በድንበር አከባቢ የመሬት ጥያቄ የሚያነሱ ኢትዮጵያውያን በአዲሱ የጦር ሃይል ይመታሉ:: በጀቱን ኢሕኣዴግ መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ይሸፍነዋል::

በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል በተደረገው የድንበር ጉዳይ ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ ወደግዛቷ 62.6 ኪሎ ሜትር ዘልቆ የሚገባ እና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የሚያፈናቅለውን የመሬት ርክክብ በምስጢር መፈጸሟን ተከትሎ በዚሁ ሱዳን በምትረከበው ድንበር አከባቢ የመሬት ጥያቄ የሚይነሱ የሚያምጹ እና የሚሸፍቱ ሊኖሩ ይችላሉ በሚል ወያኔ የሱዳን ሰራዊት እና የራሱ ምልምል የሆኑ ትውልዳቸው ሱዳን የሆነ ኢትዮጵይውያንን አሰልጥኖ ህገወጦችን መቆጣጠር በሚል ሽፋን የድንበር አከባቢ ተወላጆችን ለማስመታት በዝግጅት ላይ መሆኑ ታውቋል::

ይህ ይቋቋማል የተባለው የጋራ የጦር ሰራዊት ህገወጥ ብሎ የፈረጃቸውን እና የመሬት ጥያቄ ሊያነሱ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱትን የአማራ ገበሬዎች ለመምታት የታቀደ እና እንዲሁም ይህንን ተከትሎ የተቃዋሚ ድርጅቶች አማጺያን ሰርገው ይገባሉ በሚል ስጋት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳን ወያኔ ወደ ካርቱም ልኮ ሚኒስትሩ ሳምንት ካርቱም ሰንብተው ወደ ሃገር ቤት መጥተዋል::

በሰሜን ጎንደር በምእራብ ጎጃም በቤንሻንጉል እና በጋምቤላ አከባቢዎች ወያኔ ፋታ የማይሰጡ የለውጥ ጥያቄ ያላቸው ታጣቂ አማጽያን ጦር ወድረው እየተኮሱበት መሆኑን ያማረረው ኢሕኣዴግ የሱዳንን መንግስት በመማጸን የጋራ የጦር ሰራዊት በማቋቋም በጀቱን ኢሕኣዴግ ከህዝብ ቀረጥ ከሚከፍልበት ገንዘብ የሚሸፍን መሆኑ ተረጋግጧል::ምንሊክ ሳልሳዊ