የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ)ከባድ አደጋ ውስጥ ነው:: ሲሉ አባላቱ ገለጹ

– "መኢአድን ለማዳን እንረባረብ::" የጠቅላላ ጉባዬ አባላቱ
– ከድርጅቱ የተባረሩ የወያኔ ቅጥረኞች በእርቅ ስም ወደ ድርጅቱ ተመልሰዋል::(አባላት)
– ጠቅላላ ጉባዬው የተካሄደው ፍጹም አምባገነንነት በሞላበት ሁኔታ ነው::

Minilik Salsawi

በኢትዮጵያ በአንጋፈነቱ የሚታወቀው እና በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የተመሰረተው መአሕድን የተካው በኢንጂነር ሃይሉ ሻውል ሲመራ ቆይቶ አቶ አበባው መሃሪ የተረከቡት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ (መኢአድ)ከባድ የመፈረካከስ አደጋ ከፊቱ ተደቅኗል ሲሉ የድርጅቱ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ በላኩት መረጃ ገልጸዋል::

መኢአድ ከአንድነት ፓርቲ ጋር የሚያደርገውን ውህደት ተከትሎ ገዢው ፓርቲ ከድርጅቱ የተባረሩትን እነ አቶ ማሙሸት እና ኮሎኔል ታምሩን አደራጅቶ ውህደቱን በመበጥበጥ በመኢአድ ቢሮ ውስጥ ከዚህ ቀደም በተደረገ ስብሰባ ላይ ደህንነቶችን እና ፖሊሶችን አስከትሎ በመምጣት ከፍተኛ የሆነ ብጥብጥ አንስተው የነበረ ቢሆንም ሳይሳካላቸው ቀርቷል::

ውህደቱ የጉሮሮ ላይ አጥንት የሆነበት የወያኔው መንግስት ምርጫ ቦርድን ተገን በማድረግ መኢአድን በማጉላላት ውህደቱ እንዳይፈጸም ከፍተኛ ደባ ከቅጥረኞቹ ከነማሙሸት ጋር በመሆን ሲፈጽም ቆይቶ በስተመጨረሻ ኢንጂነር ሃይሉን በማስገደድ የተባረሩ አባላትን አቶ አበባው መልሶ እንዲያስገባ ካላስገባ ስልጣኑን እንዲለቅ በሚል ጫና የበላይ ጠባቂነታቸውን ተገን በማድረግ የወያኔ ስራ አስፈጻሚዎች ወደ ድርጅቱ ሰርገው በመግባት ድርጅቱ አደጋ ውስጥ መሆኑን የድርጅቱ አባላት በምሬት ተናግረዋል::

ኢንጂነር ሃይሉ ሻውል ከዚህ ቀደም ከወያኔ ጋር ከድርጅቱ እውቅና ውጪ በራሳቸው ፍቃድ ከሟቹ መለስ ዜናዊ ጋር የምርጫ ደንብ የሚል ስምምነት ተፈራርመው ድርጅቱ እንዲዳከም እና ለወያኔዎች በሩን እንዲከፍት ያደረጉ ሰው ቢሆንም ቀደም ብለው ለትግሉ የከፈሉት አስታውጾ ታይቶ የድርጅቱ የበላይ ጠባቂ እና አማካሪ ቢደረጉም በድርጅቱ ማህተም የተባረሩ ቅጥረኞች ወደ ድርጅቱ እንዲመለሱ አድርገዋል ሲሉ አባሎቹ ተናግረዋል::ኢ/ር ሀይሉ ሻውል በፍጹም አምባገነንነት ጉባኤተኛውን አፍነው እርሳቸው በሚፈልጉት መልኩ በእርቅ ጭምብል አንዱን አስወጥተው አንዱን አስገቡ፡፡ ሲሉ የጠቅላላ ጉባዬ አባላቱ ተናግረዋል::

ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዘዉን መኢአድን የተመለከተ የአቶ ሸንቁጥ አየለን ጽሁፍ ያንብቡት ::
viewtopic.php?f=2&t=89291