የኤርትራ ቢሻና ማይ እንደጋ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ዲፖዎች ጥቃት ደረሰባቸው::

– ጥቃቱ የውስጥ አሻጥር ይሁን የሚሳኤል አሊያም የተፈጥሮ ጥቃት እስካሁን አለየለትም::

bisha-13 የኤርትራ የወርቅ ማእድን ማውጫዎች በጋሽ ባርካ ቢሻ እና ማይ እንደጋ ዴፖዎች ካልታወቀ (ካለየለት)ሃይል ጥቃት እንደተፈጸመበት ተሰማ::ጥቃት የተፈጸመባቸው ዲፖዎች አርብ ማርች 20 2015 በ4:30 ሲሆን ለረዥም ሰአታት ሲነዱ ነበር ተብሏል::ጥቃቱ የተፈጸመው ምናልባት በሚሳኤል አሊያም በሻእቢያ ተቃዋሚዎች የተቀነባበረ የውስጥ አሻጥር ይሆናል ተብሎ ሲገመት የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ ጥቃት ወደ ደረሰባቸው ዲፖዎች በመጓዝ የጎበኙ ሲሆን ጥቃቱ የውስጥ አሻጥር ይሁን የሚሳኤል አሊያም የተፈጥሮ ጥቃት እስካሁን አለየለትም::

ከዚሁ ዜና ጋር በተያያዘ በማርች 21 2015 የወጣው እና በሱዳን ውስጥ የሚታተመው አል ሳህፋ የተባለ ጋዜጣ የኢትዮጵያ የጦር አይሮፕላኖች ጥቃቱ አደረሱት ሲል መጻፉ ታውቋል::ጋዜጣው አክሎም ከአስመራ 150 ኪ ሜትር ርቀት ላይ ከፍተኛ ጭስ እና የ እሳት ነበልባል ይታይ እንደነበር ጽፏል::ጋዜጣው ጉዳዩ እንዴት እንዳያያዘው ባይታወቅም የኢትዮጵያ መንግስት በመጭው ምርጫ አትኩሮት ለማግኘት ያደረገው መሆኑን አል ሳህፋ ጽፏል::ሳሊና የተባለው የኤርትራ ድህረገጽ ጥቃቱ መድረሱን ጽፏል::አስመሪኖ ኮም በበኩሉ ዝርዝር ጉዳዩን ለማጣራት ቢሞክርም አልተሳካለትም::ጥቃቱ የውስጥ አሻጥር ይሁን የሚሳኤል አሊያም የተፈጥሮ ጥቃት እስካሁን አለየለትም::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) -i
More- http://www.satenaw.com/eritrea-ethiopian-planes-raided-bisha-goldmine/

The post የኤርትራ ቢሻና ማይ እንደጋ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ዲፖዎች ጥቃት ደረሰባቸው:: appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.