የገና ፆምን ለመፆም ተዘጋጅተዎል??
የፊታችን ዕሁድ ፆመ ነቢያት ይጀመራል።የገና ፆምን ለመፆም ተዘጋጅተዎል?ዘንድሮ ፆም ለነፍስ ብቻ ሣይሆን ለስጋም ጠቃሚ እየሆነ ነውና ሀኪም ቀይ አብርቶ በስጋ ምክንያት ሥጋት ላይ መሆንዎን ሣያረዳዎ በንስሃ አባትዎ ምክር ፆሚ ይሁኑ።
ቢፆሙ ሸንቃጣ ይሆናሉ።ስጋዎ ፈተና ላይ አይወድቅም።መንፈስዎ ይረጋጋል።ባይፆሙ ኪሎዎ ይጨምራል።ከሀኪም ፊት አይርቁም።ቁና ቁና ይተነፍሣሉ።ወጪዎ ይጨምራል።አልጋና ብልግና ሊያዘወትሩ ይችላሉ።
ኪስዎ ከመጀመርያው ፆሚ ከሆነ የኔ ምክር እርስዎን አይመለከትምና ዘና ይበሉ።ፆም ሲፆሙ ሆድዎን ብቻ ማዕቀብ አይጣሉበት። ምላስዎን አደብ አስገዟት።ዓይንዎን ከዳሌና ጭን ላይ ይንቀሉ።ጆሮዎ የአመት ረፍት ያስወጡት።እግርዎ አይንጦልጦል።ያኔ የወጣልዎ ምርጥ ፆሚ ይሆናሉ።አንድ ነገር ረሣሁ።በልብዎ ግርግዳ ያከማቹትን የቂምና የጥላቻ ዶሴ ፈጥነው ይደልዙ።ልብዎ በቂም ኔትወርክ ተጨናንቆ ወደ ፈጣሪዎ የሚያደርጉት ማንኛውም ጥሪ አይሠማምና ውዝፍ ሂሣብዎን ያወራርዱ።ያኔ የገናን ፆም ለመፆም ሚኒማውን ያሟላሉ።
ዕሁድ ጧት ቸርች ሲመጡ ልብስዎ ብቻ ሣይሆን ልብዎም ፀዳ ብሎ ይምጣ።እኔ እንዲህ ብያለሁ ።እርስዎስ??
አክሊለ ሠማያት ዘ መካነ ሠላም