የተያዙት ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት ጸሐፍት ጉዳይ DW Amharic July 16, 2014 Tagged with Amharic, amharic news, Ethiopia, ethiopian news in amharic, Ethiopians, News in Amharic ኢትዮጵያ ውስጥ በአሸባሪነት ተጠርጥረዋል ተብለው የተያዙት 6 የኢንተርኔት ጸሐፍትና 3 ጋዜጠኞች ላይ ፖሊስ ሲያካሂድ የቆየው ምርመራ ተጠናቋል ቢባልም ምንም ዓይነት ውሳኔ እንዳልተሰጣቸው ጠበቃቸው አስታወቁ። ክሳቸው ዛሬ ወደ ሕጋዊ ሥርዓት ካልገባም ነገ ክስ ለመመሥረት ማሰባቸውን ጠበቃቸው አቶ አምሃ መኮንን ዛሬ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።