ግን ልክ እንደ አብዲራሂም ሁሉ ዋሚም በናይሮቢ ዩኒቨርስቲ በዲግሪ መርሐ ግብር የጀመረውን የህግ ትምህርት ሳያጠናቅቅ ቀርቷል፡፡

ሁለቱ ወጣቶች የከፍተኛ ትምህርት መርሐ ግብራቸውን ሳያጠናቅቁ የቀሩት ሽብርተኛ ለመሆን ከነበራቸው ፍላጎት የተነሳ ሳይሆን እንዳልቀረ አንድ የትምህርት ቤት ጓደኛቸው ለዴይሊ ኔሽን ተናግሯል፡፡
የማንዴራ ካውንቲ ኮሚሽነር አሌክስ ኮዮ ለኔሽን እንዳስረዱት ከሆነ የአብዲራሂም ወላጅ አባት ልጃቸው በተለየ የስልክ ቁጥር ሲደውልላቸው የት እንደሆነ ሲጠይቁት ስልኩን እንደሚዘጋው ለፖሊስ ሪፖርት አድርገው ነበር፡፡
ከጋሪሳ የተማሪዎች ጥቃት በኋላ ፖሊስ የገደላቸውን አራት የአል ሻባብ ታጣቂዎች ማንነት በቲዊተር አማካኝነት ለእይታ ሲያቀርብ ዋቼራ ከሟቾቹ መካከል የቀድሞው የዩኒቨርስቲ ጓደኛው መኖሩን ለመለየት ጊዜ አልወሰደበትም፡፡
ባሳለፍነው ቅዳሜ በጋሪሳ የተገደሉትን የአልሻባብ ታጣቂዎች የሚያሳይ ፎቶ ፖሊስ ለአካባቢው ነዋሪ ሲያቀርብ ብዙዎች አብዲራሂምን ለይተውታል፡፡

Source: freedom4ethiopian.wordpress.com/

(ኃይለሚካኤል ዘስላሴ) በዓለም ያለት የተለያዩ የሕግ ሥርዓቶች ከሚሰማሙባቸው የሕግ ጽንስ ሐሳቦች አንዱ የሕጋዊ ሰውነት ጽንስ ሐሳብ ነው፡፡ በዚህ ጽንስ ሐሳብ መሠረት ከተፈጥሮ ሰው በተጨማሪ እንደተፈጥሮ ሰው የሚቆጠር ወይም ሰው የሆነ አካል አለ፡፡ በዚህም መሠረት ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ ማለት ነው፡፡ አንደኛው ሰው የተፈጥሮ ወይም ግለ ሰብ ሲሆን ሁለተኛው ሰው ደግሞ በሕግ የሰውነት መብት (ግዴታም ጭምር) ያለው ወይም የተሰጠው አካል ማለትም ማኅበር፣ የንግድ ማሕበር ወይም ድርጅት ነው፡፡ በመሠረቱ ማነኛውም ሰው የተፈጥሮም ይሁን በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ወይም ያለው አካል የመብትና የግዴታ ባለቤት ነው፡፡ በዚህም ውል መዋዋል፣ የነብረት ባለቤት መሆን፣ መክሰስና መከሰስ ይችላል፡፡ ከቤተሰብ ሕጎች እና ከአንዳንድ የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎች በስተቀር የየአገሩ ሕጎች በተፈጥሮ ሰውና በሕግ የሰውነት መብት ያለው አካል በእኩልነት ተፈጻሚነት አላቸው፡፡ የተፈጥሮ ሰው የመብትና ግዴታ ባለቤት የሚሆነው እና በሕግ ኃላፊነት የሚኖረው በተፈጥሮ ሰው በመሆኑ ነው፡፡ ግዑዝ የሆኑ አካላት ማለትም ማሕበራት የንግድ ማኅበራት እንዲሁም ድርጅቶች እንደ ተፈጥሮ ሰው የሚቆጠሩትና በሕግ የሰውነት መብት ይጣቸዋል የሚል ጥያቄ ለመመለስ በርካታ ንደፈ-ሐሳቦች ተቀምሯል፡፡ እነዚህ በርካታ ንድፈ-ሐሳቦች በሁለት ክፍሎች ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያወ ምናባዊ ወይም ሕግ ወለድ ንድፈ ሐሳብ (fiction theory) የሚባለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እርግጠኛ ንድፈ ሀሳብ (Real theory) በመባል የሚታወቀው ነው፡፡ እነዚህ ንደፈ ሃሳቦች ጥልቅ መሠረት እና ትንታኔ ያላቸውና አመሠራረታቸውና ዕድገታቸው ሰፊ እና ከመንስት አመሠራረት ጋር የተያያዘ ቢሆንም ለአጠቃላይ ግንዛቤ ይረዳል በሚል በሁለቱም ንድፈ […]

click here for pdf

በቤተ ክርስቲያን የጸሎት ሕይወት ውስጥ ታላቅ ቦታ ካላቸው ቅዱሳት መጻሕፍት አንዱ ‹መጽሐፈ ግብረ ሕማማት› ነው፡፡ ሊቃውንቱ ‹ግብር› የሚለውን ‹አገልግሎት› ብለው ይተረጉሙትና ‹ግብረ ሕማማት› ማለት ‹በሕማማት ወቅት የሚፈጸም አገልግሎት› ማለት ነው ይላሉ፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ‹እርሱ ሕመማችንን ተሸከመ›(ኢሳ 53÷4) በማለት የገለጠው ኃይለ ቃል ለሰሙኑም ሆነ ለመጽሐፉ ስያሜ መነሻ መሆኑንን ሊቃውንቱ ይገልጣሉ፡፡ ሐዋርያትም በሥርዓት መጽሐፋቸው ‹ወአንትሙሰ ተዐቀቡ ወግበሩ ተዝካረ ሕማማቲሁ – እናንተ ግን ተጠበቁ፣ የሕማማቱንም መታሰቢያ አድርጉ› ብለው ደንግገዋል (ግብረ ሕማማት፣ 1996፣9)፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ‹ይትባረክ እግዚአብሔር ዘሰመየ ሕማማተ ወልዱ ክብረ ወስብሐተ – የልጁን ሕማማት ክብርና ምስጋና ብሎ የጠራ እግዚአብሔር ይመስገን› ብሎ ገልጦ ነበር፡፡ (ዝኒ ከማሁ፣10) 

ግብረ ሕማማት ከበዓለ ሆሳዕና እስከ በዓለ ፋሲካ የሚከናወነውን ሥርዓት የያዘ ትልቅ መጽሐፍ ነው፡፡ የመጽሐፉ የተወሰነ ክፍልና ሥርዓቱ ከ8ኛው መክዘ ቀደም ብሎ ጀምሮ በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ነበረ፡፡ አሁን ያለውን የግብጽ ቤተ ክርስቲያን የሰሙነ ሕማማት መጽሐፍ (ፓሻ) ያዘጋጁት አቡነ ገብርኤል 2ኛ(1131-1145) የተባሉት የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ናቸው፡፡ ፓትርያርክ ገብርኤል አያሌ የመጽሐፍ ቅዱስና የሊቃውንት ትርጓሜ ዕውቀት ያላቸው ሊቃውንት በማሰባሰብ ለየሰዓቱና ለየኩነቱ የሚነበበውን ሥርዓትና ንባብ አዘጋጁ፡፡ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው በሰላማ መተርጉም ጊዜ መሆኑን ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡(ዝኒ ከማሁ፣ 9) ከጎንደር መድኃኔዓለም ተወስዶ በብሪቲሽ ሙዝየም በሚገኘው ግብረ ሕማማት ላይ ከአባ ሕርያቆስ ድርሳን መጨረሻ ላይ ‹‹ዘንተ መጽሐፈ ዘተርጎመ ብፁዕ ወርቱዕ ሃይማኖት አቡነ አባ ሰላማ ይጽሕፍ ስሞ እግዚአብሔር ውስተ መጽሐፈ ሕይወት› ይላል፡፡ (catalogue Ethiopian manuscripts in British Library, 140) 
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ እንደሚሉት ከሆነ ግብረ ሕማማትን አሁን ባለው መልክ ያዘጋጁት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ናቸው፡፡ እስከ 14ኛው መክዘ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሰሙነ ሕማማት የሚሆኑ የጸሎት ሥርዓት ሳይኖሯት ቆየች ማለት አስቸጋሪ ነው፡፡ አቡነ ሰላማ መተርጉም የተወሰነውን የመጽሐፈ ግብረ ሕማማት ድርሳናት በመተርጎም ቀድሞ በነበረው የሰሙነ ሕማማት የጸሎት ሥርዓት ውስጥ መጨመራቸውን ይገልጣሉ፡፡ አሁን ባሉን የግብረ ሕማማት ቅጅዎች የአቡነ ሰላማን ስም የሚያነሣው ከሊቃውንቱ ደርሳናት መጨረሻ ላይ የሆነውም ለዚህ ሊሆን ይችላል፡፡ አቡነ ሰላማ መተርጉም ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትን አሰባስበው የትርጉም ሥራ ይሠሩ የነበሩት በደቡብ ጎንደር ስማዳ በምትገኘው ደብረ ዕንቁ ማርያም ነበር፡፡ አቡነ ሰላማ የግብጹን ግብረ ሕማማት ይዘውት የመጡ ይመስላል፡፡ በደብረ ዕንቁ የነበሩ ሊቃውንት መጽሐፉን መነሻ በማድረግና ከቀደመው የቤተ ክርስቲያን ጸሎት ጋር በማስማት አሁን የምናውቀውን ግብረ ሕማማት አዘጋጅተውልናል፡፡ 
እስካሁን ባሉን መረጃዎች ረጅም እድሜ ያስቆጠሩት የግብረ ሕማማት ቅጅዎች በ15ኛው መክዘ የተጻፉት ናቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል ሦስቱ በኢትዮጵያ ማይክሮ ፊልም ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ (EMML 1765, 4434, 4752) EMML 1765 የሐይቅ እስጢፋኖስ ቅጅ ሲሆን በዚህ መጽሐፍ ላይ ልዩ ልዩ ድርሳናትን የተረጎሙት አባ ሰላማ መሆናቸውን ይገልጣል፡፡ EMML 4434 የእንዳፍሬ ማርያም(ሞረት) ሲሆን EMML 4752 ደግሞ ሰሜን ሸዋ የሚገኘው የሙሽ ዜና ማርቆስ ንብረት ነው፡፡
በግብረ ሕማማት ውስጥ ከጾመ ድጓና ምዕራፍ የተወሰዱ ጸሎቶች መኖራቸው፤ በግብጹ መጽሐፍ ላይ የሌሉ ከተአምረ ማርያምና ክተአምረ ኢየሱስ የሚነበቡ ምንባባት መገኘታቸው፤ እንዲሁም የቀረቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በቅርጽ ካልሆነ በቀር በብዛትና በዓይነት የተለዩ መሆናቸው ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት የመጽሐፉን መነሻ ከግብጽ ወስደው ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እንዲሆን አድርገው ማዘጋጀታቸውን እንደሚያሳይ የሚገልጡ አሉ፡፡ ለብዙ ዘመናት ግብረ ሕማማት በግእዝ ብቻ የሚገኝ መጽሐፍ ነበር፡፡ በ1990(?)ዓም በሊቀ መዘምራን ላዕከ ማርያም ወልደ ኢየሱስ(ዘአሰላ) ወደ አማርኛ ተተርጉሞ በትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት ታትሟል፡፡
በግብረ ሕማማት ውስጥ ሦስት ነገሮች አሉ፡፡ የመጀመሪያው ጸሎት ሲሆን ‹ዐማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም› እየተባለ የሚጸለየውና ካህናትና ምእመናን በየመካከሉ የሚደግሙት ዳዊት የዚሁ መገለጫ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ስግደት ነው፡፡ በመጀመሪያው ሰዓት፣ በሦስት፣ በስድስት፣ በዘጠኝና በ11 ሰዓት ከጸሎት ጋር የሚደረግ ስግደት አለ፡፡ በዕለተ ዓርብ ደግሞ የ12 ሰዓት ጸሎትና ስግደት አለው፡፡ ከግብረ ሕማማት ትልቁን ቦታ የሚይዘው ሦስተኛው ክፍል ንባቡ ነው፡፡
በሰሙነ ሕማማት በመጽሐፈ ግብረ ሕማማት መሠረት የሚነበቡ ብዙ ምንባባት አሉ፡፡ እነዚህንም በአራት መድበን መመልከት እንችላለን፡፡
1.      መጽሐፍ ቅዱስ፡- በተለይም በዋናነት ከብሉይ ኪዳን ከኦሪት፣ ከጥበብ መጻሕፍት(ምሳሌ፣ መኃያ መኃይ፣ ጥበበ ሰሎሞን፣ ሲራክ፣ ኢዮብ)፣ ከመጽሐፈ ኢያሱ፣ ከመጽሐፈ ሩትና ከሌሎችም የሚቀርቡ ከሰሞኑ ጋር የሚሄዱ ምንባባት አሉ፡፡
2.     ትርጓሜ፡- የልዩ ልዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ትርጓሜ ይነበባል፡፡ በተለይ ደግሞ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የዕብራውያን ትርጓሜ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ከእርሱም ጋር የኤጲፋንዮስ፣ የአትናቴዎስ፣ የቄርሎስና የያዕቆብ ዘሥሩግ ትርጓሜያት ይሰማሉ፡፡
3.     ምዕዳን፡- በግብረ ሕማማት የክርስቲያንን ልዩ እሴቶች የሚመለከቱ ምክሮች ይቀርባሉ፡፡ ስለ ፍቅር፣ ይቅርታ፣ ወገንን መርዳት የተመለከቱ ምንባባት አሉ፡፡
4.     መጻሕፍተ ሊቃውንት፡- በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ከተዘጋጁና እምብዛም ከማናገኛቸው ድርሳናት መካከል በግብረ ሕማማት ውስጥ የምንሰማቸው አሉ፡፡ መጽሐፈ ዶርሖ፣ ላሃ ማርያም ለዚህ ማሳያ ናቸው፡፡ ከተለመዱት ምንባባት ደግሞ ስንክሳር፣ ተአምረ ኢየሱስና ተአምረ ማርያም ይጠቀሳሉ፡፡
   በተለይ በአሁኑ ጊዜ መጽሐፉ በአማርኛ የሚነበብ በመሆኑ ምእመናን ሁላችን በማስተዋል ብናዳምጥ በሌላ ጊዜ የማናገኛቸውን የቤተ ክርስቲያን ታሪኮች፣ ምሥጢራትና ምንባባትን የምናዳምጥበት ዕድል ይሆናል፡፡ የኛን ግብረ ሕማማት ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን ጋር ለማነጻጸር ይኼን መሥመር በመከተል የእነርሱን ግብረ ሕማማት በእንግሊዝኛ መመልከት ይችላል፡፡ http://ixoyc.net/data/Fathers/118.pdf
መልካም ሰሙነ ሕማማት፡፡

Tewodros Girma of Ethiopian FMHACA on World Health Day, 2015

(ኄኖክ የማነ) ከአቶ ገብሩ ሕይወት ጋራ የሚመሳሰሉ ታሪኮችን ከገሃዱ ዓለም ይልቅ በልብ ወለዶች ወይም በሕይወት ትርጉም ላይ በሚያተኩሩ የፍልስፍና መጽሐፍት ውስጥ በቀላሉ ማግኘት ሳይቀል አይቀርም። የሕይወትን ትርጉም የተለያዩ ጸሐፍት አያሌ መመዘኛዎችን በመጠቀም ለማብራራት ይሞክራሉ። ከነዚህ አከራካሪ መመዘኛዎች አንዱ ሰዎች በኋለኛው የዕድሜ ዘመናቸው ላይ ኾነው ያሳለፉትን የሕይወት ዘመን የኋልዮሽ በመመልከት “ሕይወቴ የተሳካ ነበረ?” ለሚለው ጥያቄ በሚሰጡት […]

The post “ያሳደግኹት ውሻ አሳጣኝ መድረሻ” ፥ የአቶ ገብሩ ዐሥራት እና ሊነበብ የሚገባው አነጋጋሪ መጽሐፋቸው appeared first on ሳተናው .

በባህር ዳር ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተማዎችና ሙሉዓለም አዳራሽ የተደረገው ስብሰባ የተፈለገውን ግብ ሳይመታ መጠናቀቁን የስብሰባው ተሳታፊዎች ተናገሩ፡፡ ቅዳሜ መጋቢት 26/2007 ዓ.ም በተደረገው ስብሰባ የብአዴን አባላትን በጥሪ ወረቀት የከተማ ነዋሪዎችን ቤት ለቤት በመዞር በስብሰባው እንዲገኙ በመመዝገብና የተለመደውን ማስፈራሪያ በመጠቀም እስከ ቀኑ 6 ሰዓት በተደረገው ስብሰባ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን በመስጠት የገዢውን መንግስት ካድሬዎች ሲያሸማቅቁ መዋላቸውን ተሳታፊዎች […]

The post የገዢው መንግስት በባህር ዳር ከተማ ያደረጋቸው የምረጡኝ ስብሰባዎች ውጤት አልባ መሆናቸው ተነገረ appeared first on ሳተናው .

አማራውን ለማዳከም ለፋሽስቶቹ ናዚ-ወያኔዎች ተገዢ የሆነ በራሳቸው በትግሬዎች ብአዴን ተብዬ የበግ ለምድ የለበሱ የትግሬ ተኩላዎች ቅጥረኛ ድርጅት እንተቋቋመው እና በውስጡ ትግሬዎች እንደተሰገሰጉ ሁሉ ፣የአማራውን ህብረተሰብ ለማንቋሸሽ እና ለማዳከም በውስጡም አንድነት እንዳይኖር እርስ በእርሱ እንዲባላ እና በጠላትነት እንዲተያይ ለማድረግ ለአማራው ተብሎ በተካለለው ክልል ያለው መሬት የፋስቱ-ናዚ-ወያኔ ቅጥረኛ ብአዴን አሽከር ካድሬ መሬት ፣ ተራ ዜጋ መሬት እና […]

The post ቅጥረኛው ትግሬ ብአዴን አማራን የመከፋፈል እና የማንቋሸሽ ሴራ appeared first on ሳተናው .

[email protected]; girmaseifu.blogspot.com ተከራካሪዎች እያሱ መኮንን እና አዳነ ታደስ                  ኤዴፓ ተሸመ ወልደ ሓዋሪያት                       መኢብን ትዕግሰቱ  ደበላ እና ግዑሽ ገ/ሰላሴ              ኢድአን ካሳሁን አበባው እና ተሰፋሁን አለምነህ          መኢሕአድ መኩሪያ ኃይሌ እና አህመድ አብተው            ኢህአዴግ በግንቦት 2007 የሚካሄደው “ምርጫ” አማራጭ በሌለበት መሆኑ በዋነኝነት የጎዳው ለምርጫ ከምር የተዘጋጁትን ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን መራጩን ህዝብ እንደሆነ መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ […]

The post ክርክር 4፡ ኢንዱስትሪ እና ከተማ ልማት- በእኔ ዕይታ – ግርማ ሠይፉ ማሩ appeared first on ሳተናው .

ትላንት አመሻሽ ላይ በዲሲ 16ኛው መንገድ “የእኛ እድር” የተሰኘ ድራማ ይታይ ነበር። ዝግጅቱን ለመታደም ከኢየሩስና አብራት ከምትማረው ታዳጊ ኤልሳ ጋር በስፍራው ተገኘን። ድራማው ይጀመራል ከተባለበት ጊዜ ለ1 ሰዓት ተኩል ዘግይቶ ነበር። (ሃበሻና ቀጠሮ መቼ እንደሚታረቁ አይታወቅም)…ዝግጅቱ እስኪጀምር ወግ ቀጠልን። ታዳጊ ኤልሳ አሜሪካ ከአባቷ ጋር የመጣችው ከ5 አመት በፊት ነበር። የ16 አመቷ ኤልሳ በገፅታዋ ብሶትና መከፋት […]

መጋቢት ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኤጀንሲው በአዳማ ስብስባ እንደሚያካሂድና አንድ የድርጅቱ ከፍተኛ የሥራ መሪ እንዲገኝ በስልክ በተነገራቸው መሠረት በአዳማ መገኘታቸውን የተናገሩት አንድ የስብሰባው ተሳታፊ ፣ በዚህ ስብሰባ ላይ ምግባረሰናይ ድርጅቶችን አላሰራ ባሉት ሕጎችና አሰራሮች ዙሪያ ምክክር ይደረጋል የሚል ሃሳብ ይዘው በቦታው ቢገኙም የገጠማቸው ግን ፈጽሞ ያላሰቡት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዚሁ ስብሰባ ላይ …

መጋቢት ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በየመን የሚካሄደውን የእርስ በርስ ጦርነት ተጋፍጠው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቢሆንም፣ ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉትን ከ2 ሺ ያላነሱ ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያንንን ለመመለስ እንቅስቃሴ እየታየ አይደለም ሲሉ የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አስታውቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ ኢምባሲው ባቀረበው ጥሪ መሰረት ምዝገባ አካሄዱ ቢሆንም ፣ መቼና እንዴት እንደሚሄዱ የሚያውቁት ነገር …

መጋቢት ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህር ዳር ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተማዎችና ሙሉዓለም አዳራሽ የተደረገው ስብሰባ የተፈለገውን ግብ ሳይመታ መጠናቀቁን የስብሰባው ተሳታፊዎች ተናገሩ፡፡ ቅዳሜ መጋቢት 26/2007 ዓ.ም በተደረገው ስብሰባ የብአዴን አባላትን በጥሪ ወረቀት የከተማ ነዋሪዎችን ቤት ለቤት በመዞር በስብሰባው እንዲገኙ በመመዝገብና የተለመደውን ማስፈራሪያ በመጠቀም እስከ ቀኑ 6 ሰዓት በተደረገው ስብሰባ ተሳታፊዎች የተለያዩ …

አንዱዓለም ተፈራ
Atse Tewodros. አፄ ቴዎድሮስ

እንደ እውነቱ ከሆነ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ገዥ ቡድን በእብሪት ተወጥሮ አገራችንን ሲጫወትባት፤ “እኛ የኔ ድርጅት! የለም የኔ ድርጅት!”፣ “እኔ ልምራ እናንተ ተከተሉኝ! የለም እኔ ልምራ እናንተ ተከተሉኝ!”፣ “እኔ እበልጣለሁ! የለም እኔ እበልጣለሁ!” እየተባባልን፤ በሌለ ሥልጣን ሽሚያ ልባችን ተወጥሮ፤ ዛሬ ትናንት፤ ነገ ደግሞ ዛሬ እየሆነ ዓመታትን አስቆጠርን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

መረጃ ለነፃነት በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ አማኑኤል ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የመምህራን ስብሰባ ላይ የምረጡን ቅስቀሳውን ይዞ የቀረበው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጠመው፣ በደረሰን መረጃ መሰረት የማቻከል ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የኔነህ እና የወረዳው የትምህርት ዝሕፈት ቤት ሃላፊው አዲሱ የተባሉት በወረዳው እየተካሄደ በነበረው የመምህራን የርዕሳነ መምህራንና የሱፐርቫዘሮች ስብሰባ ላይ በአጀንዳነት የቀረበውን የትምህርት ጥራትና የውጤት ተኮር […]

ዲ/ን ክንፈ ገብርኤል
Hosaena

ሆሣዕና ቃሉ የዕብራይስጥ ሲሆን ትርጓሜውም “አሁን አድን” ማለት ነው። እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት ከፋሲካ/ከትንሳኤ በፊት ያለው እሑድ “የሆሣዕና እሑድ” በመባል ይታወቃል። በዚህ ዕለትም በቤተ ክርስቲያናችን የሚዘመረው መዝሙር፣ ማኅሌቱ፣ ቅዳሴው፣ ምንባቡና ማንኛውም አገልግሎት ሁሉ ዕለቱን በታላቅና እጅግ ደማቅ በሆነ መንፈሳዊ ሥነ – ሥርዓት የሚዘከርበት፣ የሚታሰብበት ነው። ይህ በዓል እጅግ በደማቅና ልብን በሚመስጥ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓትና ድምቀት ከሚከበርባቸው ቅዱሳን ገዳማትና መካናት መካከል የአክሱሟ ርዕሰ አድባራት ጽዮን ማርያም እና በዚህ በአዲስ አበባችን የእንጦጦ ማርያም በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሀገሬ)
Sudanese President Omar al-Bashir, center, Egyptian President Abdel-Fattah el-Sissi, left, and Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn, right, shake hands after signing an agreement on sharing water from the Nile River, in Khartoum, Sudan, Monday, March 23, 2015. Egypt, Ethiopia and Sudan on Monday signed an initial agreement on sharing water from the Nile River that runs through the three countries, as Ethiopia constructs a massive new dam it hopes will help alleviate its electricity shortages. El-Sissi, al-Bashir and Desalegn welcomed the agreement in speeches in Khartoum’s Republican Palace on Monday. (AP Photo/Abd Raouf) (The Associated Press)

ከላይ ለዚህ ትችት የተሰጠው ርዕስ እንደሚያመለክተው በአንድ በኩል በገንዘብ እጦት ችግር ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ለማድረግ ባለመቻሉ ምክንያት የተገደበ ወይም ደግሞ እንደ ጅብራ ተገትሮ የቀረ ግድብ የሚል ትርጉምን የሚይዝ ሲሆን፤ ሌላው ትርጉሙ ደግሞ ከፍተኛ በሆነ የገንዘብ እጦት ችግር ምክንያት የተመደበለትን ገንዘብ በማብቃቃት ለመስራት በማሰብ ደረጃቸውን ባልጠበቁ ግብዓቶች በመጠቀም ለርካሽ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲባል እንደምንም ተውገርግሮ የተሰራ ግድብ ብዙም ዘለቄታ ሳይኖረው በአንድ ወቅት አውዳሚ በሆነ መልኩ ተንዶና ተደርምሶ የህዝብ ሀብት እና ጉልበት መና ሆኖ ይቀራል የሚል ፍሬ ሀሳብን የያዘ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በስፔን ላሊጋ ክሪያስቲያኖ ሮናልዶ በ8 ደቂቃ ሐትሪክ በመሥራት ለቡድኑ 5 ግቦችን አስቆጥሯል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ሊሰናበቱ እንደሆነ ተገለጠ። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዳጉ ማራቶን የሩጫ ውድድር በወንድም በሴትም አሸናፊ ሆነዋል።

የሲሚንቶ ዋጋ በስልሳ በመቶ ገደማ መጨመሩን ከሀገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን የተገኘዉ ዘገባ ያመለክታል። እንደዘገባዉ ለዋጋዉ መጨመር እንደምክንያት የቀረበዉ በጅቡቲ ወደብ ላይ የተከማቹ እቃዎችን ለማመላለስ እቃ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ወደዚያ በመሠማራታቸዉ ሳይሆን አይቀርም።

ኑክሌርን ለኢራን ያስተዋወቀችዉ ዩናይትድ ስቴትስ ናት።በ1950ዎቹ «አቶሚክ ለሠላም» በሚል መርሕ ዩናይትድ ስቴትስ ለኢራን የሐይል ማመንጪያ ተቋም ማስገባት ጀምራ ነበር።የኑክሌር ተቋም ግንባታዉን ያቋረጠችዉ ደግሞ ማንም ሳይሆን እራስዋ ኢራን ነበረች

በእርስ በርስ ግጭት የጦርነት ቀጣና የሆነችዉ የመን ይዞታ ወደሰብዓዊ ቀዉስ እያመራ መሆኑን የተመድ አመለከተ። የመንግሥታቱ ድርጅት የሕፃናት መርጃ UNICEF እንደገለፀዉ በጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩት ከቤት ንብረታቸዉ ለመፈናቀል ሲዳረጉ፤ አጋጣሚዉ ለበሽታና ለምግብ እጥረት አጋልጧቸዋል።

Image

ከኦባማ ቀጥሎ በአሜሪካ ከፍተኛው ደመወዝ ተከፋይ ነበሩ
ከ2ሺ በላይ የተሳኩ ቀዶ ህክምናዎችን አከናውነዋል
ወንድሞቻቸው፡- ፕሮቶን፣ ኒውትሮን፣ ዲዩትሮን፣ ኤሌክትሮን እና ፖሲትሮን ይባላሉ

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዶክተር ኤሌክትሮን ክበበው፤ ለ33ኛ ጊዜ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የ2015 “የዓመቱ የዓለማችን ልዩ ስም” ውድድር ላይ ከፍተኛ ድምጽ በማግኘት በቀዳሚነት እየመሩ እንደሆነ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡
በአለማቀፍ ደረጃ በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ ዘንድሮም የተለያዩ አገራት ዜጎችና በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ 64 ግለሰቦች ያልተለመዱ ስሞች ለውድድር የቀረቡ ሲሆን ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ኤልክትሮን ክበበው፤ በ1ሺህ 132 ድምጽ፣ በ89.6 በመቶ ውጤት በቀዳሚነት በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡
በኢሜልና በተለያዩ መንገዶች ከቀረቡለት በርካታ ለየት ያሉ ስሞች 64 ያህሉን በመምረጥ፣ ለአንድ ሳምንት ያህል በድረ ገጽ አማካይነት ድምጽ እንዲሰጥባቸው የሚያደርገው የውድድር ኮሚቴው፤ የመጨረሻውን ውጤት ከጥቂት ቀናት በኋላ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
የሰማይ እንሽላሊት፣ ጣፋጭ ቡና፣ ዳላስ፣ ቶክዮ፣ ቴኒስ እና የመሳሰሉ የአገር፣ የቦታ፣ የእቃ፣ የሰብል ወዘተ መጠሪያዎችን የያዙ የተለያዩ አገራት ዜጎች በዘንድሮው ውድድር እንደተሳተፉ አወዳዳሪዎቹ ገልጸዋል፡፡
በዘንድሮው ውድድር ከፍተኛ ድምጽ በማግኘት በመምራት ላይ ለሚገኙት የ47 አመቱ ዶ/ር ኤሌክትሮን ይህን ስም ያወጡላቸው፣ ኤሌክትሪካል ኢንጂነር የሆኑት ኢትዮጵያዊው አባታቸው አቶ ክበበው ነበሩ፡፡
ልጆቻቸው የእሳቸውን ፈለግ ተከትለው በሳይንሱ ዘርፍ ላይሰማሩ ይችላሉ የሚል ስጋት ያደረባቸው አቶ ክበበው፤ በልጆቻቸው ልቦና ውስጥ ገና በለጋ እድሜያቸው የሳይንስን ስሜት ለማስረጽ በማሰብ ነው፣ ባልተለመደ ሁኔታ ለልጆቻቸው ከኤሌክትሪሲቲ ጋር የተያያዙ ስሞችን ያወጡት፡፡
አቶ ክበበው፤ ለአምስቱ ልጆቻቸው ፕሮቶን፣ ኒውትሮን፣ ዲዩትሮን፣ ኤሌክትሮን እና ፖሲትሮን የሚሉ ስሞችን አውጥተዋል፡፡ ዶ/ር ኤሌክትሮን በስማቸው ብቻ አይደለም የሚለዩት፡፡ ከስማቸው በላይ ብዙዎችን ያስገረመው፣ በህክምና ሙያቸው የአሜሪካ መንግስት የሚከፍላቸው ዳጎስ ያለ ደመወዝ ነው ይላል ድረ-ገጹ፡፡
ከአራት አመታት በፊት “ዊኪኦርግቻርትስ” የተባለ ተቋም “የአመቱ የአሜሪካ መንግስት 1000 ከፍተኛ ደመወዝ ተከፋዮች” በሚል ባወጣው ዝርዝር ውስጥ፣ ዶ/ር ኤሌክትሮንን ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ቀጥሎ ከፍተኛ ደመወዝ የሚያገኙ የመንግስት ሰራተኛ በማለት በሁለተኛነት አስቀምጧቸዋል፡፡
በአዲስ አበባ በሚገኘው ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት የተማሩት ዶ/ር ኤሌክትሮን ክበበው፤ በአሜሪካ ሳንፍራንሲስኮ ከሚገኘው ዪኒቨርሲቲ ኦፍ ካሊፎርኒያ በህክምና የተመረቁ ሲሆን የአሜሪካን ቦርድ ኦፍ ሰርጀሪን የቀዶ ህክምና ሰርተፊኬትም አግኝተዋል፡፡
ላለፉት 20 አመታት በሳንፍራንሲስኮ በኢንዶክሪንና ታይሮይድ ካንሰር ዘርፍ የአጠቃላይ ቀዶ ህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት ዶክተሩ፤ በአሜሪካ ብሄራዊ የካንሰር ኢንስቲትዩት፣ የካንሰር ምርምር ማዕከል የኢንዶክራይን ኦንኮሎጂ ቅርንጫፍ ሃላፊ ሲሆኑ የካንሰር ጄኔቲክስ ክፍሉንም በበላይነት በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡
ዶክተሩ በእስካሁኑ የሙያ ዘመናቸው ከሁለት ሺህ በላይ የተሳኩ ቀዶ ህክምናዎችን ያከናወኑ ሲሆን ከ150 በላይ የጥናት ጽሁፎችንና መጽሃፍትን ለህትመት እንዳበቁ “ብሬኪንግጎቭ” የተሰኘ ድረገፅ አመልክቷል፡፡

ከግማሽ ክ/ዘመን በላይ ስለኢትዮጵያ ያጠኑ፣ኢትዮጵያን የተመለከቱ መፃህፍት እና በርካታ የምርምር ፅሁፎች ያቀረቡ የኢትዮጵያ ታላቅ ወዳጅ አሜሪካዊው ፕሮፌሠር ዶናልድ ሌቪን አረፉ።

The post ከግማሽ ክ/ዘመን በላይ ስለኢትዮጵያ ምርምር ፅሁፎች ያቀረቡ ፕሮፌሠር ዶናልድ ሌቪን አረፉ appeared first on ሳተናው .

ከኦባማ ቀጥሎ በአሜሪካ ከፍተኛው ደመወዝ ተከፋይ ነበሩ ከ2ሺ በላይ የተሳኩ ቀዶ ህክምናዎችን አከናውነዋል ወንድሞቻቸው፡- ፕሮቶን፣ ኒውትሮን፣ ዲዩትሮን፣ ኤሌክትሮን እና ፖሲትሮን ይባላሉ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዶክተር ኤሌክትሮን ክበበው፤ ለ33ኛ ጊዜ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የ2015 “የዓመቱ የዓለማችን ልዩ ስም” ውድድር ላይ ከፍተኛ ድምጽ በማግኘት በቀዳሚነት እየመሩ እንደሆነ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡ በአለማቀፍ ደረጃ በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ ዘንድሮም የተለያዩ አገራት […]

The post ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ኤሌክትሮን “የዓለማችን ልዩ ስም” ውድድርን እየመሩ ነው appeared first on ሳተናው .