ባለፈው ሳምንት የአገራችንን ፖለቲካ ለመረዳትም ይሁን ወደ ፊት ለማራመድ ከሚያስፈልጉን ነገሮች አንዱ አዲስ የርእዮተ ዓለም ትንተና መሆኑን ጠቆም አድርጌ ነበር። ይህ የመረዳት ፍለጋ ብዙ ተያያዥ ጥያቄዎችን እንዳነሳ አድርጎኛል። የዛሬው ትኩረቴ በፖለቲከኞቻች በኩል ፖለቲካችንን መረዳት ነው፤ ፖለቲከኞቻችንን መተቸት ብቻ ሳይሆን መረዳት …

[አንድ ለቅዳሜ] ስለ ፖለቲከኞቻችን ምን ይነበባል? እነርሱስ ምን ያነባሉ? Read more »

ግሩም ኤርምያስ በብሔራዊ ቴአትር በተካሄደው በ5ኛው የኢትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል በምርጥ ተዋናይ አሸናፊ በረዥሙ የሚዘረጋ ቀይ ምንጣፍ ከዚህ የለም። በቀይ ምንጣፍ ዳር እና ዳር የተኮለኮሉ አድናቂዎች እና ወፈ ሰማይ ፎቶግራፍ አንሺዎችም በቦታው ላይ አይታዩም።  በእውቅ ሰዎች አለባበስ እና በሚከተሉት ፋሽን ላይ …

የኢትዮጵያ “ኦስካር” ምሽት Read more »

“… ለምሳሌ በ1938 እኤአ የእንግሊዝ ንጉሥ እና የእንግሊዝ ንግሥት በኦፊሺያል ግብዣ ለጉብኝት ፓሪስ መጥተው ተሌሎች አምባሳደሮች ጋር እኔም ተጠርቼ ሔጀ ነበር። በፕሮቶኮሉ ደምብ የኢትዮጵያ እና የጣሊያን ጉዳይ ፈጻሚ አቀማመጣቸው ጎን ለጎን ስለነበረ፤ አጠገቡ በምኾንበት ጊዜያት ጣሊያኑ በጣም ሲቆጣ እኔም ኀይለቃል …

የአክሊሉ ሀብተወልድ ታሪክ ሌላ የኀዘን ትዝታ Read more »

(ሙሉ ገ.) የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን) ፓርቲ ለስድስት ዓመት በፕሬዝዳንትነት የመሩትን አቶ ቡልቻ ደመቅሳን ከፓርቲው የበላይ አመራርነት በክብርና በምስጋና አሰናበተ፤ ምክትላቸው የነበሩትን ዶክተር ሞጋ ፍሪሳን ደግሞ በፕሬዝዳንትነት ሾሟል፡፡ እሁድ ህዳር 26 ቀን 2003 ዓ.ም በአዲስ አበባ  ኢየሩሳሌም ሆቴል በተካሄደው …

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከኦፌዴን አመራርነት ተሰናበቱ፤ ዶክተር ሞጋ ፉሪሳ በፕሬዚዳንትነት ተሾሙ Read more »

የአገር ቤት ጋዜጦች የወረቀት ዋጋ ሲወፍር እነርሱ ይቀጭጫሉ፡፡ ኑሮ ሲንር እነርሱ ይከስማሉ፡፡ ለወራት ያህል ሲንገታገት የቆየው ሳምንታዊው አዲስ ፕሬስ ጋዜጣ በመጀመርያ አካባቢ ተጣጣረ፤ ወደ በኋላ ላይ አንድ ሳምንት እያረፈ በመውጣት አጣጣረ፡፡ በመጨረሻም ብዕሩን ሰቀለ፡፡ አዲስ ፕሬስ ላለፉት ተከታታይ ሳምንታት በአገር …

የአገር ቤት ጋዜጦች ምን ጻፉ Read more »

(ይህ ጽሑፍ ደረሰ ጌታቸው ካስነበበን መጣጥፍ ጋራ ተያይዞ ሊነበብ የሚችል ነው። ሐሳቡ ቀደም ሲልም ሲብላላ የነበረ ቢሆንም የደረሰ ጽሑፍ አንዳች ነገር እንድል አነሳስቶኛል። እንደ ወጉ ቢሆን እኔም በእንግሊዝኛ መጻፍ ነበረብኝ፤ ሆኖም ቢያንስ “አንድ ለቅዳሜ” በአማርኛ ብቻ እንድትጻፍ የተሠራውን ስርአት ማክበር …

[አንድ ለቅዳሜ] የአዲስ ርእዮተ ዓለማዊ ትንተና ጅማሮ Read more »

ነፍሰ ጡር በቃሬዛ ተሸክሞ አዋላጅ ፍለጋ ብዙ ማይል ማቋረጥ እና መንከራተት ዛሬም በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ያልተነካ እና ያልተቀረፈ ችግር ነው። የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞችን በሰፊው እያሰማራሁ ነው የሚለው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገና ያልደረሰባቸው እና መፍትሄ ያላገኘላቸው የኤችአይቪ እና የወባ በሽተኞች ቁጥርም ቀላል …

ነርሶችን የምትገፋም “የምትሸጥም” አገር Read more »

(ሙሉ ገ.) በአዲስ አበባ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ እሁድ ዕለት ሕዳር 19 ቀን 2003 ዓ.ም በተካሄደው የኢህዴን (ብአዴን- ኢሕአዴግ) 30ኛ ዓመት ዝክረ በዓል ማጠናቀቂያ ላይ የተተኮሱ ርችቶች የአዳራሹን ጣራ በእሳት በማያያዛቸው ምክንያት በተፈጠረ ድንገተኛ ድንጋጤ በርካታ ሰዎች የመረጋገጥ እና የመጋጋጥ አደጋ …

በብአዴን-ኢሕአዴግ 30ኛ ዓመት ዝክረ በዐል ላይ በርችት ምክንያት በተነሳ እሳት በሰዎች ላይ የመጋጋጥ እና የመረጋገጥ አደጋ ደረሰ Read more »

What do Americans diplomats think about Meles Zenawi? This week the American embassy in Addis Ababa briefed government officials about the Wikileaks release(which just came out). According to my sources, these state department documents(a lot of which are classified, secret …

Leaked Documents Show Unflattering Assessment of Meles Zenawi Read more »

(አሮን ፀሀዬ) ኤደን ቤቲና ሜላት ገፀ-ባሕርያት አይደሉም፡፡ የገናናው ኀይሌ ገብረ ሥላሴ ሴት ልጆች ናቸው፡፡ በአመዛኙ በእናታቸው ነው የወጡት፡፡ ሲበዛ ቆንጆ ናቸው፡፡ ቀያይ ናቸው፡፡ ፈረንጅ ነው የሚመስሉት፡፡ በዚያ ላይ አማርኛ ይከብዳቸዋል፡፡ እንግሊዝኛ  ይቀናቸዋል፡፡ ከሶስቱ ሴት ልጆቹ መሀል ሁለቱ የመስቀል በዓል ሲከበር …

የኤደን ፣ የቤቲ እና የሜላት አማርኛ Read more »

ከሁለት ዓመት በፊት፤ ዝነኛው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ “ስታፍ ላውንጅ”። በወቅቱ ከሥራዬ በተጨማሪ የዩኒቨርሲቲው የድኅረ ምረቃ ተማሪ ስለነበርኩም ጭምር ከግቢው አልጠፋም ነበር። በንባብና በመጻፍ መካከል የቡና እረፍት ለማድረግ ስታፍ ላውንጅ እንደገባሁ በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ወደ ተቀመጡት መምህራን እንድቀላቀል የተሰጠኝን የግብዣ ምልክት …

[አንድ ለቅዳሜ] የአደባባይ ምሑራኑ የት ገቡ? Read more »

(ሙሉ ገ) በምግብ እጥረት ለተጎዱ ዜጎች ከምግብ እርዳታ ውጪ 20 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የእርዳታ ድጋፍ ያስፈልገኛል ሲል የግብርና ሚንስቴር ለለጋሽ አገሮች እና ለእርዳታ ድርጅቶች አስታወቀ። ህዳር 15 ቀን 2003 ዓ.ም በቀድሞው አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኤጀንሲ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ በ10፡00 ሰዓት …

በምግብ እጥረት ለተጠቁ ወገኖች 20 ሚሊዮን ዶላር ርዳታ ተጠየቀ Read more »

መሐመድ ሰልማን ይህንን ጽሑፍ ስንጀምር እንደብዙዎቹ የጂኦግራፊ ትምህርቶች በ“ዴፊኒሽን” ስላልጀመርኩልህ ይቅርታ እጠይቅኻለሁ፡፡ ፒያሳ የሚለው ቃል የመጣው ከአውሮፓ አህጉር፣ ከጣልያን አገር ሮም ከሚባል ሰፈር ሲሆን ትርጉሙም ‹‹አደባባይ›› ወይም ‹‹ማእከል›› እንደማለት ነው፡፡ ይህ ቃል በአገራችን የትግርኛ ተናጋሪዎች ዘንድም እንደሚታወቅ ስነግርህ በታላቅ ኩራት …

ማሃሙድ ጋ ጠብቂኝ! [ክፍል ሦስት] Read more »

ፍትህ ጋዜጣ እና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ ፍትህ፡- ብርቱካን ከፓርቲያችሁ ለቀቀች እንዴ? እረፍቷ አልበዛም? ወይስ ማለቂያ የሌለው እረፍት ነው? አቶ አንዱዓለም፡- ብርቱካን ያሳለፈችው መከራ ብዙ ነው፡፡ የበርማ ጄነራሎች እንኳ ሳንሱኪን ያሰሩበት ኹኔታ ከብርቱካን ጋር አይነጻጸርም፡፡ የብርቱካን የከፋ ነው፡፡ የእኛ መሪ ተብዬዎች …

የአገር ቤት ጋዜጦች ምን ጻፉ? Read more »

(ሙሉ ገ.) ቅዳሜ ህዳር 4 ቀን 2003 ዓ.ም ብዙነሽ ብርሃኑ የተባለች የሦስተኛ ዓመት የታሪክ ዲፓርትመንት ተማሪ በዋናው ዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ አድራ ወደ አዲሱ ሰመራ ካምፓስ ከ15 እስከ 20 ደቂቃ የሚያስጉዘውን መንገድ ስታቋርጥ ዋለሜ በተባለው ወንዝ ውስጥ ሰጠመች። ይህንኑ የመስጠም አደጋ …

በዲላ ዩኒቨርስቲ በተቀሰቀሰ ሁከት ተመሪዎች ተጎዱ Read more »

(ኤርሚያስ አማረ) “የአባቴ መልካም ታሪኮች ብዙ ናቸው፤ ቢያንስ ጥቂቶቹ ሊነገሩለት እና በትክክለኛው መንገድ ሊቀርቡለት በተገባ …” ይህን ያሉት የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ ልጅ አቶ ታደለ ይድነቃቸው ናቸው። በደቡብ አፍሪካ የተዘጋጀውን የዓለም ዋንጫ ምክንያት አድርጎ የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጋዜጠኛው እስክንድር ፍሬው ካቀረበላቸው …

እንዲደበዝዝ የተፈረደበት የይድነቃቸው ተሰማ ታሪክ Read more »

(ሙሉ ገ) በአቶ ኩማ ደመቅሳ የሚመራው የአዲስ አበባ መስተዳድር በ2003 ዓ.ም የበጀት ዓመት የዲግሪ ምሩቃንን በመቅጠር በዐሥሩም ክፍለ ከተሞች ልዩ ልዩ የሥራ ዘርፎች ላይ በመመደብ እና በቦታው ላይ ብቃት ጎደላቸው ባላቸው ሠራተኞች ምትክ ብቁ የኾነ የአሠራር ለውጥ ለማምጣት በቢፒአር አስጠንቶ …

አዲስ አበባ መስተዳደር በቢፒአር አስጠንቶ ተግባራዊ አድርጋለሁ ያለውን መርኀ ግብር አጠፈ Read more »

የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሽግግር በብዙ መልኩ ከማይላወስበት ቅርቃር ውስጥ ገብቷል። መሠረታዊ ፖለቲካዊ ተሐድሶ (Political Reform) እንደሚያመጣ ተስፋ የተጣለበት ኢሕአዴግ በቀዳሚዎቹ ዓመታት ያደረጋቸውን ለውጦች ሳይቀር መልሶ እያጠፋ በኋላ ማርሽ መጓዝን መርጧል። በአጠቃላይ ሲታይም ኢትዮጵያ አዲስ የፖለቲካ ተሐድሶ እንደሚያስፈልጋት ግልጽ ነው። አሁን ለመወያየት …

[አንድ ለቅዳሜ] የፖለቲካ ተሐድሶን ፍለጋ Read more »

የማኅደረ ጊላይ የለጋነት ዕድሜ እንዲሁ እንደ ዐይን ጥቅሻ እያለፈ ነው። ወደ ኋላ ተመልሶ ሲያስብ ደስ የሚል ነገር ትዝ አይለውም።ሕይወት ልክ ከማለዳ ጣፋጭ እንቅልፍ እንደሚያባንኑት አስፈሪ የልጅነት የተረት ጭራቆች የተሞላች ትመስለዋለች::  ተረት የሚመስሉ ታሪኮችን እየኖረ፣ እየሰማ እና እየታዘበ እዚህ ደርሷል። መባረር፣ …

በ”አምቼዎች” ዓለም ውስጥ፡ ፖለቲካ ፣ ማንነት እና ስደት Read more »

(ሙሉ ገ.) በአቶ በረከት ስምዖን የሚመራው” የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት” በመንግሥት ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ የሚሠሩ አርታኢያንና ፕሮግራም አስፈፃሚዎች  የኢትዮጵያንና የመንግሥት ገጽታን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚያበላሹ ዘገባዎችን ንቁ ሆነው እንዲቆጣጠሩ የሚያዝ አዲስ መመሪያ አስተላለፈ፡፡  ከኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በቀጥታ የወረደው አዲስ መመሪያ ይበልጡኑ …

“ገጽታን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚያበላሹ ዘገባዎች” በመንግሥት ሚዲያዎች እንዳይተላለፉ ለፕሮግራም አስፈጻሚዎች ብርቱ መመሪያ ተሰጠ Read more »

ሙሉ ገ. ኢሕአዴግ በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ እና ነገ “ከፍተኛ የኾነ ሕዝባዊ ንቅናቄ እና ውይይት” ማከሄድ ጀመረ። በዚሁ “ሕዝባዊ ንቅናቄ” ላይ የአምስት ዓመቱን የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለሕዝቡ ለመስበክ የኢሕአዴግ ካድሬዎች ክፍተኛ የኾነ ርብርብ ሲያደርጉ መሰንበታቸውንም የአዲስ ነገር የአዲስ አበባ …

የአምስት ዓመቱን የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለመስበክ ዛሬ እና ነገ “ሕዝባዊ ንቅናቄ” ይካሄዳል Read more »

ኢሕአዴግ የምርጫ 2002 እፍረቱን ለማረሳሳት (ሊረሳ የሚችል ከሆነ) ብዙ ሙከራዎችን ማድረግ ነበረበት። የመጀመሪያው እና ትልቁም “የእድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ” ተብሎ የቀረበው ሰነድ ነው። ዕቅዱ በይዘቱም ሆነ በቅርጹ ሰፊ የሐሳብ ልውውጥን የሚጋብዝ ነው። እስካሁን በብዛት ትኩረት የተሰጠው ግን ዕቅዱ ሊሳካ የሚችል …

[አንድ ለቅዳሜ ] ሥልጣን እንጂ ተጠያቂነት የሌለበት “የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ” Read more »

(አሮን ፀሐዬ) የገጠር የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ነኝ፡፡ መታወቂያዬ ላይ ከስሜ ትይዩ “ሌክቸረር” የሚል ማዕረግ አለበት፡፡ ኑሮ እና ሕይወቴ ግን ማዕረግ አልባ ነው፡፡ ደሞዜ ሁለት ሺሕ ስድስት መቶ ብር ይደርሳል፡፡ ይህ ብር ግርማ ሞገሱ አፍ ይሞላል፡፡ ሲኖሩበት ግን ወፍ ነው፤ ይበራል፡፡ እውነት …

ዲቪ እና CV Read more »

(ሙሉ ገ) ለሸራተን ሆቴል ማስፋፊያ ፕሮጀክት ከአካባቢያቸው የሚፈናቀሉ ከአምስት ሺሕ በላይ የሚኾኑ አባወራዎች ባለ ሀብቱን ሼህ ሑሴን  ሙሐመድ አላሙዲንን እና መንግሥትን በምትክ የካሳ ክፍያ ጉዳይ ላይ ኢ-ፍትኀዊ አሠራር እንዳይኖር ለመለመን ከሸራተን ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው አነስተኛ ሜዳ ላይ ሊያደርጉት የነበረው …

ሸራተን ሆቴል ፊት ለፊት ሊደረግ የነበረው ሰላማዊ ምልጃ በመንግሥት የደኅንነት ሠራተኞች እና በፌዴራል ፖሊስ አባላት ተበተነ Read more »

(መሀመድ ሰልማን) ዶሮ ማነቂያ በዶሮ ማነቂያ ዶሮ አይታነቅም፡፡ ሰው ግን ይታነቃል፡፡ለምሳሌ ኑሮ አልሞላ ሲለው፤ ወይም ዶሮ እጅግ አምሮት መግዣ ሲያጣ… ኑሮን ቀለል አድርገው መኖር የሚሹ ዜጎች ዶሮ ማነቂያን ይመርጣሉ፡፡ አንተም ኪስህ ቢነጣ፣ መሄጃ ብታጣ ፒያሳ እንደ ቦሌ “ሂድ ከዚህ!”  ብላ …

“ማሃሙድ ጋ ጠብቂኝ!” [ክፍል ሁለት] Read more »