በመተማ ጭልጋ እና አርማጭሆ የህዝብ አመጽ በርትቷል::ተጨማሪ ወታደሮችን የጫኑ ኦራሎች ወደ አከባቢው እያመሩ ነው::
በመተማ ገንዳ ውሃ በአርማጮህ እንዲሁም በጭልጋ ከህዝብ አመጽን ተከትሎ ከፍተኛ ተኩስ እየተሰማ መሆኑን የአከባቢው ምንጮች ጠቁመዋል::በተልይ በመተማ ገንዳ ውሃ ከፍተኛ ውጥረት ላይ ስትሆን ኦራሎች ወታደሮችን በማመላለስ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል ሲሉ በአከባቢእ የሚገኙ የአማራ ንቅናቄ አባላት ተናግረዋል::የህዝቡ አመጽ ከፖሊሶች እና የአከባቢው ሚሊሻ በላይ በመሆኑ ተጨማሪ ወታደሮችን የጫኑ ኦራሎች ወደየከተሞቹ እያመሩ መሆኑን ታውቋል::የነጻነት ሃይሎች ነን የሚሉ ይህንን የህዝብ እንቅስቃሴ በመጠቀም ትግሉን ማስፋፋት እንደሚችሉ ተጠቁሟል::
ከባለፈው ወራት ጀምሮ መተማ ከተማ ሳሉግ በመባል የሚታወቁት የበረሃ ሰራተኞች መካከል በተነሳው አለመግባባት የሰው ህይወት መጥፋቱን ተከትሎ ግጭቱ በመባባሱ እስካሁን ከ10 በላይ ሰወች መገደላችውና በርካቶችም መቁሰላቸው የታወቀ ሲሆን፣ ችግሩን በማባባስም የወያኔ እጅ እንዳለበት ተረጋግጧል። ይህን የመሰለ ግጭት ከዚህ ቀደምም በተለይ በጎንደር፣ጎጃምና ወሎ ተወላጆች መካከል የሚደጋገም ሲሆን ወያኔ ነገሩን ሲያባብስ ቆይቶ ለአሁኑ ከባድ አደጋ አድርሶታል።
በአሁኑ ጊዜ ግጭቱ ሰፋ ባለ መልኩ እየቀጠለ ያለ እና በተለይም በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳወች መዛመቱና ከጎንደር የሚያገናኙ መንገዶችም መዛጋታቸው ታውቁኣል። ጉዳዩ የሚመለከታችሁ አካላትም ሂደቱን በቅርብ እንድትከታተሉና ወጣቶቹ የእርስበርስ መጠፋፋቱን አቁመው ወያኔን ለማስወገድ በሚደረገው ትግል ተሰላፊ እንዲሆኑ ለሚደረገው ጥረት መስራት ያስፈልጋል።
ከሳምንታት በፊት በኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ታጣቂዎች እና በፌዴራል ፖሊስ መካከል በተነሳ ግጭት አራት የፌዴራል ፖሊሶች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ ተከስቶ የነበረው ግጭት ከፖለቲአክ አጀንዳና ከህዝባዊ ጥያቄ ውጪ የነበረ መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል::