የእነ አቶ ሃብታሙ አያሌው የሃቢየስ ኮርፐስ አቤቱታ ውድቅ ተደረገ
የፌዴራሉ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ሁለተኛ ፍትሃብሄር ችሎት እነ አቶ ሃብታሙ አያሌው የተያዙት በህግ መሠረት ስለሆነ “አካልን ነፃ የማውጣት ጥያቄአችው ውድቅ ነው” አለ።
የጊዜ ቀጠሮ ወደሰጠው ፍርድ ቤት በመሄድ ለደንበኞቻቸው ህገ መንግሥታዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ጥረት እንደሚያደርጉ የታሣሪዎቹ ጠበቃ ተናግረዋል።
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡