ዩጋንዳ ያለው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በሕይወት አለ?
ዩጋንዳ ያለው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በሕይወት አለ?
ይህን ጥያቄ ለመመለስ ካምፓላን ማዳረስ ኣያስፈልግም።የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የሚሊኒየሙ አከባበር ግዜ ነበረ። ከዛ ተሽመደመደ።ጁላይ ኢለቨን ካምፖላ በአልሻባብ አጥፍቶ ጠፊዎች አሰቃቂ ፍንዳታ በደረሠ ግዜ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አለሁ ብሎ ሲሯሯጥ ታየ።ከዛ በኋላ ነበር ኖቬምበር አስራአራት ቀን ሁለት ሺ አስር የኢትዮጵያ ኮሚኒቲን
ኖቬምበር አስራአራት ከሚሊኒየሙ በፊትና በኋላ ኮሚኒቲው ያከናወናቸውን ተግባራት የሚያትት ዝርዝር የስራና የሂሣብ ሪፖርት ቀርቦ የነበረው።ለአንድ ዓመት ያህልም በወገኖች ድጋፍ ቢሮ እስከመክፈትና የአባልነት መታወቅያም ለማህበረሠቡ አዳርሶ ነበር።ኮሚኒቲው በወቅቱ ያሣየው ፍጥነት የወያኔን ወኪሎች አስግቶአቸው ይሁን ወይም በሌላ ምክንት ቢሮውም ተዘጋ ፣አመራሩም ላይገናኙ የተማማሉ መሠለ።ከወያኔ ቆንስላ ሃላፊዎች ጋርም ምስጢራዊ ስብሰባ የተወሰኑ የኮሚኒቲው አመራሮች አደረጉ የሚል ወሬ ተሠማ።ያኔ ኮሚኒቲው ተሸረሸረ።
ዩጋንዳ ያለው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ መተዳደርያ ደንቡ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ አባል መሆን እንደሚችል ስለሚገልፅ የወያኔ ቆንስላ ሠራተኞች ካሣደዱዋቸው የፖለቲካ ስደተኞች ጋር የአንድ ኮሚኒቲ አባል ለመሆን ሲመዘገቡ ታይተዋል።በየትኛውም ስፍራ የፅዋ ማህበርም ቢሆን ወያኔዋቹ በይፉም ሆነ በህቡህ ያን ማህበር ካልተቀላቀሉ፣
አልያም ካላፈረሱና ወይም በነሡ ሣንባ የሚተነፍስ ተለጣፊ ካልመሠረቱ ሞታቸው ነው።
የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በዩጋንዳ ዛሬ ስሙ ከመኖሩ ባሻገር ተሽመድምዶ ያለው ፖሊዮ ይዞት አይደለም።የኮሚኒቲው አመራሮች የያዙትን ቦታ ለመልቀቅ ፈቃደኝነት ያላቸውም አይመስልም።የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ከሚሊኒየሙ በፊትም ሆነ በኋላ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የሚያደርጋቸውን ተግባራት በቅርበት ያውቃል።እንደዜጋም አቅሙ የፈቀደውን በማድረግ በወያኔ ቆንስላ ጥቁር መዝገብ በጠላትነት ተፈርጆ እንደሚገኝ የካምፓላ ሰማይ የሚያውቀው ዕውነታ ነው።
ወያኔ የሚሊኒየሙን በዓል በሱ ፊታውራሪነት ካምፓላ ላይ ለማክበር ሲሯሯጥ በወቅቱ ወያኔ ንፁሀንን እስር ቤት አጉሮ በዓሉን በጋራ እንድናከብር ሊያግባባና ሊያስፈራራ ሲሞክር የታሠሩት ይፈቱ፣ብሔራዊ ዕርቅ ይደረግ ብለን የተወሰንን ወገኖች በመናገራችንና ሚሊኒየሙን ያለወያኔ ተሣትፎ በደመቀ ሁኔታ በማሣለፋችን ነበረ የወያኔ ጥርስ ውስጥ የገባነው።
ባለፉት ሦሥት አመታት የወያኔ ቆንስላ ዩጋንዳ ካምፖላ ላይ እውነተኛ የፖለቲካ ስደተኞችንን በማሳደድ፣በማሠለልና መፈናፈኛ በማሳጣት ሕብረተሠቡን በዘር እስከማደራጀት ሠርቷል።
ኮሚኒቲውን አሽመድምዷል።ከአመራሩ የተወሠኑትን ፖስፖርት በመስጠት ከስደተኛነት አላቋል።የወያኔ ቆንስላ ቤተኛ የሆኑም እንዳሉ የአደባባይ ሚስጥር ነው።
በርካታ ወገኖች ኮሚኒቲው ባይቀበርም እንደሞተ ያምናሉ።እንደገና ለማጠናከርም ቢሞከር አሁን ካሉት የአመራር አባላት መካከል ከወያኔ ጋር በግልፅም ይሁን ውስጥ ለውስጥ የሚሞዳሞዱትን ለይቶ ለማውጣት አስቸጋሪ መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ።
ከሁለት ዓመት በፊት በሕጋዊው ሲኖዶስ የሚመራውን የካምፖላ መካነ ሠላም መድሐንያለም ቤተክርስትያን የወያኔ ቆንስላ ካህናትና፣ ዲያቆናት እንዲሁም መዘምራንን በስውር አደራጅቶ ያካሄደው ትርምስ በእውነተኛ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ከከሸፈና የአመፁ መሪ የነበሩት የቀድሞ አስተዳዳሪ የስደተኛ እስታተሳቸውን ወርውረው በወያኔ ፖስፖርት የአምስት ኪሎውን ቤተክህነት ከተቀላቀሉ ወዲህ ነገሮች እየጠሩ መጥተዎል።
ካምፖላ ላይ የፖለቲካ ስደተኛ መታወቅያ በደረታቸው ፣የወያኔ አክቲቭ ፓስፖርት ትራሳቸው ስር ሸጉጠው ትክክለኛ ስደተኞችን የሚሠልሉና ለአደጋ የሚያጋልጡትን ሆድ አደሮች ለማጋለጥ በዩጋንዳ የሚኖሩ ስደተኞች ለህልውናቸው ሲሉ በህብረት ሊቆሙ ይገባል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጥቂት የፖለቲካ ስደተኞች ስደተኛውን ብቻ ያቀፈ የስደተኞች ማህበር ለመመስረት እንቅስቃሴ እየተከናወነ ሲሆን ለስደተኛው መብት መከበር የሚሠራ ከማናቸውም የፖለቲካ ሃይሎች ተፅዕኖ ነፃ የሆነ ማህበር ለመመስረት የበኩሌን እገዛ ሳደርግ ብቆይም ለደህንነቴ ስጋት የሚፈጥሩ ሁኔታዎች በመፈጠራቸው ከማናቸውም ማህበረሠቡን ከሚመለከቱ ጉዳዮችራሴን አግልዬ እንደምገኝ ለመጠቆም እወዳለሁ።በተቻለ አቅም ስደተኛው የራሱን ማህበር ከወያኔ ሠርጎ ገቦች እንዲጠብቅ አሳስባለሁ።
የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ እስከዛሬ የታመሙትን ወገን በማስተባበር ለማሣከም ያደረገው መልካም ተግባር ፣
የሟች ወገኖችን አስከሬን ከቤተሠብ ጋር መክሮ ለሐገራቸው አፈር እንዲበቁ በመስራቱ፣ምስኪን ስደተኞች ሲሞቱ በመቅበር የሠራውን ስራ በመዘከር ወደ ወያኔ ጉያ የተሸጎጠውና ፖራላይዝዱ ኮሚኒቲ እኔም ልክ የዛሬ ሦሥት አመት በተከናወነው የማሟያ ምርጫ የቦርድ አባል ሆኜ እስከዛሬ መቆየቴን እየጠቆምኩ በመላ ዓለም የምትገኙ ኮሚኒቲዎች ልምዳችሁን እንድታካፍሉኝ እንደ አንድ ዩጋንዳ ላይ በሚኖር ሐገር አልባ ስደተኛ በአክብሮት እጠይቃለሁ።
ተጨማሪ መረጃ ለሚፈልጉ ሁሉ ፀሀፊው በንፁህ ህሊና እውነቱን ብቻ ለመግለፅ ህሊናው ዝግጁ መሆኑን ይጠቁማል።
ጋዜጠኛ ደረጀ በጋሻው
ከኮሚኒቲው ቦርድ አባላት አንዱ