በስዑዲ ዐረቢያ መዲና በሪያድ፤ በተለይም ማንፉህ በተባለው ቀበሌ ከሁለት ወር በፊት እንደሆነው ሁሉ፤ አሠሳ ፤ ከትናንት በስቲያ በጦር ሠራዊቱ ልዩ ኃይል የተጀመረ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ኤምባሲና ቆንስላ ጽ/ቤት ሕጋዊ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ የሌላቸው

የደቡብ ሱዳን ግጭት ዛሬም አልሰከነም። የቀድሞዉ ምክትል ፕሬዝደንት ሬክ ማቻር ታማኞች ማላካል የተባለችዉ የነዳጅ ዘይት ያለባት ግዛት ቁልፍ ከተማ ይዘናል ሲሉ ዛሬ ገልጸዋል። በተቃራኒዉ የመንግስት ኃይሎች የላይኛዌዉ ናይል ግዛት የሆነችዉ ከተማ ማላካል ከቁጥጥራችን አልወጣችም እያሉ ነዉ።

የግብፅ የሽግግር መንግስት የሙስሊም ወንድማማቾች ማኅበርን በአሸባሪነት ከፈረጀ በኋላ ዛሬ ለተቃዉሞ የወጡ ደጋፊዎቹ ከፖሊስ ጋ ተጋጭተዋል። ድንጋይ ይወረዉሩ እንደነበር የተገለጸዉን የቡድኑን ደጋፊዎች ለመበተንም ፖሊስ የሚያስለቅስ ጭስ ተጠቅሟል።

ታህሳስ ፲፮( አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ተማሪዎቹ የታሰሩት ካለፈው አርብ ጀምሮ ሲሆን፣ እስካሁንም በእነርሱ ላይ እየደረሰ ያለው እንግልት አለመቆሙ ታውቋል። በግቢው ውስጥ ተማሪዎች የሚጠቀሙበት መጸዳጃ የተበላሸ መሆን፣ የምግብ ጥራት መጓደል፣ የውሀ እጥረት፣ የመብራት ለረጅም ጊዜ መቋረጥ፣ የትምህርት ስርአቱ በተገቢው መልኩ አለመከናወን፣ የመጽሀፍት እጥረት፣ የኮምፒዩተር አለመኖር እና በተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው የጤና መቃወስ …

ታህሳስ ፲፮( አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ነዋሪዎች እንደገለጹት ላለፉት 25 አመታት ከኖሩበት ቤት በጉልበት ተነሱ በመባላቸው ሜዳ ላይ ለመውደቅ ተገደዋል። ነዋሪዎቹ ስሜታቸውን በከፍተኛ ሀዘን እየገለጹ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስላቸው ተማጽነዋል። የመንግስትን እርምጃ በመቃወማቸው የተወሰኑ ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁንም ነዋሪዎች ገልጸዋል። በአዳማም በተመሳሳይ መንገድ  ከ25 ሺ በላይ ህዝብ ቤት አልባ መሆኑን መዘገባችን ይታወቃል።

ታህሳስ ፲፮( አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ባለፉት ሶስት ዓመታት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ከሕዝብ የተዋጣው ገንዘብ ከ10 ቢሊየን ብር በላይ መሆኑ በመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ሲነገር ቢቆይም አንድ ባለስልጣን ግን ትክክለኛው አሀዝ  5 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ነው ሲሉ ተናግረዋል። የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ጽ/ቤት የአቶ በረከት ስምኦን ምክትል የሆኑት አቶ …

ታህሳስ ፲፮( አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ባለፈው ረቡዕ ቦር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የታየውን ከፍተና ግጭት ተከትሎ በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አልታወቀም። በርካታ ደቡብ ሱዳናውያን በመንግስት ደጋፊና ተቃዋሚዎ ታጣቂዎች መገደላቸውን ሲኤን ኤን የዘገበ ሲሆን፣ በአካባቢው የሚኖሩ ከ1 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን እጣ ፋንታ እስካሁን በውል አለመታወቁንም ከአካባቢው ሸሽተው ወደ ኡጋንዳ ድንበር …

ታህሳስ ፲፮( አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በአቶ ካሳ ተክለብርሃን የሚመራው የፌዴሬሽን ምክርቤት ፍ/ቤት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በሙስና ወንጀል በተከሰሱት የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሰልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታ ጉዳይ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት የፊታችን ሰኞ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ታወቀ፡፡ የፌዴራሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሙስና ወንጀል በመጠርጠር በሶስት የተለያዩ መዝገቦች ስር ከባለስልጣናትና ባለሀብቶች …

 

አልክስ አብርሃም

አባቴ ስድስት ልጆቹን ሰበሰበና የመረረ ነገር ሲኖር ብቻ የሚጠቀምበትን ሰማያዊ ሽፋን ያለውን አጀንዳውን ፊቱ ዘርግቶ ስብሰባውን ከፈተ (ስለዚህ አጀንዳው ሌላ ቀን በሰፊው እና ወራለን)! ገና ከመጀመሪያው የእለቱን አጀንዳ ሲያስተዋውቅ ነበር ሁላችንም የደነገጥነው ‹‹ /ማንያህልሻል ተክሌን የሚመለከት ነው ›› ሲል ግራ ተጋባን …… የእናታችን ስም እንዲህ እንደባቡር ሃዲድ ረዝሞ ያውም በአባታችን ሙሉውን ሲጠራ ሰምተን አናውቅም! ማኑየ ….የኔገላ ….ወለላየ ነበር በደጉ ቀን ሲጠራት! ሌላው ያጨናነቀን ነገር አባባ የእናታችንን ስም እንዲህ ያራዘመ ዋናውን ጉዳይማ እስከ ነገወዲያም አይጨርሰው የሚል ስጋ ትነበር!

ሙሉውን አስነብበኝ …

በምድራችን የሚኖረው ህዝብ ብዛት ከ 7 ቢሊዮን ቢበልጥ እንጂ እንደማያንስ የታወቀ ሆኖ ሳለ ፣ ላሁኑና ለመጪውም ዘመን ፤ በዝች ምድር የሰዎችን ህልውና እንዴት አስተማማኝ ማድረግ ይቻላል ? ለሚለው ጥያቄ መልሱ የሚያከራክርም የሚያነታርክም ሊሆን ይችላል?

የለጋዋን ሀገር ደቡብ ሱዳንን ወቅታዊ የግጭት ጦርነት ሁኔታ ለማርገብና ተፋላሚዎቹ የቀድሞዉ የደቡብ ሱዳን ነፃ አዉጭ ቡድን አመራሪዎች ለማስማማት ጥረቱ ቀጥሏል። እዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ለስጋትና ዘረፋ ተጋልጠዋል።

በደቡብ ክልል የቁጫ ብሄረሰብን በሚመለከት ተደጋጋሚ ችግር እንግልቶችና የሰዉ ህይወትም የጠፋበት በመሆኑ አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል ሲል አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ አስታወቀ። የፓርቲዉ አመራር አባላት አካባቢዉን ሄደዉ በመጎብኘትም ዘገባ አቅርበዋል።

ዓለም ሲያሳስብ፥ ሲያጠነቅቅ፥ ለዲፕሎማሲ ሲጠራራ፥ አፍሪቃ ጁባ ሲመላለስ፥ጁባ አስከሬኖቻን ቆጥራ፥ቀብራ ደሟን አድርቃ ሳታበቃ ቦር ተደገማለች። ድፍን የዩኒቲ ግዛት ቀጠለች። ጃግሌዬም አሰልሳለች።

የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ 19እና 20 ልዩ የጠቅላላ ጉባኤውን እንደሚያደርግ የሚጠበቀው አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ከመላ ሀገሪቱ ተወክለው ከሚመጡ የጠቅላላ የጉባኤው ተሳታፊዎች ጋር ከመደበኛ የ2ቀን ስብሰባ በተጨማሪ ቅዳሜ ሙሉ ሌሊት የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ስለወደፊቱ የፓርቲው የትግል ስልትና ብቃት ያላቸው አባላትን በመመልመል የፓርቲውን አደረጃጀት አሁን ካለው በእጥፍ በማሳደግ በ2007ዓ.ም በሚደረገው ሀገር አቀፍ ምርጫ ህዝብን አስተባብሮ በአሸናፊ […]

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ታህሳስ 19 እና 20 ለሚያከናውነው ጠቅላላ ጉባኤ የመሰብሰቢያ አዳራሽን ሆቴሎች እንዳያከራዮት ገዢው ፓርቲ የሆቴል ቤት ባለቤቶችንና አስተዳደሮቻቸውን ማስፈራራቱን ተከትሎ ክፍያ በተፈጸመባቸው አዳራሾች ጭምር ፓርቲው መጠቀም እንደማይችል በመነገሩ የቀረው አማራጭ የምርጫ ቦርድን አዳራሽ መጠየቅ በመሆኑ ፓርቲው አዳራሽ ለመከራየት ያጋጠሙትን ችግሮች በመግለጽ ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ጥያቄው የቀረበለት ምርጫ ቦርድ በበኩሉ አዳራሹን ለመስጠት […]

ኢህአዴግ በሚከተለው የዘረኝነት ፖሊሲና የከፋፍለህ ግዛው አገዛዝ መርህ ዛሬ በሃገራችን የአንድ አካባቢ ህዝብ በሌላው አካባቢ በነፃነት ሰርቶ የመኖር ህገ-መንግስታዊ መብት በገዢው ፓርቲ አመራር አባላት ሴራ ሲጣስ ይታያል፡፡ ባሳለፍናቸው አመታት በማንነታቸውና በእምነታቸው ምክንያት ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው ተረግጠው በአስርና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ተወልደው ወልደው ሃብት ንብረት ካፈሩበት መሬት ተፈናቅለውና በዚሁ ሳቢያ ለስደትና ለልመና የመዳረጋቸው ሚስጢር በማናቸውም […]

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሁለት ሳምንት በፊት በሱዳን ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል።በእዚህ ጉብኝት ላይ አቶ ኃይለማርያም ”እጅግ ለም የሆነ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ለመስጠት ተስማምተዋል አሁን የቀረው ችካል ማስቀመጥ ነው” የሚል ዜና በኢሳት ሲዘገብ ቀናት ነጉደዋል።ትናንት ታህሳስ 16/2006 ኢሳት በአለም አቀፍ ራድዮ ስርጭቱ ላይ የኢትዮጵያ የድንበር ጉዳይ የሚከታተሉ ‘የኢትዮጵያ ድንበር ኮሚቴ’ የተሰኘ ኮሚቴ አባላትን በቃለ መጠይቅ አቅርቦ ነበር።እንደ ኮሚቴው ገለፃ ከሆነ አሁን መንግስት ለሱዳን መንግስት ለመስጠት መስማማቱ የሚነገረው መሬት ከቀድሞ ጀምሮ በኢትዮጵያ ይዞታ ላይ ያለ አሁንም ገበሬዎች የሚገኙበት እና ባዶው ቦታን ጨምሮ በትንሹ ካለምንም ማጋነን 15 ሚልዮን ሕዝብ አስፍሮ መመገብ የሚችል ቦታ ነው።15 ሚልዮን ልብ በሉ!

በሕዝብ ስም የሚደረግ ማንኛውም ውል ከህዝብ ሊደበቅ አይገባውም።ድንበር የማይቀዘቅዝ ትኩስ ደም ነው።ይህ ደም ደግሞ ለዘመናት የኢትዮጵያ አባቶች እና እናቶች ያፈሰሱት ደም ነው።ማንም መንግስት በሕዝብ ደም ሊደራደርም ሆነ ድንበር ሊሰጥ አይችልም።ለአንድ ‘ኩርማ’ መሬት ለባድሜ በሺዎች ያረገፈ ጦርነት ክተት ያወጀ መንግስት 15 ሚልዮን ሕዝብ የሚያሰፍር መሬት ለሱዳን ስለመስጠቱም ሆነ ስለ ውሉ ጉዳይ ዝርዝር ማብራርያ ለሕዝብ ሊሰጥ ይገባል።በትዊተር በብዛት የሚታዩት ባለስልጣናት ከሌላው ዜና ይልቅ የእዚህ አይነቱን ቅድምያ ሊሰጡት በተገባ ነበር።ድንበር የማይቀዘቅዝ ትኩስ ደም ነው።

http://www.youtube.com/watch?feature=pl … 86uyLReLdE

http://gudayachn.blogspot.no/2013/12/blog-post_26.html

በረዶዉ ቢጥል ኖሮ የበዓሉ አክባሪዎች «ነጩ ገና ይሉት ነበር።በቅፅሉ።ዘንድሮ ብዙ ቦታ ይሕ አልሆነም።የሰሜኑ ንፍቀ ክበብ ዓየር ነፋስ፥ ዝናብ፥ አንዳዴም ወጀቦ ነዉ ያጠላበት።ድፍርስ ዓየር፥ ጭፍግግ ድባብ።ብሪታንያ ደግሞ ብሶባታል።እንግሊዝ ግን የበዓሉ ወግ አንድም አልቀረበትም።አበሻስ?«ሮም ስትሆን እንደ ሮሞች ሁን» ብሏል ነዉ-ያሉት አዋቂዉ።

የአጼ ምኒሊክን መቶኛ የሙት አመት መከበር ምክንያት በማድረግ በ DW ሬድዮ በተደረገው ጥያቄና መልስ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ, ዶ/ር ሓይሌ ላሬቦና ዶ/ር ሹመት ሲሳይ (የታሪክ ተመራማሪዎች) ቃለ መጠይቅ ተደርጎ በሚሰጠው መልስ ላይ ስለ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በተናገሩት ላይ አስተያየቴን አቀርባለሁ።

አንባቢያንን ቃለመጠይቁን ቢያዳምጡ ጥሩ ነው ባይ ነኝ፤ ሁለቱ የታሪክ ምሁራን ትምህርታዊ ትንተና ይሰጣሉና

ውሸት ሲደጋገም እውነት ሊመስል ይችላል፤ በተለይም የአገራችንን የኢትዮጵያን ታሪክ ለማያውቁ እውነታው ምን እንደሚመስል መረጃ ለማቅረብ እሞክራለሁ።

አቶ ባልቻ ኦሮሞ ከባሌ እየተስፋፋ ሲመጣ ልብነ ድንግል እንዳይስፋፋ አቆሙት ይላሉ፤ ለምን ይህን ምሳሌ እንዳቀረቡም ግልጽ አይደለም ለሳቸው ትንታኔ የማይመች በመሆኑ፤ ለዛውም በአጼ ልብነ ድንግልና በኦሮሞች መሀከል ስለነበረው ግኑኝነት በከፊል ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ ሊያስረድዋቸው ሞክረዋል፤ ስለመስፋፋቱና እንዲያውም አማራውን እንደገፋው ለአቶ ባልቻ መረጃ ላቅርብ

ጥንት ሌላ ስም የነበራቸው በኦሮሞ ከተያዙ ማግስት ስማቸው የተቀየረ፤ ደዋሮ- ጨርጨር, ጋፋት-ሆሮ, ገራሪያ- ሰላሌ, ዳሞት- ወለጋ, አበቤ- በቾ, ሽምብራ ኩሬ- ሞጆ…(የሃያኛው ክፍለዘመን ኢትዮጵያ ገጽ 50 በጥላሁን ገ/ስላሴ) በቅኝ ተገዛ የሚሉት ኦሮሞ ተጨማሪ ቦታ እንደያዘ እንጂ እንደተወሰደበት አይደለም ታሪኩ የሚመሰክረው፤

አቶ ባልቻ የኦሮሞን ታሪክ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ሊያዛምዱት ይሞክራሉ፤ ኦሮሞም እንደ ደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች ኢትዮጵያ ውስጥ ሲረገጥ የኖረ ሕዝብ አድርገው ያቀርቡታል። መፈትሄውንም ሲጠይቁ reconciliation እርቅ ኦሮሞ ይቅርታ ተጠያቂ የተቀረው ይቅርታ ጠያቂ በተለይም የፈረደበት አማራ ለዚህ ወንጀል ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፤ ባለፉት አስተዳደሮች ስህተቶች አልተሰሩም ብሎ የሚከራከር የለም፤ ጥያቄው እንዴት አብረን ወደፊት መሄድ እንችላለን ነው?

እንደቅኝ ተገዛን የሚሉት ቡልቻ ደመቅሳ አገሪቱን በእርሻ ሚኒስቴርነትና በምክትል ገንዘብ ሚኒስቴርነት አስተዳድረዋል- ቸር ቅኝ ገዢ ነበር የነበራቸው፤ እኛ ቅኝ እየተገዛን ስለሆንን በሚኒስቴርነት ቅኝ ገዢዬን አላገለግልም ብለው አላንገራገሩም፤

ኦሮሞ በሲቢሉም ሆነ በወታደራዊው ክንፉ ታላቅ የሚባሉትን ስልጣኖች ይዞ የኖረና ያለ የህብረተሰብ ክፍል ነው፤ አገሪቱ ውስጥ ለነበሩትና ላሉትም ደግ ነገሮችም ሆነ ክፉ ነገሮች ተጠያቂነቱ እኩል ነው፤ አቶ ባልቻ ቅኝ ገዢ የሚሉትን የአማራውን ክፍለሀገር ደጃዝማች ክፍሌ ዳዲ ያስተዳድሩት ነበር- (ምሳሌ የሚያቀርብበት ደቡብ አፍሪካ የማስተዳደር ቅንጦት ይቅርና ነጭ በሚዝናናበት ቦታ ጥቁር መግባት አይፈቀድለትም ነበር)

ስለኦሮሞ ባለስልጣናት እስቲ እንመልከት

ምኒሊክ በሸዋ ሲነግሱ የረድዋቸው አብሮ አደግ ባልንጀራቸው ጎበና ዳጬ ናቸው፤ የወለጋውም አስተዳዳሪ ኩምሳ ምኒሊክን በደጃዝማችነት አግልግለዋል፤ እነ ባልቻ አባ ነፍሶም የማይረሱ ታልቅ ኢትኆጵያውያን ናቸው

የአጼ ሃይለስላሴ አባት ራስ መኮንን ወልደሚካኤል (ጉዲሳ) አባታቸው ኦሮሞ ነበሩ፤ እናታቸውም ወ/ሮ እመቤት እናታቸው ኦሮሞ ነበሩ፤

ራስ ዳርጌ የሸዋው ንጉስ ሳህለስላሴ ከወለድዋቸው አራት ወንዶች መሃከል አንዱ ሲሆኑ ጥናታቸው አርሲ ውስጥ የአንድ አካባቢ ኦሮሞ ባላባት ልጅ ነበሩ (አባ ቦራ በታቦር ዋሚ ገጽ 9)

ራስ አበበ አረጋይ መከላከያ ሚኒስትር

አቶ ይልማ ዴሬሳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር, የገንዘብ ሚኒስትር

ደጃዝማች ክፍሌ ዳዲ የጎንደር አስተዳደር

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የእርሻ ሚኒስትርን ምክትል የገንዘብ ሚኒስትር

ሜጀር ጀኔራል ሙሉጌታ ቡሊ የክብር ዘበኛ አዛዥና I,ባህል ሚኒስትር

ደጀዝማች ገረሱ ዱኪ የኢሊባቡርና I,ጎሙገፋ አስተዳዳሪ

ሜጀር ጀኔራል ደምሴ ቡልቲ የሁለተኛው ክፍለ ጦር አዛዥ

ሌ ጀኔራል ጃጌማ ኬሎ የአራተኛው ክፍለጦር አዛዥና የባሌ አስተዳደር

ፊታውራሪ ለማ ወልደጻድቅ የሲዳሞ ምክትል አስተዳደር

ሜ ጀኔራል አበራ ወልደማርያም የአየር ሓይል ምክትል አዛዥ

ደጃዝማች በቀለ ወያ የጨቦና ጉራጌ አስተዳደር ከዛም የጨርጨር አስተዳደር

ደጃዝማች ካሳ ወልደማርያም የአዲስ አበባ ዩኒጸርሲቲ ፕሬዘዳንትና የእርሻ ሚኒስቴር

አንባቢያን መረዳት ያለብን ሁላችንም በመጀመሪያ ደረጃ ኢትዮጵያውያን መሆናችን ነው፤ ሕዝባችን በጋብቻ, በእምነት በባሕል የተሳሰረ በመሆኑ መሰረት የሌለው ታሪክ እያነበነቡ ሊበታትኑን የሚያስቡትን ታሪካዊ መረጃ እያቀረብን ወግዱ ልንላቸው ይገባል፤ ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ነው፤ ምኒሊክም ያስተማሩን መቻቻልን አንድነትንና ፍቅርን ነው፤
Moresh Info.

በደረጃ ምደባው በአጥቢያዎች የተከማቸውን ከፍተኛ የአገልጋዮችና የሠራተኛ ቁጥር በማሠልጠንና ማብቃት ማደላደልና ማሸጋሸግ እንጂ ማፈናቀል አይኖርም ተብሏል ገዳማትና አድባራት በፋይናንስ ፖሊሲው መሠረት ከዓመታዊ በጀታቸው ቀሪ ከሚኾነው ገንዘባቸው 60 በመቶውን ለልማት ተቋማት ማቋቋሚያና ማስፋፊያ (የልማት ፈንድ) ይመድባሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማት፣ አድባራት እና አብያተ ክርስቲያናት ያሉበትን ኹኔታ ተገንዝበው አገልግሎታቸውን የበለጠ በማስፋፋት …

Image

ዛሬ ላስነብባችሁ ያሰብኩት ቀደም ሲል የጥራት እና ደረጃዎች መዳቢ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ተብሎ ይጠራ ስለነበረው አሁን ለአራት ተከፋፍሎ እንዲጠፋ ስለተደረገ ተቋም ነው፡፡ መስሪያቤቱ ምርት እና አገልግሎችን በመቆጣጠር የሸማቹን ደህንነት እና ጤንነነት ማስጠበቅ ፤ የገቢና ወጪ ምርቶችን ጥራት በመከታተል ጉልህ ድርሻ እንዲያበረክት ታስቦ የተቋቋመ ነው፡፡መስሪያቤቱን ለረጅም ዓመታት በበላይነት ይመሩ የነበሩት አቶ መሳይ ግርማ ሲባሉ በውስጡ የፍተሻእናካሊብሬሽን አገልግሎት ዳይሬክትሬት፣የሰርተፊኬሽ አገልግሎት ዳይሬክትሬት፣የኢንስፔክሽን አገልግሎት ዳይሬክትሬት፣የደረጃዎች ዝግጅት ዳይሬክትሬት፣ የስልጠናአገልግሎት ዳይሬክትሬት እና የፋይናንስ ዳይሬክትሬት እና ሌሎች የአገልግጎች ዘርፎች ነበሩት፡፡አቶ መሳይ መስሪያቤቱን ከ16 ዓመት በላይ አስተዳድረዋል፡፡ድንገት ባልተጠበቀ ሰዓት ከአቶ መሳይ እውቅና ውጭ 3 ሰዎች አቶ ተክኤ ብርሀኔ ከመቀሌ፣አቶ ደቻሳ ጉሩሙ ከጅማ እና አቶ ዳንኤል ዘነበ ከሀረርጌተመልምለው ወደ መስሪያቤቱ ተመደቡ፡፡ሰዎች ሳይፈለጉ መመደባቸው ብቻ ሳይሆን በወቅቱ እንዲከፈላቸው የተፃፈላቸው የደመወዝ መጠንም በመስሪያቤቱ የደመወዝ ስኬል የሌለ፤ ካላቸው የትምህርት እና የስራ ልምድ ጋር ምንም አይነት ዝምድና ስለሌለው አቶ መሳይ መክፈል አልችልም በማለት አንገራገሩ፡፡እነሱ መች የዋዛ ቢሆኑ እና እስከ ጠቅላይ ጽ/ቤት የተዘረጋ ሰንሰለት ስለነበራቸው በስልክ ተደውሎላቸው ሳይወዱ በግድ መክፈል ጀመሩ፡፡ እነዚህ ሰዎች በ2002 ዓ.ም ለሚካሄደው ምርጫ ቅድመ ዝግጅት እንዲረዳ ከየክልሉ ተፈልገው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ሀዋርያ ሁነው ወደ ፌዴራል መንግስት የመጡ ናቸው፡፡ተክኤ በስፓርት ፣ደቻሳ በሂሳብ እና ዳንኤል በማኔጅሜንት ተመርቀዋል፡፡ሲመጡ የሚያርፉበት የኪራይቤቶች የሚያስተዳድረው ሰፋፊ ግቢየተዘጋጀላቸው ሲሆን ዳንኤል ከአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጽ/ቤት አጠገብ፤ተክኤ እና ደቻሳ ደግሞ 22 አካባቢ ባለ ሰፋፊ ግቢ እንዲኖሩተመቻችቶላቸዋል፡፡ዋናው የቅርብ ጊዜ አላማቸውም በ2002 ለሚደረገው ምርጫ የመንግስት ሰራተኛውን ከኢህአዴግ ጎን ማሰለፍ እና ቀጣይ አመራሮችን ማዘጋጀትነው፡፡በዚህም መሰረት ባሉበት ቀበሌ በምርጫ ጣቢያ ሀላፊነት ተመድበው ይሰራሉ፡፡በተጨማሪም መንግስት በቢ.ፒ.አር.(business process reengineering) ብሎ ወደፊት ሊዘረጋ ላቀደው የሰራተኞች ማፈኛ መንገድ የራሱን ታማኝ የስለላ ሰዎች ወደመሲሪያቤቱ ያስገባል፡፡የአዲሶቹን ተመዳቢዎች አመጣጥ ተከተሎ በመስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የፍረሃት ድባብ ተፈጠረ፡፡እነሱ ሰራተኞችን ወደሚጭነው ሰርቪስ ሲገቡ አንድም ሰው ትንፍሽ አይልም፡፡የአውቶቡሱ ሰው ሁሉ በጸጥታ ይዋጣል፡፡ጆሮ ጆሮ እያሉ ያንሾካሽካሉ፡፡በእረፍት ሰሀት እነሱ በተቀመጡበት አካባቢ አብሮ ተቀምጦ ሻይ ቡና የሚል የለም፡፡ሲመደቡ የኮሙኒኬሽን ሰራተኞች ተብለው ሲሆን ከመስሪያቤቱ እውቅና ውጭ ከነአቶበረከት ሰምኦን ጋር በየሳምንቱ ስብሰባ እና የመረጃ ልውውጥ ያደርጋሉ፡፡ከሳይንስና ቶክኖሎጂ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ ጋር ከፈለጉ በአካል መኪና አዝዘው ካልፈለጉ በስልክ በቀጥታ መገናኘት ይችላሉ፡፡አቶ መሳይ እና ሌሎች የመስሪያቤቱ ከፍተኛ አመራሮች የማያውቁት መረጃ ከነሱጋ ይገኛል፡፡በዚህ የአንድ አመት ቆያታቸው በመስሪቤቱ ደጋፊዎችን ማፍራት አልቻሉም፡፡
በ2003ዓ.ም የቢ.ፒ.አር ጥናት ሲጀመር አዲስ የመጡት ካድሬዎች የጥናት ቡድን መሪ እየተባሉ ተመደቡ፡፡ቢ.ፒ.አር ለመስራት ቀርቶ ስለመስሪቤቱ አሰራር በቂ እውቀት የሌላቸው ሰዎች መስሪያቤቱን አፍርሶ እንደአዲስ የማደራጀት ስራ በእነዚህ ሰዎች ስር ወደቀ፡፡በዚህም ተቀራራቢ ስራዎችን በጋራ ማደራጀት በሚል ሰበብ ከብሄራዊ የጨረር መከላከያ አንዱን መምሪያ በማፍረስ፤የክሊነር ፐሮደክሽን መስሪያቤትን ሙሉ በሙሉ፤የሳይንስ መሳሪያዎች መስሪያቤትን ሙሉ በሙሉ አፈራርሰው አነዚህን መስሪያቤቶች ከደረጃ መዳቢ ባለስልጣን መስሪያቤት ጋር በማዋሀድ አራት የተለያዩ መስሪያቤቶችን ለመፍጠርጥናቱ ተጀመረ፡፡አዲስ የተጠኑት መስሪያቤቶች1.Meterology institute, 2.Accreditation biro, 3 .Standards agency4. Conformity assessment enterpriseይባላሉ፡፡ እነዚህ መስሪያቤቶች በተጠኑበት ወቅት ለጥናት ቡድኑ በየሳምንቱ በጣም ውድ በሆኑ ሆቴሎች የእራት ግብዣ እየተዘጋጀ ለ6 ወር ያክል ተደከመበት፡፡ወደመጨረሻው ምእራፍ ሲቃረብ የጥናት ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ናዝሬት ውስጥ ከ10 ቀን በላይ ሆቴል ውስጥ ተቀምጠው እንዲሰሩ ተደረገ፡፡በመጨረሻም የጥናቱን መጠናቀቅ አስመልክቶ በአቶ ጁነዲን ሳዶ አማካነት አርባምንጭ ለሶስት ቀናት ድል ያለ ግብዣ ተደረገ፡፡ከአርባምንጭ መልስ ሁሉም በሳይንስ እና ቴክኔሎጂ ሚ/ር ስር የሚገኙ ሰራተኛ ለገሀር በሚገኘው የመንገድ እና ትራንስፖርት መሰብሰቢያ አዳራሽ ጠቅላላ ስብሰባ ተካሄደ፡፡በስብሰባው የየጥንት ቡድኑ ሀላፊዎች የጥናታቸውን ውጤት ይፋ አደረጉ፡፡የሀገራችን ችግሮች ተዳሰሱ፡፡ለችግሮች መፍትሄ ይሆናሉ የተባሉ አማራጮች ከየአቅጣጫው ጎረፉ፡፡አብዛኞች ወጣቶች ተስፋ ያደረጉትን በየመስሪያቤቱ ያለውን ብልሹ አሰራር እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል አስተያየታቸውን ሰጡ፡፡በዚህ ውይይት ከተነሱት ውስጥ እስካሁን የማሰታውሳቸው አቶገብረጊዳን ገብረመስቀል በቅጽል ስሙ(GG) “በየመስሪያቤቱ ያለውን የተማረ የሰው ሀይል እጥረት ለመቅረፍ መንግስት በውጪ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ገብተው እንዲሰሩ ቢደረግ መልካም ነው፡፡ለምሳሌ እንደኢንጅነር ቅጣው እጅጉ አይነት ሰዎች ነበሩዋት ሌሎችም እንዲህ አይነቶች ይኖራሉ ብሎ ተናገረ፡፡”በእረፍት የንግድሚኒስትሩ የአቶ ታደሰ ሐይሌ ባለቤት ወ/ሮ አልማዝ ካህሳይ ይህን የተናገረውን ልጅ ጠራቸው እና ስሙን ጠይቃ “አንተማ የእኛው ነህ እየውልህ ኢ/ር ቅጣው በመንግስታችን ላይ ሊሰራ አቅዶት የነበረውን ስለማታውቅ ነው እንዲህ ያልከው፡፡በቶሎ ቀጨው እንጂ ቢቆይ በጣም አደገኛ ነበር፡፡እንዲህ አይነቱን ሰው ስሙን መጥራት የለብህም” አለችው፡፡ይቅርታ ወ/ሮ አልማዝ እኔ እሱን አላውቅም ነበር ሲል መለሰላት፡፡ሌላው ከጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት የመጣ አቶ ጸጋዬ የሚባል አንድ ተናጋሪ በንግግራቸው መሀል ጣል ያደረጉዋት ቀልድ መሰል መልክት ሁሌም ትከነክነኛለች፡፡አቶ ጸጋዬ “አማርኛ እጅዋን አገኘች በግል ትምህርት ቤት ውስጥ አማርኛ መናገር እና ድንጋይ መወርወር ያስቀጣል ተብሎ በጉልህ ተጽፎ አንድትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ አንብቤያለሁ” ብለው አረፉ፡፡ሌላው ጠያቂ አብዲ ዱጋ ይባላል፡፡አብዲ ጥያቄውን ያቀረበው ለሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ነው፡፡ጥያቄው “ኦሮሚያ ክልል ውስጥ አየተካሄደ ያለው የአበባ እርሻ ልማት የአካባቢውን አፈር እና ውሃ እየበከለው ነው፡፡በዚህም የተነሳ እንስሳት ይሞታሉ ሰዎች ይታመማሉ፡፡የሰራተኞችም ህይወት አደጋ ውስጥ ነው የሚከፈላቸውም ገንዘብ እዚህ ግባ የሚባል አደለም፡፡እንዲያውም ባለ ሀብቶች ከሌሎች ሀገሮች ሲባረሩ ነው ወደዚህ ሀገር የመጡት ይባላል እና ይህን እንዴት ያዩታል? ሲል ጠየቀ፡፡አብዲን የገጠመው ከፍተኛ ውግዘት ነው፡፡ለውግዘቱ መነሻም በወቅቱ የአበባ እርሻ ልማት ሲጀመር አቶ ጁነዲን የኦሮሚያ ርእሰመስተዳድር ስለነበሩ እሳቸውን እንደተቃወመ ተቆጠረ፡፡አብዲም ያጠናው ባዮሎጂ ስለነበር ሙያዊ ትንታኔ መስጠቱን ቀጠለ፡፡ክርክሩ እየከረረ ሲሄድ ጓደኞቹ ዝም እንዲል አደረጉት፡፡ስልጠናው ለ5 ቀናት በፍረሃት እንደተዋጠ ተጠናቀቀ፡፡ከዚህ ሰብሰባ መልስ በቀጥታ ሁሉም መስሪያቤት ወደ ሰው ኃይል ምደባ እንዲገባ መመሪያ ተላላፈ፡፡
ስብሰባው አርብ ተጠናቆ ሰኞ ጠዋት አቶ መሳይ ከመስሪያቤቱ በፍቃዳቸው እንዲለቁ ትእዛዝ እንደተሰጣቸው ለሚቀርቡዋቸው ሰዎች ሲናገሩ የኮሚኒኬሽን ሰራተኞቹ እነ ተክኤ ደግሞ ምደባውን እንዳያስተጉዋጉል በማሰብ አስቀድሞ መባረሩን በየቢሮው እየዞሩ ያውጃሉ፡ይህን ተከትሎ መስሪያቤቱ ሰው የሞተ ያክል በኡኡታ በልቅሶ ታመሰ፡፡አብዛኖች መልካም ተግባሩን ለሰራተኛ አዛኝነቱን እያሰቡ አባታቸውን በሞት የተነጠቁ ያክል ከልብ አዘኑ፡፡በዚሁ እለት የንግድ ሚኒስትሩ የአቶታደሰ ሀይሌ ባለቤት ወ/ሮ አልማዝ ካህሣዬ መስሪያቤቱን እንዲያስተዳድሩ ተሾሙ፡፡የተለያዬ ዳይሬክተሮችን ሹመት ሰጡ፡፡በዚህ ወቅት ቀደም ሲል ወያኔን እንደሚቃወሙ የሚታወቁት እና ከአቶ መሳይ ጋር ቀረቤታ አላቸው የተባሉ ነባር ዳይሬክተሮች ተነስተው በምትካቸው የኢህአዲግ አባላትንመመደብ ተጀመረ፡፡ምደባውም የሚካሄደው እያንዳንዱ ሰራተኛ እየተገመገመባለው ችሎታነው ይባል እንጅ ነገር ግን አስገራሚው እና ያን ያክል የተደከመበት ጥናት የግምገማውን 75% የሚይዘው ከስራው ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው አመለካካት የሚባል ነገር ነው፡፡ሰራተኞች በወቅቱ ያነሱት የነበረው ጥያቄ አመለካከት በምን ሊለካ ይችላል የእኔን አመለካካት ምን እንደሆነ ማን ያውቀዋል የሚል ነበር፡፡ግምገማውን የሚሞሉት ቀደም ብየ የጠቀስኳቸው እነ ተክኤ፣ደቻሳ እና ዳናኤል ናቸው፡፡እነዚህ ሰዎች እንደመሰላቸው የግምገማ ነጥቡን መስጠታቸው ሳያንስ ምደባውን በዋናነት የሚመሩት እነሱ ናቸው፡፡ወደደረጃ መዳቢ መስሪያቤት የመጡትን የሌላ አዳዲስ መስሪያቤት ሰራተኞች መልካቸውን ሳይቀር የማያውቁዋቸውን ሰዎች ግምገማ በድፍረት ይሞሉ ነበር፡፡በመሀል በተቃዋሚነት ያልተፈረጁትን እና አባል መሆን የሚፈልጉ ካሉ በምደባ እና በእድገት አያባበሉ ወደድርጅቱ የማግባባት ስራ ተከናወነ፡እኔ ስራየን እንጂ የፓርቲ አባል መሆን ፍላጎት የለኝም ያሉት ደግሞ ቀደም ሲል በተለያዩ የውጭ ሀገራት ሳይቀር ከፍተኛ ስልጠናዎችን ተከታትለው ስራቸውን በብቃት ሲወጡ የነበሩ በርካታ ባለሙያዎች አብዮታዊ ዲሞክራሲን ባለመቀበላቸው ብቻ ዘራቸው እየታየ ከስራቸው ከተባረሩትመካከል ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ለማሳያ ያክል የቀረቡ ሲሆኑ አንድም የትግራይ ብሄር ተወላጅ አለመባረሩን አንባቢያን ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ሌላው እና አስገራሚው ነገር በወቅቱ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን እያገለለ እየተካሄደ ያለው ምደባ ያሳሰባቸው የኢህዴድ አባላት ጥያቄያቸውን ለሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ቢያቀርቡም ወ/ሮ አላማዝ ካህሳይ እያንዳንዱን ኦሮሞ እቢሮአቸው ጠርተው አርፈው እንዲቀመጡ አለዚያ እንደሚባረሩ በዛቻ ገልጸውላቸዋል፡፡በወቅቱም ከፍተኛ ተቃውሞ ያሰማው አቶ ሙሉጌታ መኮነን ያለስራ ለአንድ ዓመት ደመወዝ ብቻ እየተከፈለው ሊሰራ በማይችል ዘርፍ የቡድን መሪ ሁኖ ሲመደብ በስሩ ግን ምንም ሰው አልነበረም፡፡
ተ.ቁ ስም የነበራቸው ሀላፊነት ብሄር
1 አቶ መሳይ ግርማ የጥራት እና ደረጃ መ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ኦሮሞ
2 አቶ ጋሻው ወርቅነህ የጥራት እና ደረጃ መ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር አማራ
3 አቶ ተፈራ ማሞ የኤሌክትሪክል ላብራቶር ሃላፊ ኦሮሞ
4 አቶ ሀይሉ የመሳሪያ ጥገኛ አገልግሎት ሃላፊ ኦሮሞ
5 አቶ ደሬሳ ፉፋ የሰርተፊኬሽን አገልግሎት ዳይሬክተር ኦሮሞ
6 አቶ መስፍን የስልጠና አገልግሎት ዳይሬክተር አማራ
7 አቶ አዱኛው መስፍን የጥራት ማኔጅሜንት አሰልጣኝ አማራ
8 አቶ እንዳ የኢንፎርሜሽን አገልግሎት ሀላፊ አማራ
9 አቶ አመሃ በቀለ የጥራት ማኔጅሜነት አሰልጣኝ አማራ
10 አቶ ሂርጳ የጥራት ማኔጅሜነት አሰልጣኝ ኦሮሞ
11 አቶ መረሳ የሰርትፊኬሽን ኤክስፐርት ኦሮሞ
12 አቶ ቴወድሮስ ዘካሪያስ የፍተሻ ላብራቶር ኤክስፐርት አማራ
13 አቶ ልኡል የባህርዳር ቅርንጫፍ ሀላፊ አማራ
14 የሰርትፊኬሽን ሲስተም ኦዲተር የነበሩት ኦሮሞ
15 የድሬደዋ ቅርንጫፍ ሀላፊ የነበሩት አማራ
16 የናዝሬት ቅርንጫፍ ሀላፊ የነበሩት ኦሮሞ
17 የሀዋሳ ቅርንጫፍ ሀላፊ የነበሩት ደቡብ
ታማኝ የህወአት አባላት በባትሪ ከሌላ ቦታ ተፈልገው ያለ ልምድ እና ችሌታቸው በከፍተኛ አመራርነት ሲመደቡ የተለሳለሰ አቋም ያላቸውን እና የአባልነት ጥያቄ ሲቀርብላቸው ጥያቄውን የተቀበሉ ነባር የመስሪያቤቱ ሰራተኞች የፍርፍሪው ተቋዳሽ ሁነዋል፡፡በዚህ ምደባ እስከቡድን መሪ ያለው ሀላፊነት ያለ ፓርቲ አባልነት ወይም ያለ ትግራይ ተወላጅነት በምንም መልኩ ለተራው ሰራተኛ አይሰጥም፡፡

ተ.ቁ ስም ቀደም የነበራቸው ሀላፊነት አሁን የተሰጣቸው ሀላፊነት ብሄር
1 ወ/ሮ አልማዝ ካህሳየ የኢንስፔክሽን አገልግሎት ዳይሬክተር የደረዳዎች ዋና ዳይሬክተር ትግሬ

2 አቶ ወንዶሰን ፍስሃ የካሊብሬሽን አገልግሎት ሀላፊ የሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ትግሬ

3 አቶ አርአያ መከላከያ ኢንጅነሪንግ የአክረዲቴሽን ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ትግሬ

4 አቶ ጋሻው ተስፋዬ የፍተሻ ላብራቶር ኤክስፐርት የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ትግሬ
አቶ ገብሬ ኝግድ እና ኢንዱስትሪ ኤክስፐርት በደረጃዎች ኢጀንሲ ዳይሬክተር ትግሬ

6 አቶ ብርሀኑ ተካ ረዳ የፋይንነስ አስተዳደር ዳይሬክተር የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የፋይናንስ ዳይሬክተር ጉራጌ

7 ወ/ሮ ገነት ገ/መድህን የፍተሻ እና ካሊብሬሽን አገልግሎት ዳይሬክተር የአክረዲቴሽን ጽ/ቤት ዳይሬክተር ትግሬ

8 ወ/ሮ ብርሀን ብሂል የአዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጸሀፊ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የሰው ሀብት እስተዳደር ሀላፊ ትግሬ

9 አቶ ብርሀኑ ተካ የሰርቪስ ሹፌር የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የተራንስፖርት መምሪያ ሀላፊ ትግሬ

10 አቶ ተክኤ ብርሀኔ የኮሙኒክሽን ሰራተኛ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ትግሬ

11 አቶ ዳዊት የሰርቪስ ሹፌር የሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት የትራንትፖርትመምሪያ ሀላፊ ትግሬ

12 አቶ ጸጋዬ ኢንስፔክተር የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ሀላፊ ትግሬ

13 አቶ ዘነበ ኢንስፔክተር የገበያ ጥናት ሀላፊ ትግሬ
ቀደም ሲል እንደማናኛውም ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሉ የመንግስት መስሪያቤቶች የሚታዩ ችግሮች ቢኖሩም የተወሰደው እርምጃ ግን የወቅቱን የትግሬዎች የንግድ እንቅስቃሴ ያላንዳች ተቆጣጣሪ እንደፈለጉት ለማሽከርከር ታስቦ አንደሆነ ይታወቃል፡፡ለዚህም መነሻ የሚሆነው በተለያዩ ጊዜያት በቆርቆሮ፣በብረታብረት፣በማዳበሪያ፣በሳሙና፣በከብሪት፣በሲሚንቶ ፣በዘይት፤በጨርቃ ጨርቅ ፣ በባትሪ ድንጋይ፣በኤሌክትሪክ ገመዶች የመሳሰሉት ምርቶች ላይ ተደጋጋሚ ችግር ተከስቶ በበላይ አካል የስልክ ትእዛዝ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምርቶች ለህብረተሰቡ እንዲሰራጩ ተደርጉዋል፡፡ለአብነት ያክል የአቢሲኒያ ሲሚንቶ ፋብሪካ በጥራት ጉድለት ምክንያት እንዳያመርት አገዳ መስሪያቤቱ ሲያስተላልፍ በወቅቱ የከተማ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ካሱ ኢላላ ፍተሻውን ያከናወኑ ባለሙያዎችን በግላቸው ቢሮ ድረስ በማስጠራት ትክክል አደላችሁም፤ልማታችንን እያደናቀፋችሁ ነው፤ኢንቬስተሮች ወደ ሀገራችን እየመጡ እንዳይሰሩ መሰናክል እየፈጠራችሁ ስለሆነ አቁሙ ሲባሉ የመስሪያቤቱ ሀላፊዎች እገዳውን ባስቸኩዋይ አንዲያነሱ ቀጭን ትእዛዝ አስተላለፈዋል፡፡መስሪያቤቱም እንዲፈርስ የተደረገው ባለሞያዎችም የተፈናቀሉት ሆን ተብሎ ያለ አግባብ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲረዳው ያስፈልጋል፡፡

ህዝብን ማዳመጥ ያልቻለው ራሱን የሚያዳምጠው ወያኔ
ስብሰባ ስብሰባ ስብሰባ…..ይቀጥላል ይህ ወያኔያዊ የአውሬ ወለድ በሽታ

ምንሊክ ሳልሳዊ…የህዝብ ጥያቄዎች አለመደመጣቸው ውጤቱ የችግሩን ጥልቀት ስፋት እና እያስከተለ ያለውን ቀውስ ሊታየው ያልቻለው ወያኔ በአገር ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ጫና ከመፍጠሩም በላይ ህዝቡን ወደባሰ የድህነት አረንቋ እየከተተው ነው:: ይህ ደሞ ወያኔ እንደ መንግስት ለህዝብ ጥያቄዎች አትኩሮት አለመስጠቱ ነው::ሕዝብ ችግሩን የሚናገረው በስብሰባ ብቻ አይደለም፡፡ በየቀበሌው፣ በየክፍለ ከተማው፣ በየከተማ አስተዳደር እርከኖች፣ በየመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ በየክልሉ፣ ወዘተ በማመልከቻ፣ በቃልና በጽሑፍ በየደቂቃውና በየሰኮንዱ አቤት እያለ ነው፡፡ የሰሚ ያለህ እያለ እየጮኸ ነው፡፡ መብቴ ተረገጠ፣ ንብረቴ ተቀማ፣ ጉቦ ካልሰጠህ ችግርህ አይፈታልህም ተባልኩ፣ አድልዎ ተፈጸመብኝ፣ ወዘተ እያለ ነው፡፡ ነገር ግን ሕዝቡ የሚያዳምጠው የሚያዳምተው አላገኘም ካድሬዎች ከህዝብ ጥያቄዎች በፊት ፖለቲካውን እና ተቃዋሚዎችን ወደ ማሳደድ አዘንብለዋል::

ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን እናዳምጣቹ በሚል ሰበብ ችግራችሁን ተወያይተን እንፍታ በሚል ሰበብ የተለያዩ ስብሰባዎች የህዝብን ጭንቅላት ለመስረቅ በጀት ለአበል ተመድቦ እበማካሄድ ምንም ፋይዳ ያሌላቸው እና ለሚዲያ ፍጆታ ለማዋል የሚደረጉ ከመሆናቸውም በላይ ወያኔ ግን የሚወስነው ጉዳይ ለህዝብ እንቅፋት የሆነ እና ከስብሰባው እና ከተሰብሳቢ ምልክታ ውጪ የፖለቲካ አጀንዳውን ለማስፈጸም ብቻ ነው::

በስብሰባ ስም የሰበሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የተጠሩበት አጀንዳ ውጪ ራሱ ተናግሮ ራሱ እንደፈለገ አውጥቶ እና አውርዶ ራሱ ወስኖ የራሱን ድምጾች እንደገደል ማሚቱ የሚያዳምጠው ወያኔ ምንም አይነት መንግስታዊ እና ህዝባዊ ፋይዳዎችን ሲፈጽም አልታየም::ህዝብን ማዳመጥ አለመቻሉ ህዝብ ጥያቄ ሲያነሳ እንደ ጭራቅ መመልከቱ የመብት ጥያቋ ያለሳ ሁሉ እንደ ጠላት እና እንደ ተቃዋሚ መፈረጁ ወያኔ ህዝብን ለማዳመጥ ጊዜ እንዳሌለው የሚያሳዩ ጉዳዮች ናቸው::ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አውቅልሃለሁ ከተባለው ውጭ ጥያቄ አንስቶ ቢገኝ ህገወጥ ነው:: የፖለቲካ ፓርቲ ሰልፍ ቢጠራ ህዝብ በአደባባይ የአገልግሎት መብቱን ቢጠይቅ በስብሰባ ላይ የተሰማውን ቢተነፍስ ወዘተ…ህገወጥ ነው::

በአለማችን ላይ አንዱ አንዱን ካዳመጠ የማይፈታ የማይቀረፍ ችግር የለም:: በሰለጠነ ዘመን እኔን ብቻ ስሙኝ ብሎ ድርቅ ያለ አስተሳሰብ ማንጸባረቅ ተቀባይነት የለውም:: ህዝብን ማዳመጥ የቻለ መንግስት ነኝ የሚል ሁሉ ሃገራዊ ስኬቶቹ ጉልህ ናቸው::ህዝብን ማዳመጥ ያልቻለ በጉልበት የሚኖር መንግስት የግእዜ ጀግና ስለሆነ ይወድቃል:: ወያኔም እኔ ብቻ ነኝ ህዝባዊ ሌላው ህገወጥ ነው ቢልም ለህዝብ ችግሮች ግን ምንም አይነት መፍትሄ ሊሰጥ ባለመቻሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግሮች በስፋት እየጨመሩ መተዋል::

በየስብሰባው ገበሬው ነጋዴው መምህሩ ተማሪው ፖለቲከኛው ጋዜጠኛው ….ባጠቃላህ ህዝቡ ብሶቱን አሰምቷል::የህዝብን ችግር እናዳምጣለም በሚል ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቦ ስብሰባዎች በየፈርጁ ተጠርቷል::ሁሉም ችግሩን ተንፍሷል:: …መፍትሄ ግን የለም:: የህዝብን ጥያቄ ግን ወያኔ ሊያዳምጥ አልፈቀደም ….ይልቁኑ ለሚዲያ ፍጆታ እና ለፖለቲካ አጀንዳነት ተጠቅሞበታል:: በየስብሰባው አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ተናግረዋል የተባሉ ታፍነዋል ታስረዋል ተሰደዋል ተገድለዋል ከስራ ተባረው ቤተሰባቸው እንዲበተን ተደርገዋል::ታዲያ ህዝብን ማዳመጥ ተብሎ የሚጠሩ ስብሰባዎች ወያኔ ራሱን እያዳመጠ ህዝቡን እየደፈጠጠ ነው::

ህግ አለ ህገመንግስት እናስከብራለን የሚለው ወያኔ መጀመሪያ ራሱ ህገ መንግስቱን እና ያወጣውን ህግ ማክበር አለበት::አንድ መንግስት ህዝብን ያዳምጥ ሲባል መለመን ወይንም ምጽዋት መጠየቅ አይደለም:; ህዝብም ማዳመጥ የማንኛውም አመራር ህጋዊ ግዴታ ነው::ህዝቦች ከህግ እና ከመብት አንጻር ተደምጠው መፍትሄ ሊሰጣቸው ይገባል::መንግሥት ሕዝብን የሚያዳምጠው በሕገ መንግሥቱ ግዳጅነት አይደለም፡፡ የሕዝብ ሰራተኛ ነኝ የሚል ሥልጣን የያዘ ፓርቲና መንግሥት፣ ሕዝብ መረጠኝ የሚል ፓርቲና መንግሥት፣ የሕዝብ ከበሬታና አመኔታ ሊያገኝና ዓላማውን በተግባር ላይ ሊያውል የሚችለው ሕዝብን ሲያዳምጥ ብቻ ነው፡፡ ሥልጣን ላይ የሚቆየው ሕዝብን ሲያዳምጥ ብቻ ነው፡፡ ህዝብን የማያዳምጥ ራሱን የሚያዳምጥ የማይደመጥ ይሆናል፡፡

ነጻ አውጪ እስከመች???
የትግራይ ህዝብ ነጻ አልወጣምን??? ሕወሓት ማንን ነጻ ለማውጣት ነው በዚህ ስሙ የቀጠለው?
እውን አሁንም በትግራይ ህዝብ ላይ የተንሰራፋ የጨቋኝ ቡድን አለ?

ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ከአነሳሱ ሲጠነሰስ የትግራይ ህዝብን ነጻ በማውጣት ሲሻው በመገንጠል ሲሻው ታላቋን ትግራይ በመመስረት ….በሚሉ የመከኑ ይሁኑ ገና ያልተሳኩ አሊያም (በፕሮሰስ ላይ ባሉ ?)ባልታወቁ መርሃግብሮች ላይ ተነድፎ ወደ ጫካ መግባቱ እውን ቢሆንም ያላሰለሱ ድሎች መገኘት የጀመሩት ግን በ1980ዎቹ የሃገራዊ ፋይዳው ታይቶ ከተፈጠሩት ሁሉን አቀፍ የጦር አውድማዎች በኋላ ነው::…ሕወሓቶች ኢሕዴንን እና ኦሕዴድን አጣምረው ኢሕኣዴግ በሚል ተሰይመው የነበሩት የዛኔዎቹ ታጋዮች ለዲሞክራሲያዊ ምስረታ እና ለህዝባዊ እኩልነት የታገሉ መሆኑ እሙን ቢሆንም የተነሱበት አላማ የተሰዉለት ይህ ነጥብ ግን ከአፈር ጋር ደባልቀውታል:: የሰምዓታቱንም ፍሬ እዛው በረሃ ጥለውት መተዋል::

የዳግማይ ወያኔ አነሳስ የትግራይን ህዝን ነጻ ለማውጣት ነው እስካለ ድረስ እና ራሱን የትግራይ ህዝቦች ነጻ አውጪ ብሎ ከሰየመ በኋላ ደርግን መፋለሙን ተከትሎ ከደርግ ጭቆና የትግራይን ህዝን ነጻ እንዳወጣው እየነገረን ነው::አሁንሳ ሕወሓት ማንን ነጻ ለማውጣት ነው በዚህ ስሙ የቀጠለው? እውን አሁንም በትግራይ ህዝብ ላይ የተንሰራፋ የጨቋኝ ቡድን አለ? ወይንስ ነገሩ ከወዲሁ ነው የቀድሞዎቹ ጨቋኝ መደቦች እነእንትና ካልወደሙ የህ ሕወሓት የሚለው ስሙን አይቀይርም??/

ሕውሓት የትግራይን ህዝብ ነጻ ወተሃል ካለው 22 አመት አልፎታል:: የቀድሞ ታጋዮች የአሁን ገዢዎች ግን አሁንም ይህንን ስም ይዘው ቀጥለዋል::ለምን ግን …? የትግራይ ህዝብ ነጻነቱ የሚረጋገጠው ሕወሃትም ስሙን ቀይሮ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የሚባልበት ቀን ይናፍቃል:: ኢህዴን እንኳን መዐሕድን ተከትሎ /ቀንቶ ብኣዴን ተብሏል…ሕወሓት ግን እስከመቼ ድብቅ አላማ ይዞ እንደሚጓዝ አልረዳ ብሎናል:: ወይስ ይህን ስም የሚጠቀመው አንድ የትግራይን ነጻነት እንደኤርትራ በሪፍረንደም እስኪያስረግጥ ነው ወይንስ እነእንትና…እንስም አይጠሬ የድሮዎቹ የጨቋኝ መደቦች የሚል መጠሪያ የተሰጣቸው ኢትዮጵያውያን ዘራቸው ከምድረ እትዮጵያ ተጠራርጎ እስኪጠፋ…???? የህገመንግስቱ አንቀጽ 39 ባለበት የሚቆየው ምን እስኪመሰረት ድረስ ነው? የመጀመሪያው የሆነው ኢትዮጵያዊነትን ከአያት ቅድመ አያቱ የወረሰው የትግራይ ህዝብን በአምባገነኖች ጭቆና ስር ለማስቀጠል ይሆን??/ስላልገባን ይነገረን::

ዲይስፖራ ፖለቲከኞች እና ወያኔ = ለሃገር የማይበጁ የጥላቻ አንጃዎች
የህዝብን አንደበት እንተነፍሳለን::

ምንሊክ ሳልሳዊ ሁለቱን በየፈርጃቸው በትግል አካሄዱ ዙሪያ ስንመለከታቸው የፖለቲካ አጀንዳቸውን በኢኮኖሚ በደቀቀው ህዝብ እና በነጻነት ጥያቄ በሚያነባው ህዝብ ላይ ለመጫን እየተራወጡ የሚሄዱ በጥላቸ የተሞሉ አንጃዎች ናቸው:: የወደደ ይውደድ የጠላ ይጥላ የህዝብን አንደበት ግን እንተነፍሳለን::ምናልባት ወያኔን ተወት አድርጓት እና ዲያስፖራ ፖለቲከኛ ነኝ ጋዜጠኛ ነኝ የሚለው ጣማማ እና በጥላቻ የሚያነክስ ይህ ነገር ላይዋጥለት ይችላል::
===== መዋጥ ከቻለ ይዋጥ መወጥ ካልቻለ ያስመልሰው የራሱ ጉዳይ::=======

እኛ አንዴ በሃገር ውስጥ አንዴ በውጭው በስራ ጉዳዮች የምንኖር ዜጎች ከወያኔ በባሰ መልኩ እያንገበገብን ያለው በአውሮፓ እና በአሜሪካ ተደብቆ መሰሪ እና በሃገር ላይ የጥላቻ ድብቅ አጀንዳውን እያራመደ ያለው ፖለቲከኛ ነውሃገር ወዳድ በሰው አገር የሚከራተቱ ዜጎችን ከግራ ቀኝ በተደቋቆሰ ፖለቲካ የሚያላትመው እና የዲያስፖራውን ሃገራዊነት ካለሞሶሶ ለማስቀረት የኢቶጵያን ህዝብ ትግል የሰው ሃገር የመኖሪያ ፍቃድ ማስገኛ ያደረገው የዲያስፖራ ፖለቲከኛ የጥላቻ ፖለቲካ ተሞልቶ ዘላለሙን በወሬ ትግሉን እየገደለው ይገኛል:: በሃገር ቤት ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በከፍተኛ ፍጋት ውስጥ ሲያሳልፉ ግማሹ ትግሉን መጦሪያ ሲያደርገው የኢትዮጵያን ህዝብ ከጭቆና አገዛዝ ማላቀቅ አልተቻለም::

የወያኔ ካድሬዎች ከሕወሓት መራሹ መንግስት የሚያገኙትን ጥቅም ለማስጠበቅ በከፍተኛ ጥላቻ ተሞልተው በሃገር ውስጥ በህዝብ ስቃይ ሲደሰቱ የተቃወመውን ሁሉ በማፈን በመግደር ወደ ኢስር ቤት በመወርወር የተቃወመ ሁሉ ጠላት ነው በሚል የእኛ እናውቅላቹሃለን አስተሳሰብ ተሞልቶ ህዝብን ሰቆቃ ውስጥ ከቶታል በፍራቻ አንገቱን ሰብሯል:: ውስጥ ለውስጥ በሚነዛ ሽብር የህዝብ ሚዲያዎችን ለፓርቲ ፍጆታ በማዋል በሚደረጉ የፕሮፓጋንዳ ሩጫዎች ለሃገር የማይበጁ መጥፎ ምግባራት በስፋት እየተፈጸሙ ነው::

ወያኔ የሚያራምደው የጥላቻ ፖለቲካ በጋራ ህዝቦች ለሃገራቸው በየመስኩ አስታውጾ እንዳያደርጉ በሃገራቸው ጉዳይ እንዳይሳተፉ እያደረገ ሲሆን ዲያስፖራው በተቃራኒ የሚያራምደው የጥላቻ ፖለቲካ ቁም ነገር አላባ ትግሎችን በመፍጠር ለወያኔ የስልጣን እድሜ ማስረዘሚያ በሩን ከፍቶለታል:: ዲያስፖራው የእርስ በእርስ መኮራኮም የበዛበት ፖለቲካ የሚያራምድ እና ዘላለሙን የአምባገነኖችን የማውደም ትግል ሳይሆን የወያኔን ጥላቻ የሚሰብክ አንዱ ከፍ ብሎ ሲያይ እዛው የፖለቲካ ጥጉ ላይ ጎትቶ ገደል ለመክተት የሚራወጥ ለሃገር የማይበጁ በጥላቻ የተሞሉ ስብከቶችን የሚያበዛ ትግሉን ያደነዘዘ የህዝብ እንቅፋት ነው::

ዲያስፖራው የሞላበት የጥላቻ ፖለቲካ ማስወገድ ከትግሉ በፊት ቅድሚያ ተግባሩ ነው:: አብዛኛው ዲያስፖራ በየስብሰባው እንደምናየው ሊያጨበጭብ የሚመጣው በወያኔ ላይ ያለውን የጥላቻ ፖለቲካ ተመርኩዞ እንጂ በትግል ስልቱ ላይ ያለውን ግንዛቤ ይዞ ነው:: አጨብጭቦ ዶላሩን አፍሶ የመኖሪያ ፍቃዱን የሚያድስበት የትብብር ደብዳቤ ተከብሎ ከዛ ሃገር የራሷ ጉዳይ:: ጠንከር ያለ ትግሉን የሚያጧጡፍ ሃተታ የማይዋጥላቸው ጋዜጠኞችም አንደኛው የትግሉ እሾህ ናቸው::በፖለቲካ ሽፋን ሃገር እና ህዝብ ይበዘበዛሉ ዲያስፖራው በቅንጦት ይኖራል::ይህ የጥላቻ ፖለቲካ የወለደው ጎል ነው:: ዲያስፖራው ለሃገር የሚበጅ እንቅስቃሴ የሚያደርግበትን ጊዜ እንናፍቃለን::

የወያኔ አገዛዝ እንደ እሳት የፈጀን ዜጎች የዲያስፖራው የተልፈሰፈሰ ትግል ደሞ እያንገበገን ይገኛል::ስለዚህ የህ ለሃገር የማይበጅ የጥላቻ ፖለቲካ ተወግዶ በጋራ ሃገር ከአምባገነኑ የወያኔ አገዛ የምትላቀቅበትን የጋራ ስልት መንደፍ ተገቢ ነው::

ምንሊክ ሳልሳዊ…ትናንትና ማታም ኢቲቪ ስለ አቶ መለስ ዜናዊ የተመሰከረውን ቆረጠው፡፡ ያ በ1984 ቤተሰቦቻቸውን ያጡትና አሳዛኝ ሰውዬ ትናንትናም በኢቲቪው ዶክመንተሪ እያለቀሱ ታዩ፡፡ እነ ዶክተር መረራ ጊዲና፣ ፕሮፌሰር መስፍን፣ ኢንጅነር ይልቃል፣ ግርማ ሰይፉ በሽብርተኝነት ስም መንግስት እያሸበረን ነው በማለታቸው ተብጠልጥለዋል፡፡

በሌላ በኩል ያ መከረኛ ሰውዬ የሰጡት ምስክርነት አሁንም ተቆርጧል፡፡ ባይቆረጥ ኖሮ ሰውየው ‹‹ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው መለስ ዜናዊ ነው!›› ነበር የሚሉት፡፡ ማን ይናገር የነበረ ቢሆንም የአሁኖቹ ወጣት የኢቲቪ ካድሬዎች ግን ቆርጠውታል፡፡ አዎ! ኢቲቪ አሁንም ዳግመኛ ቆረጠው፡፡ በእነ ዶክተር መረራና በእነ ፕሮፌሰር መስፍን ላይ ደግሞ የሌለውን መረጃ ቆርጦ ቀጥሏል፡፡ እነ አንዱ ዓለም አራጌ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው ይህን ነው የሚባል ምስክር ሳይቀርብባቸው እስር ቤት ውስጥ ታጉረዋል፡፡ ቤተሰባቸው ላይ ማን ጥቃት እንዳደረሰ፣ ማን ተጠያቂ እንደሆነ የተመሰከባቸው አቶ መለስ ግን ምስክርነቱ ተቆረጠላቸው፡፡ እነ አንዱ ዓለም አራጌ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ መፍትሄ አፈላላጊ እንዲህ እያለቀሰ ‹‹ቤተሰቦቼን ፈጁብኝ! ለዚህ ሁሉ ተጠያቂዎቹ እነሱ ናቸው›› የሚል ቢገኝ መስካሪው ካለው ባሻገር ሆድ አደር ‹‹ተንታኞችና ተመራማሪዎች፣ ጋዜጠኞች›› ለጥጠው፣ ጨምረውበት ስንት ሰቅጣጭ ፊልም ይሰራበት ነበር፡፡

አንዳንዴ ሳስበው ካድሬዎቹና ኢቲቪ (ያው ካድሬ ነው) አቶ መለስን ከአምላክ በላይ ይፈሯቸዋል/ያከብሯቸዋል፡፡ ምክንያቱም ቅዱስ መጽሃፉ፣ የእምነት አባቶች እግዚያብሄር ሰውን በውሃም ሆነ በሌላ ነገር ማጥፋቱን አይደብቁም፡፡ እስኪ ስለ ይሁዳም ሆነ ሌላ ከየትኛውም መላክ በተቃራኒ ስለሚገኙት አካላት የምታወቁ ንገሩኝ? ተከታዮቹ ጥፋታቸውን ይደብቁላቸዋል እንዴ?

ምስክር ምስክር ነው፡፡ ደግሞም ከኢቲቪ፣ ከኢህአዴግ፣ ከአቶ መለስ ይልቅ ዶክተር መረራ፣ ፕሮፌሰር መስፍን፣ ኢንጅነር ይልቃል፣ ግርማ ሰይፉ ያሉትን አምነዋለሁ፡፡ ምክንያቱም እነ አንዱ ዓለም፣ አቡበክር፣ እስክንድር፣ ርዕዮት ሳይሆኑ የሚያስሸብሩን ካድሬዎቹ፣ ባለስልጣናቱ፣ ኢህአዴግ፣ ኢቲቪም ናቸው፡፡

ያን መከረኛ ሰውዬ ደግሞ ከምንም በላይ አምናቸዋለሁ፡፡ እንዴት አልመናቸው? እሳቸው ስለ ሽብር ሲያወሩ በቅርብ ስለሚያውቋቸው ቤተሰቦቻቸው ጭፍጨፋ እንጅ ስለ ስልጣን አይደለም፡፡ እናም ኢቲቪ የቆረጠውን እኔም አልቆርትባቸውም፡፡ ልክ ነዎት! ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው መለስ ዜናዊ ነው፡፡ ኦነግ ፈጸመው ለተባለው ብቻ ሳይሆን አሁንም ድረስ ቤተሰቦቻቸው እንዳያዩዋቸው ተደርገው ጨለማ ቤት ውስጥ ለሚታጎሩት ሰላማዊ ታጋዮች፤ ኑሮ፣ ካድሬ፣ የመለስ ራዕይ፣ አብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ የአቅርቦት እጥረት……ለሚያሸብረው የኢትዮጵያ ህዝብ ተጠያቂው፤ ሽብርተኝነትን በመንግስት ደረጃ አዋቅረው ያለፉት አቶ መለስ ናቸው፡፡ የፈለጋችሁ ሙት ወቀሽ በሉኝ፡፡ ይህን የአቶ መለስ ‹‹ሌጋሲ›› አልረሳውም፡፡ ቢያንስ ኢህአዴግ ራሱ አምኖ ‹‹ተሳስተን ነበር፡፡ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው መለስ ዜናዊ ነው፡፡ እኛም ሆድ አደር ሆነን አብረን አጥፍተናልና ተጠያቂዎች ነን›› እስኪል ድረስ!

ከእየሩሳሌም አርአያ
ኒቆዲሞስ ዜናዊ የአቶ መለስ ዜናዊ ወንድም ነው። ከወ/ሮ አለማሽ ገ/ልኡልና ከአቶ ዜናዊ አስረሳኸኝ የተወለዱ ወንድማማቾች ናቸው። ኒቆዲሞስ በደርግ ስርአት በክብሪት ፋብሪካ ተቀጥሮ በተራ ሰራተኝነት ይሰራ ነበር። የአካል ጉዳተኛ (አንድ እግሩ) የሆነው ኒቆዲሞስ ከተራ ወዝአደርነት ወጥቶ ሚሊየነር ለመሆን የበቃው ደርግ ወድቆ ሕወሐት/ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- በደቡብ ሱዳን የተነሳውን የእርስ በርስ ግጭት ተከትሎ የተደፈሩ 4 ሴቶች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሆስፒታል በሚገኝበት ጁባ ደርሰው ምርመራ እየተደረገላቸው ነው። ሴቶቹ መደፈራቸውንና ሆስፒታል መግባታቸውን ኢሳት ለማረጋገጥ የቻለ ሲሆን፣ ሴቶቹ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ያደረገው ጥረት በመስመር ግንኙነት የተነሳ ሊሳካለት አልቻለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ በደቡብ …

ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- ሰማያዊ ፓርቲ ግንፍሌ አከባቢ የሚገኘውን እና በጽ/ቤትነት የሚጠቀምበትን ቢሮ  በአስቸኳይ እንዲለቅ  ትዕዛዝ ደረሰው። በዛሬው እለት ከሰኣት  በኋላ አቶ ሄኖክ የተባሉ አከራዩ ከአራት ግለሰቦች ጋር በመምጣት ፦”ቤቱን ለነዚህ ግለሰቦች ስለሸጥኩላቸው እንድትለቁላቸው” ሲሉ ከውል ውጪ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ቤቱን ገዛሁት የሚለው  ግለሰብ በበኩሉ፦”ቤቱን የኔ  ስለሆነ በአስቸኳይ እንድትለቁልኝ፣ ካልሆነ …

ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- ኦጋዴን ፕሬስ እንደዘገበው የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ከመከላከያ ሰራዊት እና ከልዩ ሚሊሺያዎች ጋር ባደረገው የተኩስ ልውውጥ 70 የኢትዮጵያ ወታደሮች እንደተገደሉ በእርሱ ወገንም የተወሰኑ ታጣቂዎች እንደሞቱ ገልጿል። እንደ ጋዜጣው ዘገባ 3  የመንግስት ወታደራዊ አዛዦችም ተገድለዋል። መንግስት አስተያየተቱን ባይሰጥም ልዩ ሚሊሺያ የሚባለው ሀይል የኦብነግን ወታደራዊ አዛዥ መግደሉን …

ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- ፋና እንደዘገበው በአዲስ አበባ በግሉ ዘርፍ ከተሰማሩ 470 ቀጣሪ ድርጅቶች መካከል 70 ዎቹ ሰዎችን በህወጥ መንገድ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ሰዎችን ያዘዋውራሉ ተብሎ ክስ ተመስርቶባቸዋል። የሰራተኛና የማህበራዊ ጉዳይ ሀላፊ የሆኑት ኤፍሬም ግዛው ፣ በድርጅቶች ላይ ክስ ለመመስረት አስፈላጊው መረጃ ሁሉ ተሰብስቧል። የአዲስ አበባ መስተዳድር በበኩሉ …

ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- ፓርላማው እ.ኤ.አ በ2003 በጄኔቭ የወጣው ኣለምአቀፍ የጤና ድርጅት የትምባሆ ቁጥጥር ኢትዮጽያ ፈራሚ አገር የነበረች ሲሆን ይህንን ለማጽደቅ ረቂቅ ሕግ በዛሬው ዕለት ለፓርላማው ቀርቦለት በጉዳዩ ላይ ከተወያየ በሃላ ለሚመለከተው ኮሚቴ መርቶታል፡፡ በረቂቅ አዋጁ ላይ በኢትዮጽያ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ ከሚገኙ ተማሪዎች መካከል 8በመቶ ያህሉ የትምባሆ ምርቶችን …

በአዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ በመድሐኔዓለም ቤተክርስትያን ጀርባ ቤቶችና የመንገድ ሱቆች እየፈረሱ በመሆኑ ጉዳት የደረሰባቸው ነዋሪዎች በቂ ጊዜ ሳይሰጠን ተፈናቀልን ሲሉ ያማርራሉ።

በአዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ በመድሐኔዓለም ቤተክርስትያን ጀርባ ቤቶችና የመንገድ ሱቆች እየፈረሱ በመሆኑ ጉዳት የደረሰባቸው ነዋሪዎች በቂ ጊዜ ሳይሰጠን ተፈናቀልን ሲሉ ያማርራሉ።

የተቀሰቀሰው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም ካልተደረገ ሀገሪቱ ወደ አስከፊ የእርስ በእርስ ጦርነት ልታመራ የምትችል መሆኑን በርካታ የዓለም ዓቀፍ የሠብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶችና የመንግሥታቱ ድርጅት ጽ/ቤት በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው።