«…………………………….ሴንት ሉስ እያለሁ በጣም የማከብራቸው የኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ Father Baslios
የሚባሉ ቄስ ነበሩ። ከእለታት አንድ ቀን ልጎበኛቸው ከመኖሪያ ቤታቸው ሄድኩ። በተቀመጥቁበት ወንበር ሆኜ በፊቴ ያለውን
ጠረጴዛ ስመለከት በጠረጴዛው ላይ በአረበኛ እና በእንግሊዘኛ ዓረብ አገር ተዘጋጅቶ የተላከላቸውን መጽሄቶች ሳገላብጥ፤
እሳቸው አዩኝና “የራስህ አገር መንግሥት የሚያደርገውን በውስጡ ታገኛለህ” አሉኛ፤ ውስጡን ሳገላብጥ እነ አቶ መለሰ
ያደረጉትን ደባ ተጽፎ አነበብኩ።

ታሪኩ እንደዚህ ነው፤ እነ አቶ መለሰ ከኢትዮጵያ ጋራ በሚዋጉበት ወቅት “በናንተ ሙሉ እርዳታ አሸንፈን ኢትዮጵያን
ከተቆጣጠርን ኢትዮጵያን የዓረብ ሊግ አባል የምትሆንበትን ህግ አውጥተን እናውጃለን” እያሉ ለዓረቡ ዓለም ቃል ገብተው
ኖሮ፤ እንደተመኙት ሆነላቸው እና፤ እንደገቡ ያውጃሉ ብለው እነ አቶ መለሰን ቢጠብቍ ዘገዩ ባቸው። “ለምን ዘገያችሁ ?
ብለው እነ አቶ መለሰን ዓረቦች ጠየቋቸው።

እነ አቶ መለሰ የሰጧቸው መልስ “በአገር አንድነት ህዝቡን አስተሳስራ የኖረችውን ቤተ ክርስቲያን ሳናዳክማት፤ በብሄራዊ
ወኔ ያስተሳሰረችውንም ህዝብ በመከፋፈል ኃይሉን ሳናፈርሰው ልናውጅ ብንሞክር ለህልውናችን አዳጋች ስለሆነ ጊዜ ስጡን፤
ይልቁን በኢትዮጵያ ያሉት ሙስሊሞች ባለፈው መንግስት እየተገደድን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ መቅደስን ህንጻ ሰርተናልና
እኛም ገብተን እንጸልይ እንዲሉ ግፏቸው። እኛም መብታቸው ነው በማለት እስከ በመፍቀድ ድረስ እንገፋለን። በዚህ ሁኔታ ቤተ
ክርስቲያንንም ህዝቡንም ካዳከምን በኋል እናውጃለን እንጅ፤ አሁን ብናውጅ እንዳሰብነው አይሆንም” ብለው መልስ እንደሰጧቸው
ይገልጻል። ዓረቦች ይህን ታግሰው ከመቀበል ይልቅ በጣም ቸኮሉና፤ እነ አቶ መለሰን ለመርዳት ታጥቀው የሚገቡበትን መንገድ
ተሰብስበው ሲነጋገሩ፤ ያካባቢው ሽማግሎች “ነብያችን ሀበሾች እውነተኛ የመሲህ ሰዎች ናቸው እና እንዳትነኳቸው ብለው
አዝዘውናል። ቀን ጥሏቸዋል ብለን ይህን የመሰለ ደባ በአበሾች ላይ መፈጸም ከአላህ ጋራ መጋጨት ነውና አቁሙ” አሏቸው።

እነ አቶ መለሰን ለመርዳት ታጥቀው ለመግባት የፈለጉት ዓረቦች “አሁን በኢትዮጵያ ምድር ያለው አበሻ በነቢዩ ዘመን
እንደነበሩት የመሲህ ሰዎች አይደሉም። ወደ ፈጣሪ አልባ እምነት ተለውጠዋል። ግማሹ በመስቀል ጦርነት ጊዜ ወደወረረን
ክርስትና የተገለበጡ ናቸው ብለው እነ መለሰ ነግረውናል” ብለው እንደመለሱላቸው እና፤ ሽማግሎችም ”ምንም ይሁኑ በሀበሻ
ምድር ላይ ካሉ እንዳትነኩ” ብለው አስቆሟቸው” የሚል በመጽሄቱ ላይ ተመዝግቦ አነበብኩ።

ኢትዮጵያውያን ሆይ! መጀመሪያ “ከረድችሁን እና አሸንፈን ኢትዮጵያን ከተቆጣጠርን ኢትዮጵያን የዓረብ ሊግ አባል
የምትሆንበትን ህግ አውጥተን እናውጃለን”ማለታቸውን፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ “በአገር አንድነት ህዝቡን አስተሳስራ የኖረችውን ቤተ
ክርስቲያን ሳናዳክማት፤ በብሄራዊ ወኔ ያስተሳሰረችውንም ህዝብ በመከፋፈል ኃይሉን ሳናፈርሰው ልናውጅ ብንሞክር ለህልውናችን
አዳጋች ስለሆነ ጊዜ ስጡን ማለታቸውን፤እስከዚያ ግን የኛን እቅድ በማራመድ እንዲረዱን በአገራችን ያሉት ሙስሊሞችን
በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ መቅደስ እኛም ገብተን እንጸልይ እንዲሉ ግፏቸው” ማለታቸውን ስንመለከት፤ የዓረቡን ዓልም ሳይቀር
በማታለል ኢትዮጵያን ለማፍረስ እነ አቶ መለሰ ያለ የሌለ አራዊታዊ ባህርያቸውን በግልጽ እንረዳለን። በበኩሌ ይህ
እየዘገነነኝ ሳለ፤ አሁን በቅርቡ ደግሞ እነ አቶ መለሰ የዘረጉትን ህገ አራዊት ዶክተር አረጋዊ በርሄ፦

*“**የትግራይ* *ህዝብ* *ነጻ* *አውጭ* *ግንባር* *በ**1979 **አመተ* *ምህረት* *አስተሳሰብ* *ለዋጭ*
*የፕሮፓጋንዳ* *መርሀ* *ግብር* *ለሚመለምላቸው* *ቀሳውስት* *ዘረጋ።* *የማሰልጠኑ* *ዓላማ* *ቤተ*
*ክርስቲያኗን* *ከህዝብ* *ለይቶ* *በመምታት* *ስፋቷን* *ማጥበብና* *በትግሬአዊነት* *ላይ* *ብቻ* *የተመሰረተ*
*ስሜት* *በትግራይ* *ተወላጆች* *ጭንቅላት* *መክተት* *ነው።* *ቤተ* *ክርስቲያኗ* *ለረዥም* *ዘመናት*
*በህዝቡ* *አዕምሮ* *ላይ* *ስትተቀርጸው* *የኖረችውን* *ብሄራዊ* *የኢትዮጵያነትን* *ስሜት* *ከትግራይ* *ህዝብ*
*አዕምሮ* *ጠራርጎ* *በጠባቡ* *ትግሬአዊነት* *ስሜት* *በመተካት* *የቤተ* *ክርስቲያኒቱን* *ይዘት* *እያጠበቡ*
*ራሷን* *ቤተ* *ክርስቲያኒቱን* *መምታት* *ነው**”* ብለው የገለጹትን ጽሁፍ አግኝቸ አነበብኩ። ታዲይ የኔ ቢጤ
የቆሎ ተማሪ ጭንቅላት እንደሰረዝ ቅኔ የተደራረበውን የነ ገብረ ኪዳን ደስታን ህገ አራዊት እንዴት እና በምን መንገድ
ሊገልጸው ይችላል?

በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ መነኮሳትና ሰባኪዎች መስለው ሰርገው ገብተው የነገብረ ኪዳንን አራዊታዊ ተልኮ የሚያራምዱትን
በግልጽ እስካየሁ እና የዶ ክተር አረጋዊ በርሄን ጽሁፍ አግኝቼ በማንበብ እስካረጋገጥኩ ድረስ፤ በኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን
ካገኘሁት መጽሄት ያነበብኩት ሰመመን ይሁን ይሁንብኝ እንጅ፤ በጣም አልከከነኝም ነበር።

http://www.goolgule.com/we-shall-arise-again/

ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡ መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡ በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡ በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡ ሁሌም ቢሆን መንግስት ሰበብ ፈልጎ ሊወነጅለንና ከመስመር ሊያስወጣን እንደሚፈልግ በሚገባ እናውቃለንና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ጥንቃቄ እናደርጋለን፡፡ ለሚመለከተው መስሪያ ቤት ባሳወቅን በአስራ ሁለት ሰአታት ውስጥ ምላሽ ስላልመጣ ሙሉ በሙሉ ህጋዊነታችንን አረጋግጠናል ማለት ነው፣ እነሱ ደግሞ ጠብ-መንጃ በእጃቸው አለና የፈለጉትን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡

አቶ ሽመልስ ከማል ለሚዲያወች የሰጡትን ፍጹም ከእውነት የራቀ ውንጀላና ሰበብ አዳምጨዋለው፡፡ “ሰላማዊ ሰልፉን ያገድንበት ምክንያት ጸረ-አረብ መፈክሮች ስለነበሩ ነው” ብለዋል፡፡ መጀመሪያ ደረጃ ሰልፉ ገና ከግቢው ፈቅ ሳይል ነው ያፈኑት፣ ሆኖም የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም አንድ በአንድ እየሆንን ወደ ሰላማዊ ሰልፉ መዳረሻ ለመሄድ ስንሞክር የተወሰኑ አመራሮችን አራት ኪሎ አካባቢ ያዙን፣ እነሱ ቀድሞውኑ ሰልፉ እንዳይካሄድ ስለወሰኑ ነው እንጅ ትንሽ እንኳ ተንቀሳቅሶ የሰልፉን ባህሪ ለመገምገም ምንም እድል አልሰጡንም፡፡

ለምሳሌ ሰልፉን እንደምናደርግ ይፋ ባደረግን ማግስት ከራዲዮ ፋና ተደውሎ አንዳንድ ጥያቄዎች ተጠይቄ ነበር፡፡ በቃለ-መጠይቁ ሰላማዊ ሰልፉ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም እንደምናደርግ ተናግረናል፡፡ ጋዜጠኛው ለሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች መልዕክት ካለ ብሎ በጠየቀኝ ወቅት የሳውዲ አረቢያ ሰንደቅ አላማ ላይ ያለው ምልክትና ጽሁፍ ሀይማኖትን የሚመለከት በመሆኑ ዜጎች በስሜታዊነት ባንዲራ እንዳያቃጥሉ፣ እነሱ ቢያዋርዱንም እኛ ግን ክብር ያለን ዜጎች ስለሆንን ተቃውሟችንን ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ማካሄድ እንዳለብን ተናግሬ ነበር፡፡ ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት በዚህና በተለያየ መንገድ በማያሻማ ሁኔታ መልዕክት ባስተላልፍም እነሱ ግን ይህን በመቁረጥ አላስተላለፉትም፡፡ እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች ሲደመሩ የአቶ ሽመልስ ከማል ንግግር ነጭ ውሸት መሆኑን ያስገነዝባል፡፡

ሁለተኛ የአንድ ሀገር መንግስት ዜጎቹ እየተደፈሩ፣ በማጎሪያ ካምፕ በረሀብና በውሃ ጥም፣ ሌላው ቢቀር መጸዳጃ ቤት እንኳ ተከልክለው ፍጹም ከሰውነት ክብራቸው ወርደው እየተበደሉ፣ እየተገደሉ ባለበት ወቅት ገና ለገና ተቃዋሚ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ በሚንጸባረቅ ጥላቻና ተቃውሞ የዲፕሎማሲ ግንኙነቴ ይበላሽብኛል ብለን መናገር እንችላለን? ሌላው ይቅር አንድ ክፉና ደጉን የለየ ሰው የሚያስበው ጤነኛ ሃሳብ ነው ማለትስ ይቻላል?

ከእገዳው ባሻገር የሚደንቀው ነገር ደግሞ በፓርቲያችን አመራሮችና አባላት ላይ የተደረገው ድብደባ ነው፣ የሆነ ማስተላለፍ የፈለጉት ነገር ያለ ይመስላል፡፡ የጭካኔያቸውን መጠን እንድናውቅ የሚደበድቡት አቅመ-ደካሞችን፣ ሽማግሌዎችንና ሴቶችን እየመረጡ በፍጹም አረመኔነት ነበር፡፡ ይህን ተግባራቸውን ስመለከት የደረሱበትን የዝቅጠት ደረጃ መታዘብ ችያለው፡፡ ከፖለቲካ ልዩነትም፣ ከአምባገነንነትም በላይ ሰዎቹ እንደታመሙ ነው ለመረዳት የቻልኩት፣ስር የሰደደ የቁስ ሰቀቀንና የስልጣን ጥም የተጣባቸው፣ ለዚያ ሲሉም የትኛውንም አይነት ውርደት ለመቀበል የቆረጡና የሞራል ልዕልናቸውን ሙሉ በሙሉ ያጡ ሰዎች ናቸው፡፡ ስነ-ልቦናቸው ክፉኛ ተቃውሷል እንጂ ሀገር እመራለው የሚል ቡድን እንዲህ ያለ ተግባር ይፈጽማል ለማለት እቸገራለው፡፡ በአባላቶቻችን ላይ ክፍኛ ድብደባ ተፈጽሟል፣ እስከዛሬም እግሮቻቸው መራመድ የማያስችላቸው፣ የሚያነክሱ ሰዎች አሉ፡፡ እውነት ለመናገር ይሄ እብደት ነው፡፡ አንዲት እራሷን መከላከል የማትችል ሴትን ለሶስት መደብደብን ከዚህ በተሻለ ልገልጸው አልችልም፡፡

አንድ ማስገንዘብ የምፈልገው ነገር ለኛ ዋናው ጉዳይ የዜጎቹ ህጋዊነት ወይም ህጋዊ ያለመሆን ጉዳይ አይደለም፡፡ በምንም አይነት መንገድ ሴቶች እየተደፈሩ፣ ወንዶች በየስርቻው እንደ ውሻ ተቀጥቅጠው እየተገደሉ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ታጉረው ይህን ሁሉ መከራ መቀበላቸውን ልንታገሰው፣ ወይም ከህጋዊነት አንጻር እየተራቀቅን ልንመለከተው አንችልም፣ ስለ ህግም ከተወራ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ጭፍጨፋው ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ባላቸው ላይ ጭምር ሲፈጸም እንደነበር አምኗል፡፡

ባለንበት የግሎባላይዜሽን ዘመን የአንዱ ሀገር ዜጋ ካለ ሀገሩ መገኘት አገር ይያዝ የሚያስብል አይደለም፡፡ መውጣት ካለባቸው ጊዜ በመስጠት፣ ከመንግስታቸው ጋር በመነጋገር በዘዴ ነገሩን መከዎን እየተቻለ አንድ ሀገርና መንግስት በሰዎች ላይ እንዲህ የጭካኔ ጥግ የሆነን አቋም ይዘው መንቀሳቀሳቸው ፍጹም ኢ-ሰብአዊነት ነው፡፡
ለኢትዮጵያውያን እንዲህ ያለ አስከፊ ጊዜ የለም፣ እውነቱን ለመናገር ለአገዛዙ ሰዎች የነበረኝ ጭላንጭል ተስፋም አፈር ተደፍቶባታል፣ እንዲህ ግልጽ የሆነ ጭፍጨፋ እየደረሰብን እንኳ በድፍረት ለመናገር አልፈለጉም፡፡ ስለ ኢትዮጵያውያን መገደል ለማውራት ሲፈልጉ ሌላ ሀገር ይጠቅሱና እነሱም እኮ እየተገደሉ ነው ይላሉ፣ ወገን ከምንለው የማህበረሰባችን አካል ይሄን መስማቱ ከጥቃቱ ይበልጥ ያማል፡፡

ለምሳሌ ኢቲቪ ስለ ጉዳዩ ሲያወራ ህገ ወጥ ሊባል የሚችል ድርጊት ተፈጽሟል በማለት ነው፡፡ ተመልከቱ! እንዴት ያለ ባዕድነት ነው? ኢትዮጵያውያን በድህነትም ውስጥ እንኳ ለክብራችን የመሞት ባህሪ አለን፣ ይሄ ከቀደሙት አንጡራ ኢትዮጵያውያን የወረስነውና ዛሬም ያለን ሀብታችን ነው፡፡

ትናንት ፍየል ጠባቂ የነበረ በረኸኛ ይህን ክብራችንን ገፍፎ እንደውሻ ቀጥቅጦ ስርቻ ሲጥለን ያልተቆጣ መንግስት ኢትዮጵያዊ ነው? ከዜጎቹ የወጣና ለህዝቡ የቆመ እውነተኛ መንግስት ከዚህ የበለጠ የሚቆጣበት ጉዳይ ከወዴት ይመጣል? እውነተኛ መንግስት ቢሆን ኖሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሳውዲ ካምፓኒዎችን በሰአታት ውስጥ ማባረር፣ ኤምባሲውን ዘግቶ አምባሳደሩን ማሰናበትን የመሳሰሉ ውሳኔዎችን ያሳልፉ ነበር፡፡ የሆነው ግን በተቃራኒው ነው፣ የዲፕሎማሲ ግንኙነቴ ሊበላሽ ይችላል ብሎ እኛ ድምጻችን እንዳናሰማ ደበደበን፣ አፈነን፡፡ በግልጽ እንደሚታየው የጥቅም ትስስሩ ነው አፋቸውን ያዘጋቸው፣ ይህች ጥቅማቸው እንዳትቋረጥ በዜጎች ህይዎት መደራደርን መርጠዋል፡፡

ስነ ልቦናቸው የተቃወሰ በመሆኑና ተራ ስስታሞች በመሆናቸው እንጂ ኢንቨስትመንትም ሆነ ዲፕሎማሲ ግብአትነታቸው ለሰው ልጅ ነው፣ እንደ አህያ ሲያፈጋ ከርሞ ሬሳቸውን ለላከ መንግስት እንዴት ተመጣጣኝ ምላሽ ለመመለስ ይገዳል?እንዴት እንደ ኢትዮጵያ ያለች ታሪካዊትና ለአፍሪካ የነጻነትና የኩራት ተምሳሌት የሆነች ሀገርን እየመሩ እንዴት ትናንት የነዳጅ ዘይት ባቆማቸው እረኞች ስትዋረድ ዝም ይላሉ?!::

እንዴት!

በዜጎች ህይወት የተደራደረው አገዛዝ ማለፉ አይቀርም፣ ለዚህ ጥርጥር የለኝም፡፡ ታሪክ ለመጥቀስ ብዙ ርቀት መሄድ አያስፈልግኝም፡፡ የቅርብ የሰሜን አፍሪካ አምባገነኖች የከፋ ፍጻሜ አለና፡፡ ኢትዮጵያውያን ፍቅርም ጸብም እናውቃለን፣ ሳውዲዎችም የፈጸሙትን ግፍ ማወራረዳቸው አይቀርም፡፡ በዚህ ክፉ ጊዜ ስለሰብአዊ መብት ቆመናል የሚሉ አለም አቀፍ ተቋማት ዝምታን መምረጣቸው እውነተኝነታቸውን ለመመርመር ጥሩ እድል ይሰጠናል፡፡

መንግስት ቢኖረን ኖሮ ይሄ ሁሉ ውርደት ይፈጸምብን ነበር ብየ አላስብም፡፡ በዚህ ሰአት ርዕሰ-መንግስት ብሆን ኖሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ድርጅት እንደመሆኑ፣ ወደየትኛውም ሀገር የሚደረገውን ጉዞ አቋርጨ ዜጎቸን ማስወጣትን አስቀድም ነበር፡፡ ያሄ ጥቂት ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ሊያመጣብን ቢችልም ከከፋው የዜጎች ስቃይ ጋር ግን በአንድ ሚዛን ላይ አይቀመጥም፡፡ የአደጋ መከላከያና ዝግጁነት ኮሚሽን የሚባል ድርጅት አለ፡፡ በዜጎቻችን ላይ ጎርፍና ድርቅ ሲመጣ ብቻ ነው የሚንቀሳቀሰው? ይሄም ሰው ሰራሽ አደጋ ነው ሙሉ ሀይሉን ወደዚህ አዙሮ ሊንቀሳቀስ ይገባው ነበር፡፡

እርግጥ ነው ባቀድነው መሰረት ሰላማዊ ሰልፉ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዳይሆን አድርገውታል፡፡ ጩኸቱ ግን ይቀጥላል… ባለን አቅም ሁሉ አፈናውንም፣ ወከባውንም ተቋቁመን ለዜጎቻችንና ለኢትዮጵያዊነት እንታገላለን፡፡ አገዛዙ ይሄን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያፍን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንድ መልእክት አስተላልፏል፣ ይህን መልእክት እንዲያስትላልፍ ማስገደዳችንም ለኛ ትልቅ ስኬት ነው፡፡ የሳውዲ መንግስት ያሻውን ያደርግ ዘንድ የፈቀድኩት እኔ ነኝ፣ በመሆኑም እሱን በመቃወም ግንኙነቴን አታበላሹ ብሎ እርምጃ በመውሰዱ ህዝቡ የነገሩ ቁልፍ የት እንዳለ፣ የአጥቂወቹ በራስ መተማመን ምን ላይ እንደቆመ በጠራ ሁኔታ ለመመልከት እንዲችል ሆኗል፡፡

ይሄ ሁሉ ነገር እየተፈጸመ የተስተዋለ አንድ ነገር አለ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝምታ እውነተኛ ማንነታቸው፣ እውነተኛ በአገዛዙ ውስጥ ያላቸውን ቦታ ያሳየን ክስተት ነው፡፡ እንደሚታወቀው እሳቸው በኢህአዲግ እንጂ በኢትዮጵያ ህዝብ የተመረጡ አይደሉም፡፡ ኢህአዲግ የሚናገረው ከሌለ እርሳቸው የሚሉት አይኖርም፡፡ እንደ አንድ ሀገርና ህዝብ መሪ ግን የመኮነንም ሆነ የማጽናናት ቃል ይጠበቅባቸው ነበር፡፡

ባሉበት ቦታ ያስቀመጣቸው ህወሀት ነው፤ ድርጅቱ ደግሞ ይሄን አቋም አልወሰደም፡፡ ስለዚህ እንደሚቆጣቸው ስለሚያውቁ ዝምታን መረጡ፣ ቸልታንም አስበለጡ፡፡ በሀገርም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ከዚህ በላይ ሽንፈት ያለ አይመስለኝም፡፡

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር

(ይህ ጽሁፍ በፋክት መጽሄት ተስተናግዷል፣ ነገር ግን መጽሄቱ ላልደረሳቸው ሰዎች ይደርስ ዘንድ እዚህ ለማስተናገድ ወደድኩ፡፡)

Abraha Desta
November 19
“ከህወሓት የባስክ ትሆናለህ” አሉኝ
———————————–

“ጨቋኝ ስርዓት አልፈልግም” ብዬ በፃፍኩት ላይ አንድ የፌስቡክ ወዳጄ “አንተ ራስህ ስልጣን ብትይዝ ከህወሓት የባስክ አምባገነን ትሆናለህ” አለኝ።

እኔም እላለሁ፣

ከህወሓት የተሻልኩ እንደምሆን እርግጠኛ አይደለሁም (ራሴ ለግዜው እንደ ፓርቲ ልቁጠር)። ስለ አንድ ነገር ግን እርግጠኛ ነኝ። እኔ ሰለማዊ ታጋይ ነኝ። ስልጣን የምይዘው በህዝባዊ ምርጫ እንጂ በጠመንጃ አይደለም። የምወዳደረው በሐሳብ እንጂ በሃይል አይደለም።

ስለዚህ ስልጣን ስይዝ የራሴ ወታደር፣ ፖሊስ፣ ዳኛ ወዘተ ይዤ አልመጣም። ስልጣን የምይዘው በሕገመንግስት መሰረት እስከሆነ ድረስ በኔና በወታደሮቹ ያለ ግንኙት ሕገመንግስታዊ ይሆናል። ስለዚህ ወታደሮቹ እንደፈለኩ የግሌ የስልጣን ጥም ለማርካት አላዝዛቸውም። ዳኞችም ነፃ ይሆናሉ።

ስለዚህ እኔ ስልጣን ከያዝኩ በኃላ ከህወሓት ካልተሻልኩ በህዝብ ምርጫ እንደወጣሁ ሁሉ በሚቀጥለው በህዝብ ምርጫ ከስልጣን እወርዳለሁ። ከስልጣን ላለመውረድ ምንም ዓቅም የለኝም፤ ምክንያቱም በምርጫ ስልጣን የያዘ አካል የግሉ ወታደርና ፖሊስ የለውም። የስልጣን መሰረቴ የህዝብ ድምፅ ከሆነ በስልጣን ለመቆየት ስል ህዝብን አልጨቁንም። ከጨቆንኩ ደግሞ ህዝቡ ያወርደኛል።

የኢህአዴግ መንግስት ሰለማዊ ትግልን አጨልሞብኝ በትጥቅ ትግል ስልጣን ከያዝኩ ግን አምባገነን የመሆን ዕድል አለኝ። ምክንያቱም የስልጣን ምንጬ ጠመንጃ እንጂ ህዝብ አይደለም። ለህዝብ ታማኝና አገልጋይ የምሆንበት ዕድል ይጠባል። ስለዚህ በምርጫ ስልጣን የያዘ መንግስት ቢያበላሽ እንኳ በምርጫ ይወርዳል። አሁን የቸገረን በጠመንጃ የመጣ መንግስት ነው።

ዓላማችን ስልጣን መያዝ ብቻ ሳይሆን ስልጣን በጠመንጃ ከመያዝ በምርጫ የምያዝበት ስርዓት መገንባት ጭምር ነው።

(ስልጣን የመያዝ ዕቅድም ፍላጎትም የለኝም። የኔ ፍላጎት በነፃነት የፈለኩትን ማድረግ ነው። እኔ የሌሎችን መብት ሳልዳፈር የፈለኩትን የማድረግ ነፃነት እንዲኖረኝ የህዝብ መንግስት ወይ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት አለበት። ስልጣን መያዝ ነፃነትን ይገድባል)።

It is so!!!

“የኢትዮ-ኤርትራ ችግር መፍትሄ፣ ድንበር ማስመር ሳይሆን ድንበር ማፍረስ ነው”
——————————–

ኤርትራዊው ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ እንዲህ ተጠየቀ;

አዲስ አድማስ ጋዜጣ : የኤርትራ ህዝብ አሁን ያሉበትን የነፃነት ሁኔታ ከቀድሞው ጋር ሲያስተያዩት ምን ትርጉም ይሰጥዎታል?

ተከስተ ነጋሽ: እኔ እኮ በመጀመሪያም ኤርትራውያኖች ከማን ነው የሚገነጠሉት የሚል አቋም ነው ያለኝ። ማነው ከማን የሚገነጠለው? የደቡብ ወይም የኦሮሞ ህዝቦች እንገነጠላለን ቢሉ ኖሮ ምክንያት ነበራቸው፡፡ የኤርትራ የነፃነት ጥያቄ በተነሳበት ወቅት ኤርትራውያኑና ከላይ የጠቀስኳቸው ህዝቦች በኢትዮጵያ ውስጥ ያገኙትን እድል (Comparative advantage) ስናይ፣ ኤርትራውያኑ በጣም ተጠቃሚ ነበሩ፡፡ (በጣሊያን፣ በእንግሊዝ፣ በፌዴሬሽኑ ዘመን) በ1960ዎቹ የአዲስ አበባ ሀብታሞቹ እነሱ ነበሩ። በትምህርት መስክ ሃያ አምስት በመቶ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተማሪዎች ኤርትራውያን ነበሩ። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችንም ካየሽ 25 በመቶ የሚሆኑት ኤርትራውያን ነበሩ፡፡ ከተማረው ሰላሳ አምስት በመቶው ክፍል ኤርትራውያን ነበሩ፡፡