ሳውዲ አረቢያ ስላሉት ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ ሁኔታ DW Amharic

Ethiopian migrants sleep out in the open near a transit centre where they wait to be repatriated in the western Yemeni town of Haradh, on the border with Saudi Arabia, (REUTERS/Khaled Abdullah) dailystar.com
********************************************************************************************************************
በአብዛኛው የኢህአዴግ ድርጅቶችን ብቻ በማሳተፍ የምዝገባ ዘመቻው ቀጥሏል
ዛሬ መልካም ዜናን ከሪያድ መጠለያዎች ሰማሁ !
* 66 በሚደርሱት መጠለያ የሚገኙት ኢትዮጵያን ይዞታ መሻሻል ጀምሯል
* የምግብ የውሃና የህክምና አገልግሎቱ ሽፋን አበረታች ነው ፣ አቅርቦቱ ሙሉ በሙሉ በሳውዲ መንግስት የሚሸፈን ነው
* ለህጻናትና ለአቅመ ደካማ ሴቶች ትኩረት እየተሰጠ ነው
* የተሻለ መጠለያ ለማስተላለፍ የተደረጉ ሙከራዎች በተጠላዮች ፍርሃቻ ከሽፈዋል
* ተጠላዩ ግን ፍርሃት አለበት ፣ ከመጠለያው ውጭ ያሉ ዜጎች በሚሰጡት ነዋሪው ሊያረጋገው አልቻለም
የጅዳው አስጊ ሁኔታና የቆንስል መስሪያ ቤቱ የሽሜሲ ዘመቻ፡-
* የጅዳ ቆንስል ላልተወሰነ ጊዜ ተዘግቷል
* የመረጃ እጥረት አሁንም አለ
* በጅዳ አንዳንድ አካባቢዎች ህገ ወጥ ወገኖች በመረጃ እጥረት ወደ ሁከት እንዳይሸጋገሩ ያሰጋል
* መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ነዋሪዎች እንዲታገሱ ህጋዊ ነዋሪዎች እየተማጸኑ ነው
* የቆንስላው ሃላፊዎች ትኩረት ወደ ሽሜሲ ጊዜታዊ እስር ቤት ሆኗል
* በአብዛኛው የኢህአዴግ ድርጅቶችን ብቻ በማሳተፍ የምዝገባ ዘመቻው ቀጥሏል
* በቆንስሉ መዘጋት ብዙዎችን አስቆጥቷል " የታመመ ቢሞት እንደጰት እንቅበር? ፖስፖር ቢታደስ ማስተካከል ቢያስፈልግ ምን እናድርግ? የጋብቻ ወረቀት ማረጋገጫና እና ተመሳሳይ ግልጋሎት ስንፈልግ የት እንሂድ? " ሲሉ በማጠየቅ በአስቸኳይ ቆንስሉ እንዲከፈት ነዋሪዎች መንግስትን ተማጽነዋል
* የሰው ሃይል እጥረት አለ፣ ሶስት ኢኒስፔክተሮች ከሃገር ቤት ጅዳ ገብተው ስራቸውን ጀምረዋል
* በጎ እናድርግ የሚሉ ነዋሪዎች ተበራክተዋል ፣ የቆንስሉን መልስ እየጠበቁ ነው