የቶሮንቶና የነቀምት ግንባር፤
ተክለሚካኤል አበበ (ቶሮንቶ)
የማርቆስ ብዙነህ ደብዳቤ፤
1- “በርካታ ትምህርት ቤቶች፤ ዩኒቨርስቲና የመንግስት ተቋማት በሚገኙበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የማይቻል በመሆኑ፤ የተጠየቀው የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን እንገልጻለን” ይላል፤ በአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቅ ክፍል ሀላፊ፤ በአቶ ማርቆስ ብዙነህ ማንደፍሮ፤ መጋቢት 23 ቀን 2006/2014 የተፈረመው ደብዳቤ፡፡ አንድነት፤ ሰልፉን ለማድረግ ያቀረባቸው መስመሮች 3 ሲሆኑ፤ ሶስቱም መስመሮች ከቀበናው የአንድነት ጽ/ቤት ይነሳሉ፡፡