በዘር ማጥፋት፥በሰብአዊ ፍጡር ላይ በተፈፀመ ወንጀል እና በጦር ወንጀል የሚጠረጠሩ ፖለቲከኞችን እንዲመረርምር፥ በተረጋገጠባቸዉ ላይ እንዲፈርድ የተቋቋመዉ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ግን እስካሁን ክስ የመሠረተዉ በስምት የወንጀል ጭብጦች ነዉ።በስምንቱም ጉዳዮች የከሰሳቸዉ፥ ወይም የፈረደባቸዉ ፖለቲከኞች በሙሉ ግን አፍሪቃዉያን ናቸዉ።

የአፍሪቃ ሕብረት አባል ሀገራት መሪዎች ከዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት (ICC) ጋ ስለሚኖራቸው ግንኙነት የጋራ አቋም ለመያዝ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ሲወያዩ ውለዋል።

እአአ ከ1990 ወዲህ ፣ ባለፉት 23 ዓመታት፤ በሥልጣን ላይ የሚገኙት የቻድ ፕሬዚደንት ኢድሪስ ዴቢ ሂስ የሚሰነዝሩባቸውን በቸልታ ባለማለፋቸዉ ይታወቃሉ። በሀገር ውስጥ የጭቆና አገዛዛቸውን የቀጠሉት እና ዘመናይ የጦር ኃይል ያቋቋሙት ዴቢ ሀገራቸው

የአፍሪቃ ሕብረት አባል ሀገራት መሪዎች ከዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት (ICC) ጋ ስለሚኖራቸው ግንኙነት የጋራ አቋም ለመያዝ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ሲወያዩ ውለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን፣ በመጪው ሰኔ ወር በብራዚል ለሚካሄደው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር አፍሪቃን ወክለው ከሚገኙት 5 ቡድኖች አንዱ ሆኖ ለማለፍ ፣ከናይጀሪያ ጋር የቀሩት 2 የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ናቸው።

የአንድን ወይንም የራስን ሀገር፣ ቤተ መዘክር፣ ሀውልት፣ የህንፃም ሆነ ሌሎች ቅሪቶች እና የመሳሰሉትን በመጎብኘት ስለ ሀገር ታሪካዊ ቦታዎች እና ታሪክ ማወቅ ይቻላል። ለመሆኑ ወጣቱ ስለ ሀገሩ ታሪካዊ ቦታዎች ምን ያህል ያውቃል? ምን ያህልስ ማወቅ ይፈልጋል?

በአክሱም መንግሥት መደበኛ ቋንቋ እንደነበር ይነገራል፤ የግዕዝ ቋንቋ። ዛሬም ድረስ የግዕዝ ቋንቋ በኢትዮጵያ፤ በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እንዲሁም በኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጥቅም ላይ ይዉላል።

አጋቾች ኋላ ላይ እንዳስታወቁት ጠቅላይ ሚንስትሩን ያገቱት፥ ዩናይትድ ስቴትስ በ1990 የናይሮቢና የዳሬ-ሰላም ኤምባሲዎቿን ካጋዩ «አሸባሪዎች አንዱ» ያለችዉን አቡ አነስ አል ሊቢን ባለፈዉ ሳምንት ከሊቢያ አፍና ስትወስድ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተባብረዋል በሚል ለመበቀል ነዉ።

ማይ አይኒ በተባለው የስደተኞች ካምፕ ወደ ኢጣልያ ለመሻገር ሲሞክሩ ባለፈው ሳምንት የሞቱትን ኤርትራውያን ለማሰብ ባለፈው ቅዳሜ ማታ ስደተኞቹ ካዘጋጁት የሻማ ማብራት ስነስርዓት በኃላ ባካሄዱት ሰልፍ ብሶታቸውን ሲያሰሙ ነበር ።

ከ 318 ዓመታት በፊት ፣ እ ጎ አ በ 1705 ዓ ም መሆኑ ነው፣ ታላቁ እንግሊዛዊ የፊዚክስ ና የሒሳብ ሊቅ አይዛክ ኒውተን፤ ስለ ስበት ኃይልና ስለብርሃን ምንነት ካደረገው ምርምር ውጭ ፣ ስለ ኅልፈተ ዓለም በማንሳት፤ እ ጎ አ በ 2060 ዓ ም፣

የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አልአሳድ ጀርመን የሶሪያውን ቀውስ እንድትሸመግል እንደሚፈልጉ አስታወቁ። ፕሬዝዳንቱ ለአንድ የጀርመን መጽሔት እንዳሉት የጀርመን ልዑካን ሶሪያ መጥተው የሃገሪቱን አጠቃላይ ይዞታ እንዲመለከቱና በተጨባጩ ሁኔታ ላይ ከደማስቆ መንግሥት ጋር እንዲወያዩ ጠይቀዋል። ይሁንና የጀርመን መንግስት የአሳድን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

አፍሪቃ ውስጥ ሥራ እያላቸውም በልተው ማደር ያቃታቸው ጥቂቶች አይደሉም። እንደ ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ድርጅት በምህፃሩ ILO መዘርዝር ከሆነ 40 ከመቶ የሚሆን አፍሪቃዊ የሚተዳደረው በቀን ከ25 ብር በታች በሆነ ገቢ ነው።

ዩኤስ አሜሪካ በሶማልያ እና በሊቢያ በልዩ ኮማንዶዎችዋ ባለፈው የሣምንት መጨረሻ የወሰደችው የጥቃት ርምጃ ከአብራሪ የለሽ የጦር አይሮፕላኖችዋ ይልቅ በልዩ ኃይል ላይ ያተኮረ ሥልት መከተሏን አመላካች ሆኖ ታይቶዋል።

ግዛቲቱን የሚያወድመዉ ጦርነት ለወትሮዉ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ማዕከላዊ መንግሥት እና በሩዋንዳና በዩጋንዳ ይታገዛሉ የሚባሉት የM23 አማፂያን ነበር።ከቅርብ ጊዜ ወዲሕ ግን የኮንጎ መንግሥት ጦር፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጦር፥ በዉጤቱም ጦር ያዋጡት መንግሥታት እና የአማፂያን እና የአማፂያኑ ደጋፊዎች ዉጊያ ሆኗል።

የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ልዑካን በአዲስ አበባ ከአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን ባለሥልጣናት ጋ ምክክር አካሄዱ። ባለሥልጣናቱ ከአንዱ ቀን ውይይት በኋላ ባወጡት የጋራ መግለጫ አፍሪቃ በአህጉሯ ለሚታዩ ውዝግቦች መፍትሄ ለማሰገኘት በምታደርገው ጥረትዋ የዓለሙ መንግሥታት ድርጅት ድጋፍ እንደማይለያት ተገልጾዋል።

ወባ ዛሬም ገዳይ በሽታ ነዉ በተለይ በአፍሪቃ። በበሽታዉ በግምባር ቀደምትነት የሚጠቁት ህጻናትና ነፍሰጡር እናቶች መሆናቸዉን የህክምና ባለሙያዎች ያመለክታሉ። በወባ በሽታ በዓለማችን በየዓመቱ ከሚያልቀዉ ህዝብ ቁጥር 80 በመቶዉ የሚገኘዉ አፍሪቃ ነዉ።

በቅርብ ጊዜ የአውሮፓ የጀልባ ስደተኞች ታሪክ እጅግ አስከፊው አደጋ ነው ። ባለፈው ሃሙስ በኢጣልያዋ የላምፔዱዛ ደሴት አቅራቢያ ወደ 500 የሚጠጉ ስደተኞችን ያሳፈረች ጀልባ በእሳት ከተያያዘች በኋላ ሰጥማ የደረሰው አደጋ ። እንደ እድል ሆኖ 155ቱ ቢተርፉም የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 274 ከፍ ብሏል ።

የሰማዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሥለሺ ፈይሳ እንደሚሉት ደግሞ የአዲሱ ፕሬዝዳት አዲስ ነገር በራሳቸዉ ተንቀሳቅሳዉ እንግዳ መቀበል የሚችሉ መሆናቸዉ ነዉ።ዶክተር ሙላቱ ቻይና እና ዩናይትድ ስቴትስ የተማሩ፥ ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በምክትል ሚንስትርነት፥ በሚንስትርነት፥ በአፈ-ጉባኤነት፥ በአምባሳደርነት ያገለገሉ ናቸዉ።

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤትና የፌደሬሽን ም/ቤት በዛሬው ዕለት ፣ አዲስ የሀገሪቱን ፕሬዚዳንት መርጠዋል። የተመረጡት አዲሱ ፕሬዚዳንት፤ ቃለ መሃላ መፈጸማቸውንም፣

ዶክተር ነጋሶ እንደሚሉት እሳቸዉም ሆኑ ዛሬ የአስራ-ሁለት ዓመታት ዘመነ-ሥልጣናቸዉ ያበቃዉ አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊዮስ እንደፕሬዝዳትነት የሚጠበቅባቸዉን አላደረጉም።ዛሬ በፕሬዝዳትነት የተመረጡት ዶክተር ሙላቱ ተሾመም ከእስካሁኖቹ የተለዩ ይሆናሉ ብለዉ አይጠብቁም።ምክንያት?

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ፤ ዛሬ ከበርሊን በሰጠው መግለጫ ላይ ፤ የመን በሚገኘው ኤምባሲው አንድ የኤምባሲው የፀጥታ ጉዳይ ባለሙያ መገደላቸውን አረጋግጧል። አምባሰደሯ ወ/ሮ ካሮላ ሙዑለር ሆልት ኬምፐርን አፍኖ

እጎአ በ2000 ዓም 189 ሃገራትእጎአ እስከ 2015 ለመተግበር ቃልየገቧቸው Millennium development goals ወይምየተባበሩት መንግሥታት የአምዓቱ የልማትግቦችየተቀመጠላቸውየጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ 2 ዓመትገደማ ብቻ ነውየቀረው።

በኢጣልያ የባህር ክልል አካባቢ ሐሙስ፣ መስከረም 23 ቀን፣ 2006 ዓም ወደ አውሮጳ ለመግባት በሞከሩ አፍሪቃውያን ስደተኞች ላይ እንደገና ዘግናኝ የመሰመጥ አደጋ ከደረሰ በኋላ የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት የህብረቱ የስደተኞችና እና የውጭ ዜጎች ጉዳይ ፖሊሲ ሰብዓዊነት እንዲታከልበት እና ለስደተኞች ደህንነት

በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር መስሪያ ቤት ስራ ከጀመሩ ሁለት ወራት ያስቆጠሩት ምክትል ሚንስትሯ ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ መንግሥታቸው በአፍሪቃ በተለይም በቀፍሪቃ ቀንድን የሚከተለውን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አብራርተዋል።

ምስራቅ ኢትዮጵያ ውስጥ የምድር ባቡር የቀን ሰራተኞች በቀን ክፍያ በደል ደርሶብናል እያሉ ነው። እነዚሁ በምዕራብ ሃራርጌ ዞን አሰቦት አካባቢ የሚገኙ የምድር ባቡር ሰራተኞች እንደሚሉት ሌላ ቦታ ለተመሳሳይ ስራ በቀን የሚከፈለው ከ50 እስከ 100 ብር ሲሆን እነሱ ግን 25 እና 30 ብር ብቻ እየተከፈላቸው ነው።

በኢጣልያ ደሴት፤ ላምፔዱዛ አቅራቢያ ፣ ትናንት በእሳት ከተያያዛች በኋላ በሰጠመችው ጀልባ ውስጥ ከነበሩት ስደተኞች ደብዛቸው የጠፋውን ፍለጋ ዛሬም ቀጥሏል ።ከሊቢያ የባህር ጠረፍ 500 የሚሆኑ ስደተኞች አጭቃ ላምፔዱዛ የባህር ዳርቻ የደረሰችው ይህችው ጀልባ የኤርትራ እና የሶማሊያ ስደተኞች ነበር ያሳፈረችው ።

ዩናይትድ ስቴትስ ለሩዋንዳ የምትሰጠዉን ወታደራዊ እርዳታ እንደምታቆም አስታወቀች። የዋሽንግተን አስተዳደር እንዳለው እርዳታው የሚቋረጠው ሩዋንዳ ፣ ህፃናትን በውትድርና በማሰለፍ የሚከሰሰውን

የመስተዳድሩን ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የጠቀሱ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት የከተማይቱን እቅድ ማሸጋሸግ ያስፈለገው ከፌደራሉ የእድገት እና ለውጥ (ትራንስፎርሜሽን) እቅድ ጋር ለማጣጣም ነው ተብሏል።

የአደጋ ደራሽ ሰራተኞች ካገኙት 82 አስክሪን መካከል በርካታ ሴቶች እና ሁለት ህጻናት ይገኙበታል። እንደ ከተማዋ ከንቲባ የጀልባዋ ተሳፋሪዎች ዛሪ ማለዳ በጀልባዋ ዋ ላይ ሳሉ እሳት ከተነሳ በኋላ፤ ለብዙ ሰዓታት ባህሩ ዉስጥ ነበሩ።አብዛኞቹ ተሳፋሪዎች ከኤርትራ እና ከሶማልያ እንደሆኑ ፖሊስ ተናግሯል።

በአዲሱ የጥናት ውጤት መሠረት ፣ የየብስ የመሬትና የከባቢ አየር ሙቀት መጠን ፣ ከተተነበየው በላቀ ሁኔታ በሲሦ ይጨምራል ነው የተባለው። እ ጎ አ እስከ 2100 ዓ ም፤ ውቅያኖሶች፤ ከባህር ልክ በላይ ከ 26 -82 ሴንቲሜትር ከፍታ ይኖራቸዋል ማለት ነው።

የመራሂተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ክርስቲያን ዲሞክራቶች ኅብረት ፓርቲ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። ፓርቲው በቅርቡ በተካሄደው የጀርመን የምክር ቤት እንደራሴዎች ምርጫ አብላጫውን ድምፅ ቢያገኝም፤ ሀገሪቱን በጥምረት አብሮ ሲመራ የቆየው FDP ለምክር ቤት በቂ ድምፅ ባለማግኘቱ ከሌሎች የተቃውሞ ፓርቲዎች ጋር ለመጣመር ድርድር በማድረግ ላይ ይገኛል።

የእሥራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት በኒው ዮርክ የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ንግግር አሰምተዋል። ንግግራቸው በተለይ በኢራን እና በኑክልየር መርሀግብር ላይ ያነጣጠረ ነበር።

የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ፣ በምሕፃሩ ኤራፓ፣ የብሔራዊ መግባባትን ጉዳይ አስፈላጊነትን ለማጉላት በአዲስ አበባ ለፊታችን እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቶዋል። ኤራፓ ሰልፉን በመሥቀል አደባባይ ለማድረግ ቢያቅድም፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍ እና

መስከረም 12 2006 ዓም የጀርመን ምክር ቤት ምርጫ ተካሂደ አሸናፊውና ተሸናፊው ቢለይም እስካሁን ግን አዲስ መንግሥት አልተመሰረተም ። አሸናፊዎቹ እህትማማቾቹ የክርስቲያን ዲሞክራት ህብረት ና የክርስቲያን ሶሻል ህብረት ፓርቲዎች አሁንም ተጣማሪ ፓርቲ ፍለጋ ላይ ናቸው ።

ከአራት ዓመት በፊት በአፍሪቃ በተደረገ ጥናት መሰረት የህዝቡ ቁጥር 1 ቢሊዮን ማለፉ ተመልክቷል። ይህ አሃዝ ከ 35 ዓመት በኋላ በእጥፍ እንደሚያድግ ተተንብይዋል።

በጎ አ 2011 ዓ,ም በግብፅ የተቀጣጠለ አብዮት፤ ዋና ዓላማ በሲቢሉ ላይ የሚደረገዉን ወታደራዊ እርምጃ ለማስቆም ነበር። ነገር ግን ከሁለት ዓመት ከመንፈቅ በኋላ ዛሪም፤ ወታደሩ በሲቢሉ ላይ የሚያካሂደዉ የሃይል እርምጃ እንደቀጠለ ነዉ። የሰላ ብዕር የያዙ ጋዜጠኞችም፤ ሥራቸዉን እንዳይሰሩ ይታፈናሉ።