አቡጊዳ – ኢቲቪ ስለባህር ዳሩ ሰልፍ የዘገበው የጅምናስቲክ ዘገባ
ኢቲቪ የሕዝብ ሜዲያ ነው። በሕገ መንግስቱ መሰረት ለኢሕአዴግ ሳያደላ ገለልተኛ በሆነ መንገድ እዉነትን መዘገብ ነበረበት። ነገር ግን ከሰባ እስከ ሰማኒያ የሚጠጋዉ ሕዝብ የተገኘበትን ታሪካዊ የባህር ዳሩን ሰልፍ አሳንሶ ለማቅረብ፣ ሰልፉ ከተበተነ በኋላ፣ ሁሉም ወደ የሰፈሩ በሚሄድበት ጊዜ የተነሱ ፊልሞችን በማሳየት፣ ወደ ሰማኒያ ሺህ የሚጠጋዉን ሕዝብ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ብቻ እንደሆነ ለማስመሰል የተሞከረበት ሁኔታ ነዉ፣ በኢቲቪ የታየው። 
በስብሰባው የመኢአድ እና የአንድነት ሊቀመንበር ከተናገሩትም ቀንጨብ አድርገው አሰምተዋል። ኢንጂነር ግዛቸው ሰልፉን ሲጠብቁ የነበሩ የትራፊክ ፖሊስ አባላት አመስግነው ነበር: ነገር ግን ኢቲቪ ለትራፊክ ፖሊሶች የተሰጠውን ምስጋና ለአስተዳደሩ እንደተሰጠ አደርጎም ለማቅረብ ኢቲቪ ሞክሯል።
«ሕዝብ ሁሉ ያየዉን ቀይረው ይህ አይነት ዉሸትና ማጭበርበር ለማድረግ መሞከራቸው፣ ሕዝቡ ምንም የማያውቅ ደካማ አደርገው እንደቆጠሩትና እንደናቁት የሚያሳይ» ነው ያሉት በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ «እራሳቸውን በ እንዲህ ሁኔታ ከሚያስገምቱ ፣ ዝም ቢሉ ይሻላቸው ነበር» ሲሉም ዘገባውን አሳዛኝ ፣ አሳፋሪና የኋላ ቀር ብለዉታል።