ዛሬ ዐርብ ታኅሣሥ ፲፩ – ፲፪ የሚካሄደውን የልደታ፣ አዲስ ከተማና ቂርቆስ ክፍላተ ከተማ አብያተ ክርስቲያን ልኡካን የሚሳተፉበትን ጥናታዊ ውይይት መስተንግዶ የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ካቴድራል እና የመርካቶ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን፤ ከታኅሣሥ ፲፫ – ፲፬ የሚካሄደውንና የቦሌ ክፍለ ከተማ አብያተ ክርስቲያን የሚሳተፉበትን ጥናታዊ ውይይት ደግሞ የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ስፖንሰር ለማድረግ በየሰበካ …

ታህሳስ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-9ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በጅጅጋ ለማክበር ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት ከተማ ያቆሽሻሉ ተብለው ተይዘው ከጅጅጋ 25 ኪሜ ገደማ ከምትገኘዋ ቀብሪበያህ እስር ቤት እንዲገቡ ከተደረጉት መካከል ከ40 በላይ ሰዎች ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ሁኔታ በመሞታቸው በታሰሩበት አካባቢ እንዲቀበሩ ተደርጓል። ሟቾቹ በደንብ ባለመቀበራቸውና የአንዳንዶችን አስከሬን ጅብ አውጥቶ  ስለበላው፣ ሌሎቹ ከእስር ቤቱ ራቅ ብለው …

ታህሳስ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልልን ላለፉት ስምንት ዓመታት ተኩል በፕሬዚደንትነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ አያሌው ጎበዜ ከኃላፊነታቸው ተነሱ፤ በምትካቸው ምክትል ፕሬዚደንቱ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተሹመዋል፡፡ አቶ አያሌው ከኃላፊነታቸው የተነሱት እየተካሄደ ባለው የአማራ ክልል ምክር ቤት አራተኛ ዙር ፤ አራተኛ ዓመት የስራ ዘመን አንደኛ አስቸኳይ ጉባዔ ውሳኔ መሠረት ነው፡፡ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በአቶ …

ታህሳስ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ በጉንዶመስቀል ከተማ በመስተዳድሩ ውስጥ ተቀጥረው ከሚሰሩት መካከል ከ108 በላይ ሰዎች በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች የተለያዩ የሃለፊነት ቦታዎችን ወስደዋል በሚል የአካባቢው ፖሊስ ምርመራ በማድረግ ላይ ነው። ፖሊስ እስካሁን ባደረገው ምርመራ 13 ሰዎች በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ተቀጥረው ለአመታት ደሞዝ ሲቀበሉ መቆየታቸውን በማረጋገጥ ጉዳዩን …

ታህሳስ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና በቀድሞው ምክትላቸው ሪክ ማቻር መካከል የተነሳው ውዝግብ የዲንቃና የኑዌር ጎሳዎችን እርስ በርስ እንዲዋጉ እያደረጋቸው መምጣቱን ዘገባዎች ያመለክታሉ። የሪክ ማቻር ደጋፊዎች ጆንግሌ አካባቢ የሚገኙ የተለያዩ ቦታዎችን መቆጣጠራቸው ተሰምቷል። ምንም እንኳ የአገሪቱ መሪ መፈንቅለ መንግስቱን ማክሸፋቸውን ቢናገሩም፣ በሌሎች አገሪቱ ክፍሎች አሁንም ውጊያዎች እየተካሄዱ ነው። ከስልጣን የተባረሩት ሪካ …

ታህሳስ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ዋና አቃቢ ህጓ ምርመራውን ለማቋረጥ የተገደዱት ሁለቱ ዋና ምስክሮችን ለማግኘት ባለመቻላቸው ነው። ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከ6 አመት በፊት በተነሳውና ከ1 ሺ 200 በላይ ሰዎች የተገደሉበትን የምርጫ ማግስት ረብሻ አነሳስተዋል በሚል ነው። በምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ ላይ የተጀመረው ክስ ይቀጠል አይቀጥል የታወቀ ነገር የለም። የአፍሪካ መሪዎች ክሱ እንዲቋረጥ ሲወተውቱ ቆይተዋል። ፕሬዚዳንቱ …

የኤሌክትሪክ ግንባታ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ደግሞ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገግሎት ኩባንያዎች እንዲመራ መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፓሬሽን የህዝብ ግንኑነት ሃላፊ አቶ ምስክር ነጋሽ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።

የአውሮጳ ህብረት ለመጀመሪያ ጊዜ የጦር ተልዕኮ ለማካሄድ የወሰነው በአፍሪቃ ቀንድ የሚታየውን የባህር ላይ ውንብድናን ለመታገል ቆርጦ በተነሳበት ጊዜ ነበር። « አታላንታ» በሚል መጠሪያ የሚታወቀው እና ከአምሥት ዓመት በፊት የተጀመረው ይኸው የኅብረቱ ፀረ የባህር ላይ ወንበዴዎች ተልዕኮ የተሳካ ውጤት ማስገኘቱ ነው የሚነገረው።

ለህዝብ መረጃ በማቅረብ ሰፊ አገልግሎት በመስጠት ከታወቁት ዋና -ዋና ዘርፎች ፣ማለትም ሬዲዮ ፣ ቴሌቭዥን፤ ጋዜጣና መጽሔት ሌላ ፣ ማህበራዊ የህዝብ መገናኛ ዘዴዎች ፣ ፈጣንና ማራኪ ሁለገብ መረጃ ማቅረብ እንደሚችሉ በማሥመስከር ላይ ናቸው። ማሕበራዊ ድረ

አንዲት ትውልደ ኬንያት በቆዳ ቀለሟ ምክንያት እዚህ ጀርመን የደረሰባት አድልዎ የብዙዎችን ትኩረት የሳበ የሰሞኑ መነጋገሪያ ሆኗል ። የተላከላትን ጥቅል እቃ ለመቀበል ወደ አንድ የፖስታ አገልግሎት ሰጭ ድርጅት ባለፈው ሳምንት ጎራ ያለችውን ወይዘሮዋን የድርጅቱ ሠራተኛ ጥቁር ስለሆንሽ አልሰጥም ብላ ትከለክላታለች ።

ለሶስት አስርተ ዓመታት ከመድረክ ርቆ ቆይቶ፤በቅርቡ እጅግ አስደናቂ የተባሉትን እንብሮቹን ይዞዳግም ብቅብሎአል። በ1970ዎቹ ታዋቂ በነበረው ዋሊያስ ባንድ ውስጥ በጃዝ እና በሶልስልት የተቀነባበረ ሙዚቃን በመጫወት ዕውቅናን ያገኘው ኃይሉ መርጊያ።

እ ጎ አ ታኅሣሥ 17 ቀን 2010 ዓ ም፤ ቅጠላ ቅጠልና ፍራፍሬ በመሸጥ ይተዳደር የነበረው ሙሐመድ ቡዓዚዚ የተባለው ጎልማሳ ቤንዚን አርክፈክፎ ራሱን ሲያቃጥል፤ ቤን አሊንና ዘመዶቻቸውን ከሥልጣን ለማፈናቀል አልሞ አልነበረም። ይሁንና የቡዓዚዚ በገዛ

የአውሮጳ ህብረት ለመጀመሪያ ጊዜ የጦር ተልዕኮ ለማካሄድ የወሰነው በአፍሪቃ ቀንድ የሚታየውን የባህር ላይ ውንብድናን ለመታገል ቆርጦ በተነሳበት ጊዜ ነበር። « አታላንታ» በሚል መጠሪያ የሚታወቀው እና ከአምሥት ዓመት በፊት የተጀመረው ይኸው የኅብረቱ ፀረ የባህር ላይ ወንበዴዎች ተልዕኮ የተሳካ ውጤት ማስገኘቱ ነው የሚነገረው።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለዉ ፕሬዝዳት ኪየር የሚወለዱበት የዲንካ እና ማቼር የሚወለዱበት የኑዌር ጎሳዎች መልክ እና ባሕሪ የያዘዉ ዉጊያ ፈጣን መፍትሔ ካላገኘ አደገኛ ነዉ።ደቡብ ሱዳን፥ ነፃነት ያወጀችበትን ሁለተኛ ዓመት-ከመንፈቅ፥ ከረጅም ጦርነት የተላቀቀችበትን ሥምንተኛ ዓመት፥ እነሆ በጦርነት ልታከብር ዉጊያ ጀምራለች።

ሐዲስ ዓለማየሁ Haddis Alemayehuዳንኤል ክብረት
የዛሬ 600 ዓመት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የተባለ ኢትዮጵያዊ ደራሲ “አርጋኖን” የተሰኘ መጽሐፍ ይደርሳል። ይህንን መጽሐፍ የተመለከቱ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትም እጅግ ያደንቁና ለንጉሡ ለዐፄ ዳዊት ያቀርባሉ። ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም መጽሐፉን ተመልክተው በማድነቅ በወርቅ ቀለም እንዲጻፍ አዘዙ። አባ ጊዮርጊስንም ሸለሙ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት ወደ ኋላ (ክፍል ሁለት)
ያሬድ ኃይለማርያም ከብራስልስ
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት በኢትዮጵያዊያን ላይ እያሰፈነ ስላለው የፍርሃት ባህል ቀደም ሲል ባሰራጨሁት የዚህ ጽሑፍ የመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ባለሙያዎች በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ለፍርሃት ባህል መስፈን መንሰዔዎች ያሏቸውን ነጥቦች ዘርዝሬ ነበር። 

ሙሉውን አስነብበኝ …

በሀገር ቤት የሰላማዊ ትግልን የሚከተለው ሰማያዊ ፓርቲ ባለፈው እሁድ ዲሴምበር 15 ቀን 2013 እ.ኤ.አ. በዋሽንግተን ዲሲ ህዝባዊ ስብሰባ አካሂዶ ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ የፓርቲው ሊቀመንበር ያደረጉትን ንግግር ኢሳት ዘግቦታል። (ቪዲዮውን ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

ኢትዮጵያ የሁሉም እኩል ሀገር ትሆናለች
ደመቀ በሪሁን
በዓለም ላይ በየጊዜው በርካታ የታሪክ አጋጣሚዎች ይፈጠራሉ። አንዳንዶች የተፈጠረውን አጋጣሚ በሚገባ በመጠቀም ለአገርና ለህዝብ የሚጠቅም ታላላቅ ሥራዎችን ይሠራሉ፤ ሌሎች በአንፃሩ የተፈጠረውን አጋጣሚ በማባከን ሀገርንና ህዝብን የሚጎዳ ታሪካዊ በደል ይፈጽማሉ። ወያኔ በኢትዮጵአ በተፈጠረው አጋጣሚ ለመንግሥት ሥልጣን በቅተሃል፣ የተፈጠረውን አጋጣሚ ለምንና እንዴት እየተጠቀምክበት እንደሆነ መመልከት ጠቃሚ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በልጅግ ዓሊ

የማንዴላን ሕልፈተ ሕይወት ተመልክቶ በዓለም ደረጃ የሚያስደንቅ ሁኔታ ስናይ ሰነበትን። ማንዴላ የሠራውን መስራት ሳይሆን እሱ የታሰረበትን ዓላማ በተጻራሪ የሚተገብሩ ሁሉ በቀብሩ ላይ ለመገኘት ከተደበቁበት ብቅ ብቅ ማለታቸው የሚስደምም ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት በኢትዮጵያዊያን ላይ እያሰፈነ ስላለው የፍርሃት ባህል ቀደም ሲል ባሰራጨሁት የዚህ ጽሑፍ የመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ባለሙያዎች በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ለፍርሃት ባህል መስፈን መንሰዔዎች ያሏቸውን ነጥቦች ዘርዝሬ ነበር። በክፍል አንድ ጽሑፌ መግቢያ ላይ እንደገለጽኩት ምንም እንኳን ፍርሃት የግለሰቦች ባህሪ መገለጫዎች መካከል አንዱ ቢሆንም የዚህ ጽሑፍ ትኩረት በወል የምንጋራቸውና በማኅበረሰብ ደረጃም በሚንጸባረቁት የፍርሃት ምልክቶች ላይ […]

“በትግሉ ወቅት ለነጻነት ስትዋደቁ ኢትዮጵያ በጋምቤላ አኙዋክ ምድር ላይ ሙሉ ከለላና ዋስትና በመስጠት ያበረከተችው አስተዋጽኦ የሚረሳ ነው? ከነጻነት ታጋዮችችሁ ጎን በመሰለፍ ብረት ያነሱ የአኙዋክ ኢትዮጵያውያን ልጆች መስዋዕትነት ይዘነጋችኋል? አሁን ድረስ የትግሉ የመስዋዕትነት ቁስላቸው ያልዳነ የአኙዋክ ልጆች እንዳሉ ትዘነጋላችሁ?” በማለት የተናገሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ /ጥቁሩ ሰው/ ናቸው። http://www.goolgule.com/obang-spoke-with-south-sudan-foreign-affairs-minister/ በታላላቅ መድረኮችና […]

ታህሳስ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በጌዲዮ ዞን በሚገኙ 9 ወረዳዎች ውስጥ በዚህ ወር ውስጥ ባልተለመደ ሁኔታ ከፍተኛ ረሀብ በመከሰቱ የዞኑ የአገር ሽማግሌዎች ህዝቡ ያለበትን አሳሳቢ ሁኔታ በመግለጽ የተፈራረሙበትን ደብዳቤ ዛሬ ለዞኑ መስተዳድር አስገብተዋል። በከፍተኛ ደረጃ ተደናገጡት የዞኑ ባለስልጣናት መረጃው ይፋ እንዳይወጣ ለማድረግ ዛሬ ቀኑን ሙሉ በስብሰባ ተወጥረው መዋላቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የአገር ሽማግሌዎቹ  የገጠሩ …

ታህሳስ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ህዝባዊ ሀይሉ የተመሰረተበትን አንደኛ አመት በማስመልከት ባወጣው መግለጫ ” ያለፈው አንድ አመት የመሰባሰብ ድርጅት መሰረታዊ የሆኑ የፖለቲካና የወታደራዊ ስልጠና የተሰጠበት፣ የድርጅት ማጠናከሪያና የማጥራት ሂደት የተካሄደበት ” ነበር ብሎአል። መጪውን አመት የተለየ የሚያደርገው ህዝባዊ ሀይሉ በህዝብ ላይ በሚደርሰው ግፍና ውርደት ከሚሰማው ከፍተኛ ብስጭትና ቁጭት አልፎ ባለፈው አመት ሊደርስላቸው ያልቻለውን የአገራችንን …

ታህሳስ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በአሁኑ ወቅት በሃገራችን ያሉት የቆዳ ፋብሪካዎች የግብዓት ፍላጎታቸው በዓመት ከ40 ሚሊዮን በላይ የበግና ፍየል ሌጦና ከ2 ሚሊየን በላይ የበሬ ቆዳ ሲሆን፥ እየቀረበላቸው ያለው የቆዳ መጠን  ከ16 እስክ 17 ሚሊየን ሌጦ እና በቆዳ ደግሞ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በታች ነው። ከዚህ በመነሳት ሃገሪቱ ከዘርፉ የምትጠብቀውን ገቢ ማሳካት አስቸጋሪ እንደሆነ ነው …

ታህሳስ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ሪክ ማቻር ከተደበቁበት ቦታ ሆነው ለአለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን እንደገለጹት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ተቃዋሚዎቻቸውን ለመምታት የተጠቀሙበት ዘዴ ነው ብለዋል። የፕሬዚዳንቱ ጠባቂዎች እርስበርሳቸው መጋጨታቸውን የገለጹት የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ማቻር፣ ይሁን እንጅ የሳልቫኪር መንግስት አጋጣሚውን ተጠቅሞ ተቀናቃኞችን እያሰረ ነው ሲል አክለዋል። በአገሪቱ ውስጥ የሚታየው ውጥረት በማየሉ አዲሲቷ አፍሪካዊት አገር በእርስበርስ የጎሳ ጦርነት ትታመሳለች …

የደቡብ አፍሪቃን ፀረ የዘር መድልዎ ሥርዓት (አፓርታይድ) በመታገል ህዝቡ ለድል የበቃው፤ በሕይወት ቢኖር ኖሮ በዛሬዋ ዕለት 67ኛ ዓመቱን ማክበር ይችል በነበረው ስቲቭ ቢኮን በመሳሳሉ የጥቁሩን ሕዝብ ንቃተ ሕሊና ከፍ ለማድረግ ዘመቻ ባካሄዱ ጠንካራ

የሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ከእሁዱ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በኋላ ዛሬ መረጋጋትዋ ተዘግቧል ። ነዋሪዎች ዛሬ ከቤታቸው መውጣት ጀምረዋል ። አልፎ አልፎ ተኩስ መሰማቱ ግን አልቆመም ። መንግሥት እንዳስታወቀው ከመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 10 ሰዎችን አስሯል ።

በፓሪስና በኒው ዮርክ የሚገኙት ፣ ድንበር አያግዴው የጋዜጠኞች ድርጅት (RSF) እና ለጋዜጠኞች ህልውናና መብት ተሟጋቹ ፤ (CPJ)፣ በዓለም ዙሪያ የጋዜጠኞችን ፍዳ የሚዘረዝረውን ዓመታዊ መግለጫቸውን ይፋ አደረጉ። ለመገባደድ 2 ሳምንት ገደማ በቀረው 2013 ጎርጎሪዮሳዊው ዓመት

ለዘመናት ከድህነት ወለል በታች ተፈርጃ መቆየቷ በሚነገርላት ኢትዮጵያ ምንም እንኩዋን መንግስት እና ኣንዳንድ ዓለም ዓቀፍ ተቐማትም ቢሆኑ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ፈጣን እድገት እያስመዘገበች መሆኗ ቢሰማም የድህነቱ ጥልቀት ግን እንዲህ በቀላሉ የሚቀረፍ ኣለመሆኑን ሁሉም ወገኖች ይስማሙበታል።

በመካከለኛዉ ምሥራቅ በሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ሥደተኞችን ችግር ለመግታት የተቀናጀና መጠነ-ሠፊ ጥረት መደረግ እንዳለበት ዋሽግን-ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ በጉዳዩ ላይ የተነጋገሩ ተሰብሳቢዎች አስታወቁ። ባለፈዉ ቅዳሜ በተደረገዉ ዉይይት ላይ የተካፈሉ ምሑራን፥ የሕግ ባለሙያዎችና የማሕበራት መሪዎች ጥናታዊ ፅሑፍ አቅርበዉ ነበር።

በየዓይነቱ የሚባል ምግብ መቼም ታውቃላችሁ፡፡ በጾም ጊዜ የሚዘወተር የሀገራችን ምግብ ነው፡፡ አንዳንድ ቦታ ሦስት ዓይነት ሲኖረው አንዳንድ ቦታ ደግሞ ሠላሳ ዓይነት አለው፡፡ ‹በየዓይነቱ› የሚለውን የምግብ ቤቶች መዝገበ ቃላት ሲተረጉመው ‹‹አንድ ቀይ የምሥር ወይም የሽሮ ወጥ በእንጀራው መካከል ጎላ ብሎ ይቀመጥና እነ አልጫ ሽሮ፣ እነ አልጫ ምስር፣ እነ ምጣድ ሽሮ፣ እነ ቃሪያ፣ እነ ስልጆ፣ እነ ቲማቲም ፍትፍት፣ እነ አበሻ ጎመን፣ እነ የፈረንጅ ጎመን፣ እነ ሩዝ፣ እነ ሱፍ ፍትፍት፣ እነ ቀይ ሥር፣ እነ ድንች ወጥ፣ እነ ተልባ ፍትፍት በዙሪያው አጅበው ይሰለፋሉ›› ማለት ነው ይላል፡፡

በያይነቱ ሕግም አለው፡፡ ባይጻፍም እኛ ‹የበያይነቱ ሕግ› ብለነዋል፡፡ በበያይነቱ ሕግ መሠረት በመካከል የሚቀመጠው ዋናው ወጥ በቀላሉ የሚገኝና የሚሠራ መሆን አለበት፡፡ ለዚህም ነው ወይ ምስር ወይም ሽሮ የሚሆነው፡፡ ርካሽነቱ የጥሬ ዕቃው ብቻ ሳይሆን በአንድ ትልቅ ድስት ውስጥ በቀላሉ በብዛት ሊሠራ የሚችል ማለትም ነው፡፡ ለዚህም ሳይሆን አይቀርም ምሥርና ሽሮ ወጥ፣ በልቅሶ ቤትም ዕድሮች በብዛት ይዘዋቸው የሚመጡት፡፡  አንድ ድንኳን ሙሉ ለቀስተኛና ዕድርተኛ ለማብላት እንደ ቀይ ምስርና ሽሮ ወጥ የሚበቃ አይገኝም፡፡

ሁለተኛው የበያይነቱ የሕግ ዐንቀጽ ደግሞ በወጥ ጭማሪ ጥያቄ ጊዜ ሊጨመር የሚችለው ዋናው ወጥ (ቀይ ሽሮው ወይም ምሥር ወጡ) ነው ይላል፡፡ እንጀራ ሲተርፍ ወይም እንጀራ ሲጨመር የወጥ ጭማሪ ቢጠየቅ ዋናውን ወጥ ማስጨመር ይቻላል፡፡

ሦስተኛው የበያይነቱ ሕግ በዋናው ወጥ ዙሪያ ለሚመጡት ዓይነቶች የቁጥር መጠን እንደሌላቸው ይደነግጋል፡፡ ሦስትም ሆኑ አሥራ ሦስት ችግር የለውም፡፡ ቁም ነገሩ ዋናውን ወጥ አጅበው በዙሪያው መኮልኮላቸው ነው፡፡ አራተኛውና እነዚህን በዙሪያው ያሉ ወጦችን የሚመለከተው ሕግ ደግሞ እነዚህ ወጦች ካለቁ አለቁ ነው ይላል፡፡ ዓይነት አይጨመርም፡፡ ዓይነት አለመጨመሩ ብቻ ሳይሆን በበያይነቱ ሕግ ዐንቀጽ አራት ንዑስ ዐንቀጽ አንድ መሠረት በምግብ ቤቱ ውስጥ ዋናው ወጥ አያልቅም እንጂ ዓይነት ሆነው የሚቀርቡት ወጦች ግን ሊያልቁ እንደሚችሉ ይደነግጋል፡፡ እንዲያውም በንዑስ ንዑስ ዐንቀጹ ላይ የዓይነቶቹ መጠን የምግቡ ሰዓት ሲጀመርና ሲያልቅ ሊለያይ እንደሚችልም ያስቀምጣል፡፡ ዋናው ወጥ ግን በብዛት ስለሚሠራ አያልቅም፡፡

አምስተኛው የበያይነቱ ሕግ ዐንቀጽ ዋናውን ወጥ አጅበው የሚቀርቡት ዓይነት ወጦች ‹ወጥ› ወይም ‹ዓይነት› የሚለውን ስም እስከያዙ ድረስ የፈለጉትን ዓይነት፣ መጠን፣ ቅርጽና ጣዕም ሊኖራቸው እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ ለምሳሌ ክክ ወጥ፣ ምጣድ ሽሮ፣ አልጫ ሽሮና አተር ፍትፍት በቅርጽና በስም ካልሆነ በቀር አንድ ዓይነት ናቸው፡፡ ዞሮ ዞሮ ያው ሽሮ ነው፡፡ ነገር ግን በየራሳቸው ስምና ቅርጽ ይዘው ‹ዓይነት› ሆነው መቅረብ እንደሚችሉ ‹የበያይነቱ ሕግ ይፈቅድላቸዋል፡፡

በበያይነቱ ሕግ ዐንቀጽ ስድስት መሠረት አንድ ምግብ ‹ዓይነት› ሆኖ የሚቀርበው በዋናነት ለመልኩና ቅርጹ እንጂ በውስጡ ላለው ይዘት እንዳልሆነ ይደነግጋል፡፡ ለዚህም ሳይሆን አይቀርም እነ አበሻ ጎመን፣ እነ ጥቅል ጎመንና እነ ኪያር እሳት ካደበናቸው የምግብ ይዘታቸው በሙሉ እንደሚጠፋ ቢታወቅም ቅሉ፣ ድብን ብለው በስለው ‹ዓይነት› ሆነው ለመቅረብ የቻሉት፡፡

በበያይነቱ ሕግ ዐንቀጽ ስድስት ንዑስ ዐንቀጽ ሦስት መሠረት ሁለት የበያይነቱ ወጦች የይዘትም ሆነ የቅርጽ ልዩነት ባይኖራቸውም ስማቸው ከተለያየ እንደ አንድ ወጥ ተመዝግበው መንቀሳቀስ ይችላሉ ይላል፡፡ አልጫ ምስርና ቀይ ምስር፣ አልጫ ድንችና ቀይ ድንች ቅርጻቸውም ሆነ ይዘታቸው አንድ ቢሆንም የስም ልዩነት ስላላቸው ግን ይኼው በዓይነትነት ተመዝግበው ቀጥለዋል፡፡

በበያይነቱ ውስጥ እንደ ቃሪያ የሚያቃጥሉ፣ እንደ ምስር የሚጎረብጡ፣ እንደ ተልባ ፍትፍት የሚለሰልሱ፣ እንደ ሩዝ የአበሻ ምግብ ውስጥ ለምን እንደመጡ የማይታወቁ፣ እንደ ቲማቲም ፍትፍት የንጽሕናቸው ጉዳይ ሆድ ሲያጮኽ የሚውል፣ እንደ ስልጆና እንደ አተር ፍትፍት በአንድ ጉርሻ የሚያልቁ ምግቦችም እንዲካተቱ ሕጉ ይፈቅድላቸዋል፡፡

በበያይነቱ ሕግ ዐንቀጽ ዐሥር መሠረት ዛሬ አንድ ዓይነት ሆኖ የቀረበ ወጥ ነገ ተለያይቶ ሁለት፣ ሁለት ሆኖ የነበረም እንድ ሆኖ ለመቅረብ እንደሚችል ይፈቅዳል፡፡ ለየብቻቸው ሲቀርቡ የነበሩት ቀሪያ፣ ቲማቲምና እንጀራ ከቅርብ ዘመናት ወዲህ የቲማቲም ፍትፍት ተብለው ኅብረት መሥርተው መጥተዋል፡፡ ‹ሽሮ ወጥ› ተብለው አንድ ላይ የነበሩት ‹ሽሮ ፈሰስ›ና ‹ሽሮ ተጋቢኖ› ሆነው በየራሳቸው መጥተዋል፡፡

ይህን የበያይነቱን ሕግ አይተን እስኪ የሀገራችን የፖለቲካ ሕግና ባህል እንገምግመው፡፡ ፖለቲካችን ከበያይነቷችን ወይም በያይነቷችን ከፖለቲካችን ተወስዶ ሊሆን ከቻለስ?

በበያይነቱ ሕግ አንድ ዋና ወጥ እንዳለው ሁሉ በሀገራችንም አንድ አውራ ፓርቲ አለ፡፡ ሌሎቹ በመጠናቸው አነስ አነስ ያሉ ወጦች ዋናውን ወጥ አጅበው እንደሚቀመጡ ሁሉ በሀገራችን ያሉት ከብሔረሰቦች ቁጥር የበለጡት ፓርቲዎችም ይህን አውራ ፓርቲ አጅበው የሚኖሩ ናቸው፡፡ ይህ በበያይነቱ የሚገኝ ዋናው ወጥ ይኼው በያይነቱ ከተፈጠረ ጀምሮ ምስር ዋና ሆኖ የመካከሉን ዋና ቦታ እንደያዘው አለ፤ አንድም ዓይነት ሆኖ የገባ ወጥ ቦታውን እንዳልወሰደው ሁሉ በሀገራችንም ይኼው ዋናውም ወጥ ሆነ ዓይነቶቹ ዛሬም በዚያው ቦታቸው ናቸው፡፡

በበያይነቱ ሕግ ዋናው ወጥ ይጨመራል እንጂ ዓይነት አይጨመርም፡፡ በሀገራችን ፖለቲካም አውራው እየጨመረም እየተጨመረም ይኼዳል እንጂ ዓይነቶቹ ካለቁ አለቁ ነው፡፡ ስንት ፓርቲ ዓይነት ሆኖ በሆነ የምርጫ ዘመን ከመጣ በኋላ በሌላ ጊዜ ‹ጨምሩ› ስንል ‹አልቋል፤ ከፈለጋችሁ ምስር ጨምሩ› ተብለናል፡፡  በበያይነቱ ወጥ ዋናው ወጥ በትልቁ ሰታቴ ነው የሚሠራው፤ እንዳያልቅ፡፡ በሀገራችንም ዋናው ፓርቲ በትልቁ ነው የተሠራው፡፡ ወደ ዋናው ወጥ ሰታቴ የማይገባ እህል፣ የማይጨመር ውኃ፣ የማይደረግ ቅመም የለም፡፡ ችግሩ አንዳንዱ በሚገባ ያልተቀመመ፣ አንዳንዱ ‹ኤክስፓየር› ያደረገ፣ አንዳንዱ ምን ሳይጠቅም እንዲሁ የገባ፣ አንዳንዱ እንደ ሽንኩርቱ ያረረ፣ እየሆነ ነው ችግሩ፡፡ ወጥ ሠሪዎቹም ዋናው ዓላማቸው ወጡ እንዲሰፋ፣ እንዲበዛ፤ ከዚያም አልፎ ሌሎቹ ዓይነቶች ሲያልቁ ዋናው ወጥ እንዳያልቅ ማድረግ ነውና ያገኙትን የእህል ዓይነት ሁሉ እያስገቡበት ተቸገርን፡፡

በልቅሶ ቤትም፣ በግብዣም፣ በድግስም፣ በቤታችንም፣ በየመሥሪያ ቤቱ ካፍቴሪያዎችም፣ በብዛትና በስፋት የምናገኘው ይኼንኑ ዋናውን ወጥ ሆነ፡፡ አንዳንዶች ለዚህ የሚሰጡት ምክንያት ይህንን ዋናውን ወጥ መሥራት ቀላል፣ ብዙም ችሎታ የማይጠይቅ፣ ርካሽና በትልቅ ዕቃ የሚሠራ፣ ብዙም መሥዋዕትነት የማይጠይቅ ስለሆነ ነው ብለዋል፡፡

እንደ በያይነቱ ሁሉ የሀገራችን ፓርቲዎች የቁጥር መጠን የላቸውም፤ በብሔረሰቦች ቁጥር መጠን መስሎን ነበር፤ አሁንማ ከዚያም ቁጥር አለፈ፡፡ አንዳንዶቹ የበያይነቱ ወጦች በማንኪያ ተመጥነው የሚቀርቡት ከአንድ ጉራሽ እንደማያልፉ ሁሉ፣ አንዳንዶቹ ፓርቲዎች በዐሥር ሰው ይመሠረቱና ከአንድ ምርጫ ወይም ከአንድ ስብሰባ፣ አለፍ ካለም ከአንድ ሰላማዊ ሰልፍ አያልፉም፡፡ ቀይ ሽሮ፣ አልጫ ሽሮ፣ ሽሮ ፍትፍት፣ ክክ ወጥ፣ አተር ፍትፍት እየተባለ አንዱን ባቄላ ወይም አተር በዐሥር ዓይነት እንደሚያመጡት ሁሉ ከስማቸው በቀር የፕሮግራም፣ የግብ፣ የአደረጃጀትና የአካሄድ ልዩነት የሌላቸው ፓርቲዎች ሞልተውናል፡፡ ልዩነታቸው አንዱ አበበን ነጻ ሲያወጣ ሌላኛው ጫልቱን፣ ሌላኛው ደግሞ ኪሮስን የቀረውም ደንቦባን ነጻ ማውጣቱ ነው፡፡

በበያይነቱ ውስጥ እንደሆነው ሁሉ እንደ ቃሪያ አሠራራቸው የሚያቃጥል፣ እንደ ስልጆ የሚሰነፍጥ፣ እንደ ቀይ ሥር መልክ እንጂ  ይዘት የሌላቸው፣ እንደ ሩዝ እንዴት ፓርቲ ሊሆኑ እንደቻሉ ግራ የሚያጋቡ፣ እንደ ቲማቲም ፍትፍት ሆድ ማስጮህ እንጂ አእምሮ መገንባት የማይችሉ ፓርቲዎችም አሉን፡፡

በበያይነቱ ወጥ ውስጥ እንዳሉት የሐበሻ ጎመንና ጥቅል ጎመን፤ በፖለቲካው እሳት በመንተክተካቸው የተነሣ የምግብ ይዘታቸው የጠፋ፡፡ ቢበሏቸው የማይጠቅሙ፣ ቢተዋቸው የማይጎዱ ዓይነት ፓርቲዎችም አሉን፡፡ እንደ ቃሪያና ቲማቲም ለየብቻ ጀምረው እንደ ‹ቲማቲም ፍትፍት› አንድ ሆነው የመጡ፣ እንደ ‹ሽሮ ወጥ› እንደ ሆነው ጀምረው እንደ ሽሮ ፈስስና ሽሮ ተጋቢኖ ተለያይተው የቀጠሉ ፓርቲዎችም አሉን፡፡

በበያይነቱ ምግብ የምግብ ሰዓት ሲጀመር የነበሩት ዓይነቶች እያለቁ ሄደው በስተ መጨረሻ በያይነቱ ራሱ አልቆ ‹ምስር ወይም ሽሮ ነው ያለን› እንደሚባለው ሁሉ በሀገራችን ከሃያ ዓመት በፊት ምርጫና ዘመቻ ሲጀመር እንደ አሸን ፈልተው የነበሩት ‹በዴሕ› ና በ‹ዴድ› የሚጠሩ ፓርቲዎች አሁን የት እንደደረሱ የሚያውቅ የለም፡፡ ሁሉም ዓይነቶች አልቀው ዋናው ወጥ ብቻ ቀረ፡፡

እንግዲህ የኛ የፖለቲካ ሥርዓት በያይነቱ ምግባችንን ሳይመስል አይቀርም፡፡ ምናልባት ምግቡ ከፖለቲካው ይቀድማልና ፖለቲካው ከምግቡ አሠራሩን ቀድቶት እንደሆነ እስኪ እንመርምረው፡፡ ምናልባት በያይነቱን ብናስተካክለው ፖለቲካው ይስተካከል ይሆን?

ቸር ይግጠመን፡፡

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽት ላይ የወጣ ነው

ሀ/ስብከቱ ከኑሮ ውድነት አንጻር በአጥቢያዎች ተሳትፎ እያስጠናው የሚገኘው ጊዜያዊ የደመወዝ ጭማሪ ማስተከከያ ጥናት በመዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር አሠራር መመሪያ ረቂቅ ውስጥ ካለው የአብያተ ክርስቲያናት ደረጃ መስፈርት፣ የሥራ መደብ ግምገማ፣ የአገልጋዮች ጥቅምና ጫና ጥናት ጋራ አንዳችም ግንኙነት የለውም፡፡ ለፊርማ አቤቱታው የቀረቡት ጥያቄዎች ይዘት ‹ተቃዋሚዎቹ›÷ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ከቃለ ዐዋዲ ደንቡ ጋራ ያለውን ልዩነትና በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ላይ …

የእንጀራ ነገር ሆኖብኝ እጓዛለሁ ፣ እጓዛለሁ ፣ እጓዛለሁ … እንደጨው ተበትነናልና ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወገኖቸን በየሔድኩበት ከተማ ፣ እግር በጣለኝ የሳውዲ የቀለጡ በርሃዎች ወንድም እህቶቸን አገኛለሁ ። ላፍታም ቢሆን ጊዜ ሰጥቸ እየኑሩት ስላለው ኑሮ ፣ እየገፉት ስላለው ክፉም ደግ ተሞክሮ እጠይቃቸዋለሁ አንድም ሳይደብቁ የሆድ የሆዳቸውን ያጫውቱኛል … እለተ ቅዳሜ በማለዳው ያቀናሁት በያንቦና በጅዳ መካከል በምትገኝ […]

ታህሳስ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳያስፖራ ተሳትፎ ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ጀኔራል የተገኘ መረጃ  በግምት ከ2-3 ሚሊዮን የሚደርሱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የአለም ከፍሎች ቢኖሩም ለአገራቸው ያላቸው አስተዋጽኦ ግን አነስተኛ ነው ብሎአል። አውሮፖና አሜሪካ የኢትዮጵያውያኑ ዳያስፖራዎች ዋነኛ መዳረሻዎች ሲሆኑ በርካታ የዳያስፖራው አባላትም በእነዚሁ አህጉራት ይገኛሉ ይላል። እውቅና ያገኙ ተመራማሪዎች ፤ የጤና ባለሙያዎች ፤የዩንቨርስቲ …

ታህሳስ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-የመንግስት ሰራተኛው በከፍተኛ የኑሮ ውድነት እየተሰቃዩ መሆኑን እንደሚያዉቁ የተናገሩት ሁለት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኖች፣ ይሁን እንጅ በሚቀጥሉት ሶስትና አራት አመታት በጉልህ የሚታይ ደሞዝ ጭማሪ እንደማይኖር ገልጸዋል። በየአምስት አመቱ የቤተሰብ ፍጆታቸው በተመረጡ ናሙናዎች ተወስዶ በሚለካው የግሽበት አሃዝ ስሌት መንግስት የኑሮ ውድነቱ በአንድ አሃዝ መውረዱን ቢገልጽም፣ የኑሮ ውድነት ግን አለመርገቡን ነዋሪዎች ይናገራሉ። …

ታህሳስ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በተለይ ከመሬት ይዞታ ጋር በተያያዘ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸውና በታችኛው አመራር ጭምር ሊፈቱ የሚገቡ ጉዳዮች ተጠያቂነትን ከመፍራት አኳያ ወደ መካከለኛና ከፍተኛ አመራሩ የመግፋት ጉዳይ በተደጋጋሚ መከሰቱ አሳሳቢ መሆኑ ሰሞኑን በተደረገው ግምገማ ላይ ቀርቧል፡፡ አስተዳደሩ የ2006 የመጀመሪው ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም  በገመገመበት መድረክ ላይ ተጠያቂነትን ለመሸሽ ሲባል ስራዎችን ወደላኛው አካል የመግፋት ጉዳይ …

ታህሳስ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ተሞክሮ የነበረው መፈንቅለ መንግስት መክሸፉን በተናገሩ ማግስት ግጭት መነሳቱን ረዩተርስ ዘግቧል። አልፎ አልፎ ይሰማ የነበረው ተኩስ በተከታታይ መሰማቱን የገለጸው ረዩተርስ፣ የአሜሪካ ልዩ ልኡክ የሆኑት ዶናልድ ቡዝ ሁኔታው ውጥረት የበዛበትና ያልተረጋጋ መሆኑን ገልጸዋል። እስካሁን ባለው መረጃ 26 ሰዎች እንደተገደሉ ቢታወቅም አንዳንድ የመገናኛ ብዙሀን ከ60 በላይ ወታደሮች እንደተገደሉ እየዘቡ …

የማሊ ሕዝብ ባለፈው እሁድ ሁለተኛውን ዙር ምክር ቤታዊ ምርጫ አካሂዷል። የሀገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ አሁንም አሳሳቢ የሆነበት ድርጊት በምርጫው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳረፉ አልቀረም። እንደታየው፣ ሕዝቡ በምርጫ ለመሳተፍ ፍላጎት ያለው አይመስልም። ከማሊ በተገኙ ዘገባዎች መሠረት፣ ድምፁን ለመስጠት የወጣው መራጭ ሕዝብ ቁጥር በጣም ዝቅተኛ ነበር።