ብዙዎች በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ መስሪያ ቤት አስፈላጊውን አገልግሎት በአፋጣኝ አልሰጠንም በማለት እንደሚያማርሩ እና ስጋት እንደገባቸው የጅዳዉ ወኪላችን ገልጿል። የሳውዲ መንግስት ሕገ ወጥ ስደተኞችን አስመልክቶ ያወጣውን መስፈርት ለሚያሟሉ ዜጎች የመኖሪያ ፈቃድ ለመስጠት የሰጠው የተራዘመ የምህረት አዋጅ፤

በሚቀጥለው ወር ፖላንድ ውስጥ በሚደረገው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ የአፍሪቃን አቋም ለማንፀባረቅ ይረዳል የተባለለት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አዲስ አበባ ውስጥ በአፍሪቃ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ስብሰባ ተካሂዷል።

የጀርመን መራሂተ-መንግስት የእጅ ስልክ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የስለላ ተቋም ሳይጠለፍ አይቀርም መባሉ ዩናይትድ ስቴትስና ጀርመንን እያነጋገረ ነው። ዋሽንግተን ሜርክል አልተሰለሉም፣ አይሰለሉምም ብላለች።

መዲና አዲስ አበባ ፤ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ትምህርት ቤት፤ የባቡር ጣብያ ፤ የአዉሮፕላን ማረፊያ፤ የማተሚያ ቤት ሆቴሎች የስልክ ቤት፤ የመሳሰሉ ህንጻዎችን የገነባች፤ ታሪካዊ ሃዉልቶችን ያቆመች እና በኢትዮጵያ ዘመናዊነትን ከተቀበሉት የኢትዮጵያ ከተሞች በቀደምትነት ትጠቀሳለች።

የቅሪተ አፅም እድሜ መለክያዉ እንዴት ነዉ፤ ረጅም እድሜ እንዳለዉ የሚነገረዉ ቅሪተ አፅምስ መገኛ ቦታዉ እንዴት ይታወቃል? ከመቶ ሽ በላይ እድሜ ያላቸዉን ቅሪተ አፅሞች እድሜ መለክያ ዘዴ እጅግ ቀላሉ ነዉ ያሉን ዶክተር ብርሃኔ አስፋዉ ሉሲ «ድንቅነሽ» ስትገኝ ከነበሩ ተመራማሪዎች መካከል አንዱ ነበሩ።

የዩናይትድ ሴቴትስ የአፍሪቃ እዝ አፍሪኮም ዋና አዛዥ ዴቪድ ሮድሪገዝ እና በአሜሪካን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ሊንዳ ግሪንፊልድ አሜሪካ ከሰሃራ በስተደቡብ ከሚገኙ የአፍሪቃ ሃገራት

«የጀርመንና ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ጉባኤ » የተሰኘ ውይይት እዚህ ጀርመን ኮሎኝ ከተማ ውስጥ ባሳለፍነው ሣምንት ተሰናድቶ ነበር። በውይይቱ የኢትዮጵያ እና የጀርመን መንግሥት ባለስልጣናትን ጨምሮ የተለያዩ ባለሀብቶች እና እንግዶች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ቢያንስ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት ስራ ፈላጊዎችን ወደ ሳውዲ አረቢያ እንዳይገቡ ማገዱን ኣስታወቀ።
በዚሁ መሰረት 40 ሺሽ ያህል ቀደም ሲል የተፈቀዱ ቢዛዎችም ተሰርዘዋል።

የጀርመን መከላከያ ሚኒስቴር የጀርመን የአፍጋኒስታን ኩንዱዝ ተልዕኮ ማብቃቱን ባለፈው ቅዳሜ አስታውቋል። የጀርመን ጦር ኩንዱዝን ሙሉ ለሙሉ ለቆ መውጣት የአካባቢውን ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆን ለጦሩ የተለያየ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ አፍጋናውያንን አስግቷል ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ለአሥር ቀናት በመላ ሀገሪቱ እና ከሀገር ዉጪ የሚገኙ አብያተክርስቲያናት ተወካዮች በተገኙበት የሀገረ ስብከቱን ጳጳሳት ጠርታ በውስጧ ስላሉ ችግሮች አወያይታለች።

በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የካንሰር ታማሚዎች ቁጥር እየጨመረ በመሄድ ላይ መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት ይገልጻል። ድርጅቱ አያይዞም በጎርጎሪዮሳዊዉ 2020ዓ,ም 65 በመቶ የሚሆኑ የካንሰር ታማሚ በአዳጊና በማደግ ላይ በሚገኙ ሃገራት እንደሚገኝ ከወዲሁ ጠቁሟል።

በጀርመን ባለፈው መስከረም ወር በተካሄደው ምክር ቤታዊ ምርጫ የብዙኃኑን ድምፅ ያገኙት የክርስትያን ዴሞክራቶች እና የክርስትያን ሶሻል ህብረት፣ ከሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲዎች ጋ በቅርቡ የጥምር መንግሥት ያቋቁማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ፣ የጀርመን ቡንደስ ሊጋ፣ የስፔን ላሊጋ እና የጣሊያን ሴሪ አ የእግር ኳስ ግጥሚያ በዛሬው የስፖርት ጥንቅራችን ሰፋ ያለ ቦታ ተሰጥቷቸዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድንን በተመለከተ ከአድማጮች የደረሱን አስተያየቶችን አካተናል። የአትሌቲክስ ውድድር ውጤትም የዝግጅቱ አካል ነው።

ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሚዋጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች ባለፈው ዓርብ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ በተለይም አዲስ ኣበባ በሚገኘው እና ማዕከላዊ ተብሎ በሚታወቀው የፌደራሉ የምርመራ ማዕከል በእስረኞች ላይ ይፈጸማሉ ባላቸው ሰብዓዊ ሰቆቃዎች ላይ ያነጣጠረ አዲስ ሪፓርት ይፋ ኣድርገዋል።

በጀርመን መዲና በርሊን እንብርት ላይ በሚገኘው በብራንድን ቡርገር ቶር አደባባይ ላይ፤ አፍሪቃን ጨምሮ ከሌሎች አህጉራት የተሰባሰቡ ስደተኞች ለአስር ቀናት ሲያካሂዱ የቆዩትን የርሃብ አድማ ትናንት እሁድ ማቆማቸዉ ተነግሮአል።

የአፍሪቃ ህብረት በሥልጣን ላይ ያለ መሪ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መቅጫ ፍርድ ቤት መከሰስ የለበትም በሚል አሁን ለፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ጥያቄ ለማቅረብ ሰሞኑን ወስኖዋል።

በደቡብ ሱዳን የዩኒቲ ግዛት የነዳጅ ዘይት የሚያወጣ « ግሬተር ፓየኔር » የተባለ አንድ የቻይና ኩባንያ በዚሁ የነጭ ዓባይ ዳርቻ የሚገኙ ከአምስት መቶ ሺህ የሚበልጥ ሕዝብ ለራሱ ደህንነት ሲል አካባቢውን እንዲልቅ እና ራቅ ወዳለ ቦታ እንዲሄድ የሁለት ወራት ጊዜ ሰጥቶዋል።

ማዕከላዊ ተብሎ በሚታወቀው የፌደራሉ የምርመራ ጣቢያ ሶስት የተለመዱ ስፍራዎች አሉ።አንደኛው ሰዎች ያለመብራት የሚታሰሩበት እና ጭለማ ቤት የሚባለው ነው።ሁለተኛው ለግርፋት የተመቻቸው ጣውላ ቤት የሚባለው ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ በተሻለ ደረጃ የሚታሰሩበት እና ከዚሁ የተነሳ በሌስሊ ኣባባል «ሸራተን» ተብሎ የሚታወቀው ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከተፎካካሪው የናይጀሪያ ብሔራዊ ቡድን ጋ በአዲስ አበባ ስታዲየም ግጥሚያ ያካሄደው ባለፈው እሁድ ዕለት ነበር። ይህንኑ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ዋና ምክንያት በማድረግ ወጣቱ ያሳየዉ ሥነ ምግባር በዛሬው የወጣቶች ዓለም ባጭሩ እንቃኛለን።

ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደዉ የዓመቱ የመጀመሪያ ስብሰባዉ አዲሱ ፕሬዝደንት ባለፈዉ ሳምንት ባቀረቡት የዓመቱ የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛው ምህፃር «ፍሮንቴክስ» የተባለው ለአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የድንበር ጥበቃ ድጋፍ ሰጭ ድርጅት ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በጀልባ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞችን በመመለስ የደረሰበትን ወቀሳ አመነ ።

በእንግሊዘኛው ምህፃር FRONTEX የተባለው ለአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የድንበር ጥበቃ ድጋፍ ሰጭ ድርጅት ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በጀልባ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞችን በመመለስ የደረሰበትን ወቀሳ አመነ ።

በዓሉ የሚከበረው ነቢዩ ኢብራሂም ልጃቸውን ለመስዋዕት ያቀረቡበትን ዕለት ለማሰብ ነው፡፡ በዓለም ዙርያ የሚገኙ የዕምነቱ ተከታዮች በአንድነት በመሆን በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች የአረፋን በዓል አክብረዋል ።

ዉርሰ ኢትዮጵያ የተሰኘዉ ድርጅት ሰሞኑን በጀርመኗ ታሪካዊት ከተማ ጎታ 16ኛዉን ዓመታዊ ጉባኤዉን አካሂዷል። ጎታ ኢትዮጵያዉ አባ ጎርጎርዮስና ጀርመናዊዉን ሂዮብ ሉዶልፍን ከሶስት መቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት ያስተናገደች ከተማ ናት።

የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የሃገሪቱን የበጀት ጣሪያ ከፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ስምምነት ትናንት ማታ ካፀደቀ በኋላ ለ16 ቀናት የተዘጉት የተወሰኑ የፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ዛሬ ሥራ ጀምረዋል ። የሃገሪቱ የበጀት ጣሪያ ከፍ እንዳይል ሲሟገቱ የቆዩት ወግ አጥባቂ ሪፐብሊካኖች ውሳኔውን ሊያስቀሩት ባለመቻላቸው ሽንፈታቸውን አምነዋል ።

በዩናይትድ ስቴትስ የመንግሥት በጀት ሳይፀድቅ ሣምንታት መቆጠሩ በሀገሪቱ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያስከትለው ተፅዕኖ ምን ይመስላል? የዛሬው የኢኮኖሚው ዓለም መሰናዶዋችን የሚያተኩርበት ርዕስ ነው።

«እዉቀት ለነገ» በሚል መርህ ከስድሳ የሚበልጡ ከሰሃራ በታች የሚገኙ አፍሪቃዉያት ሀገራት ምሁራንን ጭምር ያሳተፈ የሁለት ቀን ጉባዔ ጀርመን ሃኖቨር ከተማ በሚገኘዉ የፎልክስቫገን ተቋም ተካሂዶአል። ጉባዔው በአፍሪቃ በማህበራዊ፤ በሳይንስ፤ በህክምና፤ እንዲሁም በሃይማኖት ረገዶች በሚደረገዉ ሳይንሳዊ ምርምር ሥራ ላይ ተወያይቶአል፤

ዚምባቡዌ ላይ የአደንዛዥ እፅ ዝዉዉርና አጠቃቀምን አስመልክቶ የሚካሄደዉ ጉባኤ፤ መሪዎቹ ወሳኝ ርምጃ ካልወሰዱ የአህጉሩን መረጋጋት ሊጎዳ እንደሚችል አመለከተ። የምዕራብ አፍሪቃ የኤኮኖሚ ማኅበረሰብና በተመድ የእፅ ተከታታይ ጽ/ቤት አፍሪቃ ዉስጥ ሕገ ወጥ የአደንዛዥ እፅ ዝዉዉርን ለመግታት የሚያስችል አዲስ ርምጃ ላይ እየመከሩ ነዉ።

የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት በዓለማችን ከስምንት መቶ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ እየተራበ የሚታየዉ የምግብ ብክነት ተቀባይነት እንደሌለዉ አመለከተ። ድርጅቱ ዛሬ ይፋ ባደረገዉ ዘገባዉ የምግብ ማጣት ብቻ ሳይሆን የተመጣጠነና በቂ ምግብ አለማግኘት አካላዊ እድገታቸዉ ለእድሜያቸዉ የማይመጥን ልጆች ቁጥርም 165 ሚሊዮን መድረሱንም አስታዉቋል።

ዘንድሮ በተካሄደው የጀርመን ምክር ቤት አባላት ምርጫ ከሻነፉት ተወዳዳሪዎች መካከል አንድ አፍሪቃዊ ጀርመናዊ ይገኙበታል ። በዘንድሮው ምርጫ የምክር ቤት መቀመጫ ለማግኘት የበቁትን አፍሪቃዊ ጀርመናዊ የህዝብ እንደራሴን ጨምሮ የውጭ ዝርያ ያላቸው የጀርመን ምክር ቤት አባላት ቁጥር ከፍ እያለ ነው ።

የወባ በሽታን ለመከላከል የሚረዳ ክትባት የመገኘቱ ዜና በተለይ በበሽታዉ ክፉኛ ለሚጠቁ ሀገራሃት ታላቅ የምስራች ነዉ። የወባ በሽታን ጨርሶ ለማጥፋት ግን ዘመናትን የሚጠይቅ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ።