ባለፈዉ ሰኞ ከአዉሮፕላን የተጣለ ቦምብ መዝራቅ በተሰኘዉ መጠለያ ጣቢያ የተጠለሉ አርባ ስደተኞች ወይም ተፈናቃዮችን መግደሉ፤ ጦርነቱ ከተሳታፊዎቹ አልፎ የስደተኞችን ሕወት እያስገበረ መሆንኑ አረጋጧል።በጥቃቱ ከተገደሉት በተጨማሪ ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች ቆስለዋል።ከሟች ቁስለኞቹ መካካል ኢትዮጵያዉን እንደሚገኙበት አንዳድ ዘገቦች ጠቁመዉ ነበር።

ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ማረሚያ ቤት መውረዳቸው ተጠቁሟል የጣሊያን ዜግነት አላቸው የተባሉት ራንቺፍ ፎክቲዎሊ የተባሉ ግለሰብ፣ በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ዙርያ በሚገኝ ወላጅ አልባ ለሆኑና ለአካባቢው ልጆች የትምህርትና ዕርዳታ በሚሰጥ ድርጅት ውስጥ፣ በታዳጊ ወንድ ሕፃናት ላይ የግብረሰዶም በመፈጸም ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸውን የሪፖርተር ምንጮች አረጋገጡ፡፡ ተጠርጣሪው መጋቢት 17 ቀን 2007 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ውለው ሻሸመኔ 03 ፖሊስ ጣቢያ […]

The post ጣሊያናዊው በኢትዮጵያ ግብረሰዶም በመፈጸም ወንጀል ተጠርጥረው ታሠሩ – አሰግድ ታመነ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

አዲስ ቮይስ–የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤትና የሚኒስትሩ ዋና አማካሪ እንዲሁም የፖሊሲ ጥናትና ትንተና የበላይ ሃላፊ የሆኑት “ፕሮፌሰር” መኮንን ሃዲስ የሃሰት ፕሮፌሰር እደሆኑ አዲስ ቮይስ ባካሄደው እረዘም ያለ ምርመራ ማረጋገጥ ችሏል።። ግለሰቡ ለ15 አመታት በፕሮፌሰርነት አገልግየዋለሁ የሚሉት አንድ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ እንደማያውቃቸው የገለጸ ሲሆን የዶክትሬት ዲግሪ ያገኙበት ተቋምም በአሜሪካ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት “የዲፕሎማ ወፍጮ” (diploma mill) […]

The post የቴድሮስ አድሃኖም ዋና አማካሪ የሃሰት ፕሮፌሰር መሆናቸው ተረጋገጠ – አበበ ገላው appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

በአሁኑ ጊዜ ህገ ወጥ በሚባል መንገድ በአደገኛ ጉዞ አውሮፓ የሚደርሱ ስደተኞች በሙሉ አውሮፓን እንደጠበቋት ሆና አያገኟትም ።ከሞት ተርፈው ምድሪቱን ለመርገጥ ከበቁት መካከል ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠው አስከፊ ህይወት የሚገፉ ጥቂት የሚባሉ አይደሉም ። ህይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው በህገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ለመግባት የሚሞክሩ በርካታ አፍሪቃውያን ስደተኞች ካስቡበት ሳይደርሱ የበረሃና የውሐ ሲሳይ መሆናቸው ተደጋግሞ የሚነገር ጉዳይ ነው […]

The post አሳዛኙ የተገን ጠያቂዎች ይዞታ በፈረንሳይ – አሰግድ ታመነ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

-የወረዳ አስተዳዳሪና የፖሊስ አዛዥ በክሱ ተካተዋል አንዱ ወገን በሌላኛው ወገን ላይ የጦር መሣሪያ እንዲያነሳ በመስማማትና በሚያስከትለው የወንጀል ድርጊት ላይ ሙሉ በሙሉ ተካፋይ በመሆን፣ ከ55 በላይ የሌላ ብሔር ተወላጆችንና የፌዴራል ፖሊሶችን በመግደል ወንጀል የተጠረጠሩ፣ የደቡብ ክልል ቤንቺ ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ 18 ነዋሪዎች ላይ መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተ፡፡ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ […]

The post በደቡብ ክልል 55 የሌላ ብሔር ተወላጆችንና ፖሊሶችን የገደሉ 18 ተጠርጣሪዎች ተከሰሱ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

በቀልድ የታጀበው ምስክሮችን የመስማት ውሎ -የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ላይ
የኅሊና እስረኞቹ አጥናፍ፣ ማኅሌት፣ ዘላለም፣ በፍቃዱ፣ ናትናኤል፣ አቤል፣ ኤዶም፣ ተስፋለም እና አስማማው፡፡

ቀን አንድ (መጋቢት 21)

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆየው የማስረጃ መስማት ውሎ ዛሬ ምስክሮችን በማስማት ተጀምሯል፡፡ በዚህም መሰረት አቃቤ ህግ ጉዳዬን ያስረዱልኛል ያላቸውን 17 ምስክሮች ያስመዘገበ ሲሆን 15ቱ በፍርድ ቤቱ ተገኝተው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ አቃቤ ህግ ችሎቱ በዝግ ችሎት አንዲሆን የጠየቀ ሲሆን ምስክሮቼ እና የቤተሰቦቻቸውን ደህንነት ለመጠበቅ ችሎቱ በዝግ ሊሆን ይገባል የሚለውን አቤቱታውን ጠበቆች በከፍተኛ ደረጃ ተቃውመውታል፡፡ ምስክሮቹ የጭብጥ ምስክሮች ሳይሆኑ ፍተሻን የታዘቡ የደረጃ ምስክሮች በመሆናቸው እና ስማቸውም በግልጽ ተከሳሾች ጋር ስለደረሰ ምንም አይነት የደህንነተ ስጋት የለባቸውም ከሚለው የጠበቆች ክርክር በኋላ ፍርድ ቤቱ በጉዳዬ ላይ ተወያይቶ ለመወሰን ረፍት ወስዷል፡፡ በዚህም መሰረት የአቃቤ ህግን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ችሎቱ በግልጽ ሆኖ መስክሮች ምስክርነታቸውን እነዲያሰሙ ታዟል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አቃቤ ህግ ያቀረባቸው ምስክሮች አነማን ላይ አንደሚመሰክሩ እና ምን አንደሚመሰክሩ በተጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱም በጠበቆቹ ስለተነሱት ነጥቦች የአቃቤ ህግን ምላሽ ጠይቋል፡፡ አቃቤ ህግም በዛሬው ዕለት የቀረቡት ምስክሮች በ2ኛ፣ በ3ኛ፣ በ5ኛ፣ በ6ኛ፣ በ7ኛ እና 8ኛ ተከሳሾች ( በስድስቱ የዞን9 ጦማርያን ላይ እና በጋዜጠኛ አስማማው ላይ ) ላይ እንደሚመሰክሩ ገልጾ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቡድን በብርበራ ያገኛቸው ማስረጃዎች ከተከሳሾች የተገኙ ስለመሆናቸው ያስረዱልኛል ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
በምላሹም መሰረት የአቃቤ ህግ ምስክሮች ምስክርነታቸው ሰጥተዋል፡፡ ምስክርነታቸው ሲሰጡ በነበረበት ወቅት የተከሳሾችን ስም አለማወቅ አንዲሁም የተከሳሾችን መልክ አለመለየት የመሳሰሉት ጉዳዬች የተስተዋሉ ሲሆን ምስክርነታቸውን የሰጡት ሰዎች ስም ዝርዝር እና የምስክርነታቸው ጭብጥ በአጭሩ አንደሚከተለው ነው ፡፡
1.ሙሉጌታ መዝገቡ ለማ – ናዝሬት ነዋሪ ነኝ መአከላዊ ምርመራ ለግል ጉዳይ ሄጄ ፓሊስ ታዛቢ ምስክር አንድሆን ጠይቆኝ በዚያ መሰረት ምስክር ሆኜ ተገኝቻለሁ፡፡ ከአቤል ከኮምፒውተሩ ላይ ጽሁፍ ሲወጣ እና ሲፈርም አይቼ እኔም ፈርሜያለሁ ፡፡ የጽሁፉን ይዘት አላነበብኩም አንዳንድ ቦታ አፍሪካ ሪቪው ኬንያ የሚል ቃል አይቻለሁ የሚል ምስክርነት ሰጥተዋል፡፡
2.በለጡ አበበ ዮሴፍ ይባላሉ፡፡ እድሜያቸው 32 ሲሆን ከፍተኛው ፍርድ ቤት የካ ምድብ ሰራተኛ ናቸው፡፡ አዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆኑ በማን ላይ ለመመስከር እንደመጡ ሲጠየቁ በስም እንደማያስታውሱት ገልጸው በአካል ግን ለይተው አሳይተዋል፡፡ መስካሪዋ በ6ኛ ተከሳሽ ዘላለም ክብረት ላይ የሚመሰክሩ ሲሆን በተለየ ስም ሲጠሩት ተስተውለዋል
“የሽብርተኝነት ጉዳይ የሚያመለክት ይመስለኛል፡፡ ወደ 70 ገጽ አማርኛና 10 ገጽ እንግሊዝኛ ጽሁፍ ተገኝቷል፡፡ ያየሁትን አይቼ ፈርሜያለሁ፡፡” ካሉ በኋላ ተከሳሹስ ፈርሟል ተብለው ሲጠየቁ መጀመሪያ አላስታውስም ቢሉም እንደገና ሲጠየቁ ግን አዎ ፈርሟል ብለዋል፡፡
3.እታፈራሁ ጌታቸው ወልዴ የሚባሉ ሲሆን እድሜያቸው 36 ነው፡፡ በመንግስት ት/ቤት በአስተዳደር ሰራተኛነት የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ ማን ላይ እንደሚመሰክሩ ሲጠየቁ ፍቃዱ እና…..(ስሙ ጠፍቶባቸው ቆይተው) እ…አጥናፉ ብለዋል፡፡ በአካል ደግሞ በፍቃዱን አሳዩ ሲባሉ አጥናፍን አሳይተዋል፡፡ የምስክርነት ቃላቸውም ማእከላዊ ምርመራ ለግል ጉዳይ ሄደው ጽሁፎች ሲታተሙ ማየታቸውንና በፍቃዱ በፍቃደኛነት ሲፈርም ማየታቸውን ተናግረዋል፡፡ ስለጽሁፎቹ ሲጠየቁ “የአማርኛ ጽሑፎች ናቸው፡፡ 60 ገጽ የሚሆን ‹ወያኔ ይውደም› ምናምን የሚል ጽሑፍ አይቻለሁ፡፡ እንግሊዝኛም አለው 10 ገጽ ይሆናል፡፡ በምስል ከውጭ ሰው ጋር ሆነው የሚነጋገሩትም አይቻለሁ፡፡ ይዘቱ ግን ግር ይለኛል፡፡” ብለዋል፡፡ አጥናፍን አስመልክቶ ደግሞ ‹‹የእሱንም በዚያው መልኩ ነው ያየነው፡፡ ዕለቱም ግንቦት 16/2006 ነው፡፡ ኮምፒውተሩ ላይ የነበሩትን ጽሁፎች እዚያ ለነበሩት ሲያሳይ ነበር፡፡ ጽሑፎችን አይቻቸዋለሁ….‹የጨለማው ቀን….የጨለማው ንጉስ› የሚል አይቻለሁ፡፡ ‹ኢትዮጵያ አንድ ናት› የሚልም አይቻለሁ፡፡ ወደ 30 ገጽ ይሆናል፡፡ ሁሉም ፕሪንት ተደርጎ ሁላችንም ፈርመንበታል፡፡››ብለዋል
ሶስቱ ምስክሮች ከተሰሙ በኋላ ጠበቆች በሂደቱ ላይ አስተያየት አለን በማለት፣ ዶክመንቶቹ ፕብሊክ ዶክመንት ናቸው በአደባባይ የተጻፉ ጽሁፎቻቸው እና በማንኛውም ቦታ የሚገኙ ስለሆኑ ዶክመንቶቹን ክደን አልተከራከርንም የእኛ ክርክር ዶክመንቶቹ ለወንጀል ስራ የሚበቁ አይደሉም ነውና በዚህ ጭብጥ ዙሪያ ምስክር መስማቱ ያብቃልን የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡አቃቤ ህግ በበኩሉ ሁሉም ምስክሮች አንዲሰሙልኝ እፈልጋለሁ በማለቱ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ያስረዱልኛል ካለ ይቀጥል በማለቱ ምስክሮቹ ቀጥለዋል፡፡ ጠበቆች መስቀለኛ ጥያቄ ሳይጠይቁ ተከታዬቹ ምስክሮች መሰማታቸው ቀጥሏል፡፡
4.አራተኛው ምስክር አፈወርቅ ካሳ ይባላሉ፡፡ የግል ሰራተኛ ሲሆኑ እድሜያቸው 46 ነው፡፡‹‹ቀኑ ሚያዝያ 18/2006 ነው፡፡ የተከሳሹ አስማማው ቤት ጠዋት 3፡00 አካባቢ ሲፈተሸ ታዛቢ ነበርኩ፡፡ ጋዜጦች፣ መጽሔቶች፣ ፓስፖርት…ብዙ ወረቀቶች ላይ ‹‹አዎ የእኔ ናቸው›› እያለ ሲፈርም አይቻለሁ፡፡ እኔም ፈርሜያለሁ፡፡ ቤተሰቦቹም ቤት ውስጥ ነበሩ፡፡ አብዛኛው ያየሁት የግል መጽሄቶችን ነው፡፡ ማህተምም አይቻለሁ፡፡ ደሞ ቢሮው ሄደን ላፕቶፕ፣ ፍላሽ፣ ሲዲ፣ መጽሔቶች አይቻለሁ፡፡ ፖሊስ የሚፈልገውን እየለየ ፈርመናል፡፡ ወደቢሮው የሄድነው በመኪና ነበር፡፡ ከዛ ደግሞ አድራሻችንን ይዘው ስለነበር ሰኔ 4….አይ 14/2006 ነው መሰለኝ ከማዕከላዊ ተጠርተን ላፕቶፕ ላይ የነበረውን ስዕሎችና የእንግሊዝኛ ንግግሮች ሲወጡ አይቻለሁ፡፡ የእኔ ነው ብሎ ሲፈርም እኛ ታዛቢዎችም ፈርመናል፡፡›› ብለው ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡
5.አምስተኛ ምስክር አጌና አንከና ይባላሉ፡፡ እድሜያቸው 48 ሲሆን ነዋሪነታቸው አ.አ ነው፡፡ የሚመሰክሩት ደግሞ በ3ኛ ተከሳሽ ናትናኤል ላይ ነው፡፡ የምስክርነት ቃላቸው፣ ‹‹ሰኔ 17/2006 ለግል ጉዳይ ማዕከላዊ ነበርኩ፡፡ ከቀኑ 8፡00 ታዛቢ ሁነኝ ብሎ ፖሊስ ጠይቆኝ ታዝቤያለሁ፡፡ ላፕቶፑ ላይ አማርኛ ጽሑፎች አይቻለሁ፡፡ ጽሑፎቹ የተከሳሹ ስለመሆናቸው አምኖ ሲፈርምባቸው ታዛቢዎችም ፈርመናል፡፡ ይዘቱን ግን አላነበብኩትም፤ አልተረዳሁትም፡፡ የገጹን ብዛትም አላስታውስም፡፡›› የሚል የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡
6.ስድስተኛ ምስክር ገብረጨርቆስ ገብረመስቀል ይባላሉ፡፡ የ50 ዓመት የመንግስት ሰራተኛ ናቸው፡፡ ምስክሩ በአስማማው ላይ ለመመስከር እንደመጡ ቢናገሩም በአካል ግን ለይተው አላወቁትም፡፡ እንዲያውም አስማማውን አሳዩ ሲባሉ አቤልን አሳይተዋል፡፡
ከፍርድ ቤቱ ውሎ በኋላ አስተያየታቸው የሰጡት የተከሳሾች ጠበቆች አቃቤ ሀግ ያቀረባቸው ምስክሮች ወረቀት ሲፈረም አየን ከማለት ውጪ ምንም አይነት ለሂደቱ ቁም ነገር ያለው ምስክርነት የሚሰጡ አይደሉም ፡፡ ተከሳሾች ተገኘባቸው የተባለው ጽሁፍ የአደባባይ ዶክመንት ከመሆኑም በላይ አልተገኘብንም ብለን ክደን አልተከራከርንም በይዘቱ ላይ ክርክር ስላልተደረገ መስቀለኛ ጥያቄ ለማቅረብም ብዙ አልጨነቅንም ብለዋል፡፡አቃቤ ሀግ የወንጀሉን የመጀመሪያ ደረጃ ጭብጥ የሚያሳዬ ምስክሮችን ያቅርብ አይቅርብ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ የማስረጃ ማሰማት ሂደቱ ነገ ይቀጥላል፡፡
ቀን ሁለት (መጋቢት 22)

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ በ19ኛው ወንጀል ችሎት እየታየ ያለው የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች የክስ ጉዳይ ለሁለተኛ ቀን ምስክሮችን አሰምቶ በአወዛጋቢ መልኩ ለሚቀጥለው መጋቢት 30 ቀጠሮ ይዞ ተጠናቋል፡፡

ከእለቱ ዋዜማ ቃለ መሃላ ፈጽመው ሳይሰሙ የቀሩት ምስክሮች የተሰሙ ሲሆን ቃለ መሃላ በቀደመው ቀን በመግባታቸው ቀጥታ ወደ ምስክርነት ቃላቸው ተገብቷል፡፡ በሃያ ስድስተኛው የፍርድ ቤት ውሎ የተሰሙት ምስክሮች
7ተኛ ምስክር -ተስፋዬ መንግስቴ የመሰከሩት አቤል ዋበላ ላይ ሲሆን ከመንገድ ላይ ፓሊስ ሲፈትሹ አንዲታዘቡ ጠይቋቸው ቤቱ እና መስሪያ ቤቱ የተገኘው ሲዲ መጽሄቶች እና መጸሃፍት ላይ ሲገኙ አይቼ ፈርሜያለው አቤልም ፈርሟል ብለዋል፡፡
8ተኛ ምስክር- አቶ በረከት ጌታቸው በተመሳሳይ መንገድ ላይ ፓሊስ ታዘቡልኝ ብሎ የበፍቃዱ ሃይሉ ቤት ሲፈተሽ መታዘባቸውን በፍቃዱ የፈረመባቸው ነገሮች ላይም መፈረማቸውን ተናግረዋል፡፡ ጽሁፎቹ አማርኛ እና አንግሊዘኛ ከመሆናቸው ውጪ የሚያስታውሱት ይዘት አንደሌለ ተናግረዋል፡፡
9ኛ ምስክር – አቶ አንድነት ስሜ ይባለሉ አጥናፍ ብርሃኔ ላይ የመሰከሩ ሲሆን ቤቱ የተገኙ ወረቀቶች ላይ እሱም ፈርሟል አኔም ፈርሜያለው ብለዋል፡፡ የተገኙት ወረቀቶች አማርኛ እና እንግሊዘኛ ሲሆኑ ሴኩሪቲ ኢን ኤቦክስ የሚል መጽሃፍ አለበት ብለዋል፡፡ በይዘቱ ላይ አቃቤ ህግ አንዲመሰክሩ ቢጠይቅም ጠበቆች በይዘቱ ላይ ለመመስከር ስላልተመዘገቡ አንዳይመሰክሩ ተቃውሞ አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ እንዲመሰክሩ ቢፈቅድም ምስክሩ ምንም ይዘት አንደማያስታውሱ ተናግረዋል፡፡
10ኛ ምስክር -አቶ ታምራት ዓለሙ የሚባሉ ሲሆን አቤል ዋበላ ቤት ሲፈተሽ እንደነበሩ በመግለጽ ምስክርነታቸውን አሰምተዋል፡፡ አቤል የፈረመባቸው ነገሮች ላይ ፈርመናል ያሉ ሲሆን የነጻነት ጎህ ሲቀድ መጽሃፍ እስልምና በኢትዬጲያ የሚል መጽሃፍ አዲስ ጉዳይ መጽኄቶች አና እምነት እና ተስፋ በኢትዬጲያ የሚሊ ጽሁፎች ተገኝተዋል፡፡ ሲዲም ተገኝቷል ብለዋል፡፡ የፍተሻውን ቀን ሚያዝያ 11 ነው ብለዋል፡፡ ( ጦማሪ አቤል የታሰረው ሚያዝያ 17 አንደሆነ ይታወቃል)
11ኛ ምስክር አቶ ፋሲል ግርማ ሲሆኑ በፍቃዱ ሃይሉ ቤት ሲፈተሽ ማየታቸውን ተናግረዋል፡፡ ቤት ውስጥ ተገኙት እቃዎች እና ሰነዶች ላይ ተከሳሹ ሲፈርም እኛም ፈርመናል ብለዋል፡፡ የተገኙትን ሰነዶች ብዛትና ይዘት እንደማያሰታውሱም ተናግረዋል፡፡
12ኛ ምስክር አቶ ደረጀ አበበ የኮንስትራክሽን እና ቢዝነስ ባንክ ባልደረባ ሲሆኑ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ቢሮ ሲፈተሽ ፓሊስ ታዘቡ ብሏቸው አንደነበሩ እና ተገኙት ወረቀቶች ላይ ፈርመው ቢሮውን ዘግተው መውጣታቸውን ገልጸዋል፡፡ በወቅቱ የፈረሙበትን ወረቀት ይዘት የማያስታውሱት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
13ኛ ምስክር አቶ አክሊሉ ሃይለማርያም ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ ላይ የመሰከሩ ሲሆን ስሙን ብቻ ነው የማስታውሰው በማለት ያዬትን ተናግረዋል፡፡ ፈረንሳይ ለጋሲዬን አካባቢ ያለው ቤቱ ሲፈተሽ የተገኙ አማርኛ እና እንግሊዘኛ ጽሁፎች የግል ማስታወሻዎች ሲም ካርድ እና መጽሃፍት የተገኙ ሲሆን ሁሉም ላይ በፍቃዱም ሲፈርም እኔም ፈርሜያለሁ ብለዋል፡፡
በ14ኛ ምስክርነት አቶ የማነ ብርሃኔ የተባሉ ግለሰብ ቀርበው የነበር ቢሆንም አቃቤ ህግ ‹የተለየ ነገር አያስረዱልኝም› በሚል ምስክሩ ሳይደመጡ እንዲመለሱ ፍርድ ቤቱን ጠይቆ ምስክርነታቸው ሳይሰማ ቀርቷል፡፡ አቃቤ ህግ አጠቃላይ 41 ምስክሮችን እንዳስመዘገበ በመጥቀስ ትናንት ካስመዘገባቸው 17 ምስክሮች ውጭ ሌሎቹን ፖሊስ በአድራሻቸው ፈልጎ እንዳጣቸው በመግለጽ ማቅረብ አለመቻሉን አስረድቷል፡፡ በሌላ በኩል ግን 8ኛ፣ 9ኛ እና 27ኛ ላይ አቃቤ ህግ ያስመዘገባቸው ምስክሮች መጥሪያ ደብዳቤ ደርሷቸው እንዳልተገኙለት ገልጹዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ የጠበቆችን (የተከሳሾችን) አስተያየት ጠይቆ ነበር፡፡ በዚህም ጠበቆቹ አሉ የተባሉትን ምስክሮች ፌደራል ፖሊስ ሌሎችን በአድራሻቸው ፈልጎ ማቅረብ ይገባው እንደነበር፣ እግዚቢት ላይ የተመሰከሩት ቃሎችን ፍ/ቤቱ እንዳይመዘግባቸው ማመልከት፣ እንዲሁም ያልተካዱ ዶክሜንቶች ላይ ምስክር መስማቱ ተገቢ እንዳልሆነ በአስተያየታቸው አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም አቃቤ ህግ ቀሪ ምስክሮችን ማሰማት ካለበትም ምስክሮቹን በተሰጠው ቀን ( የማስረጃ መስማት ለሶሰት ተከታታይ ቀናት አንደተቀጠረ ይታወሳል) እንዲያቀርብ በማሳሰብ የደንበኞቻቸው የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብት በፍርድ ቤቱና በአቃቤ ህግ በኩል እንዲከበር ጠይቀዋል፡፡ በተለይ ባልተካዱ ዶክሜንቶች ላይ ይህን ያህል ጊዜ መውሰዱ ተገቢ አይደለም ብለዋል ጠንካራ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡ ጦማሪ ናትናኤል በበኩሉ ‹‹አቃቤ ህግ ያቀረበውን ሰምተናል፤ እኛ ብቻችንን አይደለም የታሰርነው፤ ቤተሰቦቻችንና ጓደኞቻችንም አብረውን ታስረዋል፡፡ በህሊና እና በኢኮኖሚ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰብን ነው፡፡ ስለዚህ ይሄ ሁሉ ‹ውሳኔው ላይ አብሮ እንዲታይልን እናመለክታለን ብሏል፡፡
ፍርድ ቤቱ የጠዋት ምስክር መስማቱን ሂደት አጠናቆ ለከሰአት ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ከሰጠ በኋላ ከሰአት በኋላ ሁለት ጉዳዬች ብይን ሰጥቷል፡፡ የመጀመሪያው የምስክሮች ቃል ከመዝገቡ ጋር አንዲያያዝ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ቀሩ የተባሉት ሶስት ምስክሮች ታስረው ለመጋቢት 30 አንዲቀርቡ እና አቃቤ ህግ ተጨማሪ ምስክሮች አሉኝ ካለም አንዲያቀርብ ነው፡፡በዚህም መሰረት ለሶስት ቀን የታቀደው ምስክሮችን መስማት በአንድ ቀን ከግማሽ ተጠናቋል፡፡ ጠበቆች አቃቤ ህግ ቀድሞ በተወሰነው ቀን ምስክሮችን ሊያቀርብ ሲገባ ሌላ ቀነ ቀጠሮ መሰጠት የለበትም በማለት ያቀረቡትን ተቃውሞ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ አቃቤ ህግ በበኩሉ ምስክሮቹን በፌደራል ፓሊስ እያስፈለኩ ስለሆነ ተከሳሾ ማረሚያ ቤት እንዳሉ ለፍለጋው ጊዜ ይሰጠኝ ብሎ ነበር ፡፡
ጠበቆቹ አቃቤ ህግ የእግዚቢት ሰነዶችን በተመለከተ የመዝገብ ቁጥሩን ገልጾ እንዲቀርብ በጠየቁት መሰረት ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፡፡ በትዕዛዙ መሰረት አቃቤ ህግ ዛሬ የመዝገብ ቁጥሩን ይዞ መቅረብ የነበረበት ቢሆንም፣ ጠበቆቹ ይህንኑ ጉዳይ በማንሳት ሲጠይቁ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ አልሰጠንም በሚል ክዷል፡፡


የዞን9 ማስታወሻ
አቃቤ ህግ የሌሉትን ምስክሮች ፍለጋ በማለት ለሚያባክነው ጊዜ ፍርድ ቤቱ አንደተለመደው ተባባሪ መሆኑ የፍትህ ስርአቱን በአጠቃላይ እና ይህንን መዝገብ ሂደት ይበልጥ አሳፋሪ አድርጎታል፡፡ አሁንም ቢሆን የተከሳሾች አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብት ተጠብቆ ሁሉም ተከሳሾች ነጻ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ አጥብቀን እንጠይቃለን ፡፡
ያልተሰራ ወንጀል ምስክር አይገኝለትም ፡፡

ዞን9

የዞን ዘጠኞች እና የጋዜጠኞቹን ጠቅላላ የእስካሁኑን የፍርድ ሂደት በእንግሊዘኛ በ Trial Tracker Blog ላይ ያገኙታል፡፡ 

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ ከላይ ለዚህ ትችት የተሰጠው ርዕስ እንደሚያመለክተው በአንድ በኩል በገንዘብ እጦት ችግር ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ለማድረግ ባለመቻሉ ምክንያት የተገደበ ወይም ደግሞ እንደ ጅብራ ተገትሮ የቀረ ግድብ የሚል ትርጉምን የሚይዝ ሲሆን ሌላው ትርጉሙ ደግሞ ከፍተኛ በሆነ የገንዘብ እጦት ችግር ምክንያት የተመደበለትን ገንዘብ በማብቃቃት ለመስራት በማሰብ ደረጃቸውን ባልጠበቁ ግብዓቶች በመጠቀም ለርካሽ የፖለቲካ […]

The post ኢትዮጵያ፡ በገንዘብ ዕጦት ምክንያት የተገደበ ግደብ? – አለማየሁ ገብረማርያም appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

ላለፉት 15ወራት በዲሲና አካባቢው ባንክ ሲዘረፍ ቆይቷል። ‘ባለ ሳይክሉ ሽፍታ’ የሚል ስም የተሰጠው አቶ ወሰኔ አሳየ ሰን ትረስት፣ዋሽንግተን ፈርስት እና ቢቢ እና ቲን ጨምሮ 12 ባንኮችን እንደዘረፈ ታምኖበታል። የቨርጂኒያ ፖሊስ ሲከታተለው የቆየውን ወሰኔ አሳየ የተያዘው ባለፈው ሳምንት የፌደራል ፖሊስ ምርመራ ቢሮ የስውር ካሜራዎች ላይ በተገጠሙ የስልክ ዳታ ልውውጥ መከታተያ ቴክኖሎጅን ከመረመረ በኋላ ነበር። በዚሁ ምርመራም በሁሉም […]

The post ቨርጂኒያን ያስጨነቃት አቶ ወሰኔ አሳየ ተያዘ! – አሰግድ ታመነ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

ሰኞ፣ መጋቢት ፳ ፩ ቀን፣ ፳ ፻ ፯ ዓመተ ምህረት አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ ጎንደር የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለሁ፤ ከጓደኞቼ መካከል ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ። አንድ ላይ የዘጠነኛ፣ የአስረኛና የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪዎች ነበርን። ግንብነህ አየለና አምባቸው አየለ ይባላሉ። በተለይ እሁድ እሁድ ማታ፤ ከዚያች በዚያ ወቅት ከነበረችው አንዲቷ ሲኒማ ቤት፤ ሲኒማ ጎንደር፤ የሚታዩትን ሲኒማዎች ለማየት፤ […]

The post የቅማንት ክልል መመሥረትን በሶስት መንገዶች . . .  – አንዱዓለም ተፈራ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

መጋቢት ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፉት 8 ወራት ጀምሮ በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ የታሰሩት እስረኞች አብዛኞቹ አርበኞች ግንቦት7 ትን ሊቀላቀሉ ሲሉ ተይዘዋል የሚል ክስ ሲመሰረትባቸው እስካሁን ድረስ ክስ ያልተመሰረተባቸው በርካታ እስረኞች እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል። የሰማያዊ ፓርቲ የአመራር አባላት ከሆኑት ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ፍቅረማርያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው እንዲሁም የቀድሞው የአንድነት አመራር አባል የነበረው …

መጋቢት ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በግድግዳዎች ላይ ተጽፈው የሚገኙ የተለያዩ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ጽሁፎች በአስቸኳይ እንዲጠፉ  የደህንነትና ድርጅት ጉዳይ ጽ/ቤት ለአዲስ አበባ ፖሊስ ትእዛዝ ሰጥቷል። ፖሊሶቹ በግድግዳ ላይ የተጻፉ የነፃነትና የፍትህ ጥያቄዎችን  የሚያቀርቡ የግድግዳ ላይ ጽሁፎችን እግር በእግር ተከታትለው ማጥፋት እንዳለባቸው ተነግሯቸዋል፡፡ ትእዛዙን ተከትሎም የአዲስ አበባ ፖሊሶች በየቀጣናው …

መጋቢት ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመጪውን ምርጫ መቃረብ ተከትሎ በአዲስአበባ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ 32ሺ ያህል ብዛት ያለው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ከሳምንት በፊት ቢወጣም ቅድሚያ ክፍያው የዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አቅም በላይ ሆኗል። የኮንዶሚኒየም  ቤቶች ዋጋ ካለፈው ዘጠነኛ ዙር ጋር ሲነጻጸር እስከ 20 በመቶ የዋጋ ጭማሪ እንዳሳየ ራሱ አስተዳደሩ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

በአሁኑ ጊዜ ህገ ወጥ በሚባል መንገድ በአደገኛ ጉዞ አውሮፓ የሚደርሱ ስደተኞች በሙሉ አውሮፓን እንደጠበቋት ሆና አያገኟትም ።ከሞት ተርፈው ምድሪቱን ለመርገጥ ከበቁት መካከል ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠው አስከፊ ህይወት የሚገፉ ጥቂት የሚባሉ አይደሉም ።

በናይጀሪያ ባለፈው የሳምንት መጨረሻ በተካሄደው ፕሬዚደንታዊ እና ምክር ቤታዊ ምርጫ የተቃዋሚዉ ወገን መሪ ጄኔራል ሙሃማዱ ቡሃሪ ማሸነፋቸዉ ተገለጸ። ስልጣን ላይ የነበሩት ፕሬዝደንት ጉድላክ ጆነተን ተቀናቃኛቸዉን በስልክ እንኳን ደስ ያልዎት ማለታቸዉ ተዘግቧል። ።

ለመድሃኒትነት የሚዉሉ በርካታ የእፅዋት ዓይነቶች መኖራቸዉ ይታወቃል። ከተክሎች የተቀመሙ መድሃኒቶችን መጠቀምም የተለመደ ነዉ። ለመድሃኒት የሚሆኑትን ተክሎች መንከባከቡ ግን ይጎድላል።

በሣዑዲ ዐረቢያ መራሹ የአየር ጥቃት የመን ውስጥ የተከፈተው ዘመቻ ስድስተኛ ቀኑን ባስቆጠረበት በዛሬው ቀን ከ40 በላይ ስደተኞች መገደላቸውን 65 መቁሰላቸውን የየመኑ ወኪላችን ገለጠ። የዓለም አቀፍ ስድተኞች ድርጅት (IOM) በማነጋገር ያገኘሁት ነው ባለው መረጃ መሠረት ከሟቾቹ መካከል ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል ።

በናይጀሪያ ባለፈው የሳምንት መጨረሻ የተካሄደው ፕሬዚደንታዊ እና ምክር ቤታዊ ምርጫ ውጤት አሁንም ገና እየተጠበቀ ነው። ለፕሬዚደንታዊው ምርጫ በዕጩነት ከቀረቡት 14 ተወዳዳሪዎች መካከል ጠንካራው ፉክክር የተካሄደው በፕሬዚደንት ጉድላክ ጆናታን እና በተቃውሞው ቡድን መሪ መሀማዱ ቡሀሪ መካከል ነው።

ሰሞኑን ያለማቋረጥ የመን ላይ እየተወሰደ ባለው የአየር ጥቃት ምክንያት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በከፍተኛ ችግርና ጭንቀት ውስጥ ነበሩ፡፡ ዛሬ በተደረገ የአየር ድብደባ ምክንያት ካምፕ ውስጥ የነበሩ 45 ኢትዮጵያዊን ሲሞቱ ከ60 በላይ ቆስለዋል፡፡ በIOM ካምፕ ላይ በስህተት የተወሰደ እርምጃ ነው በተባለው በዚህ ጥቃት ላይ ካምፕ ውስጥ የነበሩት የምስራቅ አፍሪካ ስደተኞች ናቸው የሞቱት የሚል መግለጫ IOM ቢያወጣም በዛ ካምፕ […]

የራስን እና የተፎካካሪን ስልትና ስትራቴጂ አለማስላት፣ የህዝብንና የሀገርን ፍላጐት አለማስቀደም፣ የመንገዶችን ኮረኮንችና ሊሾነት አለመለየት አባዜዎች ሁሌ እንደተፈታተኑን አሉ፡፡ ባለፉት የትግል ጊዜያት ብዙ አይተናል:: ብዙ ታዝበናል:: ብዙ ጉዳዮች አስደምመውናል:: ጠንካራነትን ብቻ ሳይሆን ደካማነትንም መገንዘብ ብልህነት ነው፡፡ አለመብሰል አለመሰልጠን እንደተገኘው መገስገስ ትግሉን በትንሽ ድል መወጣጠርና በትንሽ ሽንፈት መፍረክረክ ተጋጣሚን መናቅና ወሬን/አሉባልታን እንደ አቋም ወሱድ በሚደረገው ትግል ውስጥ […]

ህወሃት – የመርዝ ገበሬ፤ ጥይት ማጭዱ!! “የትግራይ ተወላጆች ታጥቀናል ሲለኝ – ደነገጥኩ” የሚል አስተያየት የሰጠው ኳስ አፍቃሪ ከጎልጉል የአዲስ አበባ ወኪል ጋር የተገናኘው አዲስ አበባ ስታዲየም ነበር። ጉዳዩ ለሚዲያ ግብዓት እንደሚውል ባይረዳም ገጠመኙን ለመናገር የተገደደው ስለ ምርጫ አንስተው ሲወያዩ ነው። ድንገት ተገናኝተው ቆሎ በመገባበዝ የጀመሩት ጨዋታ ዘጋቢውን ወደ 1997 ምርጫ ትዝታ ወረወረው። ተግባብተው አወጉና ተለያዩ። […]

The post “የትግራይ ተወላጆች ታጥቀናል” ሲለኝ – ደነገጥኩ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

ግሩም ተ/ሀይማኖት ሰሞኑን ያለማቋረጥ የመን ላይ እየተወሰደ ባለው የአየር ጥቃት ምክንያት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በከፍተኛ ችግርና ጭንቀት ውስጥ ነበሩ፡፡ ዛሬ በተደረገ የአየር ድብደባ ምክንያት ካምፕ ውስጥ የነበሩ 45 ኢትዮጵያዊን ሲሞቱ ከ60 በላይ ቆስለዋል፡፡ በIOM ካምፕ ላይ በስህተት የተወሰደ እርምጃ ነው በተባለው በዚህ ጥቃት ላይ ካምፕ ውስጥ የነበሩት የምስራቅ አፍሪካ ስደተኞች ናቸው የሞቱት የሚል መግለጫ IOM ቢያወጣም […]

The post አሳዛኝ ዜና በየመን ጦርነት 45 ኢትዮጵያዊያን ሞቱ ከ60 በላይ ቆሰሉ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

ከጊፍት ግሩፕ ኩባንያ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ይህ ጽሁፍ “ጊፍት ሪል እስቴት  ወደፊት ወይስ ወደኋላ” በሚል ርዕስ ‘አበበ ወርዶፋ’ በተባሉ ግለሰብ  ለተጻፈውና ጸሃፊው ‘ሪል እስቴቱ ጉዳት ያደረሰብኝ ደንበኛ ነኝ’ በሚል ሽፋን የኩባንያውን መልካም ስም ያለአግባብ ለመጉዳት በማሰብ እ.ኤ.አ ማርች  24 እና 25 ቀን 2015 ze-habesha.com እና satenaw.com ድረገጾች ላይ ለንባብ ላበቁት ሃተታ  የተሰጠ ምላሽ ነው። ጸሃፊው […]

The post የጊፍት ሪል እስቴት ጉዞ በስም ማጥፋት ዘመቻ ወደኋላ አይመለስም appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

“በ24 ዓመት አሁንም በአዝማሚያ ላይ ነኝ የሚለው ኢህአዴግ ……” “የ1997 የምርጫ ክርክር ይደገም ……” ግርማ ሠይፉ ማሩ [email protected]; girmaseifu.blogspot.com ተከራካሪዎች፤ አቶ ተፈራ ደርቤ እና ዶ/ር አብርሃም ተከስተ አቶ ግርማይ አደራ እና ዐዐዐዐዐ አቶ ትዕግሰቱ አወሉ እና አቶ ዮሃንስ አሰፋ አቶ ግዑሽ ገብረሰላሴ እና ትዕግሰቱ ዱባለ አቶ ጥላሁን እንዳሻው እና ሙላቱ ገመቹ በመጋቢት 18 እና 19 […]

The post የምርጫ ክርክር ሶስት- ግብርና እና ገጠር ልማት – ግርማ ሰይፉ ማሩ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

ለማፍቀር መፈቀር ፣ ሰው ለመርዳት ሰው መሆን ግድ ይላል ! ይህ ተፈጥሯዊ ህግ ሆኖ በሁላችንም ላይ ባይሰረጽም የታደሉት ሲሆኑትና ሲታደርጉት ከማየት አልፎ የድካማቸው ፍሬ አፍርቶ ሲያዩት ምስክር እማኝ መሆን መታደል ነው ። መልካም መስራት ለራስ ነው እንዲሉ ውስጥን ከሚሰጠው እርካታ ባሻገር የታደሉት የዘሩት አሽቶ መልካም ስራቸው በስኬት ጎዳና ሲታይና በውጤት ስኬቱ ሲደምቁ ማየት ከምንም በላይ […]

The post የማለዳ ወግ …” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” አንጀሊና * ዘሐራ ጥቁር አልማዝ ሆና ነጯን እናት ስታደምቅ -ነቢዩ ሲራክ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

ግሩም ተ/ሀይማኖት (ከየመን) ረቡዕ ሌሊት 8፡30 ላይ የተጀመረው የአየር ድብደባ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ የመን ነዋሪ የሆነ ሁሉ በፍርሃት ርዷል፡፡ በተለይ በትላንትናው ሌሊት የነበረው የአየር ድብደባ ከፍተኛ ስለሆነ ህዝቡ ላይ የጣለው ፍርሃት ከወትሮው የተለየ ነው፡፡ “በሁቲይን አማጽያን ሚሊሻ ላይ የተጀመረው የአየርጥቃት አሁንም በድርድሩ ካልተስማሙ ወይ ሰነዓ ከተማን ለቀው እስካወጡ አያቆምም!” ሲሉ የሳዑዲ አረቢያ ንጉስ ሰልማን ቢን […]

The post በየመን ኢትዮጵያውያኖች በጭንቅ ላይ ናቸው appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

‹‹ተጨማሪ ምርመራ ይቀረኛል›› መርማሪ ፖሊስ ‹‹መረጃዎች ካሉ ክስ ይመስረትብን ካልሆነ ከእስር እንለቀቅ›› ተጠርጣሪዎች ———- በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ የሚገኙት ብርሃኑ ተክለ ያሬድ፣ ፍቅረማሪያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው ዛሬ ከሰዓት በኋላ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ፍርድ ችሎት ቀርበው ተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል፡፡ ሶስቱም ወጣት ተጠርጣሪዎች ችሎት ከመግባታቸው በፊት ሳቅ እና ፈገግ እያሉ በፍርድ […]

መጋቢት ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የንቅናቄው መስራችና አደራጅ   ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት የህዝባዊ ወያን ሃርነት ትግራይ መንግስት በአካባቢው ያለውን መሬት ሙሉ በሙሉ ጠቅልሎ ለመውሰድ ባለው ፍላጎት በአኝዋኮችና በኑወር ብሄረሰቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ነው። ኑወሮችን በጦር መሳሪያ ከማስታጠቅ ጀምሮ ከደቡብ ሱዳን የሚፈናቀሉ ኑዌሮች በአኝዋኮች፣ መዠንገሮችና ሌሎች ብሄረሰቦች መካከል እንዲሰፍሩ በማድረግ እስከዛሬ …

መጋቢት ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር -ኦብነግ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ፣ የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር በበሁለት አመት ውስጥ ኦጋዴን  ያለውን የተፈጥሮ ጋዝ ለውጭ ገበያ እናቀርባለን በማለት የሰጡት መግለጫ፣  ያልተጨበጠና የማይሆን ነው ብሎአል። መንግስት በኦጋዴን ውሰጥ ህዝቡን በጅምላ ኢላማ በማድረግ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን የገለጸው መግለጫው፣ የቻይና ኩባንያ ይህን እያወቀ ለመንግስት ሰራዊትና …

መጋቢት ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በቁጥጥር ስር የዋሉትእና በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ በእስር ላይ የሚገኙት ብርሃኑ ተክለ ያሬድ፣ ፍቅረማሪያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ፍርድ ችሎት ቀርበው ተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ችሎት ከመግባታቸው በፊት በፈገግታ በፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ የነበሩትን ቤተሰቦቻቸውን፣ ጓደኞቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ሰላም ሲሉ መታየታቸውን ጋዜጠኛ …

መጋቢት ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገራችን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ጋር በተያያዘ በርገን የኢሳት የድጋፍ ኮሚቴ አማካኝነት የተሰራው የሳውል ፍሬዎች በፈረንጆች አቆጣጠር ማርች 28 በበርገን ኖርዌይ ከተማ ተመርቋል። በአይንሸት ገበያው  ተደርሶ በጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን አርታኢነትና አዘጋጅነት በተሰራው ፊልም ፣ በበርገን እና አካባቢዋ የሚኖሩ 11 ኢትዮጵያውያን ተሳትፈውበታል። በበርገን በተካሄደው ዝግጅት ለተሳታፊዎች የምሰክር ወረቀትና አበባ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከበርሊን ማራቶን እስከ ቻይና አገር አቋራጭ የሩጫ ፉክክር ብሎም የካርልስባድ ካሊፎርኒያ ውድድር አመርቂ ድሎችን ተቀዳጅተዋል። በዩሮ 2016 የእግር ኳስ የማጣሪያ ፍልሚያ ጆርጂያ ጀርመንን ለግማሽ ሠዓት ያህል ተገዳድራለች፤ ከመሸነፍ ግን አልዳነችም። ትንሺቱ ጅብራልታር እንደለመደችው የግብ ጎተራ ሆናለች።

ሰማያዊ ፓርቲ፣ ትናንት በ 15 የተለያዩ ከተሞች ሊያካሂድ ያሰበውን ሰላማዊ ሰልፍ ከ 4 ከተሞች በስተቀር በፖሊስ መደናቀፉን የፓርቲው ሊቀመንበር ገለጡ። አዲስ አበባ የተጠራዉ ሰልፍ በታቀደዉ መንገድ መሄድ ባለ መቻሉ ተቃዉሞ ሰልፉ ከጽ/ቤቱ ብዙም ሳይርቅ መደረጉ ተመልክቶአል

በሳዑዲ አረቢያ መሪነት በየመን የሁቲ አማጽያን ላይ የሚካሄደው የአየር ጥቃት ለአምስተኛ ቀን ቀጥሏል። ዛሬ ለሊት ሁለት የጦር አውሮፕላኖች በየመን ቤተ-መንግስት አቅራቢያ ድብደባ መፈጸማቸውን ሬውተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

በዩናይትድ ስቴትስ ከአፍሪቃዉ ቀንድ የመጡ ሶስት ግለሰቦች በጫት ንግድ በወንጀለኝነት ተከሰዉ የሶስት ዓመት እስራት ተፈረደባቸዉ። ጫት ለብዙ ወንጀሎች የሚያጋልጥ እጽ መሆኑም ተመልክቶአል።

ያሉን ታሪካዊ መዛግብት እንደሚያመላክቱት የዐባይ ወንዝ ከግብጽ ጋር በነበረን ግንኙነት ለውዝግብ ምክንያት መሆን የጀመረው ከሽህ ዓመታት ወዲህ እንደሆን ያስረዳሉ፡፡ እንዲያ እንዲያ እያለ መጥቶ በዐፄ ምኒልክ ዳግማዊ ዘመን እንግሊዝ ግብጽንና ሱዳንን ቅኝ ትገዛ በነበረበት ወቅት ለምትገዛው አካባቢ የዐባይን ወንዝ የውኃ ምንጭነት አስተማማኝ ለማድረግ በማሰብ የሀገራችን መንግሥት ሁለንተናዊ አቅም በዘመነ መሳፍንት የገጠመውን ስብራትና መዳከምን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም […]

The post ግብጽ የዓባይን ወንዝ የመጠቀም ታሪካዊ መብቴ የምትለውን የቅኝ ግዛቱን ውል ወያኔን አስፈረመች! – ሠዓሊ አምሳሉ ገብረኪዳን አርጋው appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

* በሳውዲ የሚመራው የአረብ ሀገራት ህብረት ጦር የአየር ድብደባው ተጠናክሮ ቀጥሏል * የየመን ባህርና አየር በሳውዲ አየር ሃይል ቁጥጥር ስር መዋላቸው ሲጠቆም ኢራንን ጨምሮ ለሁቲ አማጽያን ስንቅና ትጥቅ ማቀበያ በሮች መዘጋጋታቸውን የህብረቱ ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ አስታውቀዋል * ከዘመቻው መምሪያ ጋር በተደረገ ቅንጅት የመን የገባው የፖኪስታን ጃምቦ ጀት 482 ፖኪስታናውያንን ከመንን አውጥቷል […]

እንደምትመለከቱት አማራ ከቤንሻንጉል ሲፈናቀል የሚያሳይ ነዉ፡፡ ተፈናቀልን አግባብ አይደለም እያልን ስንጮህ እነ ሌንጮና ገብረ መድን ትግል ፌስ ቡክ አይደለም እንደኛ በረሃ ገብቶ ነዉ ሲሉ እነ ሌንጮ ደግሞ ነፍጠኛውን ቀብረነዋል ይህ ጅማሮ ነዉ ገና እንጠራርጋቸዋለን ይሉናል፡፡ የኞቹ ዘመዶች ደግሞ ለማበጣበጥ ነዉ ወንድሞቻችን ናቸዉ ይሉናል፡፡ እኛ ወንድሞቻችን አይደሉም መች አልን በወንድሞቻችን ተፈናቀልን ነዉ ያልነዉ በወንድም መፈናቀል ደግሞ […]

The post ትግላችን ሁለት ቀስት ያለዉ መሆን አለበት! የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ራሷን የቻለች ሀገር ከሆነች ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረችዉ ኤርትራ ከምዕራቡ ዓለም መንግሥታት ጋ ያላት ግንኙነት የቀዘቀዘ መሆኑ የሚታይ ነዉ። ምሥራቅ አፍሪቃዊቱ ትንሽ ሀገር በአቅራቢያዋ ከሚገኙ ሃገራት ጋ ያላት ግንኙነትም የሞቀ የሚባል አይደለም።