የአውሮፓ ህብረት ፍርድ ቤት ባለፈው ሰሞን በጀርመን የቪዛ አሰጣጥ ህግ በተለይም ቱርኮችን በሚመለከተው ደንብ ላይ ያሳለፈው ብይን ቱርካውያንን አስደስቷል ። በአንፃሩ አንዳንድ የጀርመን ፖለቲከኞችን ቅር አሰንኝቷል ።

ደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የረሃብ አደጋ ያሰጋታል ሲል የተመድ የሰብዓዊ እርዳታዎች አስተባባሪ ቢሮ አስጠነቀቀ። ድርጅቱ እንዳለው የደቡብ ሱዳን ሰብዓዊ ቀውስ እየተባባባሰ በመሄዱ ደቡብ ሱዳን ውስጥ በጣም በቅርቡ ከፍተኛ የረሃብ አደጋ ሊከሰት ይችላል።

በደቡብ ሱዳን ጦርነት ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱ ተፈናቃዮች ቁጥር ከ200,000 በላይ መድረሱ ተነግሯል። ስደተኞቹ በተለይ ወደ ጋምቤላ የፈለሱ ሲሆን፤ የሚገኙበት ሁናቴ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን በተመድ የሠብዓዊ ርዳታ አስተባባሪ በእንግሊዘኛ ምኅፃሩ ኦቻ ዋና ዳይሬክተር ጆን ጊንግ አስታውቀዋል።

በጎርጎሪዮሳዊዉ 2012ዓ,ም በ50 ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸዉ ሃገራት የተካሄደ ምርምር 12 በመቶ የሚሆኑት በወሲብ ንግድ የተሠማሩ ሰዎች በHIV ቫይረስ መያዛቸዉን ያመለክታል። በዚህ ተግባር ከተሠማሩት 50 በመቶዉ የሚሆኑት በቫይረሱ የተያዙባቸዉ አካባቢዎች ደግሞ ከሰሃራ በስተደቡብ የገኙት ሃገራት ናቸዉ።

እስከ ልዩ ጽ/ቤት የተዘረጋው የአማሳኞች ሰንሰለት ለአለቃው መነሣት ተጠያቂ ኾኗል ምእመናን፣ በተነሡት አለቃ ምትክ የሚደረግ ምደባን እንደማይቀበሉ አስጠንቅቀዋል ፓትርያርኩ ለክብረ በዓል ወደ ቁሉቢ ሲያልፉ ለማነጋገር ዝግጅት እየተደረገ ነው የኦዲት ሪፖርቱ የድሬዳዋ አገልጋዮች እና ምእመናን በአንድነት እንዲሰለፉ አድርጓል ‹‹የአለቃው መነሣት ሙስናን ለሚዋጉ ሌሎች አስተዳዳሪዎች ዋስትና የሚያሳጣ ነው፡፡›› ‹‹ፓትርያርኩ በቋሚ ሲኖዶስ የተወሰነውን ስለማይቀበሉና መፍትሔ ማምጣት ስላልተቻለ ሕዝቡ …

ለወረዳው አለም ከተማና አካባቢዋ አገልግሎት ይውላል ተብሎ ከብዙ ጊዜ በሁአላ የገባውን መብራት የወያኔ መንግስት ህዝቡ የሚገለገልበትን መብራት አቁሞ ትራንስፎርሜሽኖቹን ነቅሎ ለአስቸኩአይ ጉዳይ ይፈለጋል ብሎ ወደ ትግራይ ለመውሰድ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የወረዳው 27ቱም ቀበሌ ተጠራርቶ ትራንፈርመሩን በቁጥጥር ስር በማድረግ ከላይ ከተጠቀሱት የወያኔ የፀጥታ ሃይሎች ጋር ኣሁን ድረስ ውጊኣ እያደረገ ሲሆን እስካሁን 7 የወያኔ ወታደሮች የሞቱ ሲሆን ከህዝብ […]

ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ሸዋ ዞን በመርሃ ቤቴ ወረዳ በአለም  ከተማ ከመብራት ማሰራጫ ጋር በተያያዘ በተነሳ ተቃውሞ አንድ ሰው ከፌደራል ፖሊሶች በተተኮሰ ጥይት ተመትቶ ቆስሏል። መብራት ሃይል የከተማውን የመብራት ማሰራጫ በማንሳት ወደ ሌላ አካባቢ ለመውሰድ እንቅስቃሴ ሲጀምር የአካባቢው ህዝብ ተቃውሞ አሰምቷል። እሁድ እለት ወደ ከተማዋ የገባው የፌደራል ፖሊስ ከህዝቡ ጋር ፊት …

ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያሉበትን ቦታ ለማወቅ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ትክክለኛ ቦታውን ለማወቅ አልተቻለም። ይሁን እንጅ በማእከላዊም ሆነ በቃሊ እስር ቤት አለመኖራቸውን ምንጮች ገልጸዋል። የገዥው ፓርቲ ሰዎች በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የፕሮፓጋንዳ ስራ ለመስራት የተለያዩ ሰዎችን እያነጋገሩ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። ኤርትራ ውስጥ ነበርን ያሉ እና በአቶ  አንዳርጋቸው ላይ …

ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በታላቁአንዋርመስጂድበመንግስትየደህንነትኃይሎችናበፖሊስሀላፊዎችከቀናትበፊትታቅዶበሙስሊሙ ላይ በተወሰደእርምጃከ6 ሺ በላይየመንግስትቅጥረኛሲቪልለባሾችመሰታፋቸውን አስታውሷል። “ቅጥረኞቹየተከበረውየረመዳንወርየጁምአሰላትከመሰገዱበፊትበመስጊዱውጫዊሰሜናዊአቅጣጫግርግርበማስነሳትናከፖሊሶችጋርከሁለቱምአቅጣጫድንጋይበመወራወር የታለመውን ውጤትለማምጣትሞክረዋል” የሚለው ድምጻችን ይሰማ፣  በሁሉምአቅጣጫየነበሩናበአስርሺዎችየሚቆጠሩሙስሊሞችየጁምአሰላታቸውንእንዳይፈጽሙእክልከመሆናቸውም በላይበበርካታጾመኛሙስሊሞችላይእጅግአሰቃቂጭፍጨፋ”መፈጸሙን ገልጿል። “ሙስሊሙንከሁሉምአቅጣጫበቆረጣስልትለሰላትበተቀመጠበትበመቁረጥበነፍስወከፍበያዙዋቸውዱላዎችናየመሣሪያሰደፎችርህራሄአልባበሆነሁኔታመደብደባቸውንና መጨፍጨፋቸውን የገለጸው ደምጻችን ይሰማ፣   በእለቱየተወሰደውመንግስታዊሽብር ‹‹ጥቁርሽብር›› የሚልስያሜተሰጥቶታል ብሎአል። ” ‹‹ጥቁርሽብር›› በሰለጠነውይይትከማያምን፣ሰላማዊነትናዲሲፒሊንከማይገባውመንግስትየሚፈልቅ፣ሰዎችሳይሆኑዱላብቻየሚናገርበት፣ሐሳብየሚንሸራሸርበትሳይሆንነውጥናግፍ የሚሰፍንበትሂደትነው ” ብሎአል። ‹‹ጥቁርሽብር›› አይናቸውንየጋረደውጥቁርግርዶሽየህዝብንእውነታእንዳይረዱያደረጋቸውናብቃትየሌላቸውኃላፊዎችየሚወስኑት፣ሰብዓዊነትበጭካኔጭለማውስጥየሚሰጥምበት አስከፊክስተትመሆኑን የጠቀሰው ድምጻችን ይሰማ፣  ለሰላማዊሕዝብናጥያቄምላሹንዱላያደረገኃይል፣ባልታጠቀናበእጁድንጋይባልጨበጠጾመኛሕዝብላይየጥይትቃታየሚስብ መንግስት ከርሞምየሚነዳውበ‹‹ጥቁርሽብር›› ብቻነው ብሎአል። የሐምሌ 11/2006ንአሰቃቂየመንግስትጭፍጨፋየታሪክካስማበማድረግእለቱ ‹‹ጥቁርሽብር›› ሲባልከዚህበኋላያሉክስተቶችም ‹‹ከጥቁርሽብርበኋላ›› ወይም ‹‹ከጥቁርሽብርበፊት›› …

ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስሪያ ቤቱ በመግለጫው በሰሜን ኢትዮጵያ  ከ12 ዲግሪ የትይዩ መስመሮች እስከ ኤትዮ ኤርትራ ድንበር ባለው የአየር ክልል ምንም አይነት በረራ እንዳይካሄድ መክሯል። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በዚሁ ክልል የሚያልፉ የንግድም ሆነ ሌሎች አውሮፓላኖችን ሊመታ እንደሚችል አስጠንቅቋል። የአሜሪካ መንግስት ማስጠንቀቂያ ካወጣባቸው የአፍሪካ አገራት መካከል ኬንያ እና ሶማሊያ ይጠቀሳሉ። የአሜሪካ አቪየሽን እገዳ …

ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአረና የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ወይዘሪት ተክለ ደስታ የኣብራሃ ደስታ እህት በመሆንዋ ብቻ ከስራዋ ታግዳለች ። ወይዘሪት ተክለ ደስታ የጤና ባለሙያ ስትሆን የህወሓት ኣባልና የራያ ዓዘቦ ወረዳ የጤና ፅህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ ሁና ታገለግል ነበር። የወረዳው ባለስልጣናት “አንቺ እንደ ወንድምሽ ዓረናነሽ ፣ ላንቺ የሚሆን የህወሓት ሃላፊነትም ይሁን የሞያ ስራ …

ዕለተ ሰንበት ቅዳሜን ‹‹ከአፍሪካ ፒስ ኤንድ ግሪን ኢንሼቲቭ›› አገር በቀል ድርጅት መሥራች፣ አባላትና ደጋፊዎች ጋር ወደ ጥንታዊውና ታሪካዊው ገዳም ወደ ደብረ ሊባኖስ ተጉዤ ነበር፡፡ የጉዞው ዓላማም ፍቅርን፣ ሰላምን፣ ወንድማማችነትንና የአረንጓዴ ልማት/ተፈጥሮን የማፍቀርንና የመንከባበከብ ጽንሰ አሳብን በሰዎች አእምሮ ውስጥ የመዝራት ቅንና በጎ እሳቤ የወለደው ነው፡፡ ለሰብአዊ ፍጥረት ሁሉ ፍቅርና ሰላም እጅጉን አስፈላጊው እንደሆነ አንዳች ጥያቄ የለውም፡፡ […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የአውሮጳ ታላላቅ የእግር ኳስ ቡድኖች ጨዋታ በአዲስ መልክ ከመጀመሩ አስቀድሞ ቡድኖቹ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች እየተዘዋወሩ የአቋም መለኪያ ግጥሚያዎችን በማከናወን ላይ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን አዲስ አበባ ስታዲየም ውስጥ ከጋቦን አቻው ጋር እኩል ለእኩል ወጥቷል። ሌሎች ዜናዎችንም አካተናል

የእሥራኤል ጦር ትንሽቱን ሠርጥ ለቅቆ ቢወጣም ዙሪያ ገባዋን እንደከበባት ነዉ።ጋዛ ነዋሪዎችዋ እንደሚሉት ጣራ-የሌላት ትልቅ «እስር ቤት» ናት።በጀርመን የፍልስጤም አምባሳደር ኾሉድ ዳይቤስ ደግሞ የሕዝብ ጉረኖ-ይሏታል።

የብሔራዊው ሶሻሊስት ጦር መኮንኖች እአአ ሀምሌ 20፣ 1944 ዓም አዶልፍ ሂትለርን ለመግደል ያደረጉት ሙከራ ሰባኛ ዓመት ትናንት በበርሊን ፕሬዚደንት ዮአኺም ጋውክ እና የመከላከያ ሚንስትር ኡርዙላ ፎን ዴር ላየን ፣ እንዲሁም ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት ታስቦ ዋለ።

ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ የአፍሪቃ ልማት ባንክ አዲስ አበባ ላይ ጉባኤ አካሂዷል። በዚህ ጉባኤም ባንኩ የአፍሪቃ ሃገራት በምጣኔ ሃብት ረገድ የምርት ሰንሰለትን ማሳደግ እንደሚኖራባቸዉ ገምግሟል።

ሐምሌ 11፤ አርብ አዲስ አበባ አንዋር መስጊድ በተቀሰቀሰ ከፍተኛ ግጭት በርካታ ሰዎች መጎዳታቸዉ ተሰምቶአል። ተሰምቶአል። የአይን እማኞች ፖሊሶች እና የጸጥታ ኃይላት ናቸዉ ያሏቸዉ፤ በታላቁ አንዋር መስጊድ ለጁምዓ ሶላት የተሰበሰበዉን ምዕመን በያዙት ዱላ መደብደባቸዉንና ወንድ ሴት ሳይለዩ እያጋዙ መዉሰዳቸዉን ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም
በሃያኛው ምዕተ-ዓመት ላይ የታወቀ የፈረንሳይ ፈላስፋ ነበረ፤ እሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበረበት ጊዜ ከእሱ ጋር በዩኒቨርሲቲ ሁለት አፍሪካውያን አብረውት ይማሩ እንደነበሩ ይናገራል፤ እነዚህ አፍሪካውያን የፈረንሳይኛ ቋንቋን ልክ አንደፈረንሳዮች እየተናገሩ፣ እንደፈረንሳዮች እያሰቡ ከፈረንሳዮቹ ተማሪዎች ጋር እኩል በትምህርት እየጎለበቱ ነበር፤ በኋላ እነዚህ አፍሪካውያን ወደአገራቸው ተመልሰው ሥልጣን ላይ ሲወጡ ሰፊ አገራቸው ለሁለቱ የተማሩ አፍሪካውያን የማይበቃ ሆነባቸው፤ ስለዚህም አንደኛው የአገር መሪ ሆነና ሌላውን ገደለው፤ የፈረንሳዩ ፈላስፋን ያሳዘነው ትዝብት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ኢትዮጵያ ዉስጥ ለመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ጥርጊያ የሚከፍተዉ በነፃ የመደራጀት መብት በሕገ መንግስት ተደንግጎ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ከሁለት አስርት ዓመታት ያላነሰ ጊዜ አስቆጥሯል። በዚህ ጊዜም በሥልጣን ላይ ያለዉን ማለትም ገዢዉን ፓርቲ ለመፎካከር በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተቋቋሙ ፈርሰዋል።

የእስራኤል ጦር በጋዛ ሰርጥ ሟቾችን እና ቁስለኞችን ለማንሳት ለ2 ሰዓታት የተኩስ አቁም ተስማምቷል ተብሎ ነበር። ይሁንና የሀማስ ቡድን ቃሉን እንዳልጠበቀ ነው የሚነገረው። ሁለቱ ቡድኖች ባደረጉት የተኩስ አቁም ስምምነት የተነሳ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ወደ ስፍራው ሰርጎ ገብቶ ነበር።

ሐምሌ 11 ቀን 2006 ለክቡር አምባሳደር ጥሩነህ ዜና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር አዲስ አበባ ጉዳዩ፡- በጥርጣሬ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ሰብዓዊ መብት አያያዝ ይመለከታል ክቡር ኮሚሽነር ከሐምሌ አንድ ቀን ጀምሮ በ “ወንጀል” ተጠርጥረዋል በሚል የፓርቲያችን አንድነት ለፍትህና ዲሞክራሲ (አንድነት) የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው እና የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም […]

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)ብሔራዊ ምክር ቤት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ብሔራዊ ምክር ቤት በእስር ላይ በሚገኙት አመራሮችና ውህዱን ፓርቲ ደንብና ፕሮግራም መመርመርና የውህዱ ፓርቲ የፓርቲው እጩ ፕሬዚደንት ጉዳይ ላይ ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ በመወያየት – ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው – አቶ በላይ ፍቃዱናን እና – አቶ ትዕግስቱ አወሉን ለውህዱ ፓርቲ ፓርቲውን ወክለው ለፕሬዚደንትነት በእጩነት አቅርቦ ስብሰባው […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የማሊ መንግሥት እና የቱዋሬግ ዓማፅያን በአልጀሪያ የሰላም ድርድር ጀምረዋል። ማሊ ውስጥ እኢአ በ 2012 ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከተካሄደ በኋላ እና በሀገሪቱ ሰሜናዊ ከፊል የሚንቀሳቀሱት ለዘብተኛ እና አክራሪ የቱዋሬግ ዓማፅያንም በመንግሥቱ አንፃር ትግላቸውን ካጠናከሩ በኋላ ማሊ መረጋጋት አልቻለችም።

ምሥራቅ ዩክሬይን ተመቶ የወደቀው የማሌዢያዉ የመንገደኞች ማመላለሻ አይሮፕላንን ተከትሎ፤ የዮክሬይን መንግሥት መፍቀሬ ሩሲያንን ወነጀለ። እንደ ዮክሬይን መንግስት፤ መፍቀሬ ሩስያ ተገንጣዮቹ ከአይሮፕላኑ የተገኙ የምስክር ማስረጃዎችን እያሸሹ እና እያጠፉ ይገኛሉ።

አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብስባ ለመጥራት ታቅዶ ነበር በተሳሳተ አካሔዳቸው ከቀጠሉ ቋሚ ሲኖዶሱ አብሯቸው አይሠራም በአ/አበባ የአድባራት አለቆች ዝውውር ስሕተት መሥራታቸውን አምነዋል ‹‹የኔ ቃልና የነሱ ቃል በዓላማ አንድ ስለኾነ፣ የሚያመጡት ሐሳብ ስለሚመቸኝ ነው፡፡››          /ፓትርያርኩ በሰብሳቢነት የሚመሩትንና አብረው የሚወስኑበትን የቋሚ ሲኖዶስ መመሪያዎች ከአማሳኞች ጋራ እየመከሩ ስለሚገለብጡበት አካሔድ በቋሚ ሲኖዶስ ለተጠየቁት የመለሱት/ /ምንጭ፡- ፋክት፤ ቅጽ …

ለሦስት ወራት ያህል ክስ ሳይመሠረትባቸው ታስረው በቆዩት ዘጠኝ ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት ፀሃፊዎች፤ እንዲሁም በአንድ ሌላ ተጠርጣሪ ላይ አቃቢ-ህግ ዛሬ የአሸባሪነት ክሥ ከፈተ።

የታጠቁ የኢትዮጵያ ፖሊስና ደህንነት ሠራተኞች ዛሬ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው አንዋር መስጊድ የዓርብ ፀሎታቸውን ለማድረስ በወጡ ምዕመናን ላይ ድብደባና አፈሳ ማካሄዳቸውን እማኞች ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-”ለከፈልነው መስዋትነት አቻ ውጤት እናመጣለን” በሚል መፈክር የተካሄደው ተቃውሞ ወደ ደም አፋሳሽ ግጭት አምርቷል። የፌደራል ፖሊሶች ሆን ብለው ባስነሱት ግጭት ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ሙስሊሞች ቆስለዋል። በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ እየታፈሱ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ኢሳት እስካሁን ከገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ ባይችልም አንዳንድ ሙስሊሞች  ስልክ በመደወል  የተገደሉ ሙስሊሞች መኖራቸውን ተናግረዋል። …

ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ በእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት በመገኘት ፣ የኢህአዴግ መንግስት በግንቦት7 ዋና ጸሃፊ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በወሰደው ህገወጥ እርምጃ የእንግሊዝ መንግስት ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል። በስፍራው የነበረውን ዘጋቢያችን ወንድማገኝ ጋሹን አነጋግረነዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፎሬን ፖሊሲ መጽሄት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በተመለከተ ሰፊ ዘገባ አቅርቧል። በምስራቅ …

ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በጸገዴ ወረዳ አካባቢ የሚገኙ በአማራው ክልል ስር ተካለው የሚገኙ በርካታ ቀበሌዎችን መውሰዳቸውን ተከትሎ ፣ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ድርጊቱን በመቃወም ከትግራይ ክልል ታጣቂዎች ጋር ተፋጠው እንደሚገኙና በማንኛውም ሰአት ግጭት ይፈጠራል ተብሎ እንደሚፈራ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ወደ 400 የሚጠጉ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ወደ ድንበሩ የተጠጉ ሲሆን፣ …

የዐቃቤ ሕግ የመሰረተውን ሙሉ ክስ ይዘናል
የዋስትና መብት ተከልክለው ወደቃሊቲና ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተወሰዱ፣ ለሐምሌ 28 ተቀጠሩ
የታሰሩት ስድስት ጦማርያንና ሦስት ጋዜጠኞች The jailed 6 bloggers and 3 journalists

Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. July 17, 2014)፡- ዛሬ ጠዋት በ84 ቀናቸው በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተሰየመ ችሎት ስድስቱ ጦማርያን በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ ዘለዓለም ክብረት፣ አቤል ዋበላ እና ሦስቱ ጋዜጠኞች አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሣዬና ተስፋለም ወልደየስ ዐቃቤ ሕግ የመሰረተባቸው የክስ ፋይል ለመጀመሪያ ጊዜ ደርሷቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች