የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ንግግር፤
የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ በመንግስታቱ ድርጅት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ከሁለት ሺህ አስራ አምስት በሁዋላ ለሚኖረዉ የልማት አጀንዳ የዓለም አበይት ፈተናዎች በጋራ ለመጋፈጥ ነገር ግን የየራሳቸዉ ገጽታ ያላቸዉን ሃላፊነቶች መሰረት ያደረገ መተጋገዝም ለማጠናከር እንደሚረዳ ያላቸዉን እምነት ገልጸዋል።
ዓለም አሁን ያሉባትን እጂግ ከባድ ፍላጎቶች ለማሙዋላት አቅም ሃብር እንዳላት አስምረዉበታል።
አፍሪቃ በማደግ ላይ ያለች ለንግድና ለመዋእለ ንዋይ ምደባ ግዙፍ እድል የምትሰጥ አህጉር እንደሆነችና ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙዎቹ የአገሮች የሚሊኒዬሙን ግብ ለማስመዝገብ ዝግጁ መሆናቸዉን ተናግረዋል።
ሆኖም አፍሪቃ ለልማት ያላትን ጉጉት የከባቢ ዓዬር ለዉጥ ችግር እያደናቀፈ መሆኑን ጠቅሰዉ አፍሪቃ የችግሩ ምንጭ ባትሆንም የመፍትሔ…