ትግላችን ሁለት ቀስት ያለዉ መሆን አለበት! የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ

እንደምትመለከቱት አማራ ከቤንሻንጉል ሲፈናቀል የሚያሳይ ነዉ፡፡ ተፈናቀልን አግባብ አይደለም እያልን ስንጮህ እነ ሌንጮና ገብረ መድን ትግል ፌስ ቡክ አይደለም እንደኛ በረሃ ገብቶ ነዉ ሲሉ እነ ሌንጮ ደግሞ ነፍጠኛውን ቀብረነዋል ይህ ጅማሮ ነዉ ገና እንጠራርጋቸዋለን ይሉናል፡፡ የኞቹ ዘመዶች ደግሞ ለማበጣበጥ ነዉ ወንድሞቻችን ናቸዉ ይሉናል፡፡ እኛ ወንድሞቻችን አይደሉም መች አልን በወንድሞቻችን ተፈናቀልን ነዉ ያልነዉ በወንድም መፈናቀል ደግሞ ያሳምማል፡፡ ለነዚህ የአማራ መፈናቀል ጮቤ ለሚያስረግጣቸዉ የምላቸዉ ቢኖረኝ የሌሎችን ሳልወክል የኔና የኔን መሰል የትግል ስልት የሚከተለዉ በጣም ብዙ ነዉ፡፡

ይህም ልክ እንደናንተ ሁለት ቀስት ነዉ ያለን ለዛዉም ፌስ ቡክ ላይ ሳይሆን በራችሁ የሚደርስ ቀስት!!! መቸም የትግል ስልቱን ይነግረናል ብላችሁ ተስፋ እንደማታደርጉ እርግጠኛ ነኝ! ነገር ግን ትንሽ ፍንጭ ልስጣችሁ፡፡ ምን መሰላችሁ አሁን ስትለፈልፉ የሚሰማ ቃል አለ እሱም አማራን ነፍጠኛን ትምክተኛዉን ቀብረነዋል የቀረዉንም አንገቱን አስደፍተናል፡፡ ትላላችሁ! ታዲያ ለማን ነዉ በየጊዜዉ ስሙን እያነሳችሁ የምትዘልፉት? ነዉ ከቀበራችሁበት አውጥታችሁ ልታሰሙት ነዉ? ለምን በሌለ ነገር ላይ ትጮሃላችሁ? እኔ ግን በጊዜ ከድርጊታችሁ ታቅባችሁ ለአገር አንድነት በሚበጅ መስመር ብትጎዙ ጥሩ ነዉ!!! በዚህ መንገድ ከቀጠላችሁ አድፍጦ ካለዉ ሁለት ቀስት አታመልጡም! እስከአሁን ብዙ ደማውቃቸዉ ሰዎች በተቃዉሞ ጎራ ብቻ ይታገሉ ነበር፡፡

ሌሎቹ ግን በዘረኝነት ባህሪያቸዉ ምክኒያት በሁለት ቀስት እየመቱን ነበር አንደኛው በላቸዉ የተቃዉሞ ጎራ የሚመጣ ሲሆን ሁለተኛዉ በመንግስት ስር ባለዉ መዋቅራቸዉ የሚመጣ ነዉ፡፡ እኛ ግን ከቤተሰቦቻችን በወረስነዉ ከዘረኝነት የፀዳ አመለካከት የተነሳ ቀስታችን አንድ ሲሆን እሱንም ወደብዙ አቅጣጫ ለማዞር ስንሞክር እየተጎዳንበት የመጣ ነዉ፡፡ አሁን ግን መስመር ቀይረናል ይህም እኛ የመንግስትን መዋቅር መጠቀም ጀምረናል፡፡ ለዚህም በሳልና ነገሮችን መለወጥ የሚችሉ ሰዎችን አስገብተናል፡፡ ስለዚህ መቆናጠጥ የምንችለዉ እንደዚህ ቀደሙ በአንድ አቅጣጫ ብቻ አይደለም፡፡ በሁለት ነዉ! ይህ መዋቅር የለለበት አደረጃጀት የለም፡፡ ስለዚህ እንደዉም እናንተ እያወራችሁ እኛ የምንሰራበት ይሆናል ሁሉም አማራና የኢትዮጵያን አንድነት የሚፈልግ መቀላቀል ነዉ፡፡ ስለዚህ ይህን ሁለት ቀስት መያዝ ለአማራ አማራጭ የሌለው ወቅቱን ያገናዘበ መፍትሔ ነዉ!!!

The post ትግላችን ሁለት ቀስት ያለዉ መሆን አለበት! የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.