ካርቱም-ሱዳን ይደረግ የነበረዉ የሠወስትዮሾ ድርድር የተቋረጠዉ ኢትዮጵያና ግብፅ ባለመግባባታቸዉ ነበር።አሁን ግን የሁለቱ ሐገራት መሪዎች ባለፈዉ ወር ማላቦ-ኢኳቶሪያል ጊኒ ባደረጉት ዉይይት ድርድሩ እንዲቀጥል ተስማምተዋል

ትናንት ከሰዓት በኋላ በዩክሬን አየር ክልል ላይ ሲበር የወደቀው የማሌዥያ አየር መንገድ የመንገደኞች አውሮፕላን በሚሳይል ሳይመታ አልቀረም መባሉ ማነጋገሩን ቀጥሏል ። የዩክሬን ባለሥልጣናት አደጋው እንደደረሰ በሰጡት መግለጫ አውሮፕላኑ አካባቢውን በተቆጣጠሩት በዩክሬን አማፅያን ከምድር ወደ ሰማይ በተተኮሰ ሚሳይል ነው የተመታው ሲሉ አስታውቀዋል ።

የእስራኤል የ10 ቀናት የአየር ድብደባ ከ220 በላይ ፍልስጥኤማውያን የጋዛ ነዋሪዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በሚወሰደው ዘመቻ ነገን ላያዩ መቀጠፋቸውን እየሰማን ነው : ( ከአንድ ሽህ በላይ የዘለቁ በጠና የቆሰሉትን እና ከቀያቸው የተፈናቀሉት ዜጎችን መከራ እያየንም ነው። እኒህኞቹን በራሳቸው ሀገር ስደተኛ የሆኑትንማ ፍዳ ማየቱ ከሞቱት በላይ ያማል ። ሰቆቃው በዚህ ቢያቆም መልካም ነበር ፣ ግን አልሆነም ። በሳምንቱ […]

Journalist Tsion Girma, ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ
ጽዮን ግርማ
[email protected]

ከዓመታት በፊት የቅንጅት አመራሮች፣ ጋዜጠኞች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት አባሎችና ሌሎች ሰዎች ተከሰው ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ”የቅንጅት አመራሮች የፍርድ ቤት ውሎ” በሚል ርእስ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ተከታታይ ዘገባ አቀርብ ስለነበር ችሎቱ እስኪጠናቀቅ አንድም ቀን ከፍርድ ቤት ቀርቼ አላውቅም ነበር። በዚህም የተነሳ ክሱና የክርክር ሂደቱ ምን እንደሚመስል መናገር የሚያስችል መረጃ አለኝ ለማለት እደፍራለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

እስረኞቹ በሽብር መከሰሳቸውን አያውቁም
ጽዮን ግርማ
Jailed journalists and bloggers Tesfalem Weldeyes, Edom Kassaye, Assmamaw Hailegiyorgis, Atnafu Berhane, Mahlet Fantahun, Zelalem Kibret, Natnael Feleke, Befikadu Hailu, Abel Wabela

አንድ ዓመት ከአንድ ወር ኾኖታል። እስክንድር ነጋ ከታሰረ ከዐስራ ስምንት ወራት በኋላ ከባለቤቱ ከጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እና ከልጁ ከናፍቆት በተጨማሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ሌላ ሰው እንዲጠይቀው በሰኔ የመጀመሪያ ወር ላይ በ2005 ዓ.ም. እንደተፈቀደለት ነው። በወቅቱም እስክንድርን ልጠይቀው ቃሊቲ ወደሚገኘው እስር ቤት አምርቼ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

 

 

 

የፌዴራሉ አንደኛ ደረጃ  ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ሁለተኛ ፍትሃብሄር ችሎት እነ አቶ ሃብታሙ አያሌው የተያዙት በህግ መሠረት ስለሆነ “አካልን ነፃ የማውጣት ጥያቄአችው ውድቅ ነው” አለ።

የጊዜ ቀጠሮ ወደሰጠው ፍርድ ቤት በመሄድ ለደንበኞቻቸው ህገ መንግሥታዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ጥረት እንደሚያደርጉ የታሣሪዎቹ ጠበቃ ተናግረዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለሰአታት በቁም እስር ላይ የነበሩት የታዋቂው ፖለቲከኛና የሰብአዊ መብት ታጋይ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታላቅ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ጽጌ የወንድማቸውን ጉዳይ ለመከታተል በሚል ከ10 ቀናት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ቢያመሩም፣ ከትናንት በስቲያ ደህንነት ጽ/ቤት  ከተጠሩ በሁዋላ አገሪቱን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል። በታዘዙበት ሰአት ለመመለስ እንደሚቸገሩ የተናገሩት ወ/ሮ ብዙአየሁ፣ የ 24 ሰአት …

ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጹት ባለፉት 20 ቀናት ብቻ ከባድሜ ግንባር ከ 107 ያላነሱ ሰዎች ከድተው ወደ ኤርትራ እና ወደ መሃል አገር አቅንተዋል። ከ15 ቀናት በፊት በባድሜ አካባቢ ሲያጎ በተባለው ቦታ ላይ የሰፈሩ 60 የ 33ኛ ክፍለጦር አባላት በአንድ ሌሊት ሰራዊቱን ጥለው የጠፉ ሲሆን፣ ኤርትራ መድረስና አለመድረሳቸውን ለማወቅ የተደረገው ጥረት …

ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በየረር ባሪ ጎሳዎች የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከታሰሩት 19 አገር ሽማግሌዎች መካከል 2ቱ በእስር ቤት ውስጥ ማረፋቸው ታውቋል። የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች አስከሬን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ሟቾቹን በራሳቸው ጊዜ በመቅበራቸው የብሄረሰቡ ተወላጆች ተቃውሞ አስነስተዋል። ተቃውሞውን በሃይል ለመጨፍለቅ የክልሉ ፕሬዚዳንት ልዩሚሊሺያዎችን ወደ አካባቢው በመላክ ላይ እያሉ ፣ ከአዲስ አበባ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የሊቢያ ተቀናቃኝ ሚሊሽያዎች በሃገሪቱ የበላይነት ለመያዝ የሚያካሂዱት ትግል እንደቀጠለ ነው ። በተለይ በሊቢያው የትሪፖሊ አየር ማረፊያ የሚካሄደው ውጊያ ዛሬም አላበቃም። ከእሁድ አንስቶ የተዘጋው አውሮፕላን ማረፊያው ሥራ እስኪጀምር ድረስ ወራት ሊወስድ እንደሚችል ይገመታል በመገናና ብዙሃን ዘገባ መሰረት በውጊያው ሰዎች ተገድለዋል ፣ቆስለዋልም ።

የአውሮፓው ሕብረት አባል ሃገራት ፣ በብራሰልስ ያካሄዱት ጉባዔ እስከዛሬ ጧት ድረስ ቢጓተትም የ 28 ቱን ሃገራት ኮሚሽን ፤ በሚመጡት 5 ዓመታት እነማን እንደሚመሩት በመወሰን ረገድ ስምምነት ላይ ሳይደርስ መቅረቱ ተነገረ ። ጎርጎሪዮሳዊው 2014

ሠራተኞቹ እንደሚሉት የአንድ ወር ደመወዝ አልተከፈላቸውም። የዞኑ ሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ በበኩሉ የሥራ ውሉ ሲቋረጥ በአዋጅ የሚገባቸውን ጥቅማ ጥቅሞች አሠሪው በ7 ወር ጊዜ ውስጥ እንዲያሟላ ስምምነት ላይ መደረሱን አስታውቋል።

በጀርመን ሃገር የምንኖር አብዛኞች የዉጭ ሃገር ዜጎች በሃገሪቱ የፈለግነዉን ነገር ስለምናደርግ፤ አብዛኞች የዉጭ ተወላጆች ብንሆንም በዜግነት ጀርመናዊ በመሆናችን ከህዝቡ ጋር ፤ የቡድኑን ማልያ ለብሰን ባንዲራዉን አንግበን ጨዋታዉን በሚገባ በሃሳብ ተካፍለናል፤ አብረን ከቡድኑ ጋር ታመናል። ጀርመን ዋንጫዉን በመዉሰዱ በጣም ደስተኛ ሆነናል ይሉን፤

በዛሬው ዕለት በአራዳ ምድብ ፍታብሔር ችሎት ሀምሌ 8 ቀን 2006 ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ የፀረ ሽብር ዲቪዚዮን ኃላፊ ኮማንደር ተክላይ መብራህቱ የእስር ትዕዛዙንና የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀበትን ሰነድና ታሳሪዎቹን ይዘው እንዲቀርቡ ቢያዝም ኃላፊው ታሳሪዎቹን ሳይዙ ቀረቡ፡፡ ችሎቱ በ4፡30 ተሰይሞ ዳኛው ከሳሽና ተከሳሽ መቅረባቸውን ካረጋገጡ በኋላ እስረኞቹ መቅረባቸውን ዳኛው ጠየቁ፤ ተከሳሽ እስረኞቹን አለማቅረባቸውንና የሰነድ […]

የጋዛ ግጭት ውዝግቡ ካለፈው አንድ ሳምንት ወዲህ ተጠናክሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል፣ ፍልሥጤማውያን ከጋዛ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን መተኮሳቸውን፣ የእስራኤል ጦርም ጋዛን ማጥቃታቸውን ቀጥለዋል። በዚሁ መሀል እስራኤል እና

ብራዚል ውስጥ በተካሄደው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ላይ በፍጻሜ ግጥሚያ ጀርመን አርጀንቲናን አንድ ለባዶ አሸንፋ ለአራተኛ ጊዜ የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ባለቤት ከሆነች ይኸው ሁለት ቀናት አልፈዋል።

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በፍጥረተ ዓለም ፣ በተለይ በዝች እኛ ከምንኖርባት ምድር (ፕላኔት) ውጭ በሌሎች ዓለማት እጅግ የrr,ቀቀ የራሳቸው ሥልጣኔ ያላቸው ፍጡራን ይኖሩ ይሆን? የሚታሰቡት ፍጡራን ቀለማቸው፣ አረንጓዴ፤ ይሁን ፤ ግዙፍ ይሁኑ ንዑስ፤ የሰው ቅርጽ ይኑራቸው የሌላ

ትናንት የጀርመኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር፤ ዛሬ ደግሞ የኢጣሊያዋ አቻቸዉ ፌደሪካ ሞግሔሪኒ እየሩሳሌም-እየደረሱ ተመልሰዋል።የፍልጤም ፕሬዝዳንት ማሕሙድ አባስ የግብፅና የቱርክ መሪዎችን ድጋፍ ለመጠየቅ ሁለቱን ሐገራት ይጎበኛሉ።ግድያዉ ቀጥሏል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በአሸባሪነት ተጠርጥረዋል ተብለው የተያዙት 6 የኢንተርኔት ጸሐፍትና 3 ጋዜጠኞች ላይ ፖሊስ ሲያካሂድ የቆየው ምርመራ ተጠናቋል ቢባልም ምንም ዓይነት ውሳኔ እንዳልተሰጣቸው ጠበቃቸው አስታወቁ። ክሳቸው ዛሬ ወደ ሕጋዊ ሥርዓት ካልገባም ነገ ክስ ለመመሥረት ማሰባቸውን ጠበቃቸው አቶ አምሃ መኮንን ዛሬ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በርካታ ቁጥር ያላቸው በደቡብ አፍሪካ የተለያዩ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከጆሃንስበርግ ተነስተው የእንግሊዝ ቆንስላ ወደሚገኝበት ፕሪቶሪያ በማምራት በግንቦት7 ዋና ጸሃፊ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተወሰደውን ህገወጥ እርምጃ ከማውገዝ በተጨማሪ ከእነሱ የሚጠበቀውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተገኘችው ዝናሽ ሃብታሙ  ኢትዮጵያውያኑ አንዳርጋቸውን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ነጻ እናወጣለን ማለታቸውን ገልጻለች …

ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲዎቹ ለኢሳት በላኩት መግለጫ   የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የቅድመ ውህደት ስምምነት ፊርማ ካኖሩ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ውህደቱን ምሉዕ ለማድረግ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ አስታውሰው፣ ለውህደቱ መሳካት የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ሰፊ በመሆኑ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ደጋፊዎቻችን የአቅማቸውን ድጋፍ ለማድረግ በስምምነት …

ለአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አዲስ አበባ ጉዳዩ፡- የአቋም መግለጫን ስለማሳወቅ፡ ከላይ በርእሱ እንደተገለጸው የደቡብ ወሎ ዞን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በ 06/11/06 ዓ.ም በፓርቲው ጽ/ቤት በመሰብሰብ የፓርቲውን የስራ እንቅስቃሴና በቅርቡ በታሰሩ የፓርቲው የበላይ አመራሮች በአቶ ሀብታሙ አያሌው እና በአቶ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም በሰበብ አስባቡ በሚታሰሩ ሌሎች ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ህገ ወጥ […]

ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተለያዩ ሰበቦች እየቀረቡበት የሚራዘመው የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የፍርድ ሂደት ዛሬም በችሎት አዳራሽ ለውጥ ምክንያት እንዲራዘም ተደርጓል። በአቶ አቡበክር ምዝገብ የተከሰሱት ኮሚቴዎች፣ የመከላከያ ምስክር ለፍርድ ቤቱ ማስደመጥ እንደጀመሩ ነበር የችሎት ሂደቱ በሰባሰብ እንዲራዘም የተደረገው። ዳኞችና አቃቢ ህጎች በቃሊቲ የሚገኘው የችሎት አዳራሽ ለትራንስፖርት የማያመች በመሆኑ እንዲቀየርላቸው ባመለከተቱት መሰረት አዲሱ …

ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤድስ ኤጀንሲ እንደገለጸው ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በብዙ አገሮች የኤደስ ወረርሽኝ ስርጭት እየቀነ ሲሆን ፣ ስርጭቱንም ከ14 አመታት በሁዋላ  ማቆም እንደሚቻል ገልጿል። አሁንም በርካታ ዜጎች መድሃኒት አጥተው በመሰቃየት ላይ መሆናቸውን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ገልጿል። በዚህ አመት በአለም ደረጃ 2 ሚሊዮን 300 ሺ ሰዎች ብቻ በኤች …

ለውህደቱ መሳካት ጥረት እና ድጋፍ እያደረጉ ላሉ ኢትዮጵያውያን ምስጋና እናቀርባለን!1 እንደሚታወቀው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የቅድመ ውህደት ስምምነት ፊርማ ካኖሩ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ውህደቱን ምሉዕ ለማድረግ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ ይሄው ውህደት አመቻች ኮሚቴ በስምምነት ሰነዱ በተቀመጠው መሰረት ለማጠናቀቅ ቀን ከሌሊት እየሰራ ሲሆን የሁለቱ አንጋፋ ፓርቲዎች […]

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ለእንግሊዝ የአፍሪካ ክፍል ሃላፊ በጻፈው ደብዳቤ፣ አቶ አንዳርጋቸው የህግና የማማከር አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ” የሚመለከታቸው አካላት” መፍቀድ አለባቸው ብሎአል። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ” የሚመለከታቸው አካላት” ያላቸውን አካላት በስም ከመጥቀስ ተቆጥቧል። ይሁን እንጅ የመረጃው ምንጮች እንደሚሉት ” የሚመለከታቸው አካላት” የተባሉት የደህንነት ሰዎች ናቸው። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ይህን መልስ የጻፈው፣ …

ሐምሌ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ የከተማው እና የዞኑ አመራር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ኗሪዎች በመሰረተ ልማት ፤ በመልካም አሰተዳደር ችግር እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ይህ አለም ደጉ የተባሉ የደብረ ታቦር ኗሪ ” የጋማ ከብት እና ሰዎች በአንድ ላይ እየጠጡ መሆናቸውንና ይህም ሁኔታ ለውሃ ወለድ በሺታ እንደዳረጋቸው ተናግረዋል፡፡ አቶ ፍስሃ ይ …

ሐምሌ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮ ቴሌኮም በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ፈሶበት  በሥራ ላይ የነበረውን የኖኪያ ኔትወርክ ነቅሎ በመጣል በቀላሉ ለስለላሥራ በሚመች መልኩ በአዲስ መልክ ለመትከል በቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ እየተከናወነ ያለው የአዲስ አበባ የቴሌኮም ማስፋፊያ ሥራ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ማሳካት አለመቻሉን  ምንጮቻችንገልጸዋል፡፡ ሁዋዌ በ800 ሚሊየን ዶላር በያዝነው ዓመት ህዳር ወር 2006 የማስፋፊያ ስራውን በአዲስ …

የመኢአድና አንድነት ውህደት አመቻች ኮሚቴ ስራውን በቅልጥፍና እና በትጋት እየተወጣ መሆኑን ለፍኖተ ነፃነት የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በዚህም መሰረት ለጉባኤው መሳካት ይረዳ ዘንድ መላው ኢትዮጵያውያን እንዲተባበሩ ጥሪ በማድረግ የባንክ አካውንቱን ይፋ አድርጓል፡፡ የባንክ አካውንት ቁጥር UDJ A/C 47 የባንክ አካውንት ቁጥር AEUP SP 235

ሐምሌ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃማስና በእስራኤል መካከል የተጀመረው ጦርነት ፣ በግብጽ አደራዳሪነት ለሰአታት ጋብ ብሎ የቆየ ቢሆንም፣ እስራኤል ድብደባውን እንደገና መጀመሯን ቢቢሲ ዘግቧል። በግብጽ የቀረበውን የሰላም ስምምነት እስራኤል ብትቀበለውም፣ ሃማስ ግን ስምምነቱ ሽንፈትን እንደመቀበል ይቆጠራል በሚል ሳይቀበለው ቀርቷል። ይህን ተከትሎም እስራኤል የአየር ድብደባውን እንደገና ጀምራለች። እስካሁን በደረሰው ጥቃት ከ192 በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል፤ በብዙ …

የእንግሊዝ የባሕር ማዶ ትብብር ኤጀንሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ሲሰጥ ከራሱ የሰብዓዊ መብቶች ፖሊሲዎች ጋር በተጣጣመ መልክ መሆንና አለመሆኑ እንዲፈተሽ አንድ የእንግሊዝ ፍርድ ቤት መወሰኑን የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስ ዋች አድንቋል፡፡

 

 

 

 

የፌደራሉ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ሁለተኛ የፍትሐ ብሔር ችሎት በቅርቡ የታሠሩትን የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች በአርባ ስምንት ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት ስለማቅረቡ ማስረጃ እንዲያያይዝ ለፀረ-ሽብር ግብረ-ኃይሉ ኃላፊ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

የተባለውን ማስረጃ ሐምሌ 10/2006 ዓ.ም እንዲያቀርብ ቀጠሮ መያዙን ጠቅሶ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን መለስካቸው አምሃ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

 

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች