ጥቅምት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የፓለቲካ እስረኞች ላይ ምርመራ ሲያካሂዱ ስቃይ እንደሚፈጽሙ ተቀማጭነቱን በአሜሪካ ያደረገው ሂዩማን ራይትስ ዎች ዛሬ ይፋ አደረገ፡፡ መንግስት በበኩሉ የቀረበውን ውንጀላ አስተባብሎ ሪፖርቱ ከእውነት የራቀና ተአማኝነት የሌለው ነው ብሏል፡፡ ድርጅቱ ታስረው የነበሩ እማኞች ዋቢ በማድረግ ባወጣው ሪፖርት ባለስልጣናት ከእስረኞች ቃል ለመቀበል ሲሉና ምርመራ ሲያካሂዱ ድብደባ እንደሚፈጽሙ አመልክቷል፡፡ …

ጥቅምት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያና ኬንያ በግልገል ጊቤ ሶስተኛ የሀይል ማመንጫ ግድብ ላይ ያላቸውን አለመግባባት እልባት ለመስጠት የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ፕሮግራም ሁለቱንም ሀገራት በማግባባት ላይ እንደሆኑ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ በኦሞ ወንዝ ላይ በመገንባት ላይ ያለችው የሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት በቅርብ የሚገኘውን የኬንያን ቱርካና ሀይቅ ይጎዳል በሚል የኬንያ መንግስት የአካባቢ ተቆርቋሪ ድርጅቶች ቅሬታቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡ …

ጥቅምት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያዊውን የእርሻ ሳይንቲስት አዲስ ለተቋቋመ የሳይንቲስቶች አማካሪ ቦርድ አባልነት መረጠው፡፡ ሳይንቲስቱ ፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጀታ 26 አባላትን ላካተተው የተባበሩት መንግስታት የሳይንቲስቶች አማካሪ ቦርድ ሲመርጥ ብቸኛ የእርሻ ሳይንቲስት እንደሆነ ኢሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ አዲሱ የተባበሩት መንግስታት የሳይንቲስቶች አማካሪ ቦርድ በአለም አቀፍ በተለያዩ ዘርፍ የታወቁ ሳይንስቶችን በአባልነት ይዞ ይገኛል፡፡ …

ጥቅምት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በጋምቤላ ክልል ንዌር ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ሚኒኛንግ ከተማ የተፈጠረው ግጭት ተባብሶ የሞቱ የመከላከያ ሰራዊት ቁጥር መጨመሩና በርካታ መሳሪያዎች ከመከላከያ ካምፕ መወሰዳቸው ተገለጸ፡፡ ባለፋው እሁድ አንድ መሳሪያ የታጠቀ ሰው እግር ኳሱን ሲመለከቱ በነበሩ ሰዎች መካከል ባስነሳው አለመግባባት የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና ነዋሪዎች ግጭት ውስጥ ገብተው ሰንብተዋል፡፡ ግጭቱ …

ጥቅምት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል ዳውሮ ዞን ከሁለት ዓመት በፊት ተቀስቅሶ የነበረው የመልካም አስተዳደር እጦት ጥያቄ በአዲስ መልክ መቅረብ በመጀመሩ በዞኑ ውጥረት መንገሱን ተገለጸ፡፡ በዞኑ የሚኖሩ ማህበረሰብ ከፍተኛ የሆን የመልካም አስተዳደር ችግር እንዳለባቸው በመግለጽ ላይ መሆናቸውን የዳውሮ ዞን አካባቢ ተወላጅ የሆኑት አቶ ፍሰሀ ተስፋዬ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አመልክተዋል፡፡ አዲስ …


‹‹በእግዚአብሔር ስም እምልላችኋለሁ የማውቀው ነገር የለም…›› አለ እየጮኸ፡፡
‹‹ገልብጡት›› አለ ኮማንደሩ፤ አላመነውም ነበር፡፡
ከግራና ቀኙ ቆመው የነበሩት ሁለቱ ፖሊሶች ገፍትረው በአፍጢሙ ደፉት፡፡ ወለሉ የአፈር ስለነበር ብዙም አልተጎዳም፡፡ እግሮቹ ቋንጃ ላይ ወፈር ያለ ቧንቧ ብረት አስገብተው እግሮቹን የኋልዮሽ በመጎተት በጠፍር መሳይ ገመድ ከወገቡጋ አሰሯቸው፡፡ የቧንቧ ብረቱን ዳርና ዳር ይዘው ሲያነሱት ቁልቁል ተዘቀዘቀ፡፡ አንጠልጥለው ግድግዳው ላይ የተሰኩ ሁለት አግድም ምሰሶዎች ላይ ሰቀሉት፡፡
‹‹አሁንስ አትናገርም?›› አለው ኮማንደሩ፡፡
‹‹ኧረ እኔ ምንም የማውቀ…›› የጀመረውን ሳይጨርስ በፊት አንደኛው ፖሊስ በያዘው ደረቅ ጎማ ጀርባውን አደረቀው፡፡
‹‹እውነቱን ትናገራለህ ወይስ አትናገርም?›› አለው ኮማንደሩ በድጋሚ፤ ከመናገር ይልቅ ዝም ማለት ያዋጣል በማለት ዝም አለ፡፡
‹‹ትናገራለህ፣ አትናገርም›› አለው ኮማንደሩ፤ ዝም አለ!
ሁለቱም ፖሊሶች በደረቅ ጎማቸው ተፈራረቁበት፤ ‹‹እናገራለሁ፣ እናገራለሁ…›› አለ በጩኸት፡፡ ዱላውን አቆሙለት ነገር ግን የሚናገረው ስላልነበረው ዝም አለ፡፡
‹‹ተናገራ፣…›› አለ ኮማንደሩ በብስጭት ጩኸት እያምባረቀ ከጥቂት ደቂቃዎች ዝምታ በኋላ፡፡
‹‹እ…ግ…ዚ…አ…ብ…ሔ…ር…ን… ምንም የማውቀው ነገር የለም፡፡›› አለ የመሐላውን እያንዳንዷን ድምፅ አጥብቆ እየጠራ፡፡ ቁጥሩን ለማያስታውሰው ጊዜ ሁለቱ ፖሊሶች በደረቅ ጎማቸው ጀርባው ላይ ተረባረቡበት፡፡
‹‹አትናገርም፣… ›› አለ ኮማንደሩ፡፡
‹‹ምን ልናገር…? በእግዚአብሔር አታምኑም… ኧረ እባካችሁ…››
‹‹እስከ ጥዋት ድረስ አስብበት… እስክትናገር ድረስ ከዚህ አትወርድም›› ብሎት ኮማንደሩ ክፍሉን ለቆ ወጣ፡፡ ሁለቱ ፖሊሶች እጆቹን በካቴና ጠርንፈው ሲያበቁ ኮማንደሩን ተከትለው ከወጡ በኋላ በሩ በላዩ ላይ ተጠረቀመ፡፡ ቤቱ ዓይን በሚያወጣ ጨለማ ተዋጠ፡፡ እንደዘቀዘቁት ይቆያሉ ብሎ አላመነም ነበር፡፡ ከአሁን አሁን አንዳቸው ተመልሰው ይመጣሉ ብሎ አሰበ፣ ተመኘ፣ ፀለየ – ምንም የተለወጠ ነገር የለም፡፡

ያጠፋው ጥፋት ምን እንደሆነ አልገባውም፡፡ ድምፁን አውጥቶ ጮኸ፣ ተለማመነ… ነገር ግን መጥቶ የሚረዳው ሰው ቀርቶ የሚሰማው ሰው መኖሩን እስኪጠራጠር ድረስ መልስ አጣ፡፡ በካቴና የታሰሩትን እጆቹን የሚያረግበት ቦታ አጣ፡፡ ወደላይ ሲያደርጋቸው በደቂቃ ውስጥ ክንዱ ይዝላል፡፡ ወደታች ሲለቃቸው ሰውነቱን ከመጎተትም በተጨማሪ ጣቱን የሚቆጠቁጥ ድንዛዜ ይሰማዋል፡፡ ከላይ እግሮቹ መሐል ያለው ብረት ጉልበቱን ለሁለት በጥሶ ሊወጣ የደረሰ ይመስል ወጥሮ ይዞታል፡፡
እያንዳንዷ ደቂቃ የሰዓት ያክል ረዘመችበት፡፡ እልፍ የስሜት መለዋወጦችን በደቂቃዎች ውስጥ ያስተናግዳል፡፡ ድንገት የማቅለሽለሽ ስሜት ተሰማው፡፡ እዚያው የተዘቀዘቀበት ሊያስመልሰው እንደሆነ ገባው፤ ነገር ግን ውጦ ሊመልሰው አይችልም – ተዘቅዝቋል፡፡ ሆዱ ውስጥ ያለው ምግብ ወጣ፡፡ በተዘቀዘቀው ፊቱ፣ በግንባሩ ላይ ቁልቁል ፈሰሰ፡፡
‹‹አምላኬ ካላዳንከኝ ቶሎ ግደለኝ…›› ብሎ ፀለየ፡፡ ያጠፋውን ጥፋት አያውቅም፡፡ ፖለቲካ አይወድም፤ ‹ፖለቲካና ኮረንቲን ከሩቁ› ባይ ነው፡፡ ፖሊሶቹ ተመልሰው ሲመጡ ምን እንደሚላቸው ግራ ገብቶታል፡፡ ካልሆነ መዋሸት እንደሚሻል እያሰበ ነው፡፡ ምን ብሎ ይዋሻል? ውሸቱንስ እንዴት እውነት ማስመሰል ይቻላል? ሕመሙ… በአግባቡ ማሰብ አላስቻለውም፡፡ በክፍሉ ውስጥ የሚሰማው ብቸኛ ድምፅ እምባው በግንባሩ ላይ ፈሶ መሬት ላይ ሲንጠባጠብ የሚወጣው ድምፅ ብቻ ነው፡፡ አፍንጫው እየተዝረከረከ የሚያወጣው ፈሳሽ ዓይኑ ውስጥ እየገባ ያሰቃየው ጀመር፡፡ ከእግር ጥፍሩ እስከራስ ፀጉሩ ድረስ ሕመም ይሰማዋል፡፡
ቀስ በቀስ ግን ሰውነቱ እየቀዘቀዘ መጣ፡፡ መጀመሪያ እግሮቹን አጣቸው እንደተዘቀዘቀ ነው፡፡ እግሮቹ ከላይ መታሰራቸው ይታወቀዋል፡፡ ግን ሕመሙ አይሰማውም፡፡ ደንዝዟል፡፡ ሊያንቀሳቀሳቸው ሲሞክር አይችልም፡፡ እግሮቹ ከላይ ይኑሩ አይኑሩ እርግጠኛ መሆን አቃተው፡፡ ጨለማ ነው፣ ምንም ዓይታየውም፡፡ አዕምሮውም እግሮቹን ማዘዝ አቅቶታል፡፡
ወደታች የተንጠለጠሉት እጆቹ ጣቶች ደም አርግዘው በማበጣቸው ሊፈነዱ የደረሱ ይመስላሉ፡፡ ጥዝጣዜያቸው እከኩኝ፣ እከኩኝ ቢያሰኝም የሚያክበት ትርፍ እጅ አልነበረውም፡፡ ከላይ እየቀዘቀዘ፣ ከታች እየተቃጠለ ነው፡፡ ሕይወቱ ቀስ በቀስ እየወጣች እንደሆነ ተሰማው፣ ፈራ፡፡ ቀድሞ ግደለኝ ብሎ የለመነውን አምላኩን ደግሞ ‹‹አትግደለኝ›› እያለ በሹክሹክታ ይለማመነው ጀመር፤ ከዚያ በኋላ የሚያስታውሰው ነገር የለም፡፡
—-
—-
ቅዝቃዜ ይሰማዋል፡፡ ሙሉ ሰውነቱ ይቀዘቅዛል፡፡ ጭው ባለ ሜዳ ላይ ብቻውን በጀርባው ተንጋሏል፡፡ ዝናብ እየዘነበ ነው፡፡ ዝናቡ ግን የሚንጠባጠብ ዝናብ አይደለም፡፡ ሰማዩ የተቀደደ ይመስል ጎርፍ ነው እላዩ ላይ የሚወርደው፡፡ ዝናቡ ይቋረጥና፣ ጥቂት ቆይቶ መልሶ ይደፋበታል፡፡ ሰውነቱ ዝሏል፡፡ በትግል ዓይኖቹን ገለጣቸው፡፡ አንዱ ፖሊስ የውኃ ባልዲ ይዞ ቁልቁል ይመለከተዋል፡፡ አዎ፣ ትዝ አለው፡፡ ታስሮ ነበር፡፡ ተዘቅዝቆ ሲገረፍ ነበር፡፡ ዘቅዝቀው ሰቅለውት ጥለውት ሄደው ነበር፡፡ አዎ፣ ትዝ አለው፡፡ ያ ሁሉ ስቃይ፡፡ አሁን ወርዷል፡፡ መሬት ላይ ተዘርሯል፡፡ ውኃ እየደፉበት ነበር፤ ዝናብ አይደለም ማለት ነው፡፡ ድጋሚ ሊጠይቁኝ ነው የመጡት ብሎ አሰበ፤ ምን ሊላቸው ነው?
‹‹ተነስ!›› አለው ፖሊሱ፡፡
መነሳት አልቻለም፡፡ እጁን ዘረጋለት፡፡ ‹‹እንኳን ደስ አለህ፤ ነጻ መሆንህ ተረጋግጧል፡፡ ስለዚህ ከሁለት ቀን በኋላ ትለቀቃለህ›› አለው፡፡ ‹‹እንደዚያ ካሰቃያችሁኝ በኋላ…?›› ብሎ መጠየቅ አልቻለም፡፡ ፈርቷቸዋል፡፡ ለሁለት ቀናት እንዲያገግም እዚያው ‹‹ማረሚያ›› ቤት ውስጥ አቆዩትና ነጻ ወጣ፡፡ ‹‹አገሪቷን ለቅቄ መጥፋት›› አለብኝ እያለ ነው በልቡ፤ ሁሉንም ነገር በጥርጣሬና በፍርሐት እየተመለከተ ነው፡፡ ነጻ መውጣቱን እንኳ ማመን አልቻለም፡፡ ምናልባት ቅዠት ቢሆንስ?!
ሁለት፣ ሦስት እያለ አንድ ሳምንት ሞላው፡፡ መረጋጋት ጀመረ፡፡ ገጠመኙን ለማንም መናገር አልፈለገም፡፡ የገዛ ጥላውን ሳይቀር እየተጠራጠረ ነው፡፡
ብዙ ነገር አሰኘው፡፡ እንደሰው መሳቅ፣ መጫወት፣ በቀን ክፉ ያቋረጠውን ኑሮ መቀጠል አማረው፡፡ ከቤቱ ወጥቶ መንገዱ ይዞ ዝም ብሎ ይጓዝ ጀመር፡፡ በጠንካራ ሐሳብ የታጀበ መንገድ፡፡ እመንገዱ ላይ ያገኘው አንድ ኢንተርኔት ካፌ ዘው ብሎ ገባ፡፡ ኢሜይሉን ከፈተው፡፡ ምንም ያላነበበው ኢሜይል የለም፡፡
‹‹እንዴ?…›› አለ ለራሱ፡፡
የመጨረሻው ኢሜይል ከቀድሞው የሥራ ባልደረባው እሱ የታሰረ ዕለት የተላከ ነበር፡፡ አላነበበውም፤ ግን የተነበቡ ኢሜይሎች ውስጥ ተቀምጧል፡፡ ትዝ ሲለው የኢሜይል አድራሻውን እና የይለፍ ቃሉን ለኮማንደሩ ተናግሮ ነበር፡፡ ‹አንብበውታል ማለት ነው› አለ፤ የሥራ ባልደረባው የፌስቡክ ፖለቲከኛ ስለነበር በዚያ ጉዳይ አይስማሙም ነበር – በእሱ ጉዳይ ይሆን ያሰሩኝ ብሎ ጠረጠረ፤ ነገር ግን ከሱጋ የነበራቸው ግንኙነት የሩቅ ነበር፡፡ አሁን ግን ወደውጭ አገር ሄዶ ነው እየተባለ ቢወራም በድንገት ከሥራ ቀርቶ መልቀቁን ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ እንዲያውም ወደውጭ አገር መሄዱን ሲሰማ ‹‹ለካስ ፌስቡክ ላይ ፖለቲካ የሚጽፈው ጥገኝነት ለመለመኛ ነው?›› ብሎ ነበር፡፡ ምን ብሎ ጽፎልኝ ይሆን ብሎ ቢያስብም መክፈት ግን አስፈራው፡፡ ፖሊሶቹን መልሶ እንደመጥራት አስፈራው፡፡
ብዙም አላስቻለውም፤ ብዙ ካመነታ በኋላ መልሶ ኢሜይሉን ከፈተው፡፡ እንዲህ ይነበባል፡-
‹‹አሁን ለምጽፍልህ ነገር ይቅርታ እንድታደርግልኝ እለምንሃለሁ፡፡ ሆኖም፣ ነፍሴን ለማትረፍ ከዚያ ውጪ አማራጭ አልነበረኝም፡፡ ፖሊስ በማላውቀው ነገር ይዞ ሲያሰቃየኝ ነበር የከረመው፡፡ አብረውህ የሚሠሩትን አጋልጥ እያሉ ሲቀጠቅጡኝ እና ምስጢር ካወጣሁ እንደሚለቁኝ ቃል ሲገቡልኝ፥ አንተንና ሌሎችም ስማቸው የመጡልኝን የሥራ ባልደረቦቼን እና ጓደኞቼን ስም ዘርዝሬ ነገርኳቸው፡፡… ከለቀቁኝ በኋላ በሌላ ስቃይ ድንበር አሳብሬ ጎረቤት አገር ገብቻለሁ፡፡ አሁን የምመክርህ ነገር፣ ማቄን ጨርቄን ሳትል አገር ለቀህ እንድትወጣ ነው፡፡ አለበለዚያ አንተንም ይይዙህና ምንም የማያቁ ሰዎችን ስትጠቁም… ተጠቋቁመን ማለቃችን ነው…››
ያነበበውን ማመን አቃተው!
—-
ይህ አጭር ልቦለድ የተጻፈው ዛሬ በተለቀቀው የሰብኣዊ መብቶች ታዛቢ የማዕከላዊ ፖሊስ ጣብያ የማሰቃየት ተግባር ማጋለጫ ሪፖርት ላይ በወጡ ሐሳቦች ላይ በመመርኮዝ ነው፡፡

ማዕከላዊ ተብሎ በሚታወቀው የፌደራሉ የምርመራ ጣቢያ ሶስት የተለመዱ ስፍራዎች አሉ።አንደኛው ሰዎች ያለመብራት የሚታሰሩበት እና ጭለማ ቤት የሚባለው ነው።ሁለተኛው ለግርፋት የተመቻቸው ጣውላ ቤት የሚባለው ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ በተሻለ ደረጃ የሚታሰሩበት እና ከዚሁ የተነሳ በሌስሊ ኣባባል «ሸራተን» ተብሎ የሚታወቀው ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከተፎካካሪው የናይጀሪያ ብሔራዊ ቡድን ጋ በአዲስ አበባ ስታዲየም ግጥሚያ ያካሄደው ባለፈው እሁድ ዕለት ነበር። ይህንኑ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ዋና ምክንያት በማድረግ ወጣቱ ያሳየዉ ሥነ ምግባር በዛሬው የወጣቶች ዓለም ባጭሩ እንቃኛለን።

ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደዉ የዓመቱ የመጀመሪያ ስብሰባዉ አዲሱ ፕሬዝደንት ባለፈዉ ሳምንት ባቀረቡት የዓመቱ የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛው ምህፃር «ፍሮንቴክስ» የተባለው ለአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የድንበር ጥበቃ ድጋፍ ሰጭ ድርጅት ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በጀልባ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞችን በመመለስ የደረሰበትን ወቀሳ አመነ ።

አቶ ምኅረት ደበበ – የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ​​
ኅዳሴ ግድብ እና የዓለምአቀፉ ቡድን ሪፖርት
ታዋቂ የሆኑ ጋዜጦችና የዜና ወኪሎች ስለናይል ወይም ስለአባይ ወንዝ እና ስለኅዳሴ ግድብ እየፃፉ ነው፡፡

የኒው ዮርኮቹ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙኃን ብሉምበርግ፣ ዘ ዋል ስትሪት ጁርናል፣ ዘ ናሽናል ከእነዚያ መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

ዘ ዋል ስትሪት ጁርናል በረቡዕ፣ ጥቅምት 6/2006 ዓ.ም ዕትሙ ባሠፈረው ዘገባው ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በመጭው ሣምንት ማክሰኞ፣ ጥቅምት 12/2006 ዓ.ም እንደሚሰበሰቡ የኢትዮጵያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በምንጭነት ጠቅሶ ፅፏል፡፡
Ethiopia, Sudan, Egypt, Eritrea ​​
ይህ ስብሰባ የሚካሄደው በሦስቱ ሃገሮች የተመሠረተው የኤክስፐርቶች ቡድን የቅኝት ሪፖርቱን ካስገባ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ …

ጥቅምት ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን በጨንጫ ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤት መምህራን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ከደሞዛቸው ላይ ገንዘብ መቆረጡን ተከትሎ ካለፉት 3 ቀናት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ እያደረጉ ነው፡፡ የጨንጫ ፣ ጭነቶ፣ ጦሎላ፣ ጨፌ፣ ጺዳ እና ቱክሻ  ትምህርት ቤቶች መምህራን በአድማ ላይ መሆናቸውን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ተማሪዎች ቤታቸው …

ጥቅምት ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚ ሀይለማርያም ዛሬ በተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከፓርላማ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ መንግስት የጎዳና ላይ ነውጥ ከሚያሰቡት ሀይሎች ጋር ለመነጋገር የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል። አቶ ሀይለማርያም በተቃዋሚዎች በኩል የሚቀርበው ቅጥ ያጣ ፍረጃ እና የጥላቻ ፖለቲካ እንዲቆም  እንዲሁም የጎዳና ላይ ነውጥ እናደርጋለን በማለት የሚያስቡ ሀይሎችም ሀሳባቸውን እንዲያቆሙ ጠይቀዋል። “የጎዳና …

ጥቅምት ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስብሰባው ላይ የተሳተፉ አባቶች ለኢሳት እንደገለጹት በዛሬው ስብሰባ የልማት ኮሚሽኑ ሪፖርት ሰፊ ሽፋን የተሰጠው ሲሆን፣ መንግስት በቤተክርስቲያኑዋ ገቢ ላይ እየተጠቀመ መሆኑ ተነግሯል። የኮሚሽኑ መሪ ” በጭንቅ ውስጥ ነው እየሰራን ያለነው ፣ በመኖርና ባለመኖር ውስጥ እንገኛለን ያሉ” ሲሆን፣ ስሜታቸውን በድፍረት ሲናገሩ ከዋሉት ጳጳሳት መካከል ብጹዕ አቡነ ቄርሊዎስ ” ዛሬ ጀመርነው፣ …

ጥቅምት ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ኃ/ማርያም ዛሬ ጠዋት የአገር አቀፍ የጸረ ሙስና ጥምረት 2ኛ መደበኛ ስብሰባ በሸራተን አዲስ በተካሄደበት ስነስርኣት ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር አንዳንዶቹ ባለሃብቶች ከከፍተኛ መንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ሳይቀር የጠበቀ ቁርኝት ፈጥረው እንደነበር አምነው በዚህም ምክንያት ሰዎቹን መንግስት አይደፍራቸውም ተብሎ በህብረተሰቡ ዘንድ እስከመገመት ደርሶ ነበር ሲሉ ተናግረዋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት የመንግስት …

ጥቅምት ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ በአዲስ አበባ የውሀ ቀለም አይቶ የማያውቅ ህዝብ አለ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ 65 በመቶ የሚሆነው የአዲስ አበባ ህዝብ ውሀ 24 ሰአት እንደሚያገኝ ገልጸው፣ 20 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በሳምንት 5 ቀናት፣ ከ10-15 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በሳምንት አንድ ቀን ውሀ ያገኛል ብለዋል። በአብዛኛው የአፍሪካ ዋና ዋና ከተሞች የውሀ …

በእንግሊዘኛው ምህፃር FRONTEX የተባለው ለአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የድንበር ጥበቃ ድጋፍ ሰጭ ድርጅት ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በጀልባ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞችን በመመለስ የደረሰበትን ወቀሳ አመነ ።

በዓሉ የሚከበረው ነቢዩ ኢብራሂም ልጃቸውን ለመስዋዕት ያቀረቡበትን ዕለት ለማሰብ ነው፡፡ በዓለም ዙርያ የሚገኙ የዕምነቱ ተከታዮች በአንድነት በመሆን በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች የአረፋን በዓል አክብረዋል ።

ዉርሰ ኢትዮጵያ የተሰኘዉ ድርጅት ሰሞኑን በጀርመኗ ታሪካዊት ከተማ ጎታ 16ኛዉን ዓመታዊ ጉባኤዉን አካሂዷል። ጎታ ኢትዮጵያዉ አባ ጎርጎርዮስና ጀርመናዊዉን ሂዮብ ሉዶልፍን ከሶስት መቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት ያስተናገደች ከተማ ናት።

የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የሃገሪቱን የበጀት ጣሪያ ከፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ስምምነት ትናንት ማታ ካፀደቀ በኋላ ለ16 ቀናት የተዘጉት የተወሰኑ የፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ዛሬ ሥራ ጀምረዋል ። የሃገሪቱ የበጀት ጣሪያ ከፍ እንዳይል ሲሟገቱ የቆዩት ወግ አጥባቂ ሪፐብሊካኖች ውሳኔውን ሊያስቀሩት ባለመቻላቸው ሽንፈታቸውን አምነዋል ።

የመንበረ ፓትርያርክ 32ኛው ጉባኤ የረቡዕ ዕለት ከሰዓት ውሎ ካለፉት የተለየ ነበር፡፡ ዋና አጀንዳው ‹መቻቻልን› የተመለከተ ሲሆን አቅራቢዎቹም ከፌዴራል ጉዳዮች የተወከሉ አካላት መሆናቸውን በዕለቱ የመርሐ ግብር ዝርዝር ላይ ተገልጧል፡፡ ከሰኞ ጀምሮ ይቀርብ በነበረው የአህጉረ ስብከት ሪፖርቶች ላይ የመብት ጥሰትና ሥልጣንን ለግል ሃይማኖት ማስፋፊያ የመጠቀም አዝማሚያዎች መኖራቸውን፣ በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠው እምነትን የመያዝ፣ የማስፋፋትና የአምልኮ ቦታ የማግኘት መብት እየተጣሰ መሆኑን የሚገልጡ ዘገባዎች ይሰሙ ነበር፡፡

በትናንትናው የከሰዓት ውሎ ስለ መቻቻል ገለጣ ከተሰጠ በኋላ ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳትና የጉባኤው ተሰብሳቢዎች የየአካባቢያቸውን ችግሮች በዝርዝር ነበር ያነሷቸው፡፡ ‹‹መቻቻል እስከ ምን ድረስ ነው›› ብለው ነበር ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ የጠየቁት፡፡ ‹‹አሁን በምዕራብ ወለጋ ያለው ሁኔታ መንግሥት በአገሩ ያለ ይመስላል ወይ? ሰው እግሩን እሳት እየበላው ቻል ይባላል እንዴእንድንቻቻል አድርጉን፣ እንችላለን›› ነበር ያሉት፡፡

የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሄኖክ ‹በነጆ ወረዳ በሕጋዊ መንገድ ተሠርቶ የነበረው ቤተ ክርስቲያን በአካባቢው ባለ ሥልጣናት ተጽዕኖ እንዲፈርስ መደረጉን፣ ለምን ታፈርሳላችሁ ብለው ድርጊቱን የተቃወሙ ስድሳ ምእመናን መታሠራቸውን›› በኀዘን ነበር የገለጡት፡፡ አያይዘውም ‹‹በባኮ ወረዳ የተመደቡ አንድ ካህን እያረሱ እያሉ የአካባቢው ባለ ሥልጣናት መጡ፤ ካህኑን በሰደፍ እየደበደቡ ‹ከዚህ ሀገር ልቀቁ፣ ይህ የነፍጠኛ መኖሪያ አይደለም› እያሉ አሰቃዩዋቸው፡፡ ካህኑን ሲደበድቧቸው አንበርክከው፣ ለ15 ደቂቃ አተኩረው ፀሐይዋን እንዲያዩ እያስገደዱ ነበር፡፡ ድብደባውን ሰምተው የወጡት ባለቤታቸው በድንጋጤ ታመው ከጥቂት ቀናት በኋላ ሕይወታቸው አለፈ››

‹‹በሰንበትና በቅዱስ ሚካኤል ቀን ምእመናን ሊያስቀድሱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄዱ ‹ለቅዳሴ ካህናቱ ይበቃሉ፤ እናንተ ውጡ›› እየተባሉ እንዳያስቀድሱ ይደረጋሉ፡፡ ከእኛ ቤተ ክርስቲያን 70 ሜትር ርቀት ላይ ሆን ተብሎ እርስ በርስ ለማጋጨት ለፕሮቴስታንቶች የጸሎት ቦታ ተሰጠ፡፡ ለምን ታጨቃጭቁናላችሁ፤ ይህ ቦታ ለእነርሱ አይሆንም ብሎ በመከራከሩ አንድ ዲያቆን ተደብድቦ ሞተ፡፡ የሕክምና ውጤቱም ሆን ተብሎ በወባ በሽታ ሞተ ተብሎ ተሠራ፡፡ ለሁለት ዓመት ያህል ተከራክረን አሁን ቦታው ለእኛ ተወሰነ፡፡

ጊምቢና መንዲ ላይ የምእመናን ልጆች ትምህርት ቤት ውስጥ በፖሊስ ማተባችሁን በጥሱ እየተባሉ ነው፡፡ ለምን ስንላቸው ከላይ የወረደ መመሪያ አለ ይሉናል፡፡››

ቀጥለው የሀገረ ስብከታቸውን ችግር ያቀረቡት የጋሞጎፋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤልያስ ነበሩ፡፡ ‹‹በጋሞ ጎፋ መቱ ወረዳ፣ ዋጁ ኡቆ ላይ የመስቀል ማክበሪያ ቦታችን ለሱቅ መሥሪያ ቦታ ተሰጠ፡፡ አቤት ብንል የሚሰማን በማጣታችን ዘንድሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መስቀል ሳናከብር ዋልን፡፡ ሀገሪቱ በችግር ላይ በነበረች ጊዜ እንኳን መስቀል ሳይከበር ቀርቶ አያውቅም ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያን የይዞታ ቦታ ለመንግሥት እየተሰጠ ነው፡፡ በአቡነ ጳውሎስ ዘመን በቅዱስነታቸው በኩል ለክልሉ ደብዳቤ ጻፍን፡፡ ክልሉ ወሰነልን፡፡ ነገር ግን እስካሁን አልተረከብንም፡፡››

ቀጥለው ሃሳባቸውን የሰጡት የባሰ ካልመጣ በቀር ድምጻቸው ማይሰማው ብጹዕ አቡነ ያሬድ የሶማሌ ክልል ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነበሩ፡፡ ‹‹በሶማሌ ክልል አምስት አብያተ ክርስቲያናት ብቻ ናቸው ያሉን፡፡ ምእመናኑ ብዙ ናቸው፡፡ ሲወልዱ የሚያስጠምቁበት፣ ሲያርፉ የሚቀበሩበት ቤተ ክርስቲያን እንትከል ብንል የሚሰማን አጥተናል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን የሚረዱ ምእመናን በግላቸው ጥቃት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ለዚህ መልሳችሁ ምንድን ነው›› ብለዋል፡፡

በገለጻው ላይ ኢትዮጵያ ክርስትናን የተቀበለችው በ4ኛው መክዘ ነው የሚለውን የተቃወሙት ብጹዕ አቡነ ማርቆስ ‹‹ታሪክ ክፉም ሆነ በጎ እንደ ታሪክነቱ መተረክ አለበት፤ አቅራቢው ወንድማችን በ4ኛው መክዘ ክርስትና ገባ ያልከው ተሳስተሃል፡፡ ለመሆኑ ይህንን ለማለት ‹ላይሰንስ አለህ?› አባቱን የሚኮንን ልጅ ምን ያደርጋል? ነገሥታቱን ወቀሳችሁ፣ ቤተ ክርስቲያንን ነቀፋችሁ፤ ለመሆኑ ከማን ነው ይህቺን ሀገር የተረከባችሁት? ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገባው ጌታ ባረገ ዓመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8 ላይ አለ፡፡ ይህንን ዛሬ ‹ግራጁዌት አድርገው›፤ ልዑካኑ ስትመጡ ስለምትናገሩት ነገር ዕወቁ፤››

የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ እንድርያስም ‹‹በቤተ መንግሥት የወርቅ ዕቃ ብቻ አይኖርም፣ የእንጨትም፣ የድንጋይም ዕቃ አለ፡፡ በቤተ ክርስቲያንም ሁሉም ጥሩ አይሆንም፣ መጥፎም ይኖራል፡፡ ነገር ግን እስከ መጨረሻው የጸና ይድናል ብሏል፡፡ በእኔ ሀገረ ስብከት ስድስት አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፡፡ ሦስቱ በአንድ አካባቢ፣ ሦስቱ በሌላ ቦታ፡፡ ይህንን ለክልሉ መንግሥት ብናሳውቅ አልረዱንም፡፡ የተበደለ ሰው ይጮኻል፤ ሲጮህ ደግሞ ፖለቲካ ነው ይባላል፡፡ ድሮ ያስቸገረን የንዋያተ ቅድሳት ዘረፋ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ወደ ማቃጠል ተዛውሯል፡፡ አንዱ ባለ ሥልጣን እንዲያውም ችግሩን ሳቀርብለት ተቆጣኝ፤ ብዙ ብናገር ነፋስ ስለሚወስደው እዚህ ላይ ይብቃ››

ከብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳት ቀጥሎ የተናገሩት የወላይታ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ‹‹በበዴሳ ወረዳ ያለ አንድ የሌላ እመነት ተከታይ የሆነ ዳኛ ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጋር ቄራ አንካፈልም፤ በመኪና አብረን አንሄድም› ብሎ ዐወጀ፡፡ በጋራ በመቻቻል የኖርንበትን ዕድር ሁሉ ለዩ ብሏል፡፡ ታድያ እንዴት መቻቻል ሊመጣ ይችላል፡፡››

ከጉባኤው የቀረበውን ቅሬታና ሃሳብ ያዳመጡት የፌዴራል ጉዳዮች የሥራ ኃላፊዎች የቀረቡት ቅሬታዎች በሰነድ ተደግፈው ቢደርሷቸው እነርሱም በመፍትሔው ላይ መሥራት እንደሚችሉ፤ ኢትዮጵያ የሃይማኖቶች ጉባኤም ጉዳዩ በየደረጃው ቢቀርብለት መፍታት እንደሚችል፡፡ ቅሬታዎችን እንደዚህ ባለ መድረክ ከሚሆን በየጊዜው እየተገናኙ መፍታት ቢቻል›. የሚሉ ሃሳቦችን ሠንዝረዋል፡፡

የዘንድሮው የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ በአደረጃጀቱ ውበት፣ በተሳታፊዎቹ ብዛት፣ በአህጉረ ስብከቶች ቁጥር(50 ደርሰዋል)፣ በስብሰባው ቁም ነገረኛነት ካለፉት የተለየ ነበር፡፡ እነ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን በብርቱ እንደ ደከሙበት ያሳያል፡፡ በየዘገባዎቹ የተሰሙትን የመብት ጥሰቶች፣ ሥልጣንን ተገን በማድረግ የሚፈጸሙ ጫናዎች፣ የአምልኮ ቦታ እጥረቶች፣ በካህናቱ ላይ የሚፈጸሙትን ግፎችና፣ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታ የመንጠቅ ርምጃዎች ግን ሊገቱ ይገባቸዋል፡፡ ከአንዳንድ ክልሎች በቀር በብዙዎቹ የዞንና የክልል ባለ ሥልጣናት ችግሩን ተረድተው ለመፍታት እንደሚጥሩ ተገልጧል፡፡ በወረዳ ደረጃ የሚገኙት ግን ሥልጣንን ተገን በማድረግ የግል እምነታቸውን እያስፋፉ መሆኑን ያሳያል፡፡ በደቡብ ጎንደርና በምሥራቅ ጎጃም የተፈጸሙት የአብያተ ክርስቲያናትን የማቃጠል ርምጃዎች በጊዜው ተጣርተው መፍትሔ ካልተሰጣቸው ፍጻሜያቸው አያምርም፡፡

በየአካባቢው በሚገኙ ባለ ሥልጣናት የሚፈጸሙ ትንኮሳዎችም መቆም አለባቸው፡፡ ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳቱ ‹አታስቆጡን› እያሉ ደጋግመው የተናገሩት ነገር የዋዛ አይደለም፡፡ ኃላፊነት የማይሰማቸው አካላት የሚፈጽሙት ገደብ አልባ ትንኮሳና ጫና ወዴት እያመራ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱም አደረጃጀቷንና አሠራርዋን ይበልጥ የምትፈትሽበት፣ አሁን ለገጠማት ተግዳሮት ብቁ የሚሆን አሠራና አወቃቀር የምትይዝበት፣ ችግሮችን በስብሰባ ብቻ ሳይሆን በአካባቢያዊ ውይይት፣ በሕግ መሥመርና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀራርቦ በመሥራት የምትፈታበት መንገድ ሊኖር ይገባል፡፡  

ያለበለዚያ መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል የተረተው ተረት መድረሱ የማይቀር ነው፡፡

በጣልያን ጊዜ ነው አሉ፡፡ ጎንደር ላይ ጣልያን በድማሚት አንዱን ተራራ ያናውጠዋል፡፡ ተራራው ‹እድም› እያለ ይፈርሳል፡፡ አንዲት የከብት እረኛ ልጅ ፈርታ ወደ እናቷ ሄደችና ‹እማዬ ኧረ ጣልያን ተራራውን እያፈረሰው ነው›› አለቻት፡፡ እናቷም ‹‹እነ ደጃዝማች እገሌ፣ እነ ፊታውራሪ እገሌ፣ እነ ራስ እገሌ እጅ አንሰጥም ብለው እየተጋደሉ ዐለፉ፡፡ ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡›› አለቻት አሉ፡፡ 

ከጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘውና ሦስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው ፴፪ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ከቀትር በኋላ በነበረው ውሎ የተለየ ክሥተት አስተናግዷል፡፡ ‹‹የሃይማኖት መቻቻል›› በሚል ርእስ በ፴፪ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ በተካሄደው ውይይት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ባለሥልጣናት ጋራ በተለይም በመቻቻልና […]

ጥቅምት ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው መንበረ ፓትሪያርክ ስብሰባ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ባለው 32ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በቤተክርስቲያኑዋ ታሪክ  ተሰምቶ የማያውቅ ተቃውሞ ተከስቷል። አንድ በስብሰባው ላይ የተሳተፉ አባት እንደገለጹት በስብሰባው ላይ ”  ይህ መንግስት የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ እንደተነሳ በስፋት ተነግሯል። የፌደራል ጉዳዮች የሀይማኖት ክፍል ሃላፊዎች ዛሬ ስለ አክራሪነትና ጽንፈኝነት …

ጥቅምት ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ልዩ ሀይል እየተባለ በሚጠራው ታጣቂ ሚሊሺያ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት፣ አስገድዶ መድፈርና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈጸሙን የሚያመለክት ዛጋቢ ፊልም በስዊድን ቴሌቪዥን መለቀቁን ተከትሎ ፣ የክልሉ መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንቱን ቃለመጠይቅ በማድረግ አዲስ ዘጋቢ ፊልም ሰርቶ አቀረበ። የክልሉ መንግስት በለቀቀው አዲስ ፊልም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አድናቆታቸውን የገለጹበት ክፍል የተካተተ ሲሆን፣ …

ጥቅምት ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከተማሪዎች አለባበስ ጋር  በተያያዘ ከቀናት በፊት የተጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ እልባት ሳያገኝ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፡ ትናንትና ከትናንት ወዲያ ምሽት ላይ ጥይት ሲተኮስ ማምሸቱን የገለጹት አንዳንድ የተማሪዎች ቤተሰቦች፣ የተኩሱ ምክንያት ጩሀት የሚያሰሙ ተማሪዎችን ዝም ለማሰኘት ያለመ ነው ብለዋል። ተማሪዎች በየክፍላቸው ሆነው ተቃውሞ እአሰሙ እንደሚገኙ የገለጹት ቤተሰቦች፣ አንዳንዶች …

ሃገር ውስጥ የተገኙ ዝሆኖች ሁሉ ይታሰሩ የሚል አዋጅ ይወጣል። አንድ አይጥ ከላይ ወደ ታች ትራወጣለች። ምን ሆነሽ ነው ብለው ይጠይቋታል። በሃገር ውስጥ ያሉ ዝሆኖች ሁሉ ይታሰሩ ተብሎ የወጣውን አዋጅ አልሰማችሁም እንዴ? ብላ ትነግራቸዋለች። ታዲያ አንቺ አይጥ እንጂ ዝሆን አይደለሽ ብለው ሲጠይቋት ። እሲኪጣራስ ብላ መለስች አሉ። እሲኪጣራ በዝሆንና በአይጥ መካከል ያለውን ልዩነት ጊዜ ይወስዳል። የተስፋዬ […]

በሀገራችን የስም አወጣጥ ወግና ልማድ እልም ያለችዋ ጥሩራ ባሪያ “አልማዝ” ወይም “ፀሐይ”፣ በነጭናጫነቷና በምግባረ ብልሹነቷ መንደርተኛው ሁሉ የሚያውቃት ሴት ወይዘሮ “ዐመለወርቅ” ወይም “አበቅየለሽ”፣ እልም ያለው ቦቅቧቃ “ደም መላሽ” ወይም “ሺመክት”፣ ቤሣቤስቲን የሌለው የኔቢጤው መናጢ ድሃ “ሀብታሙ” ወይም “አዱኛ”፣ እንዴት ያለው ንፉግና ክፉ ሰው “ቸሩ” ወይም “ደጉ”፣ … ተብሎ ሲጠራ እናውቃለን፡፡ መቼም ‹ስም አይገዛም› ይባላልና በዚህ […]

ክፍል ስድስት በስምምነት ላይ የተመሰረተ የባህል አንድነት (CCU) የእድገት አቅጣጫዎች በዚህ ንድፈ ሃሳብ መሰረት ባህል አዳጊ ነው፡፡ ባህል በተፈጥሮው ዳይናሚክ በመሆኑ በኣንድ ቡድን ህይወት ውስጥ ትውልዶች በራሳቸው ዘመን የየራሳቸውን ፈጠራ እየጨመሩበት ወደላይ ያድጋል:: በሌላ በኩል ደሞ ባህል ወደ ጎን ካለው ሌላ ቡድን ጋር ሲነካካ(interact ሲያደርግ) እሴት እየተጋባ ወደ ጎንም ያድጋል።ወደ ጎን ሲያድግ ብዙ ያጋራ እሴቶችን […]

የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ÷ በጉባኤው አዘጋጆችና ተሳታፊዎች የተለመደ አነጋገር÷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከእግር እስከ ራሷ በአንድ አዳራሽ የምትገኝበት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ዓመታዊ ስብሰባው÷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፍ ጉባኤ ነው፡፡ ይኸውም ቤተ ክርስቲያናችን በውጭ እና በሀገር ውስጥ ካሏት የመንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት መንፈሳውያን አስተዳደር ጉባኤያት ተመርጠው የተወከሉ …

ወለላዬ ከስዊድን (ክፍል አራት)

The Secret ሚስጢሩ

ሚስጢሩ አሁን በኃይለኛ ሂደት ላይ ወቷል። እርስዎም የውለታ ምስጋናን፤ የሚፈልጉትን ነገር በዓይነ ህሊና አስቀድሞ ማየትን፤ የተግባር ኃይልን ሂደቶች የሚረዱበት ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል ማለት ነው። ለመሆኑ አስቀድመው ይሄን ሁኔታ የተሸጋገሩ ምን ይላሉ?

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይሄይስ አእምሮ

በሀገራችን የስም አወጣጥ ወግና ልማድ እልም ያለችዋ ጥሩራ ባሪያ “አልማዝ” ወይም “ፀሐይ”፣ በነጭናጫነቷና በምግባረ ብልሹነቷ መንደርተኛው ሁሉ የሚያውቃት ሴት ወይዘሮ “ዐመለወርቅ” ወይም “አበቅየለሽ”፣ እልም ያለው ቦቅቧቃ “ደም መላሽ” ወይም “ሺመክት”፣ ቤሣቤስቲን የሌለው የኔቢጤው መናጢ ድሃ “ሀብታሙ” ወይም “አዱኛ”፣ እንዴት ያለው ንፉግና ክፉ ሰው “ቸሩ” ወይም “ደጉ”፣ … ተብሎ ሲጠራ እናውቃለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በዩናይትድ ስቴትስ የመንግሥት በጀት ሳይፀድቅ ሣምንታት መቆጠሩ በሀገሪቱ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያስከትለው ተፅዕኖ ምን ይመስላል? የዛሬው የኢኮኖሚው ዓለም መሰናዶዋችን የሚያተኩርበት ርዕስ ነው።

«እዉቀት ለነገ» በሚል መርህ ከስድሳ የሚበልጡ ከሰሃራ በታች የሚገኙ አፍሪቃዉያት ሀገራት ምሁራንን ጭምር ያሳተፈ የሁለት ቀን ጉባዔ ጀርመን ሃኖቨር ከተማ በሚገኘዉ የፎልክስቫገን ተቋም ተካሂዶአል። ጉባዔው በአፍሪቃ በማህበራዊ፤ በሳይንስ፤ በህክምና፤ እንዲሁም በሃይማኖት ረገዶች በሚደረገዉ ሳይንሳዊ ምርምር ሥራ ላይ ተወያይቶአል፤

ዚምባቡዌ ላይ የአደንዛዥ እፅ ዝዉዉርና አጠቃቀምን አስመልክቶ የሚካሄደዉ ጉባኤ፤ መሪዎቹ ወሳኝ ርምጃ ካልወሰዱ የአህጉሩን መረጋጋት ሊጎዳ እንደሚችል አመለከተ። የምዕራብ አፍሪቃ የኤኮኖሚ ማኅበረሰብና በተመድ የእፅ ተከታታይ ጽ/ቤት አፍሪቃ ዉስጥ ሕገ ወጥ የአደንዛዥ እፅ ዝዉዉርን ለመግታት የሚያስችል አዲስ ርምጃ ላይ እየመከሩ ነዉ።

የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት በዓለማችን ከስምንት መቶ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ እየተራበ የሚታየዉ የምግብ ብክነት ተቀባይነት እንደሌለዉ አመለከተ። ድርጅቱ ዛሬ ይፋ ባደረገዉ ዘገባዉ የምግብ ማጣት ብቻ ሳይሆን የተመጣጠነና በቂ ምግብ አለማግኘት አካላዊ እድገታቸዉ ለእድሜያቸዉ የማይመጥን ልጆች ቁጥርም 165 ሚሊዮን መድረሱንም አስታዉቋል።

ከጉጂ ቦረናና ሊበን ዞኖች ሀገረ ስብከትና ሌሎች አብያተ ክርስቲያን በዘረፉት ገንዘብ ‹‹ሺበሺ›› በሚለው አስከፊ የሙስና ስያሜ የሚታወቁትና በነፍስ ግድያ ወንጀሎች የሚጠረጠሩት አቡነ ሳዊሮስ የሚያስተባብሯቸው የግብር አምሳሎቻቸው፣ መልአከ ገነት አባ አፈ ወርቅ ዮሐንስ እና መልአከ ገነት አባ ዮናስ ታደሰ ዋነኛ ተጠያቂዎች ይኾናሉ ተብሏል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን ‹‹የዐፄ ምኒልክ ሥርዐት እንዲመለስና የዐፄ ምኒልክ ባንዴራ እንዲሰቀል የሚፈልጉ ናቸው›› ብለው …