ዘንድሮ የተስፋ አድማሥ ጨልሟል።ለመግለፅ በሚከብድ እርምጃ የዋሐን በመገደላቸዉ ልባችን ደምቷል።የቀዝቃዛዉ ጦርነት የጣረ ሞት ድባብ ተምልሶ በዚሕ ዘመንም እያደነን ነዉ።የአረብ አብዮት በሁከት ሲደመደም አየን።ዓለም ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወዲሕ አይታዉ በታዉቀዉ ሥደተኛ፤ተፈናቃይና ጥገኝነት ጠያቂ ሕዝብ ተጥለቅላቀች—

የሞ ኢብራሒም ተቋም በየዓመቱ ፤ በመልካም አስተዳደር፣ በሰብዓዊ መብት ጥበቃ፤ በልማት ፣ በትምህርት እና በሌሎች ዘርፍ የአፍሪቃ ሀገራት የት እንደሚገኙ የሚገመግምበትን ሰንጠረዥ ዛሬ ይፋ አድርጓል።

ዛሬው የሙዚቃ ቃና ፕሮግራም በአሜሪካ የቢል ቦርድ ሰንጠረዥ ላይ ከመቶዎቹ ምርጥ ዜማዎች መካከል በዚህ ሳምንት ከአንድኛ እስከ ሶስትኛ ደረጃ የወጡትን ምርጥ ዜማዎች እና ስለ Chris Brown አዲስ አልበም እንዲሁም ስለሞን ክፍሌ ስለ Lionel Richie የሕይዎት ታሪክ ያዘጋጀውን ፕሮግራም አካቷል፡፡

በስታቲስቲክስ የተደገፈ የጥናትና ምርምር ዘገባ ማቅረብ ባልችልም፤ ባካባቢዬ ያለውን ሀቅ ተከታትዬ የሚኖረኝ ግንዛቤ፤ መንገዱኝ ይከፍትልኛል። የኢትዮጵያን ሕዝብ ፍላጎት ሰብስቤ፤ ይሄ ነው ብዬ የማቀርበው የጥናት ዘገባ የለኝም። ውጪሰው ኢትዮጵያዊያን ስለሚፈልጉት ወይንም ስለሚያደርጉት ተጨባጭ ማስረጃ ያጠራቀምኩት ዝርዝር የለኝም። ነገር ግን፤ በመጀመሪያ እኔ ራሴ የውጪሰው ኢትዮጵያዊያን አካል በመሆኔ፤ በዙሪያዬ ከምገናኛቸው እንደኔው የውጪሰው ኢትዮጵያዊያን ጋር ስለሀገራችን ሁኔታ እወያያለሁ። ለጥቆም […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ዛሬ በጀርመን በርሊን ከተማ በተካሄደው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያቱ ትርፊ ፀጋዬ እና ፈይሴ ታደሰ ተከታትለው በመግባት አንደኛ እና ሁለተኛ ወጡ። በእዚሁ የበርሊኑ የማራቶን ሩጫ ፉክክር ኬንያዊው ዴኒስ ኪሜቶ የዓለም ክብረ ወሰን ሰብሯል።

ሦስት ቀለማት ያላቸው ክሮች የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ሲኾኑ አንድ ላይ መፈተላቸው ወይም አንድ መኾናቸው ቅድስት ሥላሴ ማለት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በመለኰት በህልውና አንድ አምላክ መኾናቸውን ያመለክታል፡፡ ጥቁሩ፡- ክርስቲያን ስለ ሃይማኖት የሚቀበለው መከራ የሚሸከመው መስቀል፣ ቀዩ፡- በሰማዕትነት ደም የማፍሰስ ሲኾን ቢጫው ደግሞ የክርስቲያን ተስፋ የሃይማኖት ምልክት ነው፡፡ ክርስቲያን ለክርስቶስ ታማኝ በመኾኑ በነፍሱ ሞግዚት …

ቦስተን መስከረም 17/2007 (ሴፕቴምበር 27፣ 2014 ዓ.ም) የደመራ በዓል በካምብሪድጅ ከተማ 808 Memorial Dr. አጠገብ በሚገኘው ፓርክ በቦስተን እና አካባቢዋ ነዋሪ በሆኑ የመካነ ሕይወት ቅዱስ ሚካዔል ቤተ ክርስቲያን እና የመካነ ሰላም ቅዱስ ሚካዔል ቤተ ክርስቲያን እና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕምናን ዘንድ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ተከበረ። በበዓሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን የመካነ ሕይወት ቅዱስ ሚካዔል ቤተ […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የናይጀሪያ ጦር በቦኮ ሀራም አንፃር በጀመረው ትግሉ እንደቀናው ገለጸ። የናይጀሪያ ጦር ባለፉት ጊዚያት በአሸባሪው ድርጅት ቦኮ ሀራም አንፃር በተደጋጋሚ አሰመዘገብኩት ያለው ድል ብዙ ማነጋገር ይዞዋል።

መስከረም ፲፮(አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ዓመት በዘጠኝ ወራት ብቻ የሥራ ፈላጊዎችን መረጃ ለማጠናቀር ታስቦ በተካሄደ ምዝገባ በመላ ሀገሪቱ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ሥራ ፈላጊዎች በፈቃደኝነት መመዝገባቸውንና ከነዚህ ውስጥ ከ351ሺህ በላይ የዩኒቨርሲቲና የኮሌጆች ምሩቃን መሆናቸውን ከከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተገኘ ጥናት አመለከተ፡፡ ይህ ጉዳይ መጪው ምርጫ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል …

መስከረም ፲፮(አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት መሪ የሆኑት አቶ አለማየሁ መኮንን ለኢሳት እንደገለጹት መንግስት ከጀመረው የሸንኮራ እርሻ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ እየጠፋ ያለው ሰው ህይወት መንግስት መፍትሄ ሊሰጠው ካለመቻሉ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ነው። በጅንካ ነዋሪ የሆነው  ኡመር ንጋቱ  በሙርሲ ብሄረሰብ አባላት በጥይት ተደብድቦ እንደሞተ መነገሩን ተከትሎ ሃሙስ እለት ከቀብር መልስ …

መስከረም ፲፮(አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋር የተገናኙነት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፣ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በሰላም ማስጠበቅና ሽብርተኝነትን በመዋጋት በኩል እያደረገች ያለውን ሚና አወድሰዋል። አገሪቱ በደቡብ ሱዳንና በሶማሊያ ሰላም በማስጠበቅ በኩለ ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ኢትዮጵያ  የሰላም አስከባሪ በመላክ ቁጥር በአለም ግንባር ቀደም ከሆኑ መንግስታት ተርታ እንደምትመደብም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግስት …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የአንድነት ፓርቲ የኦዲት ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዳግም ተሰማ ከትላንት መስከረም 15 ቀን ጀመሮ መሰወራቸዉን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። « ዳግም፣ ድህንነቶች መኖሪያ ቤቱድረስ (ኦሎምፒያ) ሰሞኑን በዲኤክስ መኪና መጥተው ያነጋሩትንና ያስፈራሩትን አውግቶን ነበር፡፡ ይህንን ሲያወጋን ግን በራስ መታማመኑ እና ድፍረቱ ከራሱ ጋር ሆኖ ነው፡፡ ለዛሬጥዋት ፖሊስ ጋር ተጠርቶ ቀጠሮ ቢኖርበትም እሱ ግን ይበልጥ ትኩረት […]

በአንድነት ፓርቲ ወጣቶች አነሳሽነት፣ በአዲሱ የ2007 ዓ.ም ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ወጣቶች ኮሚቴ እየተንቀሳቀሰ ነው። እንደለመዱትና እንደከዚህ በፊቱም ሕወአት/ኢሕአዴጎች የዜጎችን ነጻ የመስብሰብ መብት እየረገጡ ፣ ሕገ መንግስቱን እየሻሩ ፣ እነርሱ ከሚፈልጉት ስብሰባ በቀር ምንም አይነት ሕዝባዊ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ ጫና እያሳደሩ ነው። የፓርቲው ብሄራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በቢሮ ዉስጥ በሚደረጉ ስራዎች ተጠምዶ፣ […]

“ምንም አይነት ደብዳቤ አልደረሰንም” አቶ ማርቆስ ብዙነህ የአ.አ.ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ማሳወቂያ ቢሮ አንድነት ለዴሞክራሲ ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የህሊና እስረኞችን ለማሰብ በመስከረም 3 እና መስከረም 11 ቀን 2007 ዓ.ም ለማድረግ ያሰብኩት የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ሊሳካልኝ ባይችልም፣ በመጪው መስከረም 25 ቀን 2007 ዓ.ም ግን ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አቅጃለሁ ሲል አስታወቀ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር […]

በይርጋለም ከተማ የሚገኘው የቤዛዊት የወጣቶች ማዕከል ባዘጋጀው የበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች የክረምት መርሃግብር የተሳተፉ ወጣቶችን እና ስራዎቻቸውን ዝግጅቱ ባጭሩ ይቃኛል።

ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (CPJ) መሰረት ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ለስደት በመዳረግ ኤርትራን ተከትላ ከአፍሪቃ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። የኢትዮጵያ መንግስት በአከራካሪው የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ጋዜጠኞችን ለእስር፤እንግልትና ስደት ይዳርጋል ሲሉ አለም አቀፍ ተቋማት ይተቻሉ።

የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በሁለቱ ሀገራት ዙርያ ዉይይት አደረጉ። የሁለቱ መንግሥታት መሪዎች ትናንት ኒዮርክ ላይ ዉይይት ከማድረጋቸዉ በፊት በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤

ያ ትውልድ ያመነበትን ተግባራዊ ለማድረግ ብዙ መስዋዕትነትን እንደከፈለው ሁሉ እህት በወንድም ላይ ጠቁማ ወደ ሞት የነዳችበትም አጋጣሚዎች ተፈጥረዋል ወንድም ከወንድም ጋር የሚያፋጅ ግዜ ላይም ነበሩ፤ ዛሬ ላይ እንደቀልድ ምንሰማው ለመፍረድም ቀላል የሚመስሉትአስቀያሚ የታሪኮቻችን አጋጣሚዎች ዛሬም ላይ ይከሰታሉ እኛም ስህተቶችን የምንደግም እንጂ ከስህተቶቻችን የምንማር ዓይነቶች አይደለንም፡፡
ከኢህአዴግ ወገን ላልሆነው ፖለቲካ የሚወደድ ሆኖባይሆንም በአገር ጉዳይ ያገባኛል ያሉ ሰዎች የሚገናኙባቸው ቦታዎች የተለመዱ ናቸው እስር ቤት፣ ሰላማዊ ሰልፍ(እጥረት ቢኖርብንም)እንዲሁም ፌስቡክ የመጀመሪያውን ተርታ ይይዛሉ፡፡ እንደውም ማህበረሰብ ሚዲያው እርስ በርስ ለመግባባት ለመገማገምና  ለመተዋወቅ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡ በኤዶም ካሳዬ እና በእኔ መካከልም ትውውቅምክንያት የሆነውና በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘነው ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት ለመሄድ ከተሰባሰቡት የዞን ዘጠኝ አባላት ጋር ተሰባስበን በነበረበት ወቅት ነበር ወዲያውም ኤዲ ጆማ ተባብለን ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ሞቅ ወዳለው የፖለቲካ ጨዋታ ስንገባ አይተውን የተጠራጠሩት ጓደኞቻችን ከዛሬ በፊትም ሳትገናኙ አልቀራችሁም አይነት ትንኮሳ ጀምረው ነበር የምንታጨቅበት ታክሲ ሲመጣ ወሬያችን ቢቋረጥም፡፡
Journalist Edom Kassaye
ከቂሊንጦው እስር ቤት የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ጥየቃ በኋላ በተለያዩ አጋጣሚዎች ተገናኝተን ተጨዋውተናል፣ እንደውም በአንድ ወቅት በጨዋታችን ውስጥ ደጋፊና ተቃዋሚ ጥግ እና ጥግ (አንዳንዴም ጽንፍ) የያዙ ፍረጃዎች ኑሮ ፈተና ለሆነባቸው የቤተሰብ ሃላፊዎች ስራቸው አስተማማኝ ይሆን ዘንድ አባልነት ግዴታ ሆኖባቸው አባል የሆኑትንና ያልሆኑት ግን ውሳኔዎችን ለማስቀየር ምንም ዓይነት አቅም እና ስልጣን የሌላቸው ነገር ግን በተቃውሞ ጎራ በካድሬነት የመፈረጅና የመዘለፍ አጋጣሚዎችን ያስተናገዱ ሰዎች ስለመኖራቸውና አንዳንዶች በብሔር ፖለቲካ ቅርቃር ውስጥ ተቸንክረው ወደ መከላከልና ጽንፍ የያዙ ደጋፊ ሆነው ስለመገኘታቸው እንዲሁም በኑሮ ውድነት ምክንያት መቃወም እየፈለገ ቤተሰቡን ማስተዳደር ፈተና ሆኖበት ከቤት ኪራይና ከሌሎች ወጪዎች የሚናጡ ባልና ሚስቶች ብሶትን መሰረት አድርገን መሃከል ላይ ስለምንገናኝበት አልያም የእነኚህን ሰዎች ስሜት ሌሎች እንዲረዱ ለማድረግ አንድ ጽሁፍ በጋራ ለመጻፍ ሁሉ ተመካክረን ነበር፡፡

በጋዜጠኛነት በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶችውስጥ ያሳለፈችው ኤዶም ከዞን ዘጠኞችና ከእነ አስማማውና ተስፋለም ጋር ስትከሰስ የግድ ዞን ዘጠኝ ነሽ እያሉ ነበር በሕግ የሚቀልዱትፖሊሶች የከሰሷት፡፡

ከዛ በፊት ግን ዞን ዘጠኝ ባትሆኚም ከእነሱ ጋርስለምትቀራረቢ መረጃ ስጪን እያሉ የገባችበት የሚገቡ በስልክ ፋታ የሚያሳጧት “ደህንነቶች” ነበሩ፤ ኤዲ በአንድ ወቅት የሆነ መስሪያ ቤት ስራ ለማመልከት ጎራ ብላ ስትወጣ አፍታም ሳይቆይ ይደወልላታል በዚህ ወቅት የደወለው ደህንነቱ ነበር የመስሪያ ቤቱን ባለቤትስም ጠርቶ “ ሥራ እንዳመለከትሽ ሰምቼያለሁ ከእኛ ጋር እኮ ብትተባበሪ የተሻለ ደረጃ በተሻለ ደሞዝ አስቀጥርሻለሁ” ብሏት ነበር፤በተደጋጋሚ ወቅትም “ዞን ዘጠኞች ለምን መጻፍ አቆሙ የተደበቀ ህቡህ ሥራ ስለጀመሩ ነውና መረጃ እንድትሰጪኝ እፈልጋለሁ አለበለዚያ ውጪ አገር ስብሰባ ላይ መንግስትን ለማሳጣት የተናገርሻቸውን ምክንያት አድርገን ልናስርሽ እንችላለን አንቺ ብቻ ተባበሪን እንጂ ወደ ውጪም መሄድ ከፈለግሽ አሜሪካም ሆነ አውሮፓ ምንም ችግር የለውም ትሄጃለሽ አንቺ ብቻ ተባበሪን “ የሚሉ ማስፈራሪያዎችና ማግባቢያዎች ይቀርቡላት ነበር ፡፡ ኤዶም በመልሷ “እኔ እስከማውቀው ልጆቹ ምንም እየሰሩ አይደለም ትልልቅ ሆቴል ውስጥ ኢንተርኔት ነጻ ስለሆነ እና ሰውም ስለማይበዛ ማኪያቶ  እየጠጡ የሚጨዋወቱናቸው መጻፍ ስላቆሙ ጓደኝታቸው ተቋረጠ ማለት ስላልሆነ ይገናኛሉ ከመንግስት ጫና ስላበዛችሁባቸው እንዲሁም በግል ምክንያቶቻቸውእንጂ ሌላ ነገር ስላሰቡ አይደለም” ብላ መልሳላቸው ነበር፡፡ የደህንነቶች ክትትል አሁንም የተባበሪና መረጃ አምጪ ትዕዛዝ ለረጅም ጊዜ ፋታ አልሰጣትም ነበር ፡፡በአንድ ወቅት ስብሰባ ላይ ሆና ስልክ ባለማንሳቷ የገባችበት እንደሚገባ እና እንደማታመልጣቸው ከዛቻ ጋር የጽሁፍ መልዕክት ተልኮላት እነደነበር ትዝ ይለኛል፡፡
ደህንነቱና አለቆቹ የሆነ ነገር እየተካሄደ ነው የሚል ስጋት መስከራቸው ምንም የሚያጠያይቅ አልነበረም፡፡ ( እኛም እነደ ቡድን አውነቱን ሲያውቁ ይተውታል የሚል የዋህነት ነበረብን) እናም ኤዶም የምታቀርበው እውነተኛ መረጃ ከሌለ በፈጠራም ቢሆን እንድትተባበራቸው ግፊት ሲደርጉባት የቆየ ቢሆንምለእንደዚህ አይነት ርካሽ ተግባር ተባባሪ ባለመሆኗ የጅምላ እስሩ ተቋዳሽ ሆናለች፡፡ የእኔም መትረፍ ያለኤዶም እና ናትናኤል ፈለቀ(ናቲ) የሚቻል አልነበረም፡፡ “freedom of expression ትሰራላችሁ ወንጀል አንደሆነ አታውቁም?” የሚሉ የእውቀት ደረጃቸው ለመግባባት አንኳን የሚያስቸግሩ ሰዎቸን እነ ኤዲ ለወራት ለማሳመን ሲጥሩ ከርመዋል፡፡
በታሰሩ ቀን ማግስት በነበረው ቅዳሜ ጠዋት ላይ በቅርቡ የልጅ አባት የሆኑትን ወዳጆቼንለመጠየቅ ከሰአት በኋላ ከዞን ዘጠኞች ጋር ቴስት ኦፍ አዲስ የምግብ ፌስቲቫልን ለመታደም ማታ ላይ የቴዲ አፍሮን ኮንሰርት ለመታደምአስቀድሜ አቅጄ የነበረ ቢሆንም ሰው ያስባል ኢህአዴግ ያስራል ሆነና የሕይወቴ አንዱ እና ትልቁ የምለው ብዙ ወንድሞቼንና እህቶቼን በእስር ያጣሁበት ማግስት ሆነ፡፡
#TimeStandStill pic edited by Mahilet Solomon
ጊዜው አምስት ወራት ተቆጥረዋል ቢልም ለብዙዎቻችን እንደቆመ ነው፣ ንጹህ ኅሊና ያላቸው ለትውልድ ምሳሌ የሚሆኑ ጓደኞቼን ህገ መንግስታዊ መብት ባልተከበረበት፣ የህግ የበላይነት እና የህግ ስርአት መመራት ቀልድ በሆነበት በስርአቱ አገልጋዩች መነካታቸው ያንገበግበኛል፣  ለኔ ጊዜው አሁንም እንደቆመ ነው ሻንጣዬ ውስጥ ያለውን እቃ አውጥቼ ቁምሳጥን ውስጥ ለመጨመር አዲስ ሕይወት ከጀመርኩ እነሱን የምረሳ እየመሰለኝ እንዳለ አለ ተመልሶ እነሱን እንደሚያገኝ ለጉዞ እነደተሰናዳ ሰው ልቤ እንደተሰቀለ እስካሁን አለሁ፡፡ ይህ እኔም ሆነ የተረፍነው ወዳጆቼ የምንጋራው ስሜት ነው፡፡
ራሳቸውንም ሆነ ቤተሰባቸውን የሚያኮራ መከራን ለመጋፈጥ የቆረጡ እውነተኛና ሃቀኛ ሰዎች ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል፤ እነሱንም የወለዱ እናትና አባቶች ሊኮሩ እንጂ ሊያዝኑ አይገባም፡፡
ኤዲ ያንቺ ጓደኛ ስለሆንኩ ኩራት ይሰማኛል፡፡

 #TimeStandStill #FreeZone9Bloggres #FreeEdom#FreeTesfalem #FreeAsmamaw #FreeAllPoliticalPrisoners

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የሟቹ የመለስ ዜናዊ ሰላባ ከሆኑት ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆች መካከል አንዱ ነበሩ። ከ19 ዘጠኝ አመታት በፊት፣ በኩወቤክ ካናዳ የቀድሞ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስተር ጆን ክሬቲየን፣ ባለፈው ሳምንት ደግሞ በስክቶላንድ የአሁኑ የእንግሊዘ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዴቪድ ካሜሮን ፣ የአገራቸውን አንድነት ለማስጠበቅ፣ ክዌቤክና ስኮትላንድ እንዳይገነጠሉ ብዙ የደከሙ፣ የድካማቸውን ፍሬ ያዩ አገራቸዉን እና ህዝባቸውን የሚወዱ መሪዎች መሆናቸውን ያስመሰከሩ […]

የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ በመንግስታቱ ድርጅት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ከሁለት ሺህ አስራ አምስት በሁዋላ ለሚኖረዉ የልማት አጀንዳ የዓለም አበይት ፈተናዎች በጋራ ለመጋፈጥ ነገር ግን የየራሳቸዉ ገጽታ ያላቸዉን ሃላፊነቶች መሰረት ያደረገ መተጋገዝም ለማጠናከር እንደሚረዳ ያላቸዉን እምነት ገልጸዋል።

ዓለም አሁን ያሉባትን እጂግ ከባድ ፍላጎቶች ለማሙዋላት አቅም ሃብር እንዳላት አስምረዉበታል።

አፍሪቃ በማደግ ላይ ያለች ለንግድና ለመዋእለ ንዋይ ምደባ ግዙፍ እድል የምትሰጥ አህጉር እንደሆነችና  ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙዎቹ የአገሮች የሚሊኒዬሙን ግብ ለማስመዝገብ ዝግጁ መሆናቸዉን ተናግረዋል።

ሆኖም አፍሪቃ ለልማት ያላትን ጉጉት የከባቢ ዓዬር ለዉጥ ችግር  እያደናቀፈ መሆኑን ጠቅሰዉ አፍሪቃ የችግሩ ምንጭ ባትሆንም የመፍትሔ…

ከሁለት ሳምንት በፊት በአቶ በረከት ስምኦን የተከፈተውና 15 ቀን የፈጀው ባህርዳር ላይ የተደረገው የ‹‹ፍትህ አካላት›› ስብሰባ ትናንት መስከረም 14/2007 ዓ.ም በአቶ በረከት ስምኦን ማስጠንቀቂያ መጠናቀቁን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ ስብሰባውን የዘጉት አቶ በረከት ስምኦን ‹‹ፖሊስ፣ አቀቤ ህግና ዳኛ ከአስፈጻሚው (ከካቢኔው) ጋር ተስማምቶና እጅና ጓንት ሆኖ መስራ አለበት፡፡ ይህ ነው ልማታዊ የፍትህ ስርዓት፡፡›› ማለታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ […]

ከመስከረም 10/2007 ዓ.ም እስከ መስከረም 12/2007 ዓ.ም በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተሰጠው የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› የማጥመቅ ስልጠና በምርጫው ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ኢህአዴግ እንዲመረጥ እንዲሰሩ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸውና እቅዱን ካላሳኩ ሸዳቸውን መስሪያ ቦታውን እንደሚያጡ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ሰልጣኞቹ ‹‹ግብር በዝቶብናል፣ ደንብ አስከባሪዎች በየጊዜው እየመጡ ገንዘብ ይወስዱብናል፣ በየወረዳው የመልካም አስተዳደር ችግር መፍትሄ ልናኝ አልቻልንም፣ ስለዚህ […]

የትግራይዋ ህወሓት ማለቴ በሰማእታት ሓወልት ፅሕፈት ቤትዋ ያደረገችው ህወሓት( ኣዲስ ኣበባ የህወሓት ኣንጃ ሰላለች ነው) “ኣብራሃ ደስታ የታሰረበት ምክንያት ኣላውቅም” ኣለች። ይህ ኑዛዜ የተሰማው በኣገር ደረጃ ለመንግስት ሰራተኞች እየተሰጠ ያለው ስልጠና የሚሉት(ተቃዋሚና ያለፉት ስርዓቶች የሚሰድቡበት መድረክ ስለመሰለ ነው) በትግራይ ክልል ፅህፈት ቤት(ደጀን ቢሮ) የሚሰሩ ሰራቶኞች በፕላኔት ሆቴል እየተካሄደ ባለው መድረክ ነው። በዚህ መድረክ እየተነሱ ያሉት […]

መስከረም ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 98 በመቶ የሚሆነውን የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ የአዛዥነት ቦታዎችን ከተቆጣጠሩት የህወሃት ጄኔራሎች ባልተናነሰ በከፍተኛ የስልጣን ቦታ ላይ የነበሩት ብቸኛው የአማራ ተወላጁ ጄኔራል አበባው ታደሰ በጄ/ል ሳሞራ የኑስ ትእዛዝ ከሃላፊነታቸው ዝቅ ብልው እንዲሰሩ ከተወሰነባቸው በሁዋላ፣ በመጨረሻ ከመከላከያ ሰራዊት መሰናበታቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ጄ/ል አበባው ከጄ/ል ሞላ ሃ/ማርያም እና ከጄ/ል […]

መስከረም ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን በጅንካ ከተማ በአይነቱ ልዩ ነው ተባለ የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉን የአካባቢው ምንቾች ገልጸዋል። የተቃውሞ ሰልፉ የተደረገው ከጅንካ ከተማ  ወደ ሃና በመጓዝ ላይ የነበረ አንድ ሰራተኛ መገደሉን ተከትሎ ነው። ሃና አዲሱ የስኳር ፋብሪካ ግንባታ የሚካሄድበት ቦታ ሲሆን፣ ግድያውን የፈጸሙትም የስኳር ልማቱ ከቀያቸው ያፈናቀላቸው የሙርሲ ብሄረሰብ አባላት …

መስከረም ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-98 በመቶ የሚሆነውን  የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ የአዛዥነት ቦታዎችን ከተቆጣጠሩት የህወሃት ጄኔራሎች ባልተናነሰ  በከፍተኛ የስልጣን ቦታ ላይ የነበሩት ብቸኛው የአማራ ተወላጁ ጄኔራል አበባው ታደሰ በጄ/ል ሳሞራ የኑስ ትእዛዝ ከሃላፊነታቸው ዝቅ ብልው እንዲሰሩ ከተወሰነባቸው በሁዋላ በመጨረሻ ከመከላከያ ሰራዊት መሰናበታቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ጄ/ል አበባው ከጄ/ል ሞላ ሃ/ማርያም እና ከጄ/ል ሰአረ …

መስከረም ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የመንግስትን ፖሊሲና ስትራቴጂ አልተቀበሉም ባላቸው አርሶ አደሮች ላይ በይፋ የማሸማቀቅ ስራ እየሰራ መሆኑን አርሶ አደሮች ለዘጋቢያችን ገልጸዋል። የገዢውን ፓርቲ ፖሊሶች ተቀብለው አባል ለመሆን ፈቃደኛ ያልሆኑ አርሶአደሮች ” ታካች አርሶ አደር “የሚል ስያሜ እየተሰጣቸው በተለያዩ መንገዶች እየተዋከቡና በእዳ እየተጠየቁ ሲሆን፣ የስርአቱ ደጋፊ የሆኑ አርሶአደሮች ደግሞ …

መስከረም ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላ አገሪቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ሀሰተኛ የብር ኖቶች የተሰራጩ ሲሆን፣ ፖሊስ በየቀኑ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ለመሰብሰብ ቢችልም ችግሩ አሁንም በስፋት እየታየ ነው። የፌደራል ፖሊስ መረጃ እንደሚያመለክተው በመላ አገሪቱ በተሰራጨው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሃሰት የብር ኖቶች መንግስት በየቀኑ ከባንኮችና ከገበያ ሱቆች ለመሰብሰብ ተገዷል። ፖሊስ በዚህ ስራ ላይ ተሰማርተዋል …

የፊታችን ግንቦት 2007 ዓ.ም ምርጫ ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል። ነገሮች ሳይበላሹና ሳይቆላለፉ ከወዲሁ እንዲታሰብበት ይችን አጭር ጽሁፍ ላቅርብ:: ምርጫ ማለት ከቀረቡ በርካታ አማራጮች መካከል አንዱን መምረጥ ማለት ነው። ሬስቶራንት ስንሄድ አስተናጋጆች ይመጣሉ። ሜኒዩ ይሰጡናል። የምግብ አይነቶች ተዘርዝረው እናነባለን።። ክትፎ፣ ጥብስ፣ ምጥን ሽሮ ..እያለ ብዙ አማራጮች ተደርድረዋል። አንዱን እንመርጣለን። ምርጫ ማለት ይሄ ነው። አማራጮች ካልቀረቡ፣ የተሰጠንን ተመገብን […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

“ይህ ውሣኔ ሰብዓዊ መብቶች፣ መሠረታዊ መብቶች፣ ለሕግ ተገዥነት አንደአማራጭ የሚቀመጡ አለመሆናቸውን፤ እንዲያውም የፀረ ሽብር ጥረቶቹ ቁልፍ አካላት መሆናቸውን ግልፅ ያደርጋል፡፡ እንዲያውም እነዚህን መብቶችና ነፃነቶች አለመጠበቅ አመፀኛ የሆነ ፅንፈኝነትን ይበልጥ እንደሚያራግብ ታሪክ ያስተምረናል፡፡”

ርዕሰ አዉዳ ዓመት፤ ወርኃ አደይ ወርኃ ጽጌን ተከትሎ በኢትዮጵያ በተለያዩ ብሄር ብሔረሰቦች በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ለመከበር በጉጉት የሚጠበቀዉ የመስቀል በዓል፤ ከሐይማኖታዊ ስርዓቱ ባሻገር ባህላዊ ገፅታዉ አከባበሩ ህብረ- ቀለማዊ ነዉ።

የተመድ አባል ሀገራት ፅንፈኞችን ለመቆጣጠር ጠንካራ ርምጃ እንዲወስዱ የየተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ትናንት ባሳለፈው ውሳኔ አሳሰበ። ሽብርተኝነትን ለማሸነፍ አባል ሀገራት ባጋራ መስራት እንዳለባቸው የተመድ ዋና ጸሐፊ ፓን ኪ ሙን ተማፀነዋል።

ስኖደን የተሸለመዉ በዓለም የማትደፈረዉን ሐያል ሐገር በማጋለጥ ለመናገር ነፃነት መከበር መቆሙን በማረጋገጡ ነዉ።ለወትሮዉ የተሸላሚዎች ሥም ዝርዝር በይፋ የሚነገርበት የሲዊድን ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ግን መስሪያ ቤት ግን የዘንድሮ ተሸላሚዎች ስም ዝርዝር ከቢሮዉ እንዳይነገር አግዷል