ለግንቦት 7ም ሆነ ለሌሎች ተቃዋሚዎች ያለመተቸትን ከለላ ማን ሰጠ?
የእነ “… ወይም ሞት” ፖለቲካ
ያሬድ ኃይለማርያም ከብራስልስ
ከ1960ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ የአገራችንን ፖለቲካ የተጠናወተው የ”…. ወይም ሞት” አስተሳሰብ ከአስርት አመታት በኋላም አለቅ ብሎን ዛሬም እኔ ከምደግፈው ፓርቲ ወይም የፖለቲካ ቡድን ወይም አስተሳሰብ ውጭ ያለው መንገድ ወይም አማራጭ ሁሉ ገደልና ሞት ነው ብለው የሚያስቡ ፖለቲከኞችና ዓጃቢዎችን ቁጥር በብዙ እጥፍ አባዝቶ ቀጥሏል።