35 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በዕጣ ለዕድለኞች ተላለፉ 35 thousand condo units transferred to owners

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ10ኛው ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የማውጣት ሂደት 35 ሺህቤቶችን ባለ ዕድለኞች በዕጣ አስተላለፈ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ ያለውን የቤት ፍላጎት ለማርካት እያስገነባቸው ካት ቤቶች ከ95 በመቶ በላይ የተጠናቀቁትንና መሰረተ ልማት የተሟላላቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነው ለባለ ዕድለኞች ያስተላለፈው፡፡

በዕጣ የተላለፉት ቤቶች በባሻ ወልዴ፣ በልደታ መልሶ ማልማት፣በየካ አባዶ፣በቦሌ ቡልቡላ፣በገነት መናፈሻና በቱሉ ድምቱ ሳይቶች የሚገኙ ናቸው፡፡

እሁድ መጋቢት 13 ቀን 2007 በይፋ ለባለ ዕድለኞች የተላለፉት የጋራ መኖያ ቤቶች ለ140 ሺ ሰዎች መጠለያነት እንደሚያገለግሉ የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

በስነ ስርዓቱ ላይ 7 ሺህ የመንግስት ሰራተኞች ለመጀመሪያ ግዜ የ20 በመቶ እድል ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ዕጣ ወጥቶላቸዋል፡፡

የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ደሪባ ኩማ በስነ ስርኣቱ ላይ እንደተናገሩት በ10ዓው ዙር ዕጣ የወጣባቸውን ቤቶች ገንብቶ ለማጠናቀቅ 9 ነጥብ 4 ቢከሊዮን ብር ወጪ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በዚህም መንግስት የተጎሰቆለው 60 በመቶ የአዲስ አበባ ክፍል ለማደስ የሚያደርገውን ጥረት ተጨባጭ ለውጥ የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል፡፡

ቤቶቹ ከዚህም በለፈ መንግስት ከ10 እስከ 50 በመቶ ድጎማ ያደረጋበቸው በመሆናቸው የፍትሃዊ የሀብት ክፍፍሉ ማሳያ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

ቁጠባና የስራ ዕድል ፈጣራም የቤት ልማት ፕሮግራሙ እያመጣው ያለው ዘርፈ ብዙ የተቃናጀ ለውጥ መሆኑን የከተማ ልማት ፣ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚንስትሩ አቶ መኩሪያ ሀይሌ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜም 40/60 መርሃ ግብርን ጨምሮ 136 ሺህ ቤቶች እየተገነቡ መሆኑንም አቶ መኩሪያ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቤች ግንባታ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት በዚህ ዓመት 74 ሺ የሚደርሱ ቤቶችን በ3 ዙር ለነዋሪዎች እንደሚያስተላልፍ አስታውቋል፡፡

የ20/80 የቤት ዕድለኞች ዝርዝር

የ 20/80 የቤት ዕድለኞች ዝርዝር ክፍል 1

የ20/80 የቤት ዕድለኞች ዝረዝር ክፍል 2

የ20/80 የቤት ዕድለኞች ስም ዝርዝር ክፍል 3

የ20/80 የቤት ዕድለኞች ዝርዘር ክፍል 4

የ10/90 የቤት ዕድለኞች ዝርዝር

More Names

Not labeled 1

Not labeled 2

Not labeled 3

 

Watch Ethiopian movies legally. Upto 5 movies added daily. Here are the top 10 most viewed movies today.

Receive Ethiopian News, Movies and Videos by email. Sign up for Email alerts ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎችን፣ ድራማዎችን፣ሙዚቃዎችን፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በኢሜል አድራሻዎ እንልካለን። ኢሜሎን ያስመዘግቡ።