የአንድነት ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ቅዳሜ ሌሊቱን ሙሉ ስለቀጣዩ የፓርቲው የትግል ስልት ከአባላቱ ጋር የጠለቀ ውይይት እንደሚያደርግ አስታወቀ – ፍኖተ ነጻነት

የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ 19እና 20 ልዩ የጠቅላላ ጉባኤውን እንደሚያደርግ የሚጠበቀው አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ከመላ ሀገሪቱ ተወክለው ከሚመጡ የጠቅላላ የጉባኤው ተሳታፊዎች ጋር ከመደበኛ የ2ቀን ስብሰባ በተጨማሪ ቅዳሜ ሙሉ ሌሊት የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ስለወደፊቱ የፓርቲው የትግል ስልትና ብቃት ያላቸው አባላትን በመመልመል የፓርቲውን አደረጃጀት አሁን ካለው በእጥፍ በማሳደግ በ2007ዓ.ም በሚደረገው ሀገር አቀፍ ምርጫ ህዝብን አስተባብሮ በአሸናፊ ለመውጣት በሚቻልባቸው ስልቶች ዙሪያ የጠለቀ ውይይት እንደሚደረግ የፓርቲው ድርጅት ጉዳይ ሀላፊ አቶ ስዩም መንገሻ ገልጸዋል፡፤
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ‹‹2007ን ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ ›› በሚል መሪ ቃል የፊታችን ቅዳሜና እሁድ በሚያደርገው ልዩ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ከመላ ሀገሪቱ የተወከሉ ከ450 በላይ አባላት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡