አንድነት ፓርቲ በሊበራሊዝም ርዕዮተ ዓለም ላይ ደማቅ ውይይት አካሄደ
በዛሬው ዕለት ህዳር 7 ቀን 2007 ዓ.ም. በፓርቲው የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ አቶ እንግዳ ወልደጻዲቅ አቅራቢነት በሊበራሊዝም ርዕዮተ ዓለም ላይ እጅግ ደማቅ የሆነ ውይይት ያደረገ ሲሆን በውይይቱ ላይ በርካታ ተሳታፊ ተገኝቶ ውይይቱን ተካፍሏል። በዚህ ውይይት ላይ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ተገኝተው ተጨማሪ ጠቃሚ የሆነ ሀሳቦች አካፍለዋል።
ይህ ውይይት በወጣቶች ጉዳይና በህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴዎች የተዘጋጀ ሲሆን በቀጣይነትም በልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተከታታይ የሆኑ የውይይት ፕሮግራሞች ተይዘው ዝግጅት እየተደረገባው ይገኛል።