ምነው ሰቆቃችን በዛ?

ምነው ሰቆቃችን በዛ?
ሐገር እንደሌለው በዋዛ።
ለውጡ ሆኖብን ከድጡ ወደማጡ
ስንቶች ሐገራቸውን ጥለው ወጡ?
ብልሹ አገዛዝ ነግሶብን
ኢትዮጵያዊያን ተዋረድን።
ያዋረድን ግን ወያኔ ነው
ዓይን እያለሁ የማያየው
ጆሮ እያለው የማይሰማው።
ሴቶቻችን ሲደፈሩ ክብራችን ሲንኮታኮት
ኢቲቪ የወያኔ የውሸት ቋት።
አንቺ ያልታደልሽ ሐገር
አኬልዳማ የደም ምድር።
አምላክ ሆይ እንባችንን አብስና
ገላግለን ከዚህ ዘመን ፍጠንና
ሐገር እያለን እንደሌለን
በጣም እናሣዝናለን።
በርጉማን እየተመራን እስከመቼ
በሣውዲ እያለቁ ወገኖቼ
ዱሮ ግንደበረት የቀረው
ሣውዲ ላይ ባርነታችን የነገሠው
በወያኔ የተነሣ ነው።
ለአፍሪካ የምትተርፍ ሐገር
እንዲህ ሆና ስትቀር?
ጌታ ሆይ ገላግለን ከእዬዬ
መሪ ስጠንና እንደ እምዬ።
*በሣውዲ መከራ ላይ ለወደቁ ወገኖቼ መታሠቢያ
18/11/2013
penethiopian