የምሥራቅ ኮንጎ ውጊያ ማብቃት
የዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ መንግሥት እና አማፅያኑ «ኤም 23» ቡድን በምሥራቃዊ የሀገሪቱ አካባቢ የሚያካሂዱትን ውጊያ ለማብቃት በካምፓላ ዩጋንዳ ከብዙ ወራት ወዲህ የጀመሩት ድርድር ካለውጤት በተበተነበት ባሁኑ ጊዜ የኮንጎ ጦር በአማፅያኑ ላይ ሙሉ ድል ተቀዳጅቶዋል።
የዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ መንግሥት እና አማፅያኑ «ኤም 23» ቡድን በምሥራቃዊ የሀገሪቱ አካባቢ የሚያካሂዱትን ውጊያ ለማብቃት በካምፓላ ዩጋንዳ ከብዙ ወራት ወዲህ የጀመሩት ድርድር ካለውጤት በተበተነበት ባሁኑ ጊዜ የኮንጎ ጦር በአማፅያኑ ላይ ሙሉ ድል ተቀዳጅቶዋል።
ባለፈዉ ሰሞን የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ኮርፕሬሽን ከአንድ የዉጭ ኩባንያ ጋር ከከርሰ ምድር እንፋሎት ኃይል ለማመንጨት እና ከእንፋሎት የሚገኝን የኤሌትሪክ ኃይል ጥቅም ላይ ለማዋል ተስማምቷል። የመሬት ዉስጥ የእንፋሎት ኃይል ምንጭ ምንድን ነዉ?
የነፃ ትምህርት እድል አግኝተው በመጡባት ጀርመን ሲኖሩ ከ27 ዓመት በላይ ሆኗቸዋል ። የግብርና ውጤቶችን የምግብ ይዘትና ጠባይ አጥንቶ ለምግብነት ማዘጋጀት የሚያስችል ትምህርት ነው ያጠኑት ። የተማሩትም በበርሊኖቹ አሌክሳንደር ሁምቦልትና የቴክኒክ ዩኒቨርስቲዎች ነው ። ዶክተር አየለ ጉግሳ ይባላሉ
በዓለም ላይ 80 በመቶዉ የሚሆነዉ የማህፀን በር ካንሰር ተጠቂ የሚገኘዉ አዳጊ ሃገራት ዉስጥ መሆኑን ጥናቶች ያመለክታሉ።
የጀርመን አየር መንገድ የሆነው ሉፍታንዛ ከፍራንክፈርት ከተማ ወደ አስመራ ኤርትራ በረራ ካቋረጠ ሳምንት አንዳለፈው አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እስካለፈዉ ሳምንት ድረስ ባደረገዉ ጉባኤዉ የተለያዩ ዉሳኔዎች አሳልፏል።የቤተ-ክርስቲያኒቱ መሪዎች እንዳስታወቁት ለአስራ-አንድ ቀናት የተደረገዉ ጉባኤ ያሳለፋቸዉ ዉሳኔዎች የቤተ-ክርስቲያኒቱን አሠራራር ለማሻሻል የሚጠቅሙ ናቸዉ።
ሮም የታተመ የኢጣሊያ ጋዜጣ እንደዘገበዉ የሶሪያ ስደተኞችን እንረዳለን የሚሉ ሐይላት ከዘጠና አምስት ስደተኞች ላይ መቶ ሺሕ ዩሮ የሚያወጣ ወርቅ፥ሌላ ጌጣ ጌጥና ገንዘብ ዘርፈዋል።ዶን ሙሴ ዘርዓይ እንዳሉት ደግሞ አዉሮጳ የሚገቡ ስደተኞችን እንረዳለን የሚሉ፥ በተለይ የሚያስተረጉሙ ኤርትራዉን የስደተኞቹን ሚስጥር ለኤርትራ መንግሥት አሳልፈዉ ይሰጣሉ
የአሜሪካንን ምስጢራዊ መረጃዎች ያጋለጠው የቀድሞው የአሜሪካን የስለላ ድርጅት ባልደረባ ኤድዋርድ ስኖውደን፤ ባለፈዉ ሳምንት ሐሙስ ከታዋቂዉ የጀርመን ፖለቲከኛ ጋር ሞስኮ ላይ ሲገኛኝ ጀርመን ሁኔታዎችን ካመቻቸችለት በጀርመን ምክር ቤት ተገኝቶ ስለ አሜሪካ የስለላ ጉዳይ በግልፅ ለመናገር እንደሚፈልግ መናገሩ ይታወቃል።
የዕለቱ ዜና
የእስራኤል መንግሥት ከኢትዮጵያ የመጨረሻ ያላቸውን ተጓዞች ናቸው ባለፈው ነሐሴ 28 2013 ሀገሩ አስገብቶዋል። እሥራኤል እነዚህኑ አዲስ ገቦችን በተለያዩ የሀገሪቱ ከፊሎች ባዘጋጀቻቸው የመጠለያ ጣቢያዎች ያሰፈረች ሲሆን፣
የኢትዮ ምሕዳር ዋና አዘጋጅ ጌታቸው ወርቁ እና ዋና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ሚልዮን ደግነው በኦሮሙያ ፖሊስ ለገጣፎ ውስጥ ታሰሩ። ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር እንደገለጸልን፣ ጋዜጠኛ ሚልዮን ባለፈው ቅዳሜ፣
የጋራ ማሕበር ለመመስረት የተስማማሙት ፖለከኞች እንደሚሉት የመጨረሻ አላማቸዉ ቢቻል ሁሉንም በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ተቃዋሚዎችን ይሕ ቢቀር ሰላሳ ሰወስት ፓርቲዎችን አስተባብሮ አንድ ጠንካራ ተቃዋሚ ጎራ ለመፍጠር ነዉ።ይሕ ምናልባት ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት በተቃዋሚዉ ጎራ የሚታየዉን መከፋፋል፥ መሰነጣጠቅና መጠላለፍ ለማስቀረት ይረዳ ይሆን?
የዕለቱ ዜና
ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በደሴቲቱ ማዳጋስካር ከዘጠኝ ቀናት በፊት የተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የመጀመሪያ ውጤቶች እንዳሳዩት፣ በተወዳዳሪነት ከቀረቡት 33 ዕጩዎች መካከል አንዱም ለድል የሚያበቃውን ድምፅ ባለማግኘቱ በሀገሪቱ እአአ የፊታቸን ታህሳስ ፣ 2013 ዓም ሁለተኛው ዙር ምርጫ ይደረጋል።
የዕለቱ ዜና
በበርካታ አዝናኛ መነባንቦቹ የሚታወቀው ኢትዮጵያዊው አርቲስት አብርሃም አስመላሽ አረፈ ። አርቲስት አብርሃም ላለፉት 3 ወራት በኑርንበርግ ጀርመን በህክምና ሲረዳ ነበር ።
አርቲስት አብርሃም አስመላሽ ለበርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ ራድዮ የቅዳሜ መዝናኛ ዝግጅት ልዩ ልዩ ማህበራዊ ጉዳዮችን አዋዝቶ በሚያቀርብበት ተወዳጅ መነባንቦቹና ጭውውቶቹ ይታወቃል ።
ትላንት ዘሄግ ኔዘርላንድ ውስጥ ያስቻለው ዓ/ዓቀፉ የወንጀል ፍ/ቤት በኬኒያው ፕ/ት ኡሁሩ ኬኒያታ ላይ የተያዘውን የክስ ሂደት እስከሚቀጥለው የካቲት ወር ድረስ ለሶስት ወር ማራዘሙን ኣስታወቀ። የኣፍሪካ ህብረት ግን በቂ ኣይደለም እያለ ነው።
እንግዳችን የኤሌክትሪላል ኢንጂነሪንግ ምሩቅ ነው። በተማረበት ሙያ ሥራ አግኝቶ ነበር ይሁንና በፍላጎት ወደ ንግድ ሥራ ነው የገባው። ለምን? ስለዚህ ወጣት ማንነት እና ከሌሎች አራት ባልደረቦቹ ጋ ተደራጅቶ ስለሚሠራው ያስረዳናል።
እስከ ተነ ገወዲያ የሚቀጥለው ይኽው ጉባኤ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከልና በመግታት ላይ ያተኩራል
የዓለም ዜና
በአዲስ ግንኙነት ዓለምን መቀየር በሚል መሪ ሃሳብ በታላቋ ብሪታንያ ዋና ከተማ ሎንዶን ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየዉ የዘጠነኛዉ የዓለም ዕስልምና ምጣኔ ሃብት መድረክ ዛሬ ተጠናቋል።
ኣንዲት የጉዲፈቻ ልጃቸውን ኣሰቃይተው ለሞት ያበቁ ባልና ሚስት አሜሪካውያን ከ28 እስከ37 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተፈረደባቸው።
« በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያዊ ሕጻናት ስሞችን ስንመለከት በአብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ ይዘት እንደሌላቸዉ እንረዳለን፤ አብዛኞች ስሞች ቅላጼያቸዉ ለጆሮ እንዲጥሙ እንጂ ፤ ታሪኩ ምን ማለት ነዉ ብለን ጠይቀን ለልጆቻችን ስም ስንሰጥ አንታይም። ይህ ደግሞ የባህል ወረራ እንዳያመጣብን እሰጋለሁ» ያሉን
የዕለቱ ዜና
በዚምባቡዌ አቋርጠዉ ወደ ደቡብ አፍሪቃ ለመሻገር የሞኮሩ 38 ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች የዚምባቡዌን ድንበር ሲያቋርጡ ተይዘዉ በመታሰራቸዉ ለከፋ ችግር መጋለጣቸዉ ተነገረ።
አየር መንገዱ ወደ ፍራንክፈርት ጀርመን በረራ የጀመረበትን 55 ተኛ ዓመት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ፍራንክፈርት ውስጥ ባሰበበት ወቅት የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም እንደተናገሩት ድርጅታቸው 2025 በተሰኘው እቅዱ በርካታ ውጥኖቹን ተግባራዊ አድርጓል ።
አደጋው ከደረሰባቸው ጋዜጠኛ አንዱ ጌታቸው ወርቁ እንዳስታወቀዉ ለአደጋ የተጋለጡት የተሳፈሩበት ባጃጅ በሞተር ብስኪሌት በመገጨቱ ነዉ።የሃዋሳ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን የለውም መከሰስ ያለበትም ዋና አዘጋጁ ነው ሲሉ ጋዜጠኞቹ ያቀረቡትን ጥያቄ ዛሬ ከሰዓት ውድቅ አድርጓል።
በዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ ምሥራቃዊ አካባቢ «ኤም 23» በመባል በሚታወቀው የዓማፅያን ቡድን እና በመንግሥት መካከል ጥቃቱ ዛሬም መቀጠሉ ተገለጸ።
የዓለም ዜና
ተጣማሪ መንግሥት ለመመስረት ከአንድ ሳምንት በፊት መደራደር የጀመሩት የጀርመን ትላላቅ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤የክርስቲያን ዲሞክራቶች እና የክርስቲያን ሶሻል ህብረት ፓርቲዎች እንዲሁም የሶሻል ዲሞክራቶች ህብረት ፓርቲ ወደ መግባባት መቃረባቸው እየተነገረ ነው።
ሴይንት ጁድ ወይም ክርስቲያን የሚል መጠሪያ የተሰጠው ኃይለኛው አውሎ ንፋስ በሰሜን አውሮጳ ሀገራት የ13 ሰዎች ሕይወት አጠፋ፣ በሰዓት 120 ኪሎ ሜትር ፍጥነት የሚነፍሰው ዝናብ የቀላቀለው
ደቡብና ሰሜን ሱዳንን የምታወዛግበዉ የነዳጅ ሃብት ያላት ግዛት አብዬ ሕዝበ ዉሳኔ አካሂዳለች። ረዥም ጊዜ የተጠበቀዉ ይህ ታሪካዊ ህዝበ ዉሳኔ የግዛቷ ኗሪዎች የወደፊት እጣ ፈንታቸዉን ከሰሜን ወይም ከደቡብ ሱዳን ጋ እንመራለን ብለዉ እንዲመርጡ የሚያደር ይሆናል ተብሏል።
በደቡብ ክልል ጋሞጎፋ ዞን የቁጫ ወረዳ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ካልሆነ አንማርም በማለት ትምህርት አቋረጡ። ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንዲርቁ አነሳስታችኋል በሚል የተጠረጠሩ
በየዓመቱ በጎርጎሪዮሳዊዉ የዘመን ቀመር ኦክቶበር 24 የልጅነት ልምሻ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚታሰብበት ዕለት ነዉ። በአንድ ወቅት ይህ በሽታ ድንገት የያዛቸዉን ህጻናት የእድሜ ልክ መፃጉዕ አድርጎ እንደሚያስቀር በመታየቱ እጅግ የሚፈራ ነበር። ክትባቱ የዛሬ 58ዓመት ገደማ ተገኘና ስጋቱ ቀነሰ። አሁን ደግሞ ፈፅሞ ለማጥፋት ጥረቱ ቀጥሏል።
የዕለቱ ዜና
አሜሪካዊ እንደራሴና የሥለላ ጉዳይ አዋቂ ፔተ ሆክስትራን የሚያስደንቀዉ ግን የአሜሪካ ሰላዮች የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥትን ስልክን መጥለፋቸዉ አይደለም።የነፍሬድሪሽ ቁጣና ብስጭት እንጂ።ሆክስትራ እንደሚሉት ካስደነቀ-የሚያስደንቀዉ የጀርመን መሪ ሥልክ መጠለፉን ፍሬድሪሽ የሚመሩት የጀርመን የስለላ ድርጅት አለማወቁ ነዉ።
የኢትዮጲያ የንፋስ ማመንጫ አቅምን ወደ ስምንት ከመቶ ከፍ ያደርጋል የተባለውና 120 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪል ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው የአሸጎዳ የንፋስ ኃይል ማመንጫ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ተመረቀ።
በርካታ ንፁሐን የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል፤ አዳዲስ የጭካኔ ርምጃዎቹ ዜጎችን ፍርሃትና ስጋት ላይ ጥሏል። የናይጀሪያ መንግስት ጦር አሸባሪዉን ቡድን ቦኮ ሃራምን በተጠናከረ ኃይል እንዳያንሰራራ አድርጎ ለመምታት አልሟል። ምንም እንኳን በርካታ የፀጥታ ኃይሎች ለዚህ ተግባር ቢሰማሩም ቡድኑ አሁንም በጥቃቱ የብዙዎችን ህይወት እየቀጠፈ ነዉ።
ከ 3 ሳምንት በፊት ከሊቢያ በጀልባ ተሳፍረው ወደ ኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ በመጠጋት ላይ ከነበሩ 500 ያህል ኤርትራውያን ከሚያመዝኑባቸው ስደተኞች የ364 ቱ ህይወት ያለፈበት አደጋ በሜዴትራንያን ባህር ላይ እስከ ዛሬ ከደረሱት የሞት አደጋዎች እጅግ የከፋው ነው ።
በሞዛምቢክ እአአ ከ1976 እስከ 1992 ዓም በገዢው ፓርቲ ፣ ፍሬሊሞ እና በተቀናቃኙ ሬናሞ መካከል የተከሄደው የርስ በርስ ጦርነት ካበቃ ከ21 ዓመት በኋላ በቀድሞዎቹ ተቀናቃኝ ወገኖች መካከል ውጥረቱ እንደገና እየተካረረ መጥቶዋል።
አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች የኢትዮጵያ መንግስት ለቤት ሠራተኝነት ዜጎች ወደስዑድ አረቢያ እንዳይሄዱ ማገዱ ትክክል አይደለም እያሉ ነዉ።
ኢትዮጵያ ውስጥ አጋጣሚዎች ካልፈቀዱ በስተቀር ከቤተሰብ ተለይቶ መኖር ብዙም አልተለመደም። ከነዚህ ከአጋጣሚዎች አንዱ ወጣቶች ለዮንቨርስቲ ትምህርት ወደ ሌላ ከተማ ተመድበው ሲሄዱ ነው።
የአዉሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት መሪዎች ከትናንት ከቀትር በኋላ አንስቶ እስከዛሬ ያካሄዱትን የሁለት ቀናት ጉባኤ አጠናቀቁ።
የጀርመን መራሂተ-መንግስት አንጌላ ሜርክል የእጅ ስልክ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የስለላ ተቋም ተጠልፏል የሚለዉ ዜና እያነጋገረ ነዉ። ዩናይትድ ስቴትስ ድርጊቱን እንዳልፈፀመች በመጥቀስ አስተባብላለች። ጉዳዩ በአውሮጳ መሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶታል።