የደረጀ የሕክምና ሥርዓትና አቅርቦት ባለቸው የበለጸጉ አገሮች እና በወረርሽኙ በተጠቁት የምዕራብ አፍሪቃ አገሮች ለኢቦላ ሕሙማን የሚሰጠው ሕክምናና እንክብካቤ የውይይቱ ትኩረት ነው።

የሙከራ ሕክምናና ክትባቶች፤ በእስካሁኑ የበሽታው ሕክምና የሠሩና ያልሰመሩ ጥረቶች በተከታታይ ፕሮግራሙ ይቃኛሉ።

ዶ/ር ብስራት በሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ትምህርት ቤት ተባባሪ ፕሮፌሰርና የመድሃኒቶች መረጃ አገልግሎት ክፍል ዲሬክተር ናቸው።

አፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊግ ያወጠው ሪፖርት እንደሚያሳየው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በአምቦ ከተማ እና በሚዳ ቀኒ ወረዳ ከ20 ያላነሱ ተማሪዎች፣ መምህራንና አርሶ አደሮች ታስረዋል። እስራቱ የተፈጸመው መንግስት የአካባቢውን መሬት ለኢንቨስተሮች መስጠቱን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ ነው።ኦሮምያ የሚታሰሩ ዜጎች ቁጥር መበራከት የአለምን የመገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን ባገኘ ማግስት፣ አሁንም ዜጎችን በሰበብ አስባቡ እያሰሩ ለፍርድ አቅርቦ ማስፈረድ ቀጥሎአል::
Image

ከታሰሩት መካከል አርሶ አደር ኪጣጣ ረጋሳ፣ ተማሪ ቶሎሳ ተሾመ፣ ድሬ ማሾ፣ ታሪኩ ቡልሾ፣ ያለው ባንቲ፣ ቢንያሳ ኢባ፣ ተስፋይ ቢይነሳ እና ነጋዴ መግስቱ ሞሲሳ ይገኙበታል።
እንዲሁም ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የጅምላ እስራቶች እየተከናወነ ነው። ብዙዎቹ በህጋዊ መንገድ የሚታገለው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አባላት በመሆናቸው ብቻ መታሰራቸውን የሚገልጸው ሊጉ፣ በጅማ የድርጅቱ አመራሮች የሆኑት አቶ አጀብ ሼክ ሙሃመድ፣ አቶ ሙሃመድ አሚን ካልፋና አቶ ነቢብ ጀማል ታስረው 2 አመት ከስድስት ወር እንደተፈረደባቸው ጠቅሷል።

ተፈጸመ ስለተባለው እስራት ያነጋገርናቸው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ተጠሪ አቶ በቀለ ነገአ ሰዎቹ በሃሰት እንደተፈረደባቸው አረጋግጠዋል። መሳሪያ የሌላቸውን ህገወጥ መሳሪያ ደብቃችሁዋል በሚል በሃሰት ተመስክሮባቸው መታሰራቸውን አቶ በቀለ አስረድተዋል

ከታሳሪዎች መካከል የአቶ አጀብ ሼክ ሙሃመድባለቤት የሆኑት ወ/ሮ አዳነች ለኢሳት እንደገለጹት ደግሞ ባለቤታቸው በሀሰት ተመስክሮባቸው ከታሰሩ ጀምሮ እርሳቸውም በሚደርስባቸው ማስፈራሪያ ከቤት ለመውጣት መቸገራቸውን ገልዋል። ወደ ጎረቤት ሄደው እሳት እንዳይጭሩ ከመከልከላቸውም ሌላ፣ ቤታቸው በደንጋይ የደበደባል። የባለቤታቸው ወንድም ተመሳሳይ ችግር ስላጋጠመው ስራውን ትቶ ወደ ከተማ መምጣቱንም ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሰሞኑን እስር ቤቶች በኦሮሞ ተወላጆች መሞላቱን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ አለም የመገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል።
Minilik Salsawi Via ESAT

በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቄራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ አየር ጤና አካባቢ አንዲት የአሥረኛ ክፍል ተማሪ በተሳፈረችበት ታክሲ ታፍና ከተወሰደች በኋላ በደረሰባት አስገድዶ መደፈር ጉዳት ሕይወቷ ማለፉን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

ሟቿ ተማሪ ሃና ላላንጎ ጥቅምት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. አየር ጤና በተለምዶ ሳሚ ካፌ በሚባለው አካባቢ በአንድ ሚኒባስ ውስጥ ተሳፍራ ወደ ጦር ኃይሎች እየመጣች እንደነበር ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡

ከትምህርት ቤት ወጥታ ወደ ቤተሰቦቿ በመጓዝ ላይ የነበረችው ሟች ተማሪ የተወሰነ ርቀት ከተጓዘች በኋላ መድረሷን ተናግራ ‹‹ወራጅ አለ›› ስትል፣ በሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ አራት ወንዶችና ሾፌሩ ስለት በማውጣት አስፈራርተው እንዳገቷትም ተጠቁሟል፡፡

ሟች እንዳትናገር በማድረግ በሰዋራ ቦታ በታክሲው ውስጥ እንድታመሽ ከተደረገች በኋላ፣ ከተጠርጣሪዎቹ አንደኛው ቤት ወስደው ለአምስት እየተፈራረቁ እንደደፈሯት ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

አንደኛው ተጠርጣሪ በራሱ ቤት ውስጥ እንድትቆይ በማድረግ ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲደፍራት እንደከረመም ምንጮቹ አክለዋል፡፡

ሁለተኛ ተጠርጣሪ ነው የተባለው ግለሰብ ለአምስት ቀናት በተደጋጋሚ ሲደፍራት ከከረመ በኋላ፣ ከቤት አውጥቶ ጭር ባለ ቦታ ጥሏት መገኘቷንም ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

ሟች ከፍተኛ የሆነ የማሕፀንና የፊንጢጣ ጉዳት አጋጥሟት ስለነበር በተለያዩ ሆስፒታሎች ሕክምና ያደረገች ቢሆንም፣ በደረሰባት ከባድ ጉዳት በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል በመታከም ላይ እያለች ሕይወቷ ማለፉን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

ሟች በመሀል በአንደኛው ተጠርጣሪ ስልክ ወደ ቅርብ ጓደኛዋ በመደወል ስልኩን በመዝጋቷ ጓደኛዋ የደወለችበትን ስልክ ለቤተሰቦቿ ትሰጣለች፡፡

የሟች ቤተሰቦች የሞባይሉን ቁጥር ለፖሊስ አሳልፈው በመስጠታቸው ፖሊስ ባደረገው ከፍተኛ የክትትል ሥራ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ሁሉም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው በአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት ቀርበው በወንጀል መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 35 መሠረት የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸውንም ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡

Reporter
Image

ማእከላዊ አፍሪካ ሪፑብሊክ ውስጥ ዳግም በተቀሰቀሰው ግጭት ባለፈው አንድ አመት ተመንፈቅ ጊዜ ውስጥ ብቻ በ 10 ሺህ የሚገመቱ ሕጻናት በታጣቂ ቡድኖች ለውትድርና ተመልምለዋል።

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

የአውሮጳ ህብረት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በምሥራቅ ዩክሬይን ዓማፅያን አንፃር አዲስ ማዕቀብ ለመጣል ተስማሙ። የህብረቱ ዲፕሎማቲክ ክፍል በዚህ በተያዘው የህዳር ወር መጨረሻ ውሳኔ የሚሰጥበት አንድ የዩክሬይንን ዓማፅያን ዒላማ ያደረገ አዲስ ዝርዝር እንዲያቀርብ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቹ ጠይቀዋል።

ኩፍኝን ከዓለም ፈፅሞ ለማጥፋት የሚደረገዉ ጥረት መሻሻል አለማሳየቱን የዓለም የጤና ድርጅት ባለፈዉ ሳምንት ይፋ አድርጓል። በምክንያትነት ከተጠቀሱት የበሽታዉ ከሰዉ ወደሰዉ ፈጥኖ የመተላለፍ ባህሪ አንዱ ሲሆን የክትባት አለመዳረስም ሌላዉ ጉዳይ ነዉ።

ከመስከረም ወር አጋማሽ አንስቶ በቻይናዋራስ-ገዝግዛትሆንግኮንግ የተጀመረው የተቃዉሞ ሠልፍ እና አድማ አልተጠናቀቀም። አሁንም ሰልፈኞቹ የፋይናንስ ቦታዎችን ይዘው ይገኛሉ። ይሁንና ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ የሆንግ ኮንግ ፖሊስ የተወሰኑ ቦታዎችን ከሰልፈኞች አስለቅቋል።

በየእሩሳሌም ሙክራብ ላይ የደረሰ ጥቃትእየሩሳሌም ውስጥ የተነሳው ብጥብጥ ይበልጥ ከሯል። ዛሬ ዳግም አዲስ ጥቃት ከተማዋን አናግቷል። ይህም በአይሁዳውያን ቤተ ፀሎት ላይ ነው። በዚህም ጥቃት 6 ሰዎች ሰዎች ተገድለዋል። ሁለት ጥቃት አድራሾች እና አራት ሲቪሎች።


‹ሐተታ ዘርአ ያዕቆብ› የተሰኘውን መጽሐፍ በተመለከተ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ(እድሜያቸውን ያርዝምና) ከመልካም ሐተታ ጋር አዘጋጅተውታል፡፡ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ ማን ጻፈው? ዘርአ ያዕቆብ ማነው? ትውልዱስ የት ነው? ፍልስፍናው ከየት መጣ? እውነት ኢትዮጵያዊ ነው ወይስ የውጭ ሰው? ኢትዮጵያዊ ነው ብሎ ለመከራከር በመጽሐፉ ውስጥ ማስረጃዎች አሉን? የሚሉትንና ሌሎች ጥያቄዎችን አንሥተው ይተነትናሉ፡፡ መጽሐፉንም ተርጉመውና አትተው አቅርበውታል፡፡ የሚከተለውን ሊንክ ተጫኑና በነጻ አንብቡት፡፡

ኀዳር ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ የሚታሰሩ ዜጎች ቁጥር መበራከት የአለምን የመገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን ባገኘ ማግስት፣ አሁንም ዜጎችን በሰበብ አስባቡ እያሰሩ ለፍርድ አቅርቦ ማስፈረድ ቀጥሎአል። አፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊግ ያወጠው ሪፖርት እንደሚያሳየው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በአምቦ ከተማ እና በሚዳ ቀኒ ወረዳ ከ20 ያላነሱ ተማሪዎች፣ መምህራንና አርሶ አደሮች ታስረዋል። እስራቱ የተፈጸመው መንግስት …

ኀዳር ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የማጅራት ገትር ወረርሺኝ ጋር ተያይዞ ከሳምንት በፊት ለ10 ተከታታይ ቀናት ዕድሜያቸው ከ1 እስከ 29 ኣመት ክልል ላሉ ዜጎች ክትባት የመስጠት ሒደት የተከናወነ ቢሆንም አፈጻጸሙ ከተጠበቀው ውጪ ሆኖአል፡፡ በተለይ ዕድሜያቸው ከ29 ዓመት በላይ መከተብ አያስፈልጋቸውም፣ ከተከተቡ የጎንዮሽ ችግር ያመጣባቸዋል መባሉ ግማሽ ያህል የህብረተሰብ ክፍል ቢሞትም ግድ የለንም እንደማለት ተደርጎ …

የሙግትና የአዕምሮ አክሮባት ከመሥራት ይልቅ፤ የህዝቡስ ሁኔታ እንዴት ነው? ማለት ዋና ጉዳይ ነው፡፡ በሀገራችን “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል” የተባለው ተረት ዕድሜው እጅግ ረጅም ነው፡፡ የሥርዓቶቻችንን ያህል አርጅቷል፡፡ በተግባር ሲተረጐም ግን ገና ዛሬ የተወለደ ነው የሚመስለው፡፡ በየቢሮው፣ በየማህበሩ፣ በየፓርቲው የምናየው ሀቅ ነው፡፡ “አዲስ እረኛ ከብት አያስተኛ”፣ “እከክልኝ ልከክልህም” አብሮ ሲተረት የኖረ ነው፡፡ ማናቸውም ዕቅድና ስትራቴጂ ህዝብ […]

በቅርቡ የሚከተለውን ጽፌ ነበር፡ “አገር ቤት ላሉ ተቃዋሚዎች ደግሞ የሚከተለዉን መልእክት አስተላልፋለሁ። የምርጫ ፓርቲ ናችሁ። ነገር ግን በባዶ እግራችሁ ብስክሌት ከያዘ ጋር እንወዳደራለን ብሎ መነሳት፣ ራሳችሁን ከማስገመት በተጨማሪም ለገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ፍጆታ መጠቀሚያ ብቻ ነው የምትሆኑት። ምርጫ የምትሳተፉ ከሆነ፣ የምርጫ ዘመቻ ማድረግ አለባችሁ። ምርጫው ሰባት ወራት ነው የቀሩት። በሚቀጥለው አንድ ወራት ዉስጥ አገዛዙ ነገሮችን ካላስተካከለ […]

የሙግትና የአዕምሮ አክሮባት ከመሥራት ይልቅ፤ የህዝቡስ ሁኔታ እንዴት ነው? ማለት ዋና ጉዳይ ነው፡፡
Minilik Salsawi

በሀገራችን “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል” የተባለው ተረት ዕድሜው እጅግ ረጅም ነው፡፡ የሥርዓቶቻችንን ያህል አርጅቷል፡፡ በተግባር ሲተረጐም ግን ገና ዛሬ የተወለደ ነው የሚመስለው፡፡ በየቢሮው፣ በየማህበሩ፣ በየፓርቲው የምናየው ሀቅ ነው፡፡ “አዲስ እረኛ ከብት አያስተኛ”፣ “እከክልኝ ልከክልህም” አብሮ ሲተረት የኖረ ነው፡፡ ማናቸውም ዕቅድና ስትራቴጂ ህዝብ ኑሮ ላይ ያነጣጠረ መሆን አለበት፡፡ ይሄ ማለት የእርስ በርስ ሙግትና የአዕምሮ አክሮባት ከመሥራት ይልቅ፤ የህዝቡስ ሁኔታ እንዴት ነው? ማለት ዋና ጉዳይ ነው፣ ማለት ነው፡፡

ሕዝቡ የኑሮ ውድነት ከበደኝ! የእቃ ዋጋ ንረት አስመረረኝ! ግፍ በዛብኝ! ሸምቶ መቃመስ አቃኝ የሚል ምሬት ሲያሰማ.. ሹመኞች አፍ ለማስያዝንና ለማሸማቀቅ ይሽቀዳደማሉ፡፡ የህዝብን የኑሮ ደረጃ ዝቅ ብሎ ወርዶ የሚያይ መሪ፣ አለቃ፣ ኃላፊ ማግኘት መታደል ነው፡፡ ያስቀናል፡፡ የዋጋ መናርና የታክስ ማሻቀብ አንድን ማህበረሰብ የጦርነትን ያህል ያጠፋዋል፡፡ ለዚህ ነው መሪዎች ሁሉ የህዝባቸውን ኑሮ በቅርብ ያስተውሉ የሚባለው፡፡ ህዝብ የሀገር ሙቀት መለኪያ ነው፡፡ ህዝብ የሚከፍለው ግብር ከሚያገኘው አገልግሎት ጋር ካልተመጣጠነ የቀዘቀዘች አገር ውስጥ ነው የሚኖረው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እውነት እና በገሃድ የሚታየው ህዝብ ደሞዙ ከሚኖረው ኑሮ ጋር ስለማይመጣጠን ኖረ አይባልም፡፡ ህዝብ ከዕለት ዕለት ህይወት እየከበደው በመሄዱ ከሳቁ ምሬቱ፣ ከደስታው ሐዘኑ እየበረታ ሥርዓቱን፣ አገዛዙን፣ ገዢዎቹን፣ አስተዳዳሪዎቹን እጅግ ጠልቷቸዋል፡፡ ሀገሩም የእሱ አትመስለውም፡፡ ህዝብ መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን ለማግኘት ነግ-ሠርክ መሰለፉ ፤ አልፎ ተርፎም ከናካቴው ዕጥረት የሚከሰትበት ሁኔታ፣ ብሶቱ ወሰን የለውም በብሶት ተሞልቷል፡፡ ህዝብ በመኖሪያ ቤት ችግር እየተሰቃየ ሲሆን መሰረታዊ የኑሮ አስፈላጊ ነገር ጎሎበታል ፡፡

ከዚህ ሁሉ የሚከፋው ደግሞ ይህንን የሚገልፅበት መንገድ እንዳያገኝና በፍርሃት ተሸማቆ እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡ “አዲስ ያይጥ – ወጥመድ በሰራህ ቁጥር” አዲስ አይጥ የምትወለድ ከሆነ፣ ወይ ወጥመዷ ላይ ወይ አጥማጁ ላይ ችግር አለ ማለት ነው” ይባላል፡፡ በሙስና የተሞላ ልማት ዘርዛራ ወንፊት ነው፡፡ ዕብቁንም፤ እንክርዳዱንም፤ እያሳለፈ፤ እያዩ እህል አለን እንደሚሉት አይነት የዋህነት ይሆናል፡፡ የዚህ ሁሉ መጨረሻው ድህነት ነው፡፡ ድህነት ሲመጣ ቃላት ይበዛል። ስብሰባ፣ ንግግር፣ የማይተገበር ቃል – መግባት እንደህይወት ይወሰዳል፡፡ እንደኑሮ ይለመዳል፡፡ይህ በወያኔዎች በተግባር እያየነው ያለው ሃቅ ነው::

ሃገራችን እና ወገናችን በጨለማ ውስጥ እየዳከረ ባለበት በዚህ የወያኔ አገዛዝ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በመረባረብ የዜግነት ግዴታውን አውቆ ለህዝቦች መብት እና ነጻነት መታገል አለበን። ሃገሪቷ በዚህ አደጋ ውስጥ ባለችበት ሰአት ላይ ህዝብ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ለኑሮ ውድነት ለሞት ለስደት እየተዳረገ ኢትዮጵያዊነት እየተዋረደ ከመሆኑም ባሻገር ሃገሪቷን ወደ ፍርስራሽነት ለመቀየር የሚሮጡ ጥቂት ሆዳሞች ባሉበት ልንቀብራቸው ይገባል።

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ በአፍሪካ የአሜሪካ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት ሚስጥር፡ “በሚቀጥለው ትውልድ ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ“    ባለፈው ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ በጣም የተጋነነ የዩኤስ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ፌሽታ ነበር፡፡ ሁሉም ነገር “በጣም ፈጣን እድገት እያስመዘገበ ስላለው አህጉር፣ በወጣት ትውልድ ስለተሞላው እና ከፍተኛ የሆነ መዋዕለ ንዋይ እየፈሰሰበት ስላለው“ የአፍሪካ አህጉር ነበር፡፡ …

በአፍሪካ የልማት እና የመዋዕለ ንዋይ ፍሰትን ሚስጥር ሀሰትነት ማጋለጥ፣ Read more »

የግብፅ መንግሥታት፣ ደካማ ኢትዮጵያን ለማየት ካላቸው ፍላጎት የተነሳ የኤርትራ ነፃነት ግንባሮችን መልምለው፣ አሠልጥነውና አስታጥቀው በኢትዮጵያ ላይ አዘመቱ፡፡ የኤርትራ ግንባሮች በበኩላቸው ጦርነቱ በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች እንዲዳረስ ለማድረግ የተጠቀሙበት መንገድ የብሔረሰብ ንቅናቄዎችን መፍጠር እንዲሁም ሌሎች የእነሱን አርዓያ ተከትለው እንዲቋቋሙ ማገዝ ነው፡፡ የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተመሠረተውን የፌዴሬሽን ግንኙነት ማፍረሱ በቀጣናው ጦርነት እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኗል፡፡ ዘውዳዊውም […]

በሰሜን አሜሪካና አውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከቅርብና ከሩቅ ተጠራርተው ቅዳሜለት በአርሊንግተን ቨርጂኒያ ስብሰባ አድርገው ነበር። ውይይታቸው በኢትዮጵያ ዘለቄታ ያለው ትብብር ለመገንባት የሚያስችሉ አዳዲስ ሃሳቦችና የጋር እሴቶችን በመመርመር ላይ ያተኮረ ነበር።

በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የጋራ እንቅስቃሴ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የተባለ የሲቪክ ድርጅት ያሰናዳው ጉባዔ ከተለያዩ ብሄሮች፤ ጾታና የሃይማኖት አባላት፤ እራሳቸውን እንደግለሰብ ወክለው የተሳተፉበት ነበር።

ቅዳሜለት በዋሽንግተን ዲሲ አቅራቢያ በምትገኘው አርሊንግተን ቨርጂኒያ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያዊያን፤ በሀገራቸው ተቋማዊ አስተዳድር ባልተጠናከረበት መልኩ፤ ማህበረሰቦች ሊጫወቱት የሚገባቸው ሚና፣ እንዲሁም እርስ በርስ የመተባበር ሃሳቦች ላይ ያተኮረ ነው።

የጋራ እንቅስቃሴ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ በዋሽንግተን…

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር : በትናንትናው ዕለት ህዳር 7/2007 ዓ.ም ሰብሰባ ጠርቶ በገዥው ፓርቲ ደህንነቶችና ፖሊስ የተበተነበት የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የኢትዮጵያ ችግር ከአንድ ፓርቲ አቅም በላይ በመሆኑ በትብብሩ ምስረታ ወቅት የነበሩትንና ሌሎቹም ፓርቲዎች ትብብሩን በመቀላቀል የተቃውሞ ጎራውን እንዲያጠናክሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጥሪ አቅርቧል፡፡

መግለጫው አክሎም አገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የአገራቸውንና የዜግነት ክብራቸውን ለማስመለስ በቀጣይነት ለሚደረገው ሰላማዊ ትግል ጥሪ አወንታዊ ምላሽ በመስጠት በጋራ ‹‹በቃን›› ብለው እንዲነሱ ጥሪ አቅርቧል፡፡ በአንጻሩ የፖሊስ ኃይልና ሌሎች አስፈጻሚ አካላት በገዥው ፓርቲ ሴራ ተጠልፈው ከሰላማዊ ዜጎች ጋር እንዳይጋጩና ህገ መንግስቱንም እንዲያከብሩ እንዲሁም ገዥው ፓርቲም ካለበት ፍርሃትና ስጋት ወጥቶ ለለውጥ ዝግጁ እንዲሆን ትብብሩ አሳስቧል፡፡

በሌላ በኩል ‹‹በህዝብ ሀብት የሚተዳደሩት መገናኛ ብዙሃን ሙሉ በሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር ውለው ገዥውን ፓርቲ ከማገልገል አልፈው በሰላማዊ ትግል የፖለቲካ ኃይሎች ላይ አፍራሽ ፕሮፖጋንዳ›› እንደሚነዙ ያስታወሰው ትብብሩ በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን ስላደረጉት አወንታዊ አስተዋጽኦ አመስግኗል፡፡ በቀጣይም ለህዝብ በመወገን ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለአፍሪቃ ዋንጫ የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታውን እጅግ የጠበበ ዕድል ይዞ ረቡዕ ያከናውናል። ቡድኑ በአዲስ የውጭ ሀገር አሠልጣኝ መመራት ከጀመረ ወዲህ ለማሸነፍ የቻለው አንድ ጨዋታ ብቻ ነው። ምክንያቱ ምንድን ነው? ጂብራልታርን 4 ለ0 ያሸነፈው የጀርመን ቡድን አሠልጣኝ በውጤቱ አልተደሰቱም።

አንዱ ቡድን በ15ለ 1 ተፃራሪ ሐይላት የተወጠረ፤ በ4መሐል ሰፋሪዎች የተትመከመከ መሆኑን መስካሪ ነዉ።ለዘንድሮዉ ጉባኤ የመነጋገሪያ ርዕስ፤ የአቋም መግለጫምከቡድኑ ይፋዊ አላማ ጋር የሚጣጠም ነዉ።ምጣኔ ሐብት።

በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ በኢትዮጵያ ሶስት የኢቦላ ተጠርጣሪ ህሙማን ተገኙ የሚል ደብዳቤ እየተሰራጨ ነው። የክልሉ ጤና ቢሮ ደብዳቤውን እንደማያውቀው የኢቦላ በሽታም በክልሉ አለመኖሩን አስታውቋል።

ከጀርመን ወደ 450 ጀርመናዉያን ሳላፊስቶች ወደ ሶርያ መጓዛቸዉ ተመልክቶአል። ከነዚህ መካከል ደግሞ 10 በመቶዉ የሚሆኑት ራድዮ ጣብያችን ከሚገኝበት ከቦን ከተማ መምጣታቸዉ ነዉ የተነገረዉ። የቀድሞዋ የምዕራብ ጀርመን መዲና ቦን ለምን የፅንፈኞች ማዕከል ለመሆን በቃች?

ኀዳር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪነት 9 የፖለቲካ ድርጅቶች በጋራ የጠሩት የአደባባይ ስብሰባ በገዢው ፓርቲ የጸጥታ ሃይሎች እንዲበተን ከተደረገ በሁዋላ ድርጅቶቹ ባወጡት መግለጫ ” መንግሥት ከገባበት ከፍተኛ የፍርኃት ስሜት ለመውጣት ያስቀመጠው የሴራ መፍትሄ  መስዋዕትነቱን ይጨምር እንደሆን እንጂ፣ ትግሉን አያቆመውም” ብለዋል። ፓርቲዎቹ ለአንድ ወር ባወጡት የስራ መርሃ ግብር መሰረት ከአራት ኪሎ እና …

ኀዳር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ፣ በደቡብ እና  በአማራ ክልሎች በተካሄደ የመረጃ አመራር ስልጠና ላይ አሰተያየት የሰጡ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ጋዜጠኞች ‹‹ቡጨ›› በማለት የሚጠሩት  ቡጨቃ ፤ቆረጣ ወይም ሃብትን መካፈል የሚባለው አሰራር  እንዳማረራቸው ገልጸዋል። ባለስልጣኖቹ “መንግስት ከከፈላቸው አበል ውጭ በድጋሜ አበል ካልተከፈላቸው ፕሮግራሞቻችን በደንብ አይሸፈኑም፤ ምንም አይነት ሂሳብ ካላገኙ ወይም የምግብ ፤ የነዳጅ እና …

ኀዳር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብሌስ ካምፓወሬ መንግስት በ2 ቀናት አመጽ ከተገለበጠ በሁዋላ ስልጣን ለሳምንታት ተረክቦ የነበረው የመከላከያ ሰራዊት ስልጣኑን ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ለተመረጡት ለቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚኬል ካፋንዶ እንደሚያስረክብ ታውቋል፤፡ሌ/ኮ አይሳክ ዚዳ ስልጣናቸውን በፍጥነት እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል። የ72 አመቱ ካፋንዶ ከሃይማኖት፣ ከጦር ሰራዊት፣ ከፖለቲካ፣ ከሲቪክ ማህበረሰቡና ከባህላዊ መሪዎች ተውጣጦ በተመሰረተው ጉባኤ …

(አዲስ ቮይስ) የአሜሪካን ድምጽ ዳይሬክተር ዴቪድ አንሶር የአፍሪካ ቀንድ የበላይ ሃላፊ የነበረው ፒተር ሃይንላይን ከሃላፊነቱ መነሳቱን አሳወቁ። ዳይሬክተሩ ባለፈው አርብ የክፍሉን ሰራተኞች በድንገት ሰብስብስበው እንዳስታወቁት ሃይንላይን ከሃላፊነቱ ተነስቶ በምትኩ የርሳቸው ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ዊሊያም ማርሽ በግዚያዊነት መሾማቸውን ገልጸዋል። በቅርቡ በአሱዛ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ ለአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ተሰጥቶ የነበረ ክብር መሰረዙ ጋር በተያየዘ ከሄኖክ ሰማእግዜር ጋር በመተባበር […]

– በኬንያ ሰላም እያለች ራሷን የምታስተዋውቀው ገዳይ ሴት ተልእኮዋን አልተሳካላትም::
– በኬንያ የሚገኙ ስደተኞች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ መረጃውን ያስተላልፉ::
Minilik Salsawi

በኬንያ የሚገኙ ስደተኞችን ለማፈን የሚረዳ የደህንነት ግብረሃይል ወደ ናይሮቢ መጓዙን ከኤምባሲው የደህንነት አታቼ ቅርብ የሆኑ ዲፕሎማቶች ያደረሱኝ መረጃ ይጠቁማል::አዲስ የተላከው ሃይል በናይሮቢ የከተመውን CID ብሎ ራሱን የሚጠራው የወያኔ የስለላ መዋቅር ጋር በመቀናጀት አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ሰዎችን በማፈን ወደ ኢትዮጵያ በሰአታት ውስጥ ለመላክ የሚያስችለውን ስራዎች እንደሚሰራ ታውቋል::
Image
የCID አባላት ታፍነው ይወሰዳሉ የተባሉትን አዋዋል ተከታትለው የጨረሱ ሲሆን እንዲሁም በቡድን የሚገናኙ ኢትዮጵያውያንን የሚገናኙበትን ጊዜ እና አከባቢ ጠብቀው ለማፈን ክትትል ላይ መሆናቸው ታውቋል:: ከኤምባሲው የደህንነት አታቼ ቢሮ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው አዳዲስ ስደተኞች አንድ ላይ ሲሆኑ ለማፈስ ዝግጅት ጨርሰዋል ስልካቸውን እንዲቀይሩ እና ከሚያውኩት ሰው ውጪ ከማንም ጋር ናይሮቢ ውስጥ እንዳይደዋወሉ ሲል እየነጠሉ እንዳይወስዷቸው ሌሎቹ ያመልጡናል ብለው ስላሰቡ ለስራው የሚሆኑ ደህንነቶች ከኢትዮጵያ ገብተዋል ብሏል:: እንዲሁም አፈናው ስደተኞቹን በተዋወቁ አዛኝ መሳይ ቆነጃጅት ቀጠሮ ይፈጸማል የሚል ተጨማሪ መረጃ ተገኝቷል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በናይሮቢ ስደተኞችን እያጠመደች በተመረዘ ምግብ የምትገለው እና ራሷን ሰላ እያለች የምትጠራው ቆንጆ የተሰማራችበት ተልእኮ እንዳልተሳካ ታውቋል::በኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ እንደ ዲፕሎማት የተመዘገበቸው እና ለአምባሳደሩና ለደህንነት አታቼው ቅርብ እንደሆነች የምትታወቀው እንዲሁን ከCID አባላት ጋር በጋራ እንደምትሰራ የተደረሰባት ይህች ግለሰብ ከዚህ ቀደም በሚሊዮን ሹሩቤ ላይ የተጠቀመችውን ቃላቶች ልረዳህ እችላለሁ የፈለከው አደርግልሃለሁ ከማለት ጀምሮ ማግባት እና መውለድ ስለምፈልግ ከእንዳተ አይነት እውቀት ካለው ሰው ጋር …አንተን ለማኖርም ሆነ ለማዝናናት እችላለሁ ና ወደ ቤቴ ልውሰድህ …ወዘተ የሚል የማጃጃያ ዘዴ እና ውድ ግብዣዎችን በማድረግ አንድን ወጣት ለማጥመድ ያደረገችው ሙከራ ሳይሳካላት እንደቀረ የኤምባሲው ምንጮች ጠቁመዋል::ግለሰቧ ቋሚ ስልክ ቁጥር የሌላት ሲሆን በምትፈለግበት ሰአት የማትገኝ ድንገት ደውላ ለግብዣ የምታመቻች ናት::እንዲሁም በደወለችው ቁጥር ተመልሶ ቢደወል ስልኩ ዝግ መሆኑን ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት /መአሕድ/ በ1984 ዓ.ም ተመስርቶ ገዢው ፖርቲ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላና በደቡብ ክልሎች በሚኖሩ በአማራ ብሔረሰብ ላይ እየደረሰ ያለውን የግፍ ጭፍጨፋና የመብት ረገጣ ለመታገል፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችንና የሕግ የበላይነትን እንዲሁም የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታን ዕውን ለማድረግ ሰንቆ በተነሳው አላማ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ እንቅስቃሴ በማድረጉ የፖርቲው መስራችና እውቁ የሕክምና ምሁር ኘሮፌሰር አስራት ወልደየስ […]

አቶ አስራት አብርሃም በእስር ላይ የሚገኘው የአቶ ሃብታሙ አያሌው የስራ ኃላፊነት ተክቶ የአንድነት ፓርቲ ተጠባባቂ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሆኖ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ስለ ፓርቲው ወቅታዊ ሁኔታና የወደፊት አቅጣጫ በተመለከተ ከአቶ አስራት ጋር ተወያይተናል፡፡ ፍቱን፡-በዚህ ወቅት መንግሥት በያዘው አቋም እና ተቃዋሚዎች ባላቸው ደካማ አደረጃጀት እና ምላሽ ምክንያት ፓርቲዎቹ እንኳን የህዝቡን መብት ከጥቃት ሊከላከሉ ለራሣቸው መሆን አቅቷቸዋል፣ […]

ዜጎች ሐሳባቸዉን በነጻነት የመገልጽ መብት፣ ዩኒቨርሳል መብት ነው። በተባበሩት መንግስት የሰብአዊ መብት ድንጋጌ ላይ በግልጽ ተቀምጧል። በአገራችን ሕግ መንግስትም ሐሳብን በነጻነት የመገልጽና ሰላማዊ ሰልፎች የማድረግ መብት ባልተሸራረፈ መልኩ ተጠቅሷል። ህዝባዊ ስብሰባም ሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግ፣ ከአዘጋጆች የሚጠበቀው ሰልፉ ወይም ስብሰባው እንደሚደረግ ማሳወቅ ብቻ ነበር። የሰማያዊ ፓርቲ ሕጉንና ደንቡን በመከተል መደረግ ያለበትን ሁሉ አድርጓል። ሆኖም አገዛዙ […]

በኦሮሞዉና በአማርኛ ተናገሪው መካከል ጥላቻ እንዲሰርጽ ተብሎ አንድ የተጻፈ መርዛማ መጽሐፍ አለ። የቡርቃ ዝምታ የሚባል መጽሃፍ። የዚህ መጽሀፍ ደራሱ አቶ ተስፋዬ ገበረ አብ ይባላሉ። የሕወሃት/ኢሓአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩ ጊዜ የጻፉት መጽሀፍ ነው። በቅርቡ “በሞጋሳ ኦሮሞ ሆኛለሁ” ሲሉ አቶ ተስፋዬ ተናግረዋል። ምን ያህል የሞጋሳ ሚስጠር እንደገባቸው ግን አላውቅም። ከአራት መቶ አመታት በፊት፣ የኦሮሞ ጦረኞች አንድ አካባቢን […]

ዛሬ ህዳር 7/2007 ዓ.ም 9ኙ ፓርቲዎች በትብብር የጠሩት የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ በፖሊስና በደህንነት ኃይሎች ተበትኗል፡፡ ፓርቲዎቹ ለሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ያሳወቁ ሲሆን የፓርቲዎቹ አመራሮች ለፖሊስና ደህንነቶች ቢያሳዩም ‹‹የምናውቀው ነገር የለም፣ እኛ ታዘን ነው፡፡ ከፈለጋችሁ አለቆቻችን ሂዳችሁ አናግሩ፡፡›› በማለት ለስብሰባው የተዘጋጁትን ቁሳቁሶች ስብሰባው ሊደረግበት ከታሰበው ሜዳ እንዲነሱ አድርገዋል፡፡ የፓርቲዎቹ አመራሮችና በስብሰባው ለመሳተፍ ወደቦታው ያቀኑ አካላት […]

በቅርቡ የአንድነት ፓርቲ በመቀሌ ከተማ ጽ/ቤቱን መክፈቱ ተዘግቧል። በተመሳስይ ሁኔታ በኦሮሚያ የምስራቅ ሸዋ ዞን ፣ በአዳማም በአዲስ መልኩ የዞኑ ጽ/ቤት ተከፍቷል። የምስራቅ ሸዋ ዞን በዉስጡ 11 ወረዳዎች ያሉት ሲሆን የዞኑ ወረዳዎችን በሙሉ ለለዉጥ፣ ለአንድነት ለማስቀሳቀስ ሥራ ተጀምሯል። የአዲስ አበባ ፓርቲ ብቻ ሆኖ ለዉጥ ማምጣት አይቻልም። በአገራችን ለዉጥ እንዲመጣ የለዉጥ ባለቤት የሆነውን መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ ማደራጀትና […]

በዛሬው ዕለት ህዳር 7 ቀን 2007 ዓ.ም. በፓርቲው የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ አቶ እንግዳ ወልደጻዲቅ አቅራቢነት በሊበራሊዝም ርዕዮተ ዓለም ላይ እጅግ ደማቅ የሆነ ውይይት ያደረገ ሲሆን በውይይቱ ላይ በርካታ ተሳታፊ ተገኝቶ ውይይቱን ተካፍሏል። በዚህ ውይይት ላይ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ተገኝተው ተጨማሪ ጠቃሚ የሆነ ሀሳቦች አካፍለዋል። ይህ ውይይት በወጣቶች ጉዳይና በህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴዎች የተዘጋጀ ሲሆን […]

የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በህዳር 6/2007 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ የ2007 ምርጫ በተቀናጀ ሁኔታ ለመምራት እንዲቻል 10 አባላት ያሉት በከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች የሚመራ የምርጫ ግብረ ኃይል አቋቁሟል። ይህ የምርጫ ግብረ ኃይል ፓርቲው በ2007 ምርጫ ውጤታማ ሆኖ እንዲወጣ አጠቃላይ የምርጫ ዘመቻውን በበላይነት የሚመራ ሲሆን፤ በተጨማረም በቅርቡ የሚጀመረው የሚሊዮኖች ድምፅ ለፍትሀዊና ነፃ ምርጫ ህዝባዊ ንቅናቄ ዘመቻ […]

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡