ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የተሰጠ መግለጫ

የኢህአዴግ አምባገነናዊ ሥርዓት በሕዝቦቻችን ሕይወት፣ መብትና ክብር ላይ እያደረሰ ያለው ወንጀል በመልካም አስተዳደር እጦት ላይ ብቻ ተሳብቦና ተድበስብሶ ሊታለፍ አይችልም!!
(ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የተሰጠ መግለጫ)
በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ከዳር እስከ ዳር እየተስፋፉ ያሉት የሕዝብ ምሬቶችና ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች መንስኤ ፀረ ዴሞክራሲው የኢህአዴግ አምባገነናዊ አገዛዝ የፈጠረው ብልሹ አስተዳደር መሆኑን ምልአተ-ሕዝቡ ከመራር የሕይወት ልምዱ እና ተሞክሮዎቹ የተገነዘበው ጉዳይ ነው፡፡ የሕዝቡን ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ከፋሽስታዊ ጭካኔ ባልተናነሰ ሁኔታ የመጨፍለቅ እርምጃ እየወሰደ ያለው የኢህአዴግ መንግሥት፣ የሀገራችንን ችግሮች በመልካም አስተዳደር እጦት ላይ ብቻ በማሳበብ የሽንገላ መግለጫዎችን እየሰጠ መሆኑን መድረክ በትዝብት እየተከታተለው ይገኛል፡፡
መልካም አስተዳደር አሳጡ የሚላቸውንም ባለስልጣናቱን ከአንዱ ሥልጣን ወደ ሌላ እያሸጋሸጉዋቸው እያየን ነው፡፡ ከዚያም አልፎ “በተፈጠረው ጉዳትም የፌደራል መንግሥቱ ያዘነ ሲሆን ለተፈጠረው ችግር ሁሉ ይቅርታ ይጠይቃል” በማለት ሲቀናጡ ይታያሉ፡፡ በሕዝቡ ላይ ይህን ወንጀል የፈጸመውን ተኩሶ ገዳይ ኃይልም ሆነ አስተዳደራዊ በደል እየፈጸመ ያለውን ሙሰኛ ለሕግ አቅርቦ ሳያስቀጣ “በይቅርታ” እና “አጥፍተናል” በሚሉ ቃላት የመሸንገል አላማቸው የምዕራቡን ለጋሽ ሀገሮች ቀልብ ከመሳብ የተወጠነ ከመሆን አያልፍም፡፡ በምዕራቡ አለም አንድ መንግሥት “አጥፍቻለሁ ይቅርታ” እስካለ ድረስ የትልቅነትና የቅንነት መገለጫ ተደርጎ ስለሚወሰድ የኢህአዴግም ብልሀት ይህንን ክብር ከምዕራቡ ለጋሽ ሀገራት ለመጎናጸፍ በመወጠን የያዘው ስልት ከመሆን አያልፍም፡፡
ኢህአዴግ መሠረቱ ሕዝባዊ ውክልና የሌለው አምባገንን መንግሥት በመሆኑ የሕዝቡን ምሬትና የተቃውሞ እንቅስቃሴን ከዚህ በላይ እንደተገለጸው በአገዛዙ በሰፈነው ብልሹ አስተዳደር ላይ ብቻ ለማሳበብ ይሞክራል፡፡ በሌላ አንጻር ደግሞ የሕዝቡን ሕገመንግሥታዊ፣ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በመጣስና በፖለቲካ ወገንተኝነት፣ በሰላማዊ አግባብ በዚሁ ብልሹ አስተዳደሩ ላይ ተቃውሞአቸውን የገለጹትን ዜጎች በገፍ እያፈሰ ማሰሩንና ማሰቃየቱን እያባባሰው ይገኛል፡፡ በሀገሪቱ ለሚካሄደው ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በተግባር እየሰጠ ያለው ምላሽም በተቃውሞ እንቅስቃሴው ተሳትፎአል ብሎ የጠረጠራቸውን ዜጎች ሁሉ ከየመኖሪያ ቤታቸውና ከየሥራ ቦታቸው እያፈሰ ከማሰርና ከማሰቃየት አልፎ፣ እንደደርግ መንግሥት ዘመን እየገደሉ በየቦታው አስከሬን መጣል ድረስ የደረሰ ሆኖአል፡፡
እንደማስረጃም፣ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ቀርበው መግለጫ ከሰጡ ወዲህ ብቻ በሰላማዊ አግባብ ተቃውሞ ባሰሙትና በዚህ ተግባርም በተጠረጠሩት ዜጎች ላይ ከተፈጸሙት አፈሳዎችና እስራቶች ውስጥ ከኦሮሚያ ክልል ለመድረክ ጽ/ቤት የደረሰውን መረጃ ለአብነት ያህል ከዚህ በታች እንጠቅሳለን፡፡
1ኛ፡- ከምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሂርናና ዳሮ ላቡ ወረዳዎች——– 1000
2ኛ፡-ከምዕራብ ወለጋ ዞን ዳሌ ሰዲ ወረዳ ———————– 28
3ኛ፡- >> >> ሀዋ ጋላን ወረዳ ——————— 26
4ኛ፡- >> >> መናሲቡ ወረዳ ———————- 39
5ኛ፡- ከሆሮጉዱሩ ዞን ከጃርቴ ወረዳ —————————— 21
6ኛ፡- ከምዕራብ ሸዋ ዞን ከኢልፈታ ወረዳ ———————— 41
7ኛ፡- >> >> ከጨሊያ ወረዳ ————————- 20
8ኛ፡- >> >> አዳአበረጋ ወረዳ ——————– 20
9ኛ፡- ከምዕራብ አርሲ ዞን 13 ወረዳዎች ——————— 1200
10ኛ፡- ከቦረና ዞን ቀርጫ ወረዳ ——————————— 150
11ኛ፡- ከቡራዩ ወረዳ ——————————————— 2
12ኛ፡- ከነቀምቴ ከተማና አከባቢው —————————— 80
በድምሩ————- 2627 ዜጎች ከኦሮሚያ ክልል ብቻ ከሕግ አግባብ ውጭ ታስረው በጠባብ ክፍሎች ውስጥ በመታጎር ስቃይ እየደረሰባቸው ለመሆኑ ለመድረክ ሪፖርት ተደርጎለታል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዜጎች ከየሥራ ቦታዎችና ከየመኖሪያ ቤታቸው በገፍ ታፍሰው አብዘኛዎቹም ቤተሰቦቻቸውና ዘመዶቻቸው በማያውቁዋቸው አከባቢዎች ተወስደው የተሳሩ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የሚገኙበትን ሁኔታ ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኖአል፡፡ ከዚህም ሌላ በርካታ ዜጎች “ትፈለጋላችሁ” በሚል መሠረተብስ የማሸበሪያ ፕሮፓጋንዳ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተለይተው ለአሳዛኝ ስዴት ተዳርገው የምርት ተግባራቸውን እንዳያከናውኑ ተደርገዋል፡፡ አገዛዙ በብልሹ አስተዳደሩ ላይ በሰላማዊ አግባብ ተቃውሞ በማሰማታቸው የታሰሩትንና በተለያዩ እስር ቤቶች ታጉረው የሚገኙትን የኦፌኮ/መድረክ የአመራር አባላት፣ አባላትና ደጋፊዎች፣ እንዲሁም በአገዛዙ ላይ ምሬታቸውንና ተቃውሞአቸውን ለመግለጽ የተንቀሳቀሱ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ዜጎችን ከእስር በመፍታት ረገድ አንዳችም ተጨባጭ እርምጃ ሳይወስድና በአገዛዙ በግፍ ለተገደሉ ዜጎችም ኃላፊነት ወስዶ ተጠያቂዎችን ለሕግ ሳያቀርብ፣ አሁንም ተቃውሞ አሰምታችኋል ባላቸው ዜጎች ላይ ሕገ ወጥ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ የሕግ የበላይነት የሌለበት ሥርዓተ መንግሥት መሆኑን ግልጽ ያደርገዋል፡፡

አምባገነኑ የኢህአዴግ ሥርዓት ሕዝባችንን አፍኖ ለመግዛት ከሚጠቀምባቸው ስልቶች መካከል፣ የመድረክ አባላትንና የበታች አመራር አካላትን ሕገ ወጥ በሆነ አግባብ ደጋግሞ እያሰረና እየደበደበ ዋስ አስጠርቶ በመፍታት እንደዚሁም የተለያዩ መንግሥታዊ አገልግሎቶችንና ሰብአዊ ዕርዳታዎችን እንዳያገኙ በመከልከል ስነልቦናዊ ጫና መፍጠርና ለተለያዩ ችግሮች መዳረግ አንዱ ስልት ነው፡፡ በዚህ ስልቱም በዕለት ከዕለት የኑሮ ውጣውረድ ተጠምዶ ያለውንም ዜጋ ሁሉ በፖለቲካ አቋሙና በሚያነሳቸው ሕጋዊ የመብት ጥያቄዎች ምክንያት በደል እያደረሰ ይገኛል፡፡ የዚህ አይነት ጥቃቶች እየደረሱባቸው ካሉት አከባቢዎች መካከል በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የከፋ ሸካ ዞን፣ የጋሞ ጎፋ ዞን፣ የሰገን አከባቢ ሕዝቦች ዞን ውስጥ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማሕበረ ዴሞክራሲ-ደቡብ ሕብረት አንድነት ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ከዚህም ሌላ በካፋ ዞን በቦንጋ ከተማ የነበረው የኢማዴ-ደህአፓ ቅ/ጽ/ቤት በአሁኑ ወቅት በዞኑ ፖሊሶችና የመንግሥት ባለሥልጣናት እንዲዘጋ ተደርጎ ይገኛል፡፡ እንደዚሁም ለልማት እየተባለ በመንግሥትና የሙስና አጋሮቹ በሚካሄደው የመሬት ነጠቃ ላይ ተቃውሞ ያሰሙ ዜጎች ላይ እስራትና ግዲያ ጭምር ከተፈጸመባቸው መካከል የቤንች ማጂ ዞን፣ የደቡብ ኦሞና የጋምቤላ ሕዝቦች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ እንደዚሁም የኮንሶ ወረዳ ሕዝብ ላነሳው ሰላማዊ ሕገመንግሥታዊ ጥያቄ የኃይል እርምጃ ምላሽ መሰጠቱም የሚታወስ ነው፡፡ በተጨማሪም በድርቅ ምክንያት ምርት ጠፍቶ ለረሃብ ጥቃት ተዳረገ የተባለለት ሕዝብ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መሆኑ እየታወቀም የኢህአዴግ የንግድ ተቋማት ሀብት የሆነውን የማዳበሪያ ዕዳ ካልከፈላችሁ በማለት ሕዝቡን በእስራትና ንብረቱን በመውረስ ማወክብ በመላው ሀገሪቱ ተስፋፍቶ የሚገኝ ሲሆን ለአብነት ያሕልም በሀዲያ ዞን የሌሞ፣ አንሌሞ፣ ሶሮ፣ ጎምቦራ፣ ዱናና በባድዋቾ ወረዳዎች በሚኖሩ የኢትዮጵያ ማሕበረ ዴሞክራሲ- ደቡብ ሕብረት አንድነት ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የከፋ ወከባ እየፈጸመባቸው ይገኛል፡፡
እንደዚሁም የመድረክ አባል የሆነውን የአረና ትግራይ የአመራር አባላትን አስረው ማስፈራራታቸው፣ ማዋከባቸውና የፓርቲውንም ድርጅታዊ ሥራ ለማደናቀፍና በሰበብ አስባቡ ሕልውናውን ለመፈታተን በምርጫ ቦርድ አማካይነት በቅርቡ እየተፈጸሙ ያሉት ድርጊቶች ተጠቃሾች ናቸው፡፡
ከዚህም ሌላ የመድረክ አባል የሆነው የሲዳማ አርነት ንቅንቄ አመራር አባላት የሆኑት፡-
1ኛ፡- አቶ ደሳለኝ መሳ፣ 2ኛ፡- አቶ ተሾመ ደበበ፣ 3ኛ፡- አቶ ደዋሳ ዳሳ፣ 4ኛ፡- አቶ ሹራ ቻቻራ 5ኛ፡- አቶ ግሼ አማዶ ከየሥራ ቦታቸው ተይዘው ሕዝባዊ የተቃው እንቅስቃሴ ያነሳሳሉ በሚል መሠረተብስ ስጋት በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡
በአጠቃላዩም፣ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በአንድ በኩል እስከ አሁን በፈጸማቸው ወንጀሎች የተጸጸተና ያዘነ ለመምሰል አስመሳይ መግለጫዎችን እየሰጠ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ብልሹ አስተዳደሩን የተቃወሙትን የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትንም ሆነ ሌሎች ዜጎችን በገፍ እያሰረ ማንገላታቱን በተግባር እያባባሰው ይገኛል፡፡
ስለሆነም እነዚህ ከተግባሩ ጋር የሚቃረኑ መግለጫዎቹ ሕዝቡን ግራ በማጋባት ውዥንብር ውስጥ ከመክተትና ችግሩንም ከማወሳሰብ ውጭ ለሀገራችን ወቅታዊና ዘላቂ ችግሮች መፍትሔ ሊሆኑ ስለማይችሉ፣ በማስመሰያ መግለጫዎች ሕዝቡን ለመሸንገል የሚያደርገውን ፋይዳብስ ሙከራ አቁሞ፡-

1ኛ፡- ኢህአዴግ በአደባባይ ባመነበት ብልሹ አስተዳደሩ ላይ በሰላማዊ አግባብ ተቃውሞአቸውን በማሰማታቸው ምክንያት በገፍ ያሰራቸውን አባሎቻችንንና ደጋፊዎቻችንን እንደዚሁም ሌሎች ሰላማዊ ዜጎች በአስቸኳይ እንዲፈታቸው እንጠይቃለን፡፡
2ኛ፡- በሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ የተሳተፉትን ዜጎች በግፍ የገደሉት ወንጀለኞች በገለልተኛ አጣሪ አካል ተጣርቶ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡
3ኛ፡- በብልሹ አስተዳደራቸው ምክንያት በሕዝቡና በንብረቱ ላይ ለደረሰው ጉዳት የኢህአዴግ መንግሥት ኃላፊነት ወስዶ ለተጎጂዎቹና ለቤተሰባቻቸው ተገቢውን ካሳ እንዲከፍል እንጠይቃለን፡፡
4ኛ፡- የሕዝቦቻችን ሕገመንግሥታዊ፣ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ተከብረውና መልካም አስተዳደር ሰፍኖ፣ ሀገራችን ወደ ሁለንተናዊ የልማት ጎዳና እንዲታመራ ለማብቃት፣ ኢህአዴግ ከመድረክና ሌሎች ሀቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር የፖለቲካ ምህዳሩን ነፃ፣ ፍትሐዊና ታአማኒ ለማድረግ በአስቸኳይ እንዲደራደር በአጽንኦት እንጠይቃለን፡፡
በመጨረሻም፣ ኢህአዴግ ፋይዳቢስ ባዶ የቃላት ሽንገላዎችን አቁሞ ከላይ የተጠቀሱትን ተጨባጭ የሆኑ የእርምት እርምጃዎች በመውሰድ የሕዝባችንን መብቶች እንዲያከብርና ሀገራችንን ከገባችበት የፖለቲካ አዘቅት ለማውጣት፣ ወደ ድርድር መድረክ እንዲመጣ መላው ሕዝባችንና ሰላም ወዳዱ የዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ ሁሉ የየበኩላቸውን ጫናዎች በኢህአዴግ ላይ እንዲያሳርፉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ድል ለሕዝባዊ ትግላችን!!
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ
መጋቢት 23 ቀን 2008 ዓ ም
አዲስ አበባ

16 Comments on “ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የተሰጠ መግለጫ”

  1. Medrek le ysmula andnet mtl neger leTfual lk ende felefelew tgrie woyanie leysmula aTftenal yqrta andalew.
    Dnqiem andnet asabi.
    Ene gebru, merara, bulcha, beqele gerba ke woyanie yalanesu zereña, le bhierachew yebelaynet yeteselefu nachew.
    Sle welqait Tgedie altenefesum. Be qmant sm woyanie yeserawn wonkel lafachew leysmula enkua alastawesum.
    Amara oromon yqrta yTeyq yemil sew beqele gerba new.
    Ke 150 amet befit mnilk oromon slasgebere, amara bedlual oromon maletu new.
    Minilk gemashu benatu aromo sleneber ke meqabru hido yfaredew.
    Amara balseraw Tfat, balneberebet, bemayawqew tarik, ediyawm ke woyanie gar bemetebaber oneg, ohdd, ofco cimr bafenaqelut, begedelut yiqerta yiTeyq malet yeleyelet ye aemro zegemteñanet new.
    Slegedelachuhn yiqerta adergulun belu ylal.
    Becirash medrek ke woyanie slemayshal amaraci ayhonm.
    Ye tgrie woyanie biwodq yewoyanien alama lemasqeTel new medrek yetefeTerew.
    medrek emrca semon parlama gebto demoz lemagñet kemeruaruaT besteqer mnm woyanien lemeTal miyadergew enqsqasie yelewm.
    medrek woyanien kemr aytagelm, ke woyanie mot behualm ayTeqmenem.
    Be mehonum kla belut medrekn. Jib kehiede wusha cohe aynet new.
    Snt teblo teblo yeqoyen neger bekefil gelbTo bemaqerb tagay bememsel woyanien maregagatu new.

  2. Bench of idiots .
    Where has the homeless
    Professor gone ?
    Belew Iyale indalchefr
    ahun iye iye yilal .
    Zeregnoch .

  3. you 2 idiots underneath me what kind of animals are you? since you supporting weyane you are no better than those thugs. you are not ETHIOPIAN you are most definitely son of a bitches.

  4. Obo zorbulu and ur friend..r u two still singing about that toxic abissinian unity which have been seen for century or western bona fide one ? Or else is it about anko minilik who came to kush land with sheephide barefooted(uncivilized) ?and u need to know, u cant do the same as the world always keep changing.But EFDU omitted ogaden .i think it must b all about kush. u can say any thing about those cowered amhara ,wallamo ,kimant minilik ,mengstu bla bla acording to ur blood relation.u love us we love u ,u hate us we hate u.thats all.

  5. Sidamaol = tefa gebreb? Oneg?
    Toxic abyssinian unity yemil gleseb oneg woim ke shabiya new
    Ye ethiopia Telat new.
    Alem telewTual, ethiopian cemro.
    Gn shabiya, woyanie, oneg, ke medrek ene merera, bekele gerba, gebru, asegd g/slasie ena andand ye ohdd sewoch be Tere-amara, beTere-ethiopianet teselfew ahunm toxic abyssinian unity ylalu, alteleweTum.
    medrekn, woyanien, Tere-amara, Tere-ye ethiopia bhierochna Tere-ethiopia yehonachuhn awegzalehu.
    Hulun bhier, bhiereseb bekul akebralehu, ekulnetachew endikeber Tnu aquam aleñ.
    Be ethiopia andnet amnalehu.
    Be oromo, amara, gambiela, konso, somali, etc tgrie woyanie yefeTemewn bedel kemr awegzalehu.
    Wanaw qum neger bandnet woyanien enawdm new

  6. So-called “ኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ” should drop tribalism to be taken seriously.

    Also it should drop the use of primitive tribalist language like
    “ሕዝቦቻችን” , there is only one people in Ethiopia whether they like it or not and there is only one land, and that land belongs to Ethiopians whether they like it or not, and not to oromos, amaras, sidamas, afars etc.

    Remaining tribalist means for medrek that it will be viewed as CIA or ferenji created and sponsored and as such as slave of foreigners.

    Their primitive, pro-ferenji and pro-arab tribalism is rejected all over Africa and they could be accused of perpetuating misery in Ethiopia, of serving enemy agendas (those of ferenjis and arabs) and get punished.

  7. Subhuman tesfaye gebreab,
    get the fuck outta here.

    ” Sidamaol says: April 2, 2016 at 1:55 am

    Obo zorbulu and ur friend..r u two still singing about that toxic abissinian unity which have been seen for century or western bona fide one ? Or else is it about anko minilik who came to kush land with sheephide barefooted(uncivilized) ?and u need to know, u cant do the same as the world always keep changing.But EFDU omitted ogaden .i think it must b all about kush. u can say any thing about those cowered amhara ,wallamo ,kimant minilik ,mengstu bla bla acording to ur blood relation.u love us we love u ,u hate us we hate u.thats all. “

  8. Medrek,
    the choice is yours.

    1. There is only 1 people in Ethiopia.

    2. There is only 1 land in Ethiopia.

    3. The people are called Ethiopians.

    4. The land is called Ethiopia.

    Medrek keep tribalism at your peril !

    Tribalists in Ethiopia = ferenji and arab agents !

    Tribalism is rejected all over Africa.

    Keeping tribalism and therefore perpetuating misery in Ethiopia could lead to the charge of treason.

    We know ferenjis, arabs and other foreigners, including tiny tiny Eritrea 😉 , like tribalism in Ethiopia, for a reason. Therefore the likes of CIA finance tribalist groups.

    So Medrek,
    the choice is yours.

    ” Medrek le ysmula andnet mtl neger leTfual lk ende felefelew tgrie woyanie leysmula aTftenal yqrta andalew.
    Dnqiem andnet asabi.
    Ene gebru, merara, bulcha, beqele gerba ke woyanie yalanesu zereña, le bhierachew yebelaynet yeteselefu nachew. “

  9. Some of the comment very low. The party changed his name to nation wide and expand it’s vision that is good thing if you like unity. still you can oppose them what policy they fallow but not point out their ethnic belonging everybody belong to in one of the ethnic that is not the issue the issue what is the policy? where stand? if you single out others ethnic group you are raciest. so fight your fight in civilized way not like a looser.

  10. Aferblue yalk aferyiblu
    medrek ke tgrie woyanie ayshalem.
    Slezih ende woyanie meTfo drjit slehone ayasfelgenm.
    Yih ababal tgrie woyanien medgef aydelem. Huletun meTfowoch meqawem new.
    Medrek wusT eko qendeña tgrie woyaniewoch ene gebru, ene asegd g/slase nachew yalu.
    Medrek eko Tere-amara new, Tere-ye ethiopia andnet new.
    Leziyam new eko yewelqait, Tegedie ejg zegnay ke rwanda yebase yezer maTfat wonjel, be tgrie woyanie ye tefeTemewn zm blo sayawegzew yalefew.
    Englizeñawo tebelashitual.
    “You are son of a bitches”, yih ye ebd englizeña new.
    You are a son of a bitch

  11. Geday Semret says:

    March 30, 2016 at 7:59 pm

    የዳግም አደዎ ዘመቻ
    ቁጥር 7 መመሪያ
    ኢሐድግዬ(1000 ምርጥ ዘር አደዎዎች) እና ሆዳቸውን የመለኩ በቺሎቹ እስከ አሁን ሕዝባችንን በጭካኔ መግደሉን እና ስልጣኑን ለመልቀቅ እንደ አበደች ውሻ ሆነዎል። ኢትዮጵያን ምን አይነት አገር እንደሆነች ሳያቋት፣ በሱዳን 17 አስማተኞች አህያዎች ይዘው በጎርፍ ጋኔን ቤተ መንግስት ተሳካላቸው፣ ሕዝባችንንም በዘር ፓለቲካ እንደ አህያ እንዲያስብ አረጉት። ኢትዮጵያ 41 ጊዜ በላይ በመፃፍ ቅዲስ የከበረች እና ሂዱ እዛ ኑሩ የኣላ ሰላም አገር ነች ብለው ነብዩ መሐመድ ያከበራት አገር ነች። ይሁን ና የነብዪን ቃል የፈረሱት አገሮች ተቀጥተዎል ለምሳሌ ሱማሊያ፣ኢራቅ፣ግብፅ፣ሊቢያ፣የመን፣ሰውዲ ፣አራን አሁን ደግም በቅርብ ቀን አልበሽር ተረኛ ነው። የሚከተለውን ተጨማሪ መምሪያ ሕዝባችን ተግባራዊ እንዲያረግ እንገልፃለን።
    1ኛ፣ ኢሕአዴግ ስላዬቸን ኤርትራዊ ናቸው እያላቸው እንደ ስደተኞቹ ለሌላው አላም በችግራችን ግዜ ደረሶቹን ወንድም ኤርትራዊያን ስም ማጥፋት ቀጥሏል። መረጃ ለወድ ኩሩ ለሆነው አቶ ኦባንግ መቶ አስተላልፈ፣ ትክክለኛ ስደተኞችን መርዳት ሲገባ የባለሥልጣናት ልጆች ስራቸውን ስለሚያቁ እየጎረፈ ነው።
    2ኛ፣ ሕዝባችን በዚህ ጊዜ ያለውን ከአርበኞች ግንባር፣ ኢሳት፣ የአቶ ኦባንግን ድርጅት አንገብጋቢ ወቅት ላይ ስለሆን መርዳት አለበት። አቶ ኦባንግ ሰሞኑን በሙሁራኖች የተጨመቀ ሰለለውጡ ካርታ እንዴት አውራ ሸግግር መሪ እንደሚጓዝ እና በቋሚ ስርአት ለውጥ መረጃ ይሰጣል።
    3ኛ፣ ሕዝባችን እንዲሁም የትግራይ ጭቁን ወገኖቻችን፣ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አክብሮ የሰጣትን የሙሴ ፅላት አቡነ ማትያስ ፣ ጠ/ሚ፣ የስውር ተሐድሶ መሪዎች በጋሻው፣ከቤተ ክህነት ወስጥ ባሉት ሰንሰለት ሌሎችን አባቶችን፣ ማሕበራትን፣ ጥሩ አገልጋዮችን በማግለል በአለፈው ሳምንት በብዙ ሚሊዮን ለመሸጥ እና አስመሳዩን ታቦት ለማስቀመጥ በስውር የጋኔን አምላኪዎች ጋር ተማምሏል። ባዶ ቀፎ ይዞ መጓዝ አይቻልም? ኢትዮጵያዊ ሁለ በግዜህ ተነስ፣ በቃ በቁመና ሞተናል ወሬ በቃኝ።
    አቡነ መርቆርዮስ እራሳቹን ወደ ውስጥ መመልከቻቹ አሁን ነው። የአባቶቻችን ድጐማ ና ቀኖና አንዲት ሳት ቀይር ለህዝባችን ለአንድነት ጥሪ መድረግ አለቦት። አለበለዚያ የአቡነ ጴጥሮስ መስቀል እና ደም ከፊቶት ቆሟል!!!
    4ኛ፣ ማንም አስከ ዛሬ ያልቻለው የትግሉ አቀናጅ ማነው ብለው በአምቦ ክተ ት ላይ ነች። እኔ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ ሰው አንዴ በዘር ፓለቲካ ይታለላል ግን ሁለተኛ ከደገመው ግራ የገባው ነው።
    5ኛ፣ ግራ የሚያጋቡትን የታሪክ አዎራዎችን አትመለከቱ ጊዜ የለም ህዝባችን እየተገደሉ እና ረሐብ ላይ
    ነን። የትግሉ መሪ እስከ ሽግግር ድረስ የተግባር ጀግኖቹ ዲ/ር ብርሀነ ነጋ እና የጦር አስተባባሪ አዛዥ ጀነራል ከማል ገልቹ። ከዚያ በአዲሱ ህጉ መስረት ቋሚ መንግሥት ቢበዛ ለ 10 የሚያገለግል ይመረጣል። ለህዝባችነው መረጃውን አስተላልፍ በተዋረድ ትእዛዝ ተቀብላችሁ በፍቅር ተጠንቅቃቹ ጠብቁ። ወላ ዋይ ትውልድ መሆንን አቁማችሁ ፣ በአገር ወስጥ ከ10ኛ ክፍል ኢሐዲግ ተስፈህን ያጨለመብህ መሰደድን አቁመህ በአገርህ የትግሉ ወስጥ ተሳታፊ ሆነህ ቀጥል። የኢሕአዴግን ስርአት እርቃናው ላይ አድርሰናል በመርᎊ ትንሽ መንካት ነው የቀረን። በመተዛዘን ፣ በፍቅር፣ በአንድነት እንነሳ!!! ትግሉ ወዲያውኑ ሲጀመር የአገር ውስጥ መገናኛ ስለምንቆጣጠር ከህዝብ ጋር የሆነ ትግል ቢበዛ 30 ቀናት ብቻ ነው የሚያስፈልገው ለ1000 ኢሕአዴጎች ።
    ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ከ እግዚአብሔር እርዳታ ጋር!!! ንጉሡ ሞቱማ የአምቦ ንኡስ ኮር።

    [Reply]

    Reply

    Fekeru Tolcha says:

    March 26, 2016 at 10:47 pm

    Hero proud of u!!!!!!!!!!!!!!! we stand together Mote Lewyeana ena Le Faku Aba Mathis

    ABUNE MATHIAS THE WORST DEVIL AND HE LOST HIS SPRITUAL POWER. HE IS A CHAIR PERSON ON EVERY FRIDAY DEVIL SECRET MEETINGS

    [Reply]

  12. Lemetame ke tgriewoch miTebeqew ye ethiopia andnet miyasa sm yizew mederajet new lemsalie ye ethiopia tnsae drjit, ye ethiopia edget drjit, etc bemil sm ena betegbar ke lielaw tgrie kalhone yebeleTe woyanie bemetagel haqeñnetachewn masmesker alebachew. Be woyanie mkniyat baleda slehonu. Beqer mawonabed yaqumu.

  13. Prof.Beyene Petros…yaw ye Biology astemari Demoz bednb bayaznanam…ERSWO teru Metorya agegntewal….prty eyalu eyaweru yezihn jil hizb genzeb meblat….

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*