የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)ብሔራዊ ምክር ቤት ለውህዱ ፓርቲ እጩዎችን መረጠ! – የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)ብሔራዊ ምክር ቤት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ብሔራዊ ምክር ቤት በእስር ላይ በሚገኙት አመራሮችና ውህዱን ፓርቲ ደንብና ፕሮግራም መመርመርና የውህዱ ፓርቲ የፓርቲው እጩ ፕሬዚደንት ጉዳይ ላይ ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ በመወያየት
– ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው
– አቶ በላይ ፍቃዱናን እና
– አቶ ትዕግስቱ አወሉን ለውህዱ ፓርቲ ፓርቲውን ወክለው ለፕሬዚደንትነት በእጩነት አቅርቦ ስብሰባው ተጠናቋል፡፡
በተያያዘም ዜና በትናንትናው እለት በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የወጣቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ተዘጋጀው ውይይት ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ የተካሄደ መሆኑ ታውቋል፡፡ በውይይቱ ላይ በርካታ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን ጽሁፍ አቅራቢው አቶ አበባየሁ በተለይ ህዳሴውና የለውጥ ፖለቲካ በሚል በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የለውጥ ሂደት በገዢዎች ፍላጎት የተመራ እንጂ ሕዝቡን ጥያቄ ያልመለሰ፣ ተራራና ቋጥኝ ቋጥኝ የሚያክል ጥያቄ ተነስቶ ያልተመለሰበት ነው፡፡ ኢህአዴግም ልክ እንደ ትላንቱ በሕዝብ እየነገደ የኢትዮጵያን ልጆች ማግዶ የጥቂት ቡድኖች ጥቅም መሰብሰቢያ ስላደረገው እስከ ዛሬ ድረስ ለውጥ ሳይመጣ ቀርቷል ብለዋል፡፡

